አጭር ምክር ብጤ
በቅርቡ በሚደረገው የ አሜሪካ ምርጫ ሳቢያ ትውልደ ኢትዮጵያውያን-አሜሪካውያን የ አሜሪካ የ ውጭ ፖሊሲ በ ኢትዮጵያ ካለው ከ ሰብአዊ መብት አያያዝ ጋር በተያያዘ እንዲቀየር ለሚያሳስቡ ወገኖች አንድ የዘነጉት ነገር ያለ መሰለኝ።
''አሁን እየተባለ ያለው አሜሪካ የውጭ ፖሊሲሽን ቀይሪ ነው።'' ከ እንደዚህ አይነት ''ቀይሪ '' ከሚል መልክት ይልቅ በ ቅርቡ በ አሜሪካም ይደረጋል የሚባለው የ ኢትዮጵያውያን ስብሰባ የ አቀራረብ መልክ ቢኖረው ጥሩ ነው። አንዲት ሀገር የ ውጭ ፖሊሲዋ የሚመሰረተው በ ጋራ ጥቅም ላይ ነው። ከ ጥቅሟ ትንሽ ነገር ከተሸረፈች ምንም ነገር ላይ ለመገኘት 'ሞራል' የሚለው ጉዳይ በ ዜና አውታሮች ዘንድ እስካልተጋለጠ ድረስ ብዙም ችግር አደለም ብሎ ማሰብ አለሙ እየለመደው ነው።
በመሆኑም ስብሰባው የ ጥናት ፅሁፎችን ታዋቂ የ ፖሊሲ አጥኝዎችን እና ፖሊሲው ሲቀየር ከ አሜሪካ የ ዘለቂታ ጥቅም አንፃር እንጂ የ ሰብአዊ መብት ስለተጣሰ ብቻ አሜሪካንን ፖሊሲሽን ቀይሪ የሚል አቀራረብ '' ልብ ባይነካስ ?'' ብሎ ማሰብ ተገቢ ነው።እዚህ ላይ ከ እዚህ ቀደም ብዙ ሰልፍ ሲደረጉ መክረማቸውን ልብ በሉልኝ። አሁን ወደ አውነታው አለም መምጣት ያለብን ይመስለኛል።የ እዚህ አይነት ሰበአዊ መብትን እና የ ምርጫ ካርድን ብቻ በመምዘዝ የሚደረግ ተፅኖ ከ ዲፕሎማሲያው መልስ ያላለፈ ምላሽ ማለትም ''ጉዳዩን እናየዋለን '' አይነት ምላሽ እና ምርጫው እስክሳካ ድረስ መንከባከብን ብቻ ማስከተሉ አይቀርም ።በ መሆኑም ዋናው ነገር ፖሊሲዋን መከለስ ያለባት በልመና ሳይሆን ለ እራሷ ስትል ፣ ከ ዘለቄታ ጥቅም አንፃር መሆኑን ማሳመኑ ላይ ነው ቁልፉ ተግባር ያለው ።
ይህ ደግሞ አስደንጋጭ ስታትስቲክስ የያዙ ማስረጃዎች፣ የ ጥናት ፅሁፎች እና ታዋቂ ተናጋሪዎችን ማቅረብ እና አሜሪካ የውጭ ፖሊሲዋን በ ተጠየቀው መንገድ ካልቀይረች የሚደርስባትን ክስረት የሚያመላክት ማስረጃ ፈልጎ ማቅረብን ሁሉ ይጠይቃል። ይህ እንግዲህ በ አሜሪካ ፖሊስ አውጭዎችም ዘንድ ሁሉ ክርክር የሚያስነሳ አዲስ ዘገባን ሁሉ ይዞ መውጣትን ይጠይቃል። ከ ስብሰባው ጥሪ ጀምሮ መንፈሱ ሁሉ ''ለ አሜሪካ የ ዘለቂታ የ ውጭ ፖሊሲ እንሰራለን! '' የሚል መንፈስ ያለው ለ አሜሪካ ተቆርቃርነት የሚያሳይ መንፈስም ማዘል አአለበት። አሜሪካዊ ኢትዮጵያውያን ለሆኑቱ ማለት ነው። ይህ ወደ ገንቢ ተፅኖ ይመራል። ቅኝቱም መሆን ያለበት እንዲህ ይመስለኛል።
ከ እዚህ በዘለለ ግን የ ምርጫ ካርድ እና የ ሰብአዊ መብት ጉዳይ በማንሳት ብቻ ለ አሜሪካ የሚያስከትለውን የ ጥቅም ጉዳት በደንብ በማስረጃ ሳያመላክቱ የሚደረጉ ስብሰባዎች የ እቅድ አፈፃፀም ብቻ ነው የሚሆኑት። ከተሳሳትኩ አርሙኝ።
አበቃሁ
ጌታቸው
1 comment:
Thank you for sharing ideas. Hule yemnchohew yhn new here in DC.
Post a Comment