ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Friday, October 5, 2012

የ ሙስሊሙ ጉዳይ

  • ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ ማንም ሰው እንደሚረዳው መንታ መንገድ ላይ ነው፣
  • ፅንፈኝነትን  ብዙ ሙስሊም ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን አይደግፉትም። ለ እዚህም ነው ጥያቂያቸውን በ ጥንቃቄ እና በ ሰላማዊ መንገድ ብቻ በ ማቅረብ ብዙውን ሕዝብ ያስደመሙት፣
  • ሃይማኖታዊ አደረጃጀት ተይዞ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የ ሀገሪቱን ሁለንተናዊ የነበረ መሰረቷን መዳሰሱ አይቀርም።


ይህ እውነተኛ ታሪክ ነው። ደግሞም ብዙ ኢትዮጵያውን ታሪክም ስለሆነ ዛሬ ማንሳቱ ተገቢ ነው።የ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሳለሁ ትምህርት ቤት ወደ ቤትም ሆነ ቤት ወደ ትምህርት ቤት ስሄድ አብሮኝ የሚሄድ እምነቱ እስልምና ተከታይ የሆነ ጓደኛ ነበረኝ። ባህሪው ሰው ተግባቢ እና ቀልደኛም ስለነበር እግር ሃያ ደቂቃ የሚፈጀውን ትምህርትቤታችን መንገድ ሳናውቀው ነበር የምንደርሰው። ከሁሉም የማይረሳኝ እሱን ለማናደድ የሚቻለው በጣም በሚወደው ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ቡድን ላይ አንዲት ነገር ጣል ካደረኩኝ ብቻ ነው። እዛ በተለየ ግን ፈገግታ የማይለየው ፊቱን ለተመለከተ ሰው እራስን ትካዜ ያስረሳል። ሁሉ:አለፈ:እና:ሥራ:ከያዝኩ:በኋላ :ሥራ:አለም:የማውቃቸው:ሙስሊም:ወንድሞች:እና:እህቶች:አንድ:አጥር:የምንጋራው ክፉም በደግም የሚራዱን፣ የምንራዳቸው ጎረቤታችን፣ሰው አክባሪነታቸው፣ የተቸገረን ለመርዳት ያላቸው ፍላጎት እና ለሀገራቸው ያላቸው ፍቅር ሁሉ አእምሮዬ ውስጥ ተቅርፆ አሁንም አለ። ይህ ብቻ አይደለም አሁን በምገኝበት ሀገር ከሁሉ ቀድማ ሥራ እንድሰራ እንደራሷ ጉዳይ ተጨንቃ አለቃዋ በመንገር የደከመች እህቴ እስልምና እምነት ተከታይ የሆነች ኢትዮጵያዊት ነች። ይህ እኛ ኢትዮጵያውያንን ሃይማኖት ያልለያየን የጠበቀ ኢትዮጵያዊነት ትስስር እንዳለን ስለሚያመለክት ለምሳሌነት እራሴን መሰልኩ።ይህንን ለመግብያነት ካነሳሁ ካለፉት ጥቂት ወራት ጀምሮ ሀገራችን እስልምና ሃይማኖት መሃከል እና ኢህአዲግ መሃከል የተነሳው ፍጥጫ፣ሂደቱ እና ፍፃሜው ምን ሊሆን ይችላል ለሚሉት መሰረታዊ ጥያቄዎች ላይ ሃሳብ መሰንዘሩ ተገቢ መሰለኝ።
ሂደቱ ምን ነበር ?

ውዝግቡ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የሚሰሙት ሁለት ጥያቄዎች ናቸው። መጅልሱ ( እስልምና ምክርቤት ከፍተኛው አካል) ይውረድ እና ¨አህባሽ አስተምሮ'' መሰጠት ይቁም ነው። ጉዳዩን ከመጀመርያ ጀምሮ ለተከታተለ ሰው ብዙ ውስብስብ ጉዳይ ውስጥ መግባት የማይገባው በቀላሉ ሊፈታ የሚችል የነበረ መሆኑን ይገምታል። መንግስት ጥያቄው በየደረጃው የሰጠው መልስ በመጀመርያ '' ሰላማዊ መንገድ ይፈታል¨ ቀጥሎ ''ተወካይ ምረጡ እና ከተወካዮቻችሁ ጋር እንነጋገራለን ጥያቄው ተገቢ ነው'' በመጨረሻ ደግሞ ''ጥያቄውም የተመረጡትም ተወካዮች አሸባሪዎች ናችሁ/ ናቸው።'' አላቸው። እዚህ ላይ የጥያቄውን አግባብነት እና የጠየቁበትን መንገድ ብቻ ብንመለከት ሙስሊሙ ሕብረተሰብ ከፍተኛ ትግስት፣ለሀገር ሀሳቢነት፣ እና ጨዋነት በተሞላበት መንገድ በመስጊድ ብቻ የተወሰነ ''ድምፃችን ይሰማ'' ጩኸት፣በ ዝምታ፣መሬት መቀመጥ ወዘተ መንገዶች ጥያቂያቸውን አቀረቡ።

እዚህ አይነት ፍፁም ሰላማዊ መንገድ ለቀረበው ጥያቄ መንግስት እራሱ ሙስሊሙ ወገን የሆኑ ሀገር ሽማግሌዎች መርጦ ጉዳዩን ገለልተኛ ኮሚቴ ይታይ ከማለት ይልቅ ሁለት ማንንም የሚያናድዱ ስራዎች ሰራ የመጀመርያው የተመረጡትን 17 የሙስሊሙን ተወካዮች ማሰር ሲሆን ሁለተኛው ምርጫ ታደርጋላችሁ ግን ምርጫው እኔ ቢሮ ቀበሌ ነው አለ። የሚገርመው ሁለቱም እርምጃዎች ሙስሊሙን ሕብረተሰብ ወደ ንዴት እና ወደ አመፅ ይመሩታል ተብሎ የመታሰቡን ያህል ሳይሆን ሰላማዊ ጥያቄው ካለ አንዲት ግጭት መጠየቁን ቀጠለ። እዚህ ሁሉ መሃከል ግን መንግስት ፖሊሶቹ አማካይነት አንዳንድ ሙስሊም ወንድሞች እና እህቶች ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን ዜና ማሰራጫዎች ተገለፀ።

ዛሬ:መስከረም 25/2005ዓም: ሙስሊሙ ሕብረተሰብብ:አዲስ አበባ:እና: ሌሎች:ከተሞች ቢጫ ወረቀት:እና ፊኛ በመያዝ ''ለመንግስት ማስጠንቀቅያ '' ነው የተባለ ''!'' የሚል ፊደል ያለበት ፅሁፍ በየ ሃገሩ መበተኑ መረዳት ተችሏል።
ውጤቱ ምን ሊሆን ይችላል?

ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ ማንም ሰው እንደሚረዳው መንታ መንገድ ላይ ነው። እዚህ ሁኔታ ወጥታ ፖለቲካውን ነገር ለትውልድ ተሻጋሪ በሆነ መንገድ መፍታት ከቻለች እድገት ጥያቄው ጥቂት አመታት ትግስት የሚጠይቅ ሥራ ብቻ መሆኑ አያጠራጥርም።ይህ መንታ መንገድ በተለይ ኢህአዲግ አቶ መለስ ሕልፈት ቀጥሎ ባሳየው ስልጣን ክፍተት፣ ህዝቡ ፖሊሲ ለውጥ:ጥያቄ:እና:ሁሉንም ያሳተፈ የፌድራል መንግስት መኖር አስፈላጊነትየ ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን:የይዞታ ማስከበር እና ካለመንግስት ተፅኖ አስተዳደራዊ ችግሮችን የመፍታትጥያቄየ ሙስሊሙ ሕብረተሰብ ጥያቄ ሀገራችን:መንታ መንገድ:ላይ መቆም ጥቂት አመላካች:ክስተቶች ናቸው። መንግሥት የሙስሊሙን ጥያቄ በተመለከተ ካወጣቸው መግለጫዎች ውስጥ እንዳንዶቹን አረፍተ ነገሮች በምሳሌነት ብንመለከት የሚከተሉት በቀጥታ ከመግለጫው የተወሰዱ ተመልካችም ግራ የሚያጋቡ ሆነው ይገኛሉ።

Ø  መንግስት ለእስልምና እምነትና ለሙስሊሙ ህብረተሰብ ካለው አክብሮት በመነሳት እያሳዬ ያለው ሰፊ ትዕግስት፤ የተቃውሞው አስተባባሪ የሆነው ህገ ወጥ ሀይል ከፍርሀት እየተመለከተው ነው

Ø  እነዚህ ወገኖች መንግስትም ሆነ የህዝበ ሙስሊሙ ተቋም የየራሳቸውን ምላሽ እንዳልሰጧቸው በማስመሰል ሰፊ አፍራሽ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ እያካሄዱ ከመሆኑም በላይ፤ 1997 ሀገሪቱን ለብጥበጥ ዳርገው ከፍ ያለ ጉዳት ካደረሱትና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት ከተመደቡ ሀይሎች የጥፋት እንቅስቃሴ ጋር በግላጭ ተመጋጋቢ የሆነ ዘመቻም እያካሄዱ ነውየሚሉ እና ሌሎችም ይገኙበታል።

 

 
ዛሬ መስከረም 25/2005 ዓም አዲስ አበባ ሙስሊሞች ቢጫ ካርድ ለመንግስት ሲያሳዩ 

 
እና ውጤቱ ምን ሊያስከትል ይችላል? ወሳኙ ጥያቄ ነው።
 
  •  ኢህአዲግ በከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ ሊያስገባው የሚችል የቤት ሥራ ለ እራሱ ያስቀምጣል በ ኢህአዲግም ውስጥ የበለጠ ንትርክ ይፈጥራል ::

  • የ ሙስሊሙ ሕብረተሰብ እራሱ በ ከፍተኛ ደረጃ የመከፋፈል አደጋ ሊገጥመው ይችላል 
 
ይሄውም ይህንን ጥያቄ ባቀረቡት ሙስሊሙ ሕብረተሰብ አካላት እና በተለይ ከተሞች አካባቢ የማይኖሩ መረጃቸው ሰፈራቸው ያሉ መስጊዶች እማሞች እና መንግስት ራድዮ እና ቲቪ ብቻ የሆኑ ወገኖች መህል የሚኖር ክፍፍል ሊያጋጥም ይችላል።

  • ''የ ሙስሊም ፅንፈኛ ቡድን'' የ ሙስሊሙን ጥያቄ  የመሪነት ሚና ለመያዝ ቀና ማለት 
አልፎ አልፎ ብቅ ሲል የነበረው ሙስሊሙ ሃይማኖት ስም የሚንቀሳቀሰው '' ሙስሊም ፅንፈኛ ቡድን'' ቢጫ ቀጥሎ ይወሰዳል ለተባለው እርምጃ የመሪነት ሚናውን ለመያዝ ቀና ቀና ማለቱ አይቀርም።በ ኢትዮጵያ ቅርብ አመታት ወዲህ ጅማ፣ሐረር፣እልባቦር እርሲ ወዘተ እነኝህ ፅንፈኛ ቡድኖች በ አብያተ ክርስትያናት እና ምእመናን ላይ ጥቃት ሲፈፅሙ እንደነበር ይታወሳል።በመሆኑም   ሙስሊም ወንድሞቻችን እና እህቶቻችንን የማይወክሉ ግን እራሳቸውም እንግዳ ትምህርት ይዘው የመጡባቸው  ክፍሎች እዚህ አይነቱን  ቀይ ካርድ መምጣት ''ሰርግ እና ምላሽ '' አርገው እንደሚመለከቱት ሳይታለም የተፈታ ነው። እዚህ ላይ በ ነሐሴ ወር ላይ  ''አልሸባብ'' ሰዎች ሳይሆኑ አይቀሩም የተባሉ በ ከፍተኛ ደረጃ የታጠቁ ቡድኖች  በሞያሌ ከተማ ላይ ያደረጉት ጥቃት አይዘነጋም።
  •  በ አፍሪካ ቀንድ ለዘመናት ችግር ሲፈጥር የነበረው አለም አቀፍ አክራሪ እስልምና መነቃቃት ይጀምራል።
 
አፍሪካ ቀንድ ለዘመናት ችግር ሲፈጥር የነበረው አለም አቀፍ አክራሪ እስልምና በመነቃቃት ኢትዮጵያውያን ፅንፈኝነት አስተሳሰብ ያላቸውን ሙስሊሞች መንግስት ስልጣን ጥያቄ እንዲያነሱ እና ኢትዮጵያ ''እስላማዊ መንግስት'' እንዲኖራት ወደሚል ግብ እንዲሄዱ ይህን ካደረጉ ብቻ ጎናቸው እንደሚቆም ግፊቱን ሊያደርግ ይችላል። ይህንን ደግሞ ብዙ ሙስሊም ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን አይደግፉትም። እዚህም ነው ጥያቂያቸውን ጥንቃቄ እና ሰላማዊ መንገድ ብቻ ማቅረብ ብዙውን ሕዝብ ያስደመሙት። እዚህ በተጨማሪ አለም አቀፍ ፅንፈኛ እስልምና እንቅስቃሴ ኢትዮጵያ ቦታ ካገኘ ሁለት መሰረታዊ ክስተቶች ሀገራችን ላይ ሊያመጣ ይችላል። እነርሱም አንድ ሃያላኑ መንግሥታት ጣልቃ ገብነት ቢያንስ ቁሳቁስ እና ቴክኒክ እርዳታ ነገሩን ማወሳሰብ እና ሁለተኛው እስልምና ውጭ በሆነው ኢትዮጵያዊ ጋር ከፍተኛ ፍጥጫ ውስጥ መክተቱ የሚሉት ይጠቀሳሉ።
መስቀል ደመራ በዓል መስከረም 16/2005 ዓም  አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ከወጣው ሕዝብ በከፊል  
ማጠቃለያ
አሁን እየሆነ ላለው ቁጥር አንድ ተጠያቂ ኢህአዲግ ችግር አፈታት ዘዴ ነው። ማንም ሰው ሊወስደው ይችላል ተብሎ የማይገመት እርምጃ ለምሳሌ ምርጫን ቀበሌ ደረጃ ማድረግ፣ከ አወልያ ጀምሮ ብዙዎች ገና ብሶቱ ተካፋይ ሳይሆኑ አጭሩ በውይይት በመፍታት( ያልተገለፀ ችግር ቢኖር እንኳን መገናኛ ብዙሃን ሕዝቡን በማወያየት መፍታት) ሲቻል ''ከወቅቱ ውጥረት ፖለቲካዊ ጥቅም ለማግኘት ያለመ'' በሚመስል መንገድ ጥቂቶች እወልያ የጠየቁትን ጥያቄ አራዝሞ ጉልት ቸርቻርነት ደረጃ ያሉት ሁሉ የሚማረሩበት ደረጃ የደረሰ ችግር አፈታት ኃላፊነት የጎደለው መንግስት አሰራር ለመሆኑ አሌ አይባልም። እዚህ በተለየ ግን ሙስሊሞች ወንድሞቻችን ጥያቄ ሃይማኖታዊ መልኩን ይዞ ያለመሄድ ዕድል ቢገጥመው ችግሩ ሀገሪቱ ፖለቲካ፣ማህበራዊ፣ እና ምጣኔ ህብታዊ ችግር ጋር የተያያዘ መሆኑን ጥያቂያቸውንም ሃይማኖት ጥላ ስር ተጠልሎ ከመጠየቅ ይልቅ ዲሞክራሲ ጥያቄ ሲፈታ እምነቱም ላይ ያለው ተፅኖ ሆኑ ሌሎች ችግሮች የሚፈቱ መሆኑን ማስረዳት ሁሉም ፖለቲካ ኃይሎች የሚጠበቅ ይመስለኛል።
 
በመጨረሻም ህብረተሰቡ ማህበራዊ አንድነቱንም ሆነ አካባቢያዊ ችግር እና ግጭት አፈታት መንገዶቹን ሁሉ አለመዘንጋት እና በተለይ ወጣቶች ማንንም ሳይጠብቁ አባቶቻችን እና እናቶቻችን ይጠቀሙበት በነበረው አካባቢ ችግር አፈታት መንገድ ማህበረሰባዊ እና ሃይማኖታዊ ግጭቶች እንዳይነሱ ከተነሱም መንደራቸው ደረጃም ኃላፊነት ወስደው የማስታረቅ እና ጎንዮሽ ግጭቶችን ነቅተው ማረጋጋት ያለባቸው ጊዜ ይመስለኛል። ምክንያቱም ሃይማኖታዊ አደረጃጀት ተይዞ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ሀገሪቱን ሁለንተናዊ የነበረ መሰረቷን መዳሰሱ አይቀርም። በግጭቶች መሃከል ደግሞ ከላይ የተጠቀሱት ውስጣውም ሆኑ ውጫዊ ኃይላት ኢህአዲግ ደህንነቱ ሲል ጉዳዩን የሚያጦዝበት መጠን ስለማይታወቅ አሁንም መፍትሄው ቁልፍ ሁሉ ያለው ወጣቱ ሙስሊም እና ሌላ እምነት ተከታይ ዘንድ ነው።አካባቢያዊ ችግሮችን ከማራገብ ሰፈር ደረጃ በመፍታት።
አበቃሁ
ጌታቸው በቀለ
ኦስሎ



 

2 comments:

Anonymous said...

I think EPRDF prefer religious war between christians and muslims rather than loosing its power. That is what we have learnt from its past ego-based behaviour.

Anonymous said...

This is really fascinating, You are an excessively skilled blogger.
I have joined your feed and look forward to in search of more of your fantastic post.
Also, I've shared your web site in my social networks
Here is my blog post ; night guard tmj

ሐያ ገዳማት የሚገኙበት በግሪክ የሚገኘው የአቶስ ተራራ ገዳማውያን አኗኗር (ቪድዮ)

ገዳሙ ከሰርብያ፣ሮማንያ፣ቡልጋርያና ሩስያ የመጡ ዓለምን የናቁ መነኮሳት ገድመውበታል።