ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, October 1, 2012

''የእዚችን ሀገር ኬክ እንዴት እንደሚካፍሉ ሲነጋገሩ መምህሩን ፈፅመው አስበውት አያውቁም'' የመምህራን ማኅበር ሊቀመንበር ንግግር (ቪድዮ)

ትምህርት ትውልድ ያድናል ወይንም ይገድላል። በኢትዮጵያ መምህራን የመደራጀት መብታቸው እና ሃሳባቸውን የመግለፅ መብታቸው በእጅጉ አደጋ ላይ መሆኑ የታወቀ ነው።የትምህርት አካባቢ (Academic Environment) ከሚፈልጋቸው ነገሮች አንዱ ነፃ የሆነ (ከፖለቲካዊ ተፅኖም ሆነ ከማናቸውም ነገር የፀዳ) የማሰብ፣የመደራጀት እና ሃሳብን የመግለፅ መብት ነው።ከጥቂት ወራት በፊት በኢትዮጵያ የሚገኙ መምህራን ከደሞዝ ጋር በተያያዘ ጥያቄ አቅርበው በየደረጃው ባሉ ባለስልጣናት እና ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ጭምር ''ችሎታ ያነሳቸው መምህራን ያነሱት ጥያቄ ነው'' ተብለው መዘለፋቸው ቀጥሎም በ አድማው ተሳተፋችሁ ተብለው የተባረሩ ነበሩ።

የአዲስ አበባ ወግ 

ባሳለፍነው ሳምንት በአዲስ አበባ ብቻ አንድ መቶ ሃያ መምህራን ባላወቁት መንገድ ጧት ወደ ሥራ ገበታቸው ሲገቡ ወደ አልጠየቁት ቦታ መዛወራቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ ደርሷቸው በእጅጉ ማዘናቸውን ለመገናኛ ብዙሃን ገልፀዋል።የሚገርመው እነኚህ መምህራን የተባረሩት በአድማ ስለተሳተፉ ብቻ ሳይሆን በአመለካከታቸው ከኢህአዲግ ፖሊሲን ስለሚቃወሙ እና የተቀሩት የ ኢህአዲግ አባልነት ፎርም ሙሉ ተብለው ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ነው።

ዲሞክራሲ፣ ሃሳብን የመግለፅ መብትእና የ''አካዳሚክ ነፃነት'' የዳበረ የፈጠራ ችሎታ ያለው ትውልድ ለመፍጠር ወሳኝ ነው።ከተባረሩት መምህርት ውስጥ አንዲቱ እንዲህ አለች '' ደብዳቤው ሲደርሰኝ በጣም አዘንኩ ።በማህበራችን ደንብ መሰረት አንድ መምህር እንዲዛወር የሚደረግበት መመርያ እና ደንብ አለው ለምሳሌ እኔ የማስተርስ ትምህርቴን እየተማርኩ ነው ነገ የመመረቅያ ፅሁፌን ለመጀመር ዝግጅት ላይ እያለሁ ወደ አልተየኩት ቦታ እንደምዛወር ተነገረኝ።ለምን እንደሆነ ምክንያቱ አልተነገረኝም። የሚገርመው አሁን የተመደብኩት አሁን አስተምርበት ከነበረው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወደ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው።ይህ በ እውነት ግፍ ነው።''ብላለች።

የናይሮቢ ወግ

ጎረቤት- ኬንያ የ መምህራን ማህበር ከ100 እስከ 300 ፐርሰንት የሚደርስ የደሞዝ ጭማሪ በ መጠየቅ በነሐሴ የተጀመረ እና ለሳምንታት የዘለቀ የሥራ ማቆም እና የሰላማዊ ሰልፍ ባልፈው ሳምንት አጠናቀቀ። በተቃውሞው ጉዳይ ላይ ካቢኔው ደጋግሞ ተሰበሰበ ተጨማሪ በጀት ፈለገ። ከ መምህራን ማህበሩ መሪዎች ጋር ተነጋገረ በመጨረሻ ተስማማ። የሚገርመው ለሀገር የሚያስበው እና 'ትምህርት ቁልፍ የ እድገት በር' መሆኑን የተረዳው የ ጎረቤት ኬንያ መንግስት በ ትንሹ ከሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች ጋር የ220 ዶላር ጭማሪ ለእያንዳንዱ መምህር ተደረገለት። ኬንያ በ ትምህርት እድገት በጥሩ ጥራት ላይ የምትገኝ እድገትን 'በልፈፋ' ሳይሆን ትምህርትን መሰረት የማድረግ ፍላጎት ያለው፣ ዲሞክራሲን፣ሃሳብን የመግለፅ መብት፣የመቃወም እና መንግስት ኃላፊነቱን ሳይወጣ ሲቀር የሚጠይቅ ትውልድ እንዲኖራት የምታደርገው ጥረት አዲስ አበባን ያስቀናል። የኬንያ መምህራን ማህበር ሊቀመንበር የደቪድ ኦኩታ ንግግር ግን ለሁሉም ትሆናለች  ''የእዚችን ሀገር ኬክ እንዴት እንደሚያካፍሉ ሲነጋገሩ መምህሩን ፈፅመው አስበውት አያውቁም''


የኬንያ መምህራንን ጉዳይ ቪድዮ ከእዚህ በታች ይመልከቱ።(በነገራችን ላይ በቪድዮው ላይ ይምትመለከቱትን ዜና የዘገበው የኬንያ  ቴሌቭዥን (K24TV) የምዘግበው  ከኬንያ ምድር ነው።ስለ ዜናው ለመስማት ከ ዋሺግተን ሌላ ዜና አይጠብቁም።ጥያቄው ኢቲቪ እንደዚህ የሃገር ውስጥ አድማ በነፃነት ዘግቦ ያውቃል ወይ? ነው።

ወቅታዊ የዓለም ሁኔታ እንድንነታረክ ዕድል የሚሰጥ አይደለም።ብንነቃ መልካም ነው።

========== ጉዳያችን ወቅታዊ ========== የዓለም ታሪክ እንደሚያስተምረን ዓለም በወሳኝ የእጥፋት(turning point) ታሪኮች ውስጥ አልፋለች። እነኝህ የእጥፋት ጊዜዎች የዋዛና የፈዛዛ ጊዜ አይደሉም።መላው ዓለ...