ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, October 16, 2012

''ሰባተኛው ሰው ''

አለማችን እየተለወጠች ነው ለማለት ዘመናትን ሃያ አምስት አልያም ሃያ እየከፈሉ መናገር የተለመደ ነው። ይህ እንግዲህ ሁለተኛው አለም ጦርነት ወዲህ ላሉት ክንውኖች ነው። አንድ ክፍለ ዘመን ዘለል ካልን ግን ክስተቶችን ሃምሳ አመትም ልንከፍላቸው እንችላለን። ለምሳሌ የ ኢንዱስትሪው አብዮት እንደ አውሮፓውያኑ ዘመን አቆጣጠር አስራ ስምንተኛው ክፍለ ዘመን እስከ አስራ ዘጠነኛው ዘመን አጋማሽ ድረስ የተፈጠረ እና እርሻ መሰረት የሆነውን ምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴን ቀላል እና ብሎም ከባድ ኢንዱስትሪ፣ ከተሞች መስፋፋት ጋር ሰውልጅን ታሪክ እጅጉ የቀየረ ክስተት ነው።እንግሊዝ ከሀገሯ ንጉሳዊ ፈላጭ ቆራጭ አስተዳደርን ፓርላማ አስተዳደር መለወጥ ጀምሮ እስከ ዘመናዊው ኢንዱስትሪ አብዮት ድረስ አለም ሕዝብ ያደረገችውን አስተዋፆ ክረምቱ መግቢያ ላይ ባስተናገደችው ሎንዶን ኦሎምፒክ መክፈቻ ስነ-ስርአት ላይ አስታውሳናለች።

አለማችንን የታሪክ ክስተቶች ወደኋላ ስንመለከት ክስተቶቹ እረዘም ያለ ጊዜ ሲፈልጉ እንመለከታለን። ኢንዱስትሪው አብዮት የመጀመርያ እድገት ደረጃውን መከወን አንድ መቶ አመታት አስፈለጉት። ዛሬ ግን አለማችን ክስተቶች ማህበራዊው፣በ ፖለቲካውም ሆነ ምጣኔ ሀብት ረገድ ለውጦቹን መለካት የምንችለው ሃያ፣በ አስር እና በአምስት አመታት እየሆነ ነው። ምሳሌ ላስረዳ። ዛሬ ሃያ አመት ተንቀሳቃሽ ስልክን ማን አሰበው? ዛሬ አስር አመት በተንቀሳቃሽ ስልክ እየተያዩ ማውራት ቴክኖሎጂ ለተራው ሕዝብ ይደርሳል ብሎ ማን አሰበ? ዛሬ ሰባት አመት ማንኛውም ሰው ቤተሰቡ እና ከሚያውቃቸው ሰዎች ጋር ሁሉ ማህበራዊ መገናኛ መድረኮች እንደ 'ፌስ ቡክ' በመሳሰሉትን መገናኘት ማን አሰበው? አለማችን እድገት እና ለውጦች እንደ ኢንዱስትሪው አብዮት አንድ መቶ ዓመት እንደማይፈልጉ ተመልከቱ። እዚህም ነው ፖለቲካ ፓርቲዎችም ሆኑ ኢኮኖሚ ተቋማት ፖለቲካ ፕሮግራማቸውንም ሆነ ንግድ ስልታቸውን ጊዜው ፍጥነት እና ከሚመጣው ፈጣን ትውልድ እኩል መራመድ ካልቻሉ ጊዜ ያለፈባቸው አሰልቺ መሆናቸው ሳይገባቸው ትውልዱ እነርሱ ብዙ ጊዜ ልቆ መሄዱንም ሳይረዱ ባሉበት የሚሰምጡት። አንድ የፖለቲካ ፓርቲ ሃያ እና ሰላሳ አመት በፊት ስለነደፈው ፖለቲካ ፕሮግራም ¨እየዘመረ¨ ካለ ይህ በሽታ ሳይሆን ክፉ የማይለቅ ሙት መንፈስ የተጠናወተው አካል ወደመሆን እንደሚቀየር ያልጠረጠረ ካለ መጠርጠር መጀመር አለበት።

 ፅሁፌ ዳራ ግን ስለ አለፉት ዘመናት ለማውሳት ሳይሆን እዚህ ፈጣኑ አለማችን መለወጥ ይዘውት ከመጡት መሃከል ትውልዱን አስተሳሰብ በበጎም ሆነ ክፉ አስተሳሰብ ለመቅረፅ እድሉ ካላቸው ዘመን አመጣሽ ክስተቶች አንዱ ፊልም ኢንዱስትሪያችን ላይ ሃሳብ ለመስጠት ነው። ቅርብ አመታት ወዲህ በርካታ ፊልሞች በሀገራችን  ሲንማ ቤቶችም ሆነ ቪስዲ እና ዲቪዲ መልክ ብዛት አማርኛ ቋንቋ መቅረብ ጀምረዋል።ብዙዎቹን ፊልሞች አይቻቸዋለሁ ለማለት ባልደፍርም የተወሰኑትን መመልከቴ ግን አልቀረም።ስመለከት ግን ሁል ጊዜ የምለካበት መስፈርቴ ይህንን ፊልም የሚያየው ታዳጊ ወጣት ምን ያገኝበታል? ወዴት እንዲመራ የተፈለገ ፊልም ነው? የሚሉ ጥያቄዎችን እራሴ እያነሳሁ እየጣልኩ ነው። ኮመዲ ፊልሞች፣ በተለይ አሁን አሁን በሰል ያሉ አስተማሪ ፊልሞች መታየት ጀመሩ እንጂ አዳንዶቹ አመት በዓል ሰሞን የሚቀርቡ ድራማ ይዘት ያላቸው ማለትም አባት ሰክሮ ሲመጣ፣እናት በግ ለምን አልገዛህም ስትለው፣አባት በሰከረ አንድበት ብሩን እንዳጠፋው ሲነግራት ወዘተ ላይ ያጠነጠኑ ስልችት ያሉ ይልቁን ልጆችም ሆነ ለታዳጊዎች አድገው እንዴት መስከር እንደሚገባቸው የሚያስተምር ድራማ ኢቴቪ እያየ ሲማረር ያላደገ ወጣት ይናገር።

እዚህ ዘመን ግን ልብ አድርስ ፊልም ሰሪዎች የሆኑ አሁኑን ብቻ ሳይሆን መጭውን ትውልድ የሚያማትሩ ፊልሞችን ማየት እየጀመርን ነውና ወጣቶቹን ማበረታታት ተገቢ ነው።በ አዲስ አበባ ዩንቨርስት 'የቴያትር እና አርት ዲፓርትመንት' ተማሪዎች ምረቃ ስራዎች ላይ ለመገኘት ዕድል ባገኘሁባቸው  ጥቂት አመታት እውነት ኪነት ጥበብን የሚይስከብሩ፣ሀገራቸውን የሚወዱ ታሪክ እና ህዝብን ብቻ ሳይሆን ነገ እድገት ምኞታቸውን ሀገራቸው ማሳየት የሚችሉ ወጣቶች እየወጡ ተመልክቻለሁ። እነኝህ ልጆች መውጣት ደግሞ ትልቅ አስተዋፅኦ ያደረጉት አንጋፋዎቹ  ቴያትር እና ፊልም መስራች አባቶች እነ ረዳት ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሠሠ ልጆቹ ጋር እንደ ልጅ ወጣቶች ጋር እንደወጣት እየሆኑ ማስተማራቸውን መዘንጋት የለብንም። ለትውልዱ ሞራል ግንባታ እና እራስ መተማመን የሚፈጥሩ ስራዎች ውስጥ (እኔ ለማየት ዕድል ስላገኘሁት ነው የማወራው እንጂ የተሻሉ አንዳሉ እገምታለሁ ) ''ሞርያም ምድር '' እና አሁን ትንሽ ላወራለት የፈለኩት '' ሰባተኛው ሰው'' የተሰኙት ፊልሞች አትኩረቴን ስበውታል።የ ''ሞርያም ምድርን''ላቆየው እና ስለ ''ሰባተኛው ሰው'' ትንሽ ላውጋችሁ።
                            ረዳት ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሠሠ (ፎቶ ድሬ ትዩብ)

'' ሰባተኛው ሰው''

''ይህ ፊልም መታሰብያነቱ አርቲስት ጌታቸው አበራ ነው'' ብሎ ነው የሚጀምረው  ምናልባት ''ኮመዲ'' ከተሰኙት ፊልም ክፍሎች የሚመደብ መስሎዎት ዘ ብለው መከታተል እንደጀመሩ ህብረተሰባችንን መሰረታዊ ስነ-ልቦና ችግር ዝርግፍ አድርጎ ሲያሳይ ሰብሰብ ብለው '' እውነቱን ነው '' እያሉ መከታተል ይጀምራሉ።በ ንዋይ ደበበ ''ሃገሬ'' ዜማ የሚጀምረው  ፊልም ብንያም ወርቁ ደራሲነት እና ዳይሬክተርነት ተዘጋጅቶ ናትናኤል /ማርያም ኤድትነት ተዋናይ ብንያም ወርቁ፣ሰለሞን ቦጋለ፣ክሮስ /ስላሴ፣ወይንሸት በላቸው፣ጌታቸው አበራ፣ሳምሶን ታደሰ፣ተሻለ ወርቁ፣ፍቃዱ አበበ፣ዳግማዊት ፀሐዬ እና ሰለሞን ታሸ ተከሸነ ነው።

የፊልሙ ጭብጥ

አንድ መስርያቤት ሰራተኛ አስራ አምስት ቀን ስብሰባ ወደ አሜሪካ ይሄዳል። ስብሰባው በተያዘለት ጊዜ ይጠናቀቅ እና ወደ ሃገሩ ይመለሳል። ለካ ጎረቤቱ፣ ቤተሰቡ ወዳጅ ዘመድ ሁሉ አሜሪካ እንደገባ ይቀራል ''አሜሪካ ገብቶ ማን ይመጣል?'' በሚል ብሂል (ብሂል ለሚለው ማረግ ባይደርስም ቃሉ) ብለው ያስቡ ነበር እና ስብሰባውን ጨርሶ ቦሌ አየርመንገድ ወርዶ ከያዘው ታክሲ ሹፌር ጀምሮ ¨እንዴት አሜሪካ ገብተህ እዛው አልቀረህምንትርክ ይገጥሙታል። ''አሜሪካ የሄድኩት ስብሰባ ነው ልቀር አደለም ለምን አቀራለሁ ሃገረ ላይ መስራት አለብኝ¨ ይከራከራል።ታክስ ሹፌሩን ተገላግሎ ቤቱ ሲገባ እህቱ ' ታዋን' ታቀልጠዋለች፣ እናት ልጄ ' አሜሪካ ተመለሰብኝ እዛው ለምን አልቀረም' ብለው ደንግጠው ሆስፒታል ገቡ። ታሪኩን እዚሁ ተርኮ መጨረስ ተገቢ አይደለም።
አጭሩ ግን መመለሱ ''ትክክል አደለሁም እንዴ?'' ብሎ እስኪጠራጠር ድረስ መስርያቤቱ ባልደረቦች ጀምሮ እስከ ለስራ የላኩት ሚኒስትር ብሎም ዩንቨርስቲ ፕሮፌሰር ሁሉ ይጠይቃል። አሳዛኙ ክስተት ግን ሁሉም ''ታመሀል እንዴ? ለምን መጣህ?'' ይሉታል። በተለይ የሚንስትሩ አስገራሚ ነበር። ሚኒስትሩ ያስጠሩት እና አቶ መለስን ፎቶ ሰቀሉበትን ክፍል በራቸውን በመዝጋት ይሸፍኑታል እና እንዲህ ይሉታል-'' አንተ አሳፋሪ እድሉን ለሌላ ሰው ብሰጠው ኖሮ ተጠቅሞበት ስንት ደረጃ ይደርስበት የነበረውን  እንድትጠቀም ብዬ አሜሪካ ብልክህ ተመለሰህ መጣህ? እንዴት አይነቱ ወራዳ ነህ! አሁን ውጣልኝ! ነበር ያሉት።'' ቀሪውን እርስዎ ይመልከቱት።

ከፊልሙ ገፀ ባህር ውስጥ ወደ ሃገሩ የተመለሰውን በተቃራኒ መልክ  ሀገሯን ትታ ለመሄድ የተነሳች ወጣትን  ቤተሰብ አርፈሽ ሀገርሽ ውስጥ ለምን አትሰሪም የሚል ክርክር ደግሞ በጎንዮሽ ፊልሙ እንደሚያሳይ እንዳትዘነጉብኝ።

አስተማሪነቱ

ይህ ፊልም በሚልዮን የሚቆጠረውን ሕዝባችንን ስደት ኢኮኖሚያዊ ብቻ አለምሆኑን ያስረዳል። ፖለቲካው የሚያስድደው እትዬ ለሌ መሆኑን አይዘነጋም። ለ እዚህም ማስረጃ ይህንን የ ቃል ልውውጥ እንከታተል።

''ለምን መጣህ? እዚህ ሀገር ባለስልጣን ዘመድ ካልሆንክ ወይ ወደ ፖለቲካ ጠጋ ካላሉ መኖር አለመቻሉን እያወክ?''ለሚለው ጥያቄ ምላሹ ትውልዱ የሚሆን ነው።

''ለምን አልመጣም? ሀገሬ አደለችም? እኔ ካልመጣሁ ማን ይምጣ? መንግስት ያልፋል፣የ ዘውዱ ስርአት፣ደርግም አልፈዋል። ኢህአዲግም ያልፋል።የማያልፍ ሕዝብ ነው። ሕዝብ ማለት ደግሞ እኔ ነኝ።'' ሲ ወዳጁን መልሶ የጠይቀዋል።

''እባክህ ይሄ ሕዝብ ሃቀኛ ሰው አይፈልግም። ሃቀኛ ሆነህ 'ቭልስ ዋገን' ስትነዳ ከሚያይህ ሰርቀህ ' ኢም ደብሊው' ስትነዳ ቢያይህ  ያከብርሃል።'' ይለዋል።

'' ሌባ ይኖራል። ዛሬ የሸለሙትን ነገ አልሆነ ቦታ ሲያወርዱት  ታየዋለህ---ግን ሀገሬስ ---- '' ንግግሩ ይቀጥላላ።

ፊልሙ ማጠናቀቅያ ላይ ግን ፈታኝ ጥያቄ ያነሳል።ሰው ቸግሮት ይሰደዳል። ''ግን ገንዘብ ያላቸው ለምን ይሰደዳሉ?''(የፖለቲካ ችግር የሌለባቸው ለተሻለ ኑሮ እያሉ የሚሄዱትን ብቻ ማመልከቱ ነው) ብሎ ጠይቆ እውነታውን ለመረዳት አካባቢውን ይቃኛል።በ ፊልሙ ላይ ባይነሳም ገንዘብ ሳያንሳቸው በሀገራቸው መስራት ያልቻሉትን ፊልሙ ባያነሳም የ ብዙ ወጣት ችግር ላይ የጣለው የ ስነ-ልቦና መሰለብ ምክንያቱን ያገኘው ይመስላል።በ ዋናው ተዋናይ የ አካባቢውን መቃኘት ሂደት ላይ ግኝቱ ይታያል።ይሄውም  ራድዮ ሲከፍት ስለ እንግሊዝ ማንቸስተር ቡድን ያወራል፣ ኢቲቪ ደግሞ ባህር ማዶ ስላሉት አስደናቂ ነገር ይዘግባል፣ጋዜጣውን ሲመለከት ስለ ባህርማዶው የተፃፈ ነው። ''ለካ ሁሉ ነገራችን ስለውጭ ነው የሚያወራው! የስነ ልቦና ሰለባው ለካ እዚህ ነው ያለው!ሰው ሃገሩን እንዲጠላ ቀፎውን ማስቀረት ለካ እዚሁ ሻይ በምጠጣበት ካፌ  ጀምሮ ነው ችግሩ ያለው !'' የሚል በሚመስል ስሜት እንደተደመመ ፊልሙ ይቋጫል። ለትውልዳችን ቢከፋው በሀገሩ መብቱን መጠየቅን፣የ ሃገሩን ሀብት ትቶ ውጭውን ማድነቅን አባዜ ያመላከተ በተጨማሪም በእራስ የመተማመን ስሜት እንዲጎላ ማድረግ  ብቻ ሳይሆን ህብረተሰባችንን አንዱን ስነልቦና ችግር ምንጭ እዛው ከ ጋዜጣ እስከ ራድዮ ያሉ ፕሮግራሞች መፈተሽ እንዳለባቸው ያመላከተ ፊልም ነው። ለነገሩ ይህንን ፊልም ከተመለከትኩ በኋላ እስር የሚማቅቀው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ታወሰኝ። ከኖረበት ምድረ አሜሪካ ተመልሶ በሀገሩ ለበርካታ ጊዜ እየታሰረ ሃገሩን ትቶ ላለመሄድ የወሰነ እዚህ ትውልድ አካል ነው እና ትውልዱን በድፍኑ መውቀስም ተገቢ አይደለም። ሳልዘነጋው ግን አንባብያን የምመክረው ፊልሙን ተመልከቱት።

አበቃሁ

ጌታቸው
ኦስሎ

2 comments:

Anonymous said...

ጉዳያችን እውነትም ጉዳያችን!
መልካም እይታ ነው። ፊልሙ የሚወደድ ብቻ ሳይሆን የ ታሪካችንን ገጽታ የሚያሳይ ነው። ወጣቱ በተለይ ተሰዶ ካለቀ ሃገሪቱን ማን ይረከባል? ለምን ችግሩንም በደሉንም አንጋፈጥም እና የተሻለች ሃገር አይኖረንም?

Anonymous said...

It is interesting tech

የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...