=====================
ጉዳያችን ዜና / Gudayachn News
=====================
ታኅሳስ 20/2014 ዓም የኢትዮጵያ ተወካዮች ምክር ቤት በሁለተኛው ልዩ ስብሰባው አንድ ወሳኝ ውሳኔ አሳልፎ ነበር። ይሄውም የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለማቋቋም የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ በአብላጫ ድምፅ በማሳለፍ ያቋቋመበት ቀን ነበር። ኮሚሽኑ ኢትዮጵያውያን በጋራ አጀንዳዎች ላይ እንዲመክሩ እና ብሔራዊ መግባባት እንዲፈጠር እንደሚሰራ የኮሚሽኑ ምስረታ ላይም ሆነ በኋላ የኮሚሽኑ አባላት ምርጫ ከተደረገ በኋላም ጭምር በሚገባ ተብራርቷል።
ይህ ለኢትዮጵያ የቀረበ የሰለጠነ የጋራ ችግር መፍቻ ዓይነተኛ መንገድ ብቻ ሳይሆን ዕድልም ጭምር ነው። አሁን ኢትዮጵያውያን በውይይቱ ዙርያ መወያየት፣የኮሚሽኑን ሥራዎች የተሳለጡ እንዲሆኑ በሃሳብ ማዳበር እና ልምዳቸውን ማካፈል በእጅጉ ይጠበቅባቸዋል።
በእዚህ መሰረት የአሁኑ ቅዳሜ ሚያዝያ 8/2014 ዓም (አፕሪል 16/2022 ዓም) አራት የኢትዮጵያውያን ዓለም አቀፍ አደረጃጀቶች በኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ዙርያ አራት ምሑራን ማለትም ፕሮፌሰር ብርሓኑ መንግስቱ፣ዶ/ር ደሳለኝ ጫላ፣አርክቴክ ዮሓንስ መኮንን እና ዶ/ር ልዑልሰገድ አበበ በዋናነት እና ሌሎች ምሑራን ሃሳብ የሚያካፍሉበት የውይይት መርሓግብር ተዘጋጅቷል።በዝግጅቱ ላይ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
ውይይቱን
- ሲቲዝን አስፓየር-ኖርዌይ፣
- ኢትዮጵያን ስኮላርስ በኖርዲክ ሃገሮች-ኖርዌይ፣
- ኢኦቲሲ ግሎባል ፎረም እና
- የኢትዮጵያውያን ሰላም እና እርቅ በዩኬ በጥምረት አዘጋጅተውታል።
ውይይቱ በዙም የሚደረግ ሲሆን ዝርዝር የመግቢያው ማስፈንጠርያ፣ኮድ እና ሰዓቱ እንደየከተሞቹ ከእዚህ በታች ካለው ፖስተር ላይ ያገኛሉ።ላልሰሙ በማካፈል አገራዊ ግዴታዎን ይወጡ።የአገር ጉዳይ ለተወሰኑ ሰዎች የሚሰጥ ሥራ ሳይሆን የሁላችንም የጋራ ተግባር መሆኑን ለሁሉም ማሳወቅ የእያንዳንዱ ሰው ኃላፊነት ነው።
No comments:
Post a Comment