👉 በአደጋው ከ 3ሺህ በላይ የአብነት ተማሪዎች መኖርያቸው ሙሉ በሙሉ ወድሟል።
👉የአብነት ተማሪዎቹ መጻሕፍት ሙሉ በሙሉ ወድሟል።
👉የአብነት ተማሪዎቹ እንዳይበተኑ የምዕመናን መረባረብ መፍጠን እንዳለበት አጽንዖት ተሰጥቷል።
👉የእርዳታ እጅዎን የሚዘረጉበት ቀላል መንገድ በወገን ፈንድ ተዘጋጅቷል።የመርጃ ሊንክ ከስር ያገኛሉ።
👉 ስለደረሰው የእሳት አደጋ መረጃ ቪድዮ ከስር ይመልከቱ።
መጋቢት 27 ለ 28 ሌሊት ባልታወቀ ምክንያት በባሕር ዳር የደብረ ጽዮን ሰላም አርጊው ማርያም ቤተ ክርስቲያን አብነት ጉባኤ ቤት ሙሉ በሙሉ በመቃጠሉ እና ከ3ሺህ በላይ ተማሪዎች ካለመጠለያ በመቅረታቸው የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ምእመናን ለተማሪዎች እንዲደርሱላቸው ጥሪ አቅርበዋል።መነሻው ምክንያት እየተጣራ እንደሆነ የተገለጸው ድንገተኛው የእሳት አደጋ ደቀ መዛሙርት ይኖሩባቸው የነበሩ ከአራት መቶ በላይ ጎጆችና የደቀ መዛሙርት ንብረት ሙሉ ሙሉ መውደሙም ተገልጿል።
የእሳት ቃጠሎው ያደረሰው አደጋ መጠነ ሰፊ ቢሆንም የእግዚአብሔር ጥበቃም የታየበትና ምንም የተጎዳ ተማሪ የለም።
ምእመናን ለተማሪዎች የዕለት መጠለያ እና ምግብ እንዲሁም ለወደፊት በቋሚነት ለመሥራት እርዳታቸውን እንዲያደርጉ በአክብሮት ተጠይቋል።
የእርዳታ እጅዎን የሚዘረጉበት የወገን ፈንድ ሊንክ
https://www.wegenfund.com/causes/asecakwaaye-eredaataa-mulu-bamulu-lataqaathalawe-b/
ስለ የደረሰው የእሳት አደጋ መረጃ ቪድዮ
No comments:
Post a Comment