ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, March 30, 2022

ስለ ዕውነት በእዚህ ውሳኔው እና ተግባሩ የኢትዮጵያን መንግስት አለማመስገን እንዴት ይቻላል?

==============
ጉዳያችን / Gudayachn
===============
ከጥቂት ዓመታት በፊት በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ በጣም ከሚያዝንበት ጉዳይ ውስጥ አንዱ በመካከለኛው ምስራቅ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሰቆቃ ህይወት ነበር። የዛሬ 9 ዓመት ጉዳያችን ይህንኑ ሰቆቃ አስመልክታ ካወጣችው ዜና ውስጥ ይህንን በመጫን መመልከት ይቻላል።

በዘመነ ህወሓት/ኢህአዴግ ዘመን በሳውዲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ትኩረት አጥተው እንደነበር በዘመናችን የተመለከትነው እና ምስክር የምንሆንበት ጉዳይ ነው። ይህ ሁኔታ በአሁኑ ጊዜ እንደተቀየረ በግልጽ እየትመለከትን ነው። ኢትዮጵያ ካለፈው ዓመት ጀምሮ ዜጓቿን ከሳውዲአረብያ መመለስ ጀምራለች። የሳውዲ መንግስት ኢትዮጵያውያንን የማባረር ሥራውን እንዲያቆም ከፍተኛ የመንግስት እና የሃይማኖት መሪዎች ከኢትዮጵያ ወደ ሳውዲአረብያ ሄደው በዲፕሎማሲያዊ ጥረት ለመፍታት የተደረጉት ጥረቶች በቂ ፍሬ አላፈሩም። ሆኖም ግን መንግስት በሌለው ሃብት ባለው አቅም ኢትዮጵያውያንን ወደ ሃገራቸው የመመለስ ሥራውን ተያይዞታል። ይህ ታላቅ እና የሚያስመሰግን ሥራ ነው። ይህ ኢትዮጵያውያን በየትኛውም የዓለም ጥግ ብንኖር በእዚህ የመንግስት ኃላፊነት የተሞላበት ተግባር አለመደሰት እና አለማምሰገን አንችልም።

ባለፈው ዓመት መንግስት በመቶሺዎችን ወደ ሃገር ቤት የመመለስ ተግባር ፈጽሟል።በዛሬው ዕለትም ከመንግስት እንደተገለጸው በቀጣይ ከ7 እስከ 11 ወራት ውስጥ 100 ሺህ ኢትዮጵያውያንን ከሳውዲ የመመለስ ሥራ ተጀምሯል።በዛሬው ቀን ብቻ 900 በላይ ኢትዮጵያውያን ሃገራቸው ገብተዋል።ይህንን መልካም ውሳኔ በመካከለኛው ምስራቅ ያሉ ኢትዮጵያውያን ስቃይ በሚገባ ካልገባን የተግባሩ ክቡርነት አንረዳውም።

ከእዚህ በታች ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ ከሳውዲ የገቡ ወገኖቻችንን ዜና ፋና እንደዘገበው ነው።

ፋና ቴሌቭዥን መጋቢት 30/2022 ዓም እ






980 ከ100 ሺህ 

No comments:

የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...