ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Sunday, March 20, 2022

የትግራይ ተወላጅ የኢንጅነር እምብዛ ታደሰ አስከሬን ከተቀበረበት ቤተክርስቲያን አውጥቶ መልሶ ለጅብ የሰጠው ማን ነው?

ኢንጅነር እምብዛ ታደሰ
===============
ጉዳያችን /Gudayachn
===============
በኢትዮጵያ ከፋሺዝም የከፋ፣ናዚዝምን የሚያስንቅ በብዙ ግፎች የተሞላ፣ከአርባ ዓመታት በላይ ከትግራይ እስከ ሞያሌ በበርካታ ኢትዮጵያውያን ደም የተነከረው ህወሓት ከፈጸማቸው የግፍ ስራዎች ውስጥ በራሱ በትግራይ ህዝብ ላይ የፈጸመው ግፍ የሽብርተኛው ህወሓት ደጋፊዎች ሊሸፋፍኑት ይሞክራሉ እንጂ ታሪክ እና ጊዜ የሚያወጣበት ጊዜ እሩቅ አይደለም።

ህወሓት የትግራይን ህዝብ መፍጀት የጀመረው ከምስረታው ጊዜ ጀምሮ ነው።በ1967 ዓም እስከ 1970ዎቹ መጨረሻ ድረስ ትግራይ አዛውንቶችን እና የዕድሜ ባለጸጋዎች ሳይቀሩ ኢትዮጵያዊነትን ያጠብቃሉ የተባሉ ህይወታቸው  በህወሓት እየታደኑ ጠፍቷል።

በዘመናችን ህወሓት ከፈጸማቸው ግፎች ውስጥ የትግራይ ተወላጅ የኢንጅነር እምብዛ ታደሰ ላይ የተፈጸመው የሕወሓትን ከፋሺዝም እና ናዚዝም የከፋ ድርጊት አመላካች ነው። ኢንጅነር እምብዛ ታደሰ የትግራይ ተወላጅ ነው።የመከላከያ ሰራዊት መቀሌ ለሕግ ማስከበር ከገባ በኋላ ህዝቡን ለማገልገል ካለው ፍላጎት አንጻር የትግራይ ክልል ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ በመሆን ማገልገል የጀመረው።ሆኖም ህወሓት ወኪሎቹን ልኮ መቀሌ ላይ በቢላዋ አርደው አስከሬኑም እንዳይገኝ ሜዳ ላይ ጣሉት። አስከሬኑም በከፊል በጅብ ተበላ።በኋላ ፖሊስ አስከሬኑን አግኝቶ ጓደኞቹ እና ቤተሰቡ የቀረውን አስከሬኑን ወስደው በክብር ቤተክርስቲያን ቀበሩት። 

ይህ በእንዲህ እያለ መከላከያ መቀሌን ለቆ ሲወጣ ህወሓት መቀሌ ሲገባ ህወሓት በተቀበረው የኢንጅነር እምብዛ ታደሰ ተረፈ አስከሬን ላይ የፈጸመው የግፍ ግፍ የሚዘገንን ነው።የህወሓት ሰዎች ህዝብ እያየ የኢንጅነር እምብዛ ታደሰ ተረፈ አስከሬን ከተቀበረበት ቤተክርስቲያን እንዲወጣ አድርገው ሜዳ ላይ እንዲጣል ካደረጉ በኋላ የተረፈውን አስከሬን የሌሊት ጅብ እንዲበላው መደረጉ የመቀሌ ወሬ ነው።ይህ ሁሉ የሚሆነው ለትግራይ ህዝብ አይደለም።ለእነደብረጽዮን እና ጌታቸው ረዳ ስልጣን ሲባል 

ይህንን አስመልክቶ ጋዜጠኛ ሔርሜላ አረጋዊ በትዊተር ገጿ ዛሬ ኢንጅነር እምብዛን  አስታውሳዋለች።በሌላ በኩል የአሓዱ ራድዮ ጋዜጠኛ ፍሬወይኒ ገብረ ጻዲቅ ገብሩ በፌስቡክ ገጿ ላይ ድርጊቱን የገለጸችበት ከስር ይመልከቱ።

የጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ ትዊተር መጋቢት 11፣2014 ዓም






No comments:

Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሃራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)

Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሐራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)