ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, March 16, 2022

በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ባለፉት 9 ወራት ውስጥ ብቻ ወደ 1.2 ሚልዮን የኖርዌይ ክሮነር ወይንም ከ7 ሚልዮን ብር በላይ በማዋጣት ለዓባይ ግድብ ማሰርያ፣በጦርነት ለተጎዱ ወገኖች የሚሆን ለአማራ ክልል፣ለአፋር ክልል እና ለአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ልከዋል።ተቀባዮቹም የምስጋና እና ማረጋገጫ ልከዋል።(የምስጋና ደብዳቤዎቹን ይዘናል)

==============
ጉዳያችን/Gudayachn
==============

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሃገራቸው በደረሰው የጦርነት ተጎጂዎችን የማቋቋም እና የዕለት ደራሽ ዕርዳታ የሚሆን ድጋፍ ማድረጋቸው በተለያየ ጊዜ ተዘግቧል።በሰሜን አውሮፓ የምትገኘው በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም ካለፈው ግንቦት ወር ወዲህ ብቻ ከ7 ሚልዮን ብር በላይ በማዋጣት ለዓባይ ግድብ ማሰርያ፣በጦርነት ለተጎዱ ወገኖች የሚሆን ለአማራ ክልል፣ለአፋር ክልል  እና ለአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን በተናጥል ልከዋል።ተቀባዮቹም የምስጋና እና ማረጋገጫ ልከዋል።

ሁሉም መዋጮዎች ከኢትዮጵያ ማኅበረሰብ (ኮምዩኒቲ) በኖርዌይ ጋር በመተባበር እና በኖርዌይ የሚገኙ የተለያዩ የሲቪክ ድርጅቶች በጥምረት በፈጠሩት ቅንጅት የተከናወነ ነው። በእዚህም የማስተባበር ሥራ ላይ በኖርዌይ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ጋር በመተባበር በኖርዌይ የኢትዮጵያ ስኮላርስ ግሩፕ፣በቅርቡ የተመሰረተው እንቁም ለኢትዮጵያ እና ሌሎች የሲቪክ ድርጅቶች በማስተባበር ሥራው ላይ የተሳተፉ ሲሆን በሁሉም የመዋጮ ሂደት ላይ ያዋጡ ሰዎች በቫይበር ቡድን (ግሩፕ) ላይ ስማቸው እየተጻፈ እንዲያዩት በማድረግ የተከናወነ ነው። 

በእዚህ መሰረት 

1) ባለፈው ግንቦት ወር 2013 ዓም ለአባይ ግድብ ፕሮጀክት ወደ ፕሮጀክቱ ባለቤት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ባለስልጣን የግድቡ ፕሮጀክት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የባንክ ሂሳብ 331,659.00 የኖርዌይ ክሮነር የተላከ ሲሆን ከእዚህ በተጨማሪ 30ሺህ የኖርዌይ ክሮነር በስቶኮልም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለግድቡ በከፈተው ሂሳብ ገብቷል።በድምር ለግድቡ ከኖርዌይ ባለፈው 9 ወራት ውስጥ ብቻ 361,659 የኖርዌይ ክሮነር ተዋጥቶ ተልኳል።

2) ባሳለፍነው መስከረም ወር መጨረሻ ላይ ደግሞ ለአፋር እና አማራ ክልል በጦርነቱ ለተጎዱ ወገኖች ለሁለቱም ክልሎች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳባቸው ለየብቻ በመክፈል በድምር 342,411 የኖርዌይ ክሮነር ገብቷል።

3) በመጨረሻም ባሳለፍነው የየካቲት ወር 2014 ዓም ደግሞ ለአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት 525,938 የኖርዌይ ክሮነር በቀጥታ ገቢ ተደርጓል።

ባጠቃላይ በኖርዌይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በዘጠኝ ወራት ውስጥ የምንዛሪ ጊዜው በተለያየ ጊዜ እንደተላከበት ወቅት ቢለያይም ወደ 1ነጥብ 2 ሚልዮን የኖርዌይ ክሮነር ወይንም ከ7 ሚልዮን ብር በላይ ወደ ሃገር ቤት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል አስገብተዋል።

ከእዚህ በታች በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለላኩት ገንዘብ ተቀባይ ተቋማት የላኩት የምስጋና ደብዳቤ ያገኛሉ።ከላይ ከተላከው ገንዘብ ላይ በጣም አነስተኛ ገንዘብ ለባንክ ቻርጅ ተከፍሏል።የምስጋና ደብዳቤዎቹ በቫይበር ቡድን (ግሩፕ) ላይ ለሕዝብ እንዲያውቀው የተሰራጩ ሲሆን ሁሉም ገንዘብ ከኖርዌይ ወደ ኢትዮጵያ በቀጥታ የባንክ ለባንክ ስዊፍት ማስተላለፍያ መንገድ የተላከ  ነው።በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ቁጥራቸው አነስተኛ ቢሆንም ያደረጉት አስተዋጾ ግን የሚናቅ አይደለም።


ከአፋር ክልል የተላከ የምስጋና ደብዳቤ

ለዓባይ ግድብ የተዋጣ ምስጋና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ




ከአማራ ክልላዊ መንግስት የተላከ የምስጋና ደብዳቤ




የአደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን የምስጋና ደብዳቤ



No comments:

ሐያ ገዳማት የሚገኙበት በግሪክ የሚገኘው የአቶስ ተራራ ገዳማውያን አኗኗር (ቪድዮ)

ገዳሙ ከሰርብያ፣ሮማንያ፣ቡልጋርያና ሩስያ የመጡ ዓለምን የናቁ መነኮሳት ገድመውበታል።