ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Sunday, March 13, 2022

የብልፅግና ፓርቲ የሦስት ቀን ጉባዔውን ፈጽሟል።አርባ አምስት የስራ አስፈፃሚ አባላት መርጧል።የተመረጡ የሥራ አስፈፃሚ ዝርዝሩን ይዘናል።

ጉባዔው በከፊል (ፎቶ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን)
==============
ጉዳያችን/Gudayachn
==============
  • ብልፅግና ፓርቲ ከብሔር ተኮር የፖለቲካ ፓርቲነት ይልቅ ሕብረ ብሔራዊ ፌድራል የፖለቲካ ፓርቲ እንደሚሆን ገልጿል።
  •  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን በተመለከተ መንግስት በቤተክርስቲያን ጉዳይ እንደማይገባ በሕገ መንግስቱ የተደነገገ መሆኑን አንቀጽ ጠቅሰው የገለጡት የፓርቲው ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ነገር ግን  መንግስት ሲወጣ ተቃዋሚዎች ይግቡ ማለት አይደለም ብለዋል።
  • የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ሰኞ መጋቢት 5፣2014 ዓም የመጀመርያ ስብሰባውን ያደርጋል።
ባለፈው ዓመት ምርጫ ያሸነፈው ገዢው የብልፅግና ፓርቲ ጠቅላላ ጉባዔውን ከመጋቢት 2 እስከ 4፣2014 ዓም በአዲስ አበባ አድርጓል።ጉባዔው ፕሬዝዳንቱን እና ምክትል ፕሬዝዳንቱን የመረጠ ሲሆን በእዚሁ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የፓርቲው ፕሬዝዳንት፣ አቶ ደመቀ መኮንን እና አቶ አደም ፋራህ በምክትል ፕሬዝዳንትነት የተመረጡ ሲሆን ፓርቲው ብልፅግና ፓርቲ ከብሔር ተኮር የፖለቲካ ፓርቲነት ይልቅ ሕብረ ብሔራዊ ፌድራል የፖለቲካ ፓርቲ እንደሚሆን ገልጿል።

ፓርቲው በመጨረሻ ቀኑ ስብሰባ ላይም የማዕከላዊ እና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን የመረጠ ሲሆን በእዚህ መሰረት ለማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሚሆኑ መስፈርቱን አስቀምጧል። ይሄውም ለማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሚሆን ሰው ሊኖሩት ከሚገቡት መስፈርቶች ውስጥ የሚከተሉት በስብሰባው ላይ ተገልጸዋል። 

1) ቢያንስ የመጀመርያ ዲግሪ ያለው፣
2) የፖሊሲና ስትራቴጂ ጉዳዮች የሚረዳ፣
3) የወደፊቱን አሻግሮ መመልከት የሚችል፣
4) ከማናቸውም ዋልታ ረገጥ የጽንፍ አስተሳሰብ የራቀ፣
5) በስነምግባር የታነጸ፣
6) በኢትዮጵያ አንድነት የሚያምን የሚሉት ይገኙበታል።

በስብሰባው ላይ በፓርቲው ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የምጣኔ ሃብት እና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጡ ማብራርያዎችም ነበሩ።ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተነሱት ጉዳዮች መሃል ኢትዮጵያ ወቅታዊውን የዓለም ሁኔታ ተጠቅማ ለማደግ ያላትን መንገድ በቶሎ መጠቀም እንዳለባት ሲጠቅሱ ''የዓለም ወቅታዊ ሁኔታ አይሸታችሁም? ይህንን ዓይነት ሁኔታ ተጠቅመው የሚሰሩ ሃገሮች ናቸው ሊያድጉ የሚችሉት '' በማለት ጠቁመዋል። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን በተመለከተ መንግስት በቤተክርስቲያን ጉዳይ እንደማይገባ በሕገ መንግስቱ የተደነገገ መሆኑን አንቀጽ ጠቅሰው የገለጡት የፓርቲው ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ነገር ግን  መንግስት ሲወጣ ተቃዋሚዎች ይግቡ ማለት አይደለም ብለዋል።


 በምርጫው ላይ የዕጩ ጥቆማ የተደረገው ሌላው ክልል ለሌላ ክልል ዕጩ መሆኑ የብሔር ተወላጅ ብቻ የራሱን ብሔር ባብዛኛው ያልጠቆሙበት ሂደት ታይቷል።
ጉባዔው በመጨረሻ ቀን ስብሰባው የአቋም መግለጫ ያወጣ ሲሆን  225 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት እና 45 ሥራ አስፈፃሚ አባላትን መርጧል።በእዚህ መሰረት ከእዚህ በታች ያሉት ለሥራ አስፈፃሚነት ተመርጠዋል። እነርሱም፣

በዚሁ መሰረት የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት የሚከተሉት ናቸው፦

1. ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ
2. አቶ አደም ፋራህ
3. አቶ ደመቀ መኮንን
4. አቶ ደስታ ሌዳሞ
5. ዶ/ር ፍጹም አሰፋ
6. አቶ አብርሃም ማርሻሎ
7. አቶ አሻድሊ ሀሰን
8. አቶ ጌታሁን አብዲሳ
9. አቶ ኡሙድ ኡጁሉ
10. አቶ ተንኳይ ጆክ
11. አቶ ኦርዲን በድሪ
12. አቶ አሪፍ መሃመድ
13. ዶ/ር አብርሃም በላይ
14. ዶ/ር ሊያ ታደሰ
15. ሀጂ አወል አርባ
16. ሀጅሊሴ አደም
17. አቶ ኤሌማ አቡበከር
18. ወ/ሮ ሀሊማ ሀሰን
19. አቶ ሙስጠፌ መሀመድ
20. አቶ አህመድ ሽዴ
21. ዶ/ር ነጋሽ ዋጌሾ
22. አቶ ፀጋዬ ማሞ
23. ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል
24. አቶ ተስፋዬ በልጅጌ
25. አቶ ርስቱ ይርዳው
26. አቶ ተስፋዬ ይገዙ
27. አቶ ሞገስ ባልቻ
28. አቶ ጥላሁን ከበደ
29. አቶ መለሰ ዓለሙ
30. አቶ ሽመልስ አብዲሳ
31. አቶ ፍቃዱ ተሰማ
32. ዶ/ር አለሙ ስሜ
33. ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ
34. አቶ አወሉ አብዲ
35. አቶ ሳዳት ነሻ
36. ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
37. ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ
38. ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ
39. ዶ/ር ይልቃል ከፍያለ
40. ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ
41. አቶ ተመስገን ጥሩነህ
42. አቶ መላኩ አለበል
43. ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ
44. ዶ/ር ሰማ ጥሩነህ
45. አቶ ግርማ የሺጥላ ናቸው።

የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ሰኞ የመጀመርያ ስብሰባውን እንደሚያደርግ ለማወቅ ተችሏል።

No comments:

በኢትዮጵያ የእገታ ወንጀል ተሳታፊ አራት አካላት ናቸው። ለችግሩ የመፍትሄ አካላት ሁለት ናቸው።ሁለቱ አካላት ምን ይስሩ?

======= ጉዳያችን ======= በኢትዮጵያ ዜጎችን እያገቱ ገንዘብ የሚቀበሉ ወንጀለኞች ከተራ ወንጀለኝነት አልፎ በታጣቂ ቡድኖች የገንዘብ ማግኛነት መዋል ብቻ ሳይሆን ዜጎችን የማሸበርያ ፋሺሽታዊ ተግባር ሆኗል። እገታ የ...