ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, January 11, 2021

ለሁለት ወራት የሚቆይ ኢትዮጵያን እና የኢትዮጵያ የሆኑትን መልካም ነገሮች ሁሉ ለቀሪው ዓለም የማጉላት (Rising Ethiopia) የዲጂታል ዘመቻ ተጀምሯል።ኢትዮጵያውያን በያሉበት መተባበር አለባቸው።



ከስር የዘመቻው ትውተር፣ዩቱብ እና ፌስ ቡክ ሊንኮች እንዲሁም  የሦስት ወራት ፕሮግራም ያገኛሉ።
ማሳሰቢያ - ይህ ዜና ተጨማሪ መረጃዎች (updates) አሁን ተካተውበታል።

በእንግሊዝ ሀገር ነዋሪ በሆኑት ዶ/ር በላቸው ጨከነ ተስፋ በተባሉ ኢትዮጵያዊ ሃሳብ አፍላቂነት እና አስተባባሪነት ፣በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ባሕል እና ቱሪዝም ዕውቅና የተጀመረው የኢትዮጵያን ስም ለቀረው ዓለም የማጉላት (Rising Ethiopia) ዘመቻ የተጀመረው ባለፈው እኤአ ዴሴምበር 30 ሲሆን እስከ መጪው እስከ የካቲት 21/2021 ዓም እኤአ የሚቆይ ዘመቻ ነው።በዘመቻው የዌብነር መክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ ክብርት / ጽዮን ተክሉ በኢትዮጵያ በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር  የዲያስፖራ እና ኢኮኖሚ ዲፒሎማሲ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ፣ክቡር  አምባሳደር ተፊሪ መለሰ በዩኬ እና አይርላንድ  የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር፣ክብሩ አቶ ስለሺ ግርማ የቱሪዝም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስክያጅ እና የኢትዮጵያ ባሕል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከፍተኛ አማካሪ፣መቀመጫቸውን በአፍሪካ እና እስያ ያደረጉ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች፣የቱሪዝም እና አስጎብኚ ድርጅት ባለቤቶች እና ሌሎች ከ100 በላይ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን በእዚሁ መክፈቻ መርሃግብር ላይ የመርሃግብሩ ሃሳብ አመንጪ እና አስተባባሪ ዶ/ር በላቸው ጨከነ ተስፋ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ እምቅ የሆነ  የቱሪዝም መዳረሻ፣ የኢንቨስትመንት አማርጫ፣ የተማረ የሰው ሃይል ሀብት በሀገረ  ውስጥ እና 3.5 ሚሊዮን በላይ የሚገመት ኢትዮጵያዊ እና ትውልደ ኢትዮጵያው በመላው ዓለም ያላት ሀገር መሆኗን አብራርተዋል።

ዶ/ር በላቸው ጨከነ በእዚሁ ንግግራቸው በተጨማሪም የዘመቻው ዋና ዓላማ በኢትዮጵያ የሚገኘውን  ይህን ሀብት በውጪ የሚገኘውን ኢትዮጵያው እና ትውለድ ኢትይጵያዊ በመጠቀም ለዓለም ለማሳውቅ እና በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እደገት ጉልህ ድርሻ እንዲኖረው ያለመ መሆኑንና ከኢትዮጵያ ውጪ ያሉ የንግድ ድርጅቶችን በየአካባቢያቸው  በማስተዋወቅ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ አቅማቸውን ማጠናከረም ዘመቻው አካል መሆኑን አብራርተዋል።በመቀጠልም ዶ/ር በላቸው ኢትዮያን የማጉላት ዘመቻው አራት ዋና ዋና ክፍሎችን የያዘ መሆኑን ገልጠዋል።እነርሱም -

በመጀመሪያው ክፍል ማለትም ከታህሳስ 21(Dec 30) - ጥር 14(Jan 24)  እምቅ የኢትዮጵያን የቱሪዝም  መዳረሻነት እና ድንቅ የሆነውን ባህላችን  የምናስተዋውቅበት ጊዜ ሲሆን  በእነዚህ ሶስት ሳምንታት የኢትዮጵያ ታሪካዊ ቦታዎች፣ መንፈሳዊ በዓላት፣ ወንዞች እና ሐይቆች፣ ተራሮች፣ የዱር እንሰሳት፣ ሙዚየሞች፣ ኪነ ጥበባችን፣ አለባበሳችን እና አመጋገባችንን ለዓለም በማሕበራዊ ሚድያዎች በሰፈው የምናስተዋውቅበት ይሆናል በእነዚህ ሳምንታት ኢትዮጵያዊያን የባህል ልብሳቸውን እንደአመቺነቱ በሥራ ቦታቸው ለአንድ ቀን በመልበስ እና ፎቶአቸውን በማጋራት፣   ትናንሽ ስጦታዎችን ለሌው ማህብረሰብ በመሰጠት ኢትዮጵያን በቀላሉ የሚያስተዋውቁበት ነው። በዚህ ሳምንት የኢትዮጵያ አየር መንገድም በሰፊው ይተዋወቃል። ኢትዮጵያ የጎብኚዎች አማርጭ እንድትሆነ በሰፈው ይሰራል።


በሁለተኛ  ክፍል  ከጥር 15 (25 Jan) - ጥር 22 (31 Jan) ድረስ  ከኢትዮጵያ ውጪ በየሀገሩ ያሉ የንግድ ድርጅቶችን በየአካባባያቸው ባሉ ኢትዮጵያዊያን የሚተዋወቁበት ሳምንት ነው ይሄውም ኢትዮጵያዊን በዓለም አቀፍ ደረጃ በያሉበት ብቁ እና ተወዳዳሪ ድርጅቶች እንዲኖራቸው ያግዛል  


የኢትዮጵያዊያን ተወዳዳሪ መሆን ወደ ሀገር ቤትም ኢንቨስት ለማደረግ እና ከኢትዮጵያ ወደ ውጪ ለመላክ (Export) ትልቅ አቅም ይፈጥራል።  በዚህ ሳምንት ኢትዮጵያዊያን በየአሉበት ሀገር የሚያውቃቸውን  የኢትዮጵያውን የሒሳብ አማካሪዎች፣ ሱቆች፣ የሕግ ባለሞያዎች፤ ምግብ ቤቶች፣  የኢንፎርሚሸን ቴክኖሎጂ ተቋማት፣ ኮሌጆች፣ የመኪና መሸጫዎች፣ የሕክምና ተቅዋማት  አድራሻ እና ስለአገልግሎታቸው  በማኅበራዊ ሚድያ ይተዋወቃል።


ሶስተኛው ክፍል ከጥር 23 (Feb 1 ) - ይካቲት 7 (Feb 14) የኢትዮጵያ እንቨስትመንት ሳምንት ነው። በዚህ ሳምንት የኢትዮጵያን እምቅ የእንቨስትመንት አቅም በኢንዱስትሪው፣ በእርሻ በኃይል አቅርቦት፣ በማዕድን ፍለጋ ዙርያ የሚተዋውቅበት ነው። በኤምባሲዎች በኩል ውይይቶችን፣ በኢንቨስትመንት ቢሮ በኩል ደግሞ የኢንቨስትመንት አማራጮችን የሚያሳዩ ዶክምነትሪዎች ለሌሎች እንዲጋሩ ይደረጋል በኢትዮጵያም እስካሁን ኢንቨስት ያደርጉ በጎ ልምዳቸውን እንዲያጋሩ ይደረጋል። የታወቁ ኢትዮጵያዊያን  የኢንቨስት አማራጮቻችንን እንዲያስተዋውቁ ይሆናል።


የመጨረሻው እና አራተኛው ክፍል ከየካቲት 8 (Feb 15) - የካቲት 14 (Feb 21) የመስጠት ሳምንት (Giving weeks) ነው - በዚህ ሳምንት ኢትዮጵያውያን በእያሉበት በኢትዮጵያ ለሚከናወኑ መልካም ፕሮጀክቶች ማለትም  ሕዳሴ ግድብ፣ ኮቪድን ለመከላከል፣ ለበጎ አድራጊ ድርጅቶች  እና ለሌላም ፕሮጀችክቶች የገንዘብ ደጋፍ የሚያደርጉበት እና ለኢትዮጵያ የሚጠቅሙ መልካም ግንኙነቶችን የሚፈጥሩበት ሳምንት እንደሚሆን ዶ/ር በላቸው አብራርተዋል።


የኢትዮጵያን ስም ለማጠልሸት የውጭ ሚድያዎች ሳይቀሩ በተረባረቡበት በእዚህ ጊዜ፣ በሀገር ውስጥም ሆነ በመላው ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ይህንን ዘመቻ በትዊተር፣በፌስ ቡክ፣ዩቱብ እና ሌሎችም መንገዶች ሁሉ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ሊያደርጉ ይገባል። 

ከእዚህ በታች የዘመቻው ትውተር፣ዩቱብ፣ፌስ ቡክ ሊንኮች እና የሦስት ወሮች ፕሮግራም ያግኙ።

የትውተር ሊንክ = https://twitter.com/RisingEthiopia  

የፌስ ቡክ ሊንክ= https://www.facebook.com/RisingEthiopia1/


የዘመቻው የሦስት ወሮች ፕሮግራም 

============
ማስታወቂያ 
============
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...