ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, January 27, 2021

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ወጣት ዲና (Dina) በመጪው ቅዳሜ በኖርዌይ ቴሌቭዥን ለመሎዲ ግራንድ ፕሪክስ ውድድር ትቀርባለች።በስልክዎ ድምፅ በመስጠት እንድታሸንፍ ያድርጉ።

Etiopisk-norske, Dina Matheussen, er blant fire artister for Melodi Grand Prix.

በኖርዌይ ነዋሪ የሆነችው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ወጣት ዲና (Dina) ከአዲሱ ነጠላ ዜማዋ ላይ የተወሰደ ፎቶ 


ጉዳያችን/Gudayachn

ዲና ማቴዎስ ትባላለች።ነዋሪነቷ በኖርዌይ የሆነና ትውልደ ኢትዮጵያ የሆነች የ17 ዓመት ወጣት ነች።ገና 12 ዓመት እያለች ነው የዳንስ እና የድምፃዊነት ስራዋን የጀመረችው።ዲና የሙዚቃ ሰው ብቻ አይደለችም።በካራቴ ስልጠና ባለ ጥቁር ቀበቶ ተሸላሚም ድንቅ ወጣት ነች።

በ2014 ዓም እኤአ በኖርዌይ ቲቪ ቻናል 2 ላይ በሚቀርብ የኖርዌይ ታለንት ውድድር ላይ ከፍተኛ አድናቆትን አትርፋ ነበር።በ2017 ዓም በኖርዌይ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን (ኤንአርኮ) የዓመቱ የዳንስ ውድድር ላይም ተሳትፋ ነበር።ባለፈው ዓመት በኖርዌይ አይዶል 2020 ላይ የበዮንሴን "Run the World (Girls)" የተሰኘውን ሙዚቃ በማቅረብ የኖርዌይ አድናቂዎቿን አስደምማለች።በ2019 ዓም በኖርዌይ ብሮድካስት ቴሌቭዥን (ኤንአርኮ) ቻናል 3 ላይ ''አንድ ነን'' ''we are one'' በሚል ያቀረበችው ሙዚቃ ላይ የት መጣ መሰረቷ ኢትዮጵያ መሆኑን በመድረኩ ላይ አሳይታበት ተመልካቾችን ሁሉ አስደንቃለች።

የዲና ተግባራት እነኝህ ብቻ አይደሉም።በእየዓመቱ ወደ ኢትዮጵያ እየሄደች የኦቲዝም እና ልዩ ልዩ ችግር ያለባቸውን ልጆች ለእዚሁ ሥራ ብላ ባጠራቀመችው ገንዘብ ትረዳለች።በያዝነው ዓመት ወደ ኢትዮጵያ ለተመሳሳይ መልካም ተግባር መሄድ ያልቻለቸው በኮቪድ ወረርሽኝ ሳብያ ነው።አሁንም ግን ኢትዮጵያውያንን ለመርዳት ገንዘብ እያጠራቀመች እንደሆነ እና መርዳቷን እንደምትቀጥል በያዝነው ሳምንትም ባደረገችው ቃለ መጠይቅ ገልጣለች።

ከዲና ጋር ያለፉት ሌሎች አራት አርቲስቶች ካርሰን (Karsten)፣ኤሚ (Emmy) እና ኡለ ሀርዝ (Ole Hartz)
FOTO: JULIA MARIE NAGLESTAD / NRK

ዲና የአሁኑ ቅዳሜ ጥር 22/2013 ዓም (ጃንዋሪ 30/2021ዓም) የኖርዌይ ብሮድካስት ቴሌቭዥን የኖርዌይ ሜሎዲ ግራንድ ፕሪክስ (Norsk Melodi Grand Prix) ውድድር  ከተመረጡት አራቱ ውስጥ ገብታለች።በውድድሩ ሰዓት ዲና እንድታልፍ ኢትዮጵያውያን በስልክ በሚሰጠው ድምፅ በመስጠት ተሳታፊ እንዲሆኑ ተጠይቀዋል።የኖርዌይ ቴሌቭዥን (ኤን አር ኮ -NRK) ''ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ዲናዬ በዘፈኗ ውስጥ የአማርኛ ቃላት እንዲገቡ ያደረገችው መነሻዋ ከኢትዮጵያ መሆኑን ለማመልከት ነው'' በማለት ገልጦታል።

ዲና የቅዳሜውን ውድድር አልፋ ለፍፃሜው ስትደርስ በአውሮፓ ደረጃ ለሚደረገው ዋናው ውድድር ደረሰች ማለት ነው።በእዚህም አንዲት ትውልደ ኢትዮጵያዊት ለአውሮፓ ምርጥ ውስጥ ስትገባ የመጀመርያዋ ያደርጋታል ማለት ነው።በመሆኑም በቅዳሜው ምሽት ውድድር ላይ ኢትዮጵያውያውያን፣ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ኖርወጅያውያን ለዲና በስልካችሁ ድምፅ በመስጠት ኃላፊነታችሁን መወጣት አትዘንጉ።

ከእዚህ በታች ዲና ከሦስት ቀናት በፊት የለቀቀችውን ነጠላ ዜማ ከዩቱቧ ላይ ያለውን ከስር ይመለከቱ።


============
ማስታወቂያ 
============
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

No comments:

የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...