ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, January 26, 2021

አስደናቂዋ ክብርት ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ግብፅ በኢትዮጵያ አንፃር በአፍሪካ ለመቆለፍ የሞከረችውን ዲፕሎማሲ አንድ በአንድ እየተረተሩት ነው።

ክብርት ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ

ጉዳያችን/Gudayachn 

>> ከጽሁፉ ስር አንድ ወጣት ታንዛንያዊ በክብርት ፕሬዝዳንት ጉብኝት ተደስቶ ጉብኝቱን በቪድዮ ያቀናበረውን ይመልከቱ።

የአንደኛ  እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአዲስ አበባ ሊሴ ገብረማርያም የፈረንሳይኛ ትምህርት ቤት ተምረዋል።በመቀጠለም በፈረንሳይ ሀገር የሚገኘው ሞንትፒለር ዩንቨርስቲ ተምረዋል።ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከአምባሳደር ዮዲት እምሩ ቀጥለው ሁለተኛ ሴት ኢትዮጵያዊ አምባሳደር ናቸው።በአምባሳደርነት በሴኔጋል መቀመጫቸውን አድርገው የማሊ፣ከፕቨርድ፣ጊኒ ቢሳው፣ጋምብያ እና ጊኒ አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል።በጅቡቲ አምባሳደርነታቸው ደግሞ የኢጋድ ተጠሪ ሆነው አገልግለዋል።ከእዚህ በተጨማሪ በፈረንሳይ አምባሳደርነታቸው ደግሞ የመንግሥታቱ ድርጅት የዩኔስኮ ዋና ተጠሪ ሆነው አገልግለዋል።በናይሮቢ ደግሞ የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ፀሐፊ ባንኪሙን ዋና መልክተኛ እና የቢሮ ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል።

ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ላለፉት ሁለት ዓመታት ከፕሬዝዳንትነት ስራዎቻቸው በተጨማሪ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ መታገዝ ባለበት ሁሉ እየተገኙ ክፍተቱን በመሙላት እየሰሩ ያሉት ተግባር ትልቅ ፍሬ እያፈራ ነው።በዲፕሎማሲው የረጅም ጊዜ ልምድ አላቸው የሚባሉት የግብፁ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሳማህ ሽኩሪ ከሀገር ሀገር እየዞሩ በኢትዮጵያ ላይ የዲፕሎማሲ ዘመቻ እንዲከፈት ያልረገጡት ምድር የለም።ከእነኝህ ሀገሮች ውስጥ የአፍሪካ ሀገሮች ተጠቃሽ ናቸው።ከእነኝህ ሀገሮች ውስጥ ታንዛንያ እና ኮንጎ ይጠቀሳሉ።በእዚህ በኩል ክብርት ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከኬንያ እስከ ዩጋንዳ፣ከደቡብ አፍሪካ እስከ ፈረንሳይ፣ሰሞኑን ደግሞ ከታንዛንያ እስከ ኮንጎ ድረስ ግብፅ ለመቆለፍ የሞከረችውን የኢትዮጵያን ዲፕሎማሲ በአፍሪካ አንድ በአንድ እየፈቱት ነው።በእርግጥ በአፍሪካ አንፃር ቀድሞም ኢትዮጵያ በአፍሪካውያን ዘንድ ከፍ ያለ ከበሬታ አላት። ይህንን ከበሬታ ግን በአግባቡ ተረድቶ የሚያፋፍመው ጥበበኛ ዲፕሎማት ይፈልግ ነበር።ክብርት ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ  ዘውዴ ሰሞኑን በታንዛንያ እና በኮንጎ ያደረጉት ጉብኝት ትልቅ ትኩረት በአፍሪካውያን ወጣቶች ዘንድ ሳይቀር ትኩረት እና ከበሬታ አግኝቷል።

ግብፅ የታንዛንያ እና ኮንጎን ድጋፍ ለማግኘት ስትጥር ሰንብታለች።በታንዛንያ ኢንቨስትመንት ዘርፍ ሲሆን ኮንጎን ደግሞ ከደቡብ አፍሪካ ቀጥላ ቀጣይ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር በመሆኗ ማባበሉ በዝቶ ነበር።የፈረንሳይኛ ተናጋሪ ክብርት ፕሬዝዳንት ሳሕለወርቅ ዘውዴ ዛሬ ኮንጎዎችን በፈረንሳይኛ እያናገሩ ከደረሱበት አንዱ ስምምነት ውስጥ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኮንጎ እንዲከፈት የሚለው ይገኝበታል።''ነቢይ በሀገሩ'' ሆኖ ነው እንጂ ክብርት ፕሬዝዳንቷ የሰሩት ዲፕሎማሲያዊ ጀብዱ ትልቅ ከበሬታ የሚያስገኝላቸው ነው።እናመሰግናለን! ክብርት ፕሬዝዳንት ልንላቸው ይገባል።

ከእዚህ በታች የምትመለከቱት ቪድዮ ክብርት ፕሬዝዳንት ሰሞኑን በታንዛያ ያደረጉት ጉብኝት የሚያሳይ ቪድዮ ነው።ቪድዮውን ያዘጋጀው ወጣት ታንዛንያዊ ነው።ምን ይህል በአፍሪካውያን ዘንድ በተስፋ እንደምንጠበቅ አስተማሪ ነው።


============
ማስታወቂያ 
============
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...