ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, January 25, 2021

የፀጥታ ስጋት የነበረባቸው በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር አዲስ አበባ ተመለሱ።አምባሳደሩ ከካርቱም ወደ ኢትዮጵያ በመኪና ለመግባት ጠይቀው ነበር።


በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ
ጉዳያችን ዜና / Gudayachn News
  • የእስራኤል ደህንነት ሚኒስትር ኤሊ ኮህን (Eli Cohen) ዛሬ ሰኞ ካርቱም ነበሩ። 
በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በካርቱም የፀጥታ ስጋት እንደነበረባቸው እና ወደ ኢትዮጵያ በድንበር በኩል ለመግባት የሱዳንን መንግስት ጠይቀው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።ሆኖም የሱዳን መንግስት በድንበር ውጥረቱ ምክንያት በመኪና ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን ለደህንነታቸው ጥሩ አለመሆኑን እንደገለጠላቸው የቱርኩን አናዶል ዜና ወኪልን ጠቅሶ ሚድል ኢስት ሞኒተር ዛሬ ማምሻውን ገልጧል።አምባሳደሩ በአሁኑ ጊዜ ወደ አዲስ አበባ በሰላም መብረራቸው እና መግባታቸው የሄው ምንጭ የፀጥታ ምንጮቹን መሰረት አድርጎ ገልጧል።

ዜናውን በተመለከተ የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መስርያ ቤት ያለው ነገር የለም።የአምባሳደሩ ወደ ኢትዮጵያ መመለስ እና ካርቱም ለአምባሳደሩ የፀጥታ ስጋት መሆኗ በራሱ ጥያቄ ቢሆንም በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለው ግጭት በቶሎ እንዲፋጠን የሚፈልጉ የውጪ ኃይሎችም ሆኑ ከትግራይ ሸሽተው ካርቱም የሚገኙ የቀድሞው ህወሓት ቡድን ደጋፊዎች በአምባሳደሩ ላይ አንዳች ዓይነት ጥቃት ከመፈፀም እንደማይመለሱ መገመት ቀላል ነው።

ኢትዮጵያ የሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር መውረር ምክንያት የሦስተኛ ሀገር እጅ እና በሱዳን በውስጥ ኃይሎች ፉክክር ጭምር የሚከናወን በመሆኑ ጉዳዩ በዲፕሎማሲ እንዲፈታ ጥረት አድርጋለች።ሆኖም ግን ይህ የኢትዮጵያ ትዕግስት አንድ ምሽት ላይ እንደሚያበቃ እና ድንገተኛ ማጥቃት ኢትዮጵያ ልትፈፅም እንደምትችል የብዙዎች ግምት ከመሆን አልፎ በሱዳናውያንም መሃል ከባድ  ፍርሃት ፈጥሯል።

ይህ በእንዲህ እያለ የእስራኤል ደህንነት ሚኒስትር በሱዳን ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ሰኞ ካርቱም መግባታቸው ተሰምቷል።ሚኒስትሩ ከሱዳን መከላከያ ሚኒስትር እና የደህንነት ሹሞች ጋር መነጋገራቸው ለማወቅ የተቻለ ሲሆን።የተነጋገሩበት ጉዳይ ግን ግልጥ አልተደረገም።ሆኖም ሀገሪቱ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ውጥረት በተመለከተ ሊሆን እንደሚችል ለመገመት ቀላል ነው።ሚኒስትሩ ዛሬ የአንድ ቀን ጉብኝት ካደርጉ በኃላ በተመሳሳይ ቀን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን ለማወቅ ተችሏል።

===================
============
ማስታወቂያ 
============
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

No comments:

የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...