ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, February 17, 2014

'' ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፈን የማንሰጥ ለመሆናችን ዋስትና እና ጥገኝነት እንዲሰጠን እንፈልጋለን'' የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጠለፋ ጉዳይ (latest)

 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው የተጠለፈው አይሮፕላን 

-ከ አዲስ አበባ ወደ ሮም ይበር የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 702 ጄኔቭ ላይ ዛሬ የካቲት 10/2006 ዓም በማዕከላዊ የአውሮፓ ሰዓት ከማለዳው 12 ከ 02 ሲሆን  እንዲያርፍ ተገዷል።

-  ሁሉም ተሳፋሪዎች እና አይሮፕላኑም በደህና ሁኔታ ላይ ይገኛሉ።

- ለ 2 ሰዓት ከ 45 ደቂቃ ተዘግቶ የነበረው የጀኔቭ አየር ማረፍያ  ተመልሶ ተከፍቷል።

- ጠላፊው ረዳት አብራሪው ነው።

- ዋና አብራሪው ወደ ሽንት ቤት ሲሄድ ረዳቱ ሽንትቤቱን ቆለፈበት እና አይሮፕላኑን ጠለፈው።

- አብራሪው ካለ አንዳች ማንገራገር እጁን ለስዊዝ ፖሊስ ሰጥቷል።ጥገኝነት እንዲሰጠውም ይፈልጋል።

- አይሮፕላኑ ውስጥ ከነበሩት ተሳፋሪዎች 143ቱ ጣልያናውያን ናቸው።

- ''ዘ ሎካል'' የተሰኘው የስዊዝ ጋዜጣ ዛሬ እንደዘገበው በስዊዘርላንድ ሕግ መሰረት ወንጀሉ እሰከ 20 አመት እስር ሊዳርግ ይችላል።

- ''ዘ ሎካል''  ጋዜጣ  አክሎም በድረ-ገፁ ላይ የጠላፊውን ቃል በድምፅ እንዲህ ሲል አሰምቷል '' ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፈን የማንሰጥ ለመሆናችን ዋስትና እና ጥገኝነት እንዲሰጠን  እንፈልጋለን''
''The local'' Switzerland news paper http://www.thelocal.ch/20140217/ethiopian-plane-lands-in-geneva-after-hijacking

ጉዳያችን
የካቲት 10/2006 ዓም 

No comments:

እነ አቶ አካለወልድ (የቀድሞው አቡነ ሳዊሮስ) ከዐቢይ መንግስት ጋር ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ ያቀዱት ቀድሞ እንደነበር አዲስ መረጃ ወጥቷል። በአዕምሯችን ውስጥ የሚነሱ በወቅታዊ የኢትዮጵያ እና የቤተክርስቲያን ጉዳይ ዙርያ 7 ጥያቄዎች እና አጫጭር መልሶች።

ቤተመንግስትም ያለህ መከላከያም ያለ የኦርቶዶክስ ልጅ ሥራህን ለማንም ትተህ እንዳትወጣ። ሃገር በጽንፈኛ እየፈረሰ ከኦርቶዶክሳዊነት ጎን እስከቆመ ድረስ ኢትዮ 360፣የቀድሞ የህወሃት አባል፣ኢህአፓ፣ የመቀሌ ልጅ፣የሱማሌ ፕሬ...