Friday, February 7, 2014

ወደ አዋጅነት ይቀየራል የተባለው ‹የሃይማኖት ተቋማት ምዝገባና የዕድሳት አገልግሎት›› ረቂቅ መመርያ ኃላፊነት የጎደለው እንዳይሆን የብዙዎች ስጋት ነው።

ፎቶ- ሐዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን 

 የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከ‹‹ኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ›› ጽ/ቤት ጋራ በመተባበር ያዘጋጀውና ከጥር 30 – የካቲት 2 ቀን 2006 ዓ.ም. በሐዋሳ – ሌዊ ሪዞርት ‹የሃይማኖት ተቋማት ምዝገባና የዕድሳት አገልግሎት›› ረቂቅ ላይ ለውይይት እንደሚቀርብ ለማወቅ ተችሏል። ይህ ከመመሪያ ወደ ዐዋጅነት ይቀየራል እየተባለ የሚነገርለት መመርያ ምንነት እስካሁን በዝርዝር አልታወቀም።

‹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአዋጁ ረቂቅ እንዲሰጣት እና አስተያየትና አቋም ለመውሰድ ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ያቀረበችው ጥያቄ ምላሽ  አለማግኘቱን ሐራ ተዋሕዶ የተሰኘው ብሎግ ጥር 28/2006 ዓም ገልጧል።

በኢትዮጵያ ከ 1952 ዓም ወዲህ ምንም አይነት ሃይማኖትን የተመለከተ አዋጅ  ወጥቶ አያውቅም። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከ 40 ሚልዮን በላይ ተከታዮች ያሏት እና ክርስትና ከተመሰረተ ጀምሮ ላለፉት ከ 2000 አመታት በላይ ለሆኑ ዘመናት  በኢትዮጵያ መንፈሳዊ አገልግሎት ለመስጠት የፍቃድ እና የምዝገባ መስፈርት ተጠይቃ እንደማታውቅ ይታወቃል።ደርግም በዘመኑ ምንም አይነት ሃይማኖታዊ አዋጅ አለማውጣቱ ይታወሳል።ይህ ወደ አዋጅ ያድጋል የተባለው መመርያ ኃላፊነት የጎደለው እንዳይሆን የብዙዎች ስጋት ነው።

ጉዳያችን
ጥር 30/2006 ዓም 

No comments:

በአቴንስ፣ግሪክ የምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን ላለፉት 40 ዓመታት በላይ ስትጠቀምበት የነበረውን ፖሊጎኖ የሚገኘው ቤተክርስቲያን በፖሊስ ታሸገ።የቅዱስ ሲኖዶስ አፋጣኝ ምላሽ እየተጠበቀ ነው።

የአቴንስ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን የታሸገችበት የጉግል የእንግሊዝኛ ትርጉም እና የግሪክኛ ዋናው ኮፒ። በግሪክ አቴንስ የምትገኘው እና ወደ ግማሽ ክ/ዘመን አገልግሎት ስትሰጥ የነበረችው እና በአቴንስ ፖሊጎኖ የምትገኘው የ...