ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, February 19, 2014

''ካፒቴን ኃይለ መድህን በአጎቱ ሚስጥራዊ ሞት ይሰጋ የነበረ ሰው ነበር።'' 'ስካይ ኒውስ ''በክፍልም ውስጥ ሆነ በሥራ ላይ 'ስማርት'የሆነ ልጅ ነበር'' አብሮት የተማረ እና የስራ ባልደረባው የነበረው ረ/አብራሪ ምስጢር ታዬ(ጉዳያችን አጭር ጥንቅር)




ዛሬ የካቲት 12/2006 ዓም 'ስካይ ኒውስ' ስለረዳት አብራሪ ኃይለ መድህን ጉዳይ አጎቱ አቶ ዓለሙ አስማማው ለአሶሼትድ ፕሬስ  በስልክ የሰጡትን ቃለ መጠይቅ መሰረት አድርጎ እንዲህ ብሏል።

''ኢትዮጵያዊው ፓይለት በአጎቱ አሟሟት ጉዳይ ጥርጣሬ (ስጋት ነበረበት)''

''የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ መምህር የነበሩት ዶ/ር እምሩ ስዩም ከቤታቸው ወደ ሚያስተምሩበት የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ሲሄዱ ሞተው ተገኝተዋል''

''የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ድረ-ገፅም ይህንንኑ አረጋግጦ ረዳት ፕሮፌሰር አለሙ አስማማው ጃንዋሪ 1 ቀን በድንገት ማለፋቸውን ፅፏል።''

''ሰኞ እለት የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ አቶ ሬድዋን ካፒቴን ኃይለ መድህን ከእዚህ በፊት ምንም አይነት የተመዘገበበት የወንጀል ሪከርድ የለም ብለዋል'' የስካይ ኒውስ ዜና መጨረሻ።

ከእዚሁ ጋር ተያይዞ ኢሳት በትናንትና ምሽት የራድዮ ዘገባው በአሜሪካ ከምትኖር የቤተሰቡ አባል ጋር እና አብሮት ከተማረ እና ከሰራ በኢንዶኔዥያ በሥራ ላይ ከሚገኘው ረዳት አብራሪ ምስጢር ታዬ ጋር ስለ ካፒቴን ኃይለ መድህን ቃለ መጠይቅ አድርጎ ነበር።

በቃለመጠይቁ ላይ የቤተሰብ አባሉም ሆኑ የትምህርት ቤት እና የስራ ባልደረባው ቃል አንድ ነው።በጣም ጎበዝ እና ሃገሩን የሚወድ ሰው የነበረ መሆኑን ሁሉም አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም የተለያዩ ዘገባዎች ሰሞኑን ስለ ወጣቱ ካፒቴን ሲገልፁ-ኃይለ መድህን ጎበዝ፣ሃገሩን የሚወድ፣በአስራሁለተኛ ክፍል  የመልቀቅያ ፈተና ላይ በሙሉ ''ኤ'' በማምጣት ወደ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ገብቶ የኢንጅነሪንግ ትምህርት መማሩን እና በመጨረሻ ላይ የአብራሪነት ስልጠና ለመውሰድ ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ እንደገባ፣ከሀገሩ ውጭ የመኖር አንዳች ፍላጎት እንደሌለው፣በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚፈፀመው ጭቆና ግን እረፍት የነሳው ኢትዮጵያዊ መሆኑ ተነግሯል።በኢትዮጵያ አየር መንገድ የደሞዝ እስኬል መሰረት የአንድ ረዳት አብራሪ ደሞዝ ከ 27 ሺህ እስከ 30 ሺህ ብር እንደሚደርስ ዘገባዎች ያሳያሉ።

የዘገባው ምንጮች -

     ስካይ ኒውስ February 19/2014 እ ኤ አቆጣጠር  http://www.skynews.com.au/world/article.aspx?id=951493

    ኢሳት ራድዮ የካቲት 11/2006 ዓም  (February 18/2014)

ጉዳያችን 
የካቲት 12/2006 ዓም 
'

No comments:

Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሃራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)

Beynouna Village - Ethiopia (Video) ባለፈው ሳምንት የተመረቀው መተሐራ እምብርት ላይ የተገነባው አስደናቄው የበይኑና ሪዞርት መንደር (ቪድዮ)