አንጀቴን አስሬ ፣
ከእኔ ይቅር ብዬ አንተን አስተምሬ፣
ዛሬ ያወቀ መስሎት…. ''ባዶ እግር'' ነህ አለኝ፣
ትስቅብኝ ጀመር ጫማ ስለሌለኝ፣
ባለጫማ መሆን መቼ ጠፋኝ እኔ፣
መልበስ መሽቀርቀሩ አንተን አደንቁሬ።
ላስተምርህ ብዬ እንጂ ነገ እንድትሻገር፣
መስሎኝ----እኔ መራቆቴ ላንተ ልሆን ማገር።
ግና ምን ያደርጋል አንተም አልተማርክም፣
ማስተዋል ነስቶሃል ከእኔ አልተሻልክም።
እናም ---እኔ ባዶ ሆኘ ያለበስኩበትን፣
እባክህ ክፈለኝ ያስተማርኩበትን።
ጉዳያችን
ጥር 30/2006
ምሽት ኦስሎ፣ኖርዌይ
No comments:
Post a Comment