ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, February 6, 2014

በምስራቅ ሐረርጌ የኦሮምኛ ተናጋሪ ተፈናቃዮች የሰሚ ያለህ! እያሉ ነው።የክልሉ ፕሬዝዳንት ለግል መታከምያ ከ 38 ሚልዮን ብር በላይ ከመንግስት ካዝና አውጥተው ታከሙ።


የሐረር ግንብ የጀርባ ገፅታ 

በምስራቃዊቷ ሐረርጌ  ከሱማሌ ክልል የሚነሱ ታጣቂዎች የኦሮምኛ ተናጋሪ ነዋሪዎችን በድንገት እየደረሱ ለተደጋጋሚ ጊዜ ሲያጠቁ የነበረ መሆኑ ይታወሳል።ባለፈው አመት ከተለያዩ ወረዳዎች ተፈናቅለው ቁምቢ ወረዳ ሚኖ ከተማ ዙርያ የሰፈሩት ሰፋሪዎች አሁንም የደህንነት ስጋት እንዳለባቸው ገለፁ።
አቶ መሐመድ ይባላሉ  በሱማሌ ታጣቂዎች የደረሰባቸውን በኦሮምኛ  ከኢዣ ጎዳ ወረዳ በታጣቂዎቹ ከተፈናቀሉ ወደ አንድ አመት እንደሆናቸው ሲያስረዱ እንዲህ ይላሉ-

''ችግሩ ሲጀመር የሱማሌ ክልል ሰዎች ድንገት ተኩስ ከፈቱብን እኛ ምንም ስለጉዳዩ መረጃ አልነበረንም።ብዙዎች ተገደሉ የቀሩት ወዴት እንደሄዱ ሳይታወቅ ጠፉብን።አውሬ የበላቸው አሉ።እስካሁን ድረስ ምንም ያየነው መሻሻል የለም።''

ወ/ሮ አልያ አልበከሪሽ ሌላዋ ተፈናቃይ ጉዳዩን እንባ እየተናነቃቸው ይገልፃሉ-

 '' የሱማሌ ክልል ታጣቂዎች ድንገት ተኮሱብን። ከብቶቻችንን፣ግመሎቻችንን፣ፍየሎቻችንን ሁሉ ያለንን ሁሉ ፈጁብን ቤታችንን ሁሉ አቃጥለውብን ሀብታችንን ሁሉ አጥተን ይሄው እዚህ ሰፍረን እንገኛለን። ባሌን አረዱብኝ። በተጨማሪም ሀብቴን በሙሉ ወሰዱ ሁለት ልጆቼን ገደሉብኝ።'' ብለዋል።

ወ/ሮ ዋሸካ የተባሉ ሌላ እናት ጉዳዩን ሲገልፁ-
'' ተኩስ ሲ ከፍቱብን ካለ ጫማ እና ልብስ ባዷችንን ተሰደድን።ልጆቻችንን በትነን በእግራችን ሽሽት ያዝን።የሞተብኝ ልጅ አለ የጠፋብኝም አለ።በረሃብ ምክንያት የሞተችብኝም አለች።'' በማለት አስረድተዋል።

ዜናውን ጥር 27/2006 ዓም ያጠናቀረው የቪኦኤ አማርኛው ክፍል ዘጋቢ መለስካቸው አምኃ የኦሮምያ ክልል የአደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ቢሮ ኃላፊ ስለጉዳዩ ሊያናግሩት እንዳልቻሉ እና ስብሰባ ላይ መሆናቸው እንደተነገረው ገልጧል።ከተፈናቀሉ አንድ አመት ያለፋቸው ዜጎች የሰሚ ያለህ! እያሉ ይጣራሉ።

ሰሞኑን አባ ዱላ የቀድሞ የኦሮምያ ክልል ፕሬዝዳንት( የአሁኑ የምክርቤት ቃል አቀባይ) የ 7 ሚልዮን ብር መኪና መንዳት ተገቢ ስለመሆን አለመሆኑ ማብራርያ መስጠታቸው ይታወቃል።አባ ዱላ የሀገር ውስጥ አዲስ የተገጣጠሙ መኪናዎችን ከ 7 ሚልዮን ከሚያወጡ መኪናዎች ጋር እያነፃፀሩ የኢህአዲግ ባለስልጣናት የትኛው እንደሚሻል ሃሳብ ሲሰጡ ምስራቅ ሐረርጌ ላይ ዜጎች ከተፈናቀሉ አመት አልፏቸው የሰሚ ያለህ ይላሉ።

ከሁለት ወር በፊት በእዚህ ደረጃ ግፍ የተፈፀመባቸው ዜጎች ጉዳይ ወደ ጎን ተትቶ ነው እንግዲህ ''የብሔር ብሔረሰቦች በዓል'' ተብሎ በሱማሌ ክልል ጅጅጋ በሚልዮን የሚቆጠር ገንዘብ ሲወጣ የነበረው።ከሱማሌ ክልል ልዩ ሚሊሻ ታጣቂዎች ጅጅጋን በበዓሉ ሰሞን ሲያሸብሩ መክረማቸው ለድርጊቱም ዳጎስ ያለ ገንዘብ ከኢህአዲግ ማግኘታቸው ይታወቃል።ይህ ብቻ አይደለም የኦሮምያ የወቅቱ ፕሬዝዳንት አቶ አለማየሁ አቶምሳ በአውሮፓ እና ሲንጋፖር ለህክምና ከ 38 ሚልዮን ብር ከመንግስት ካዝና መውጣቱ የተዘገበው እና በኢትዮጵያ ትልቅ የመነጋገርያ አጀንዳ የሆነውም በእዚህ ሳምንት ውስጥ ነው።ዜጎች ከአንድ አመት በላይ ተፈናቅለው የሚሰማቸው አጥተዋል የክልሉ ፕሬዝዳንት 38 ሚልዮን ብር አውጥተው ይታከማሉ።እሳት ስለ ጉዳዩ ሲዘግብ በኦሮምያ ምክር ቤት ውስጥ የነበሩ የ 38 ሚልዮኑን የህክምና ወጪ ጉዳይ ሲነሳ ''ተመልካች ያጣ'' ማለታቸውን ጠቅሷል።ምስራቅ ሐረርጌ ላይ የተፈናቀሉት ኦሮሞዎች ግን ሁለት የብርድ ወራት አሳልፈው ሶስተኛውን እየጠበቁ ነው።ጠባቂ፣ተመልካች፣አዛኝ የሌላት ሀገር፣ ሹማምንቶቿ በገንዘብ የናወዙባት ሀገር-ኢትዮጵያ።

ጉዳያችን
ጥር 28/2006 ዓም

No comments:

በኢትዮጵያ የእገታ ወንጀል ተሳታፊ አራት አካላት ናቸው። ለችግሩ የመፍትሄ አካላት ሁለት ናቸው።ሁለቱ አካላት ምን ይስሩ?

======= ጉዳያችን ======= በኢትዮጵያ ዜጎችን እያገቱ ገንዘብ የሚቀበሉ ወንጀለኞች ከተራ ወንጀለኝነት አልፎ በታጣቂ ቡድኖች የገንዘብ ማግኛነት መዋል ብቻ ሳይሆን ዜጎችን የማሸበርያ ፋሺሽታዊ ተግባር ሆኗል። እገታ የ...