ዩጋንዳ ሰራዊቷን በደቡብ ሱዳን ማስገባቷ ኢህአዲግን አላስደሰተም።ባለፈው ሰሞን የደቡብ ሱዳን የዜና ወኪል ይህንኑ ገልጦ ነበር።በሳልቫኪር የሚመራው የደቡብ ሱዳን ማዕከላዊ መንግስት የዩጋንዳ ጦር መኖሩን የፈለገ መስሏል።በቀድሞው ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቸር የሚመሩት የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚዎች በሌላ በኩል ''ኢትዮጵያ ጣልቃ ትግባ'' ቀረሽ ቅስቀሳ እያደረጉ ነው።
http://www.southsudannewsagency.com/opinion/columnists/ethiopia-will-lose-its-hegemony በየካቲት 10/2014 እ ኤ አቆጣጠር በደቡብ ሱዳን ዜና አገልግሎት ድረ-ገፅ ላይ በታተመ ፅሁፍ ላይ ኢትዮጵያ ጣልቃ እንድትገባ ይጋብዛል።
በሌላ በኩል ''ሻብያ በደቡብ ሱዳን የውስጥ ጉዳይ እየገባ ነው'' ሲል ኢህአዲግ የከሰሰው የዛሬ ሶስት አመት የኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ልዑክ ኢትዮጵያን ሲጎበኝ መሆኑ ይታወሳል።አሁን የዩጋንዳ ጦር ደቡብ ሱዳን መገኘቱን ተከትሎ የመጣው ቀውስ ሳይበርድ ሻብያ ከዩጋንዳ ጋር መቆሙን የሚያመላክቱ ምልክቶች እየታዩ ነው።
የሻብያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኦስማን ሳላህ ካምፓላ መግባታቸው እየተነገረ ነው።ቀደም ብሎ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ጉዳይ ኃላፊ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሬንፊልድ ዩጋንዳን መጎብኘታቸው እና ዩጋንዳም ጦሯን እንድትስብ ማሳሰባቸው ይታወቃል።የሻብያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዩጋንዳ መግባት ዝርዝሩ ባይታወቅም ከዩጋንዳ ጎን የመቆም ጉዳይ ለመሆኑ ግን ብዙዎች አይጠራጠሩም።ሻብያ እና ኢህአዲግ/ወያኔ ከሱማልያ ቀጥሎ ለሁለተኛ ጊዜ በደቡብ ሱዳን ላይ በእጅ አዙር ፍልምያ እንዳይገናኙ ያሰጋል።
'ጉዳያችን ጡመራ' የደቡብ ሱዳን ጦርነት ሲጀመር ለዩጋንዳው ሙሰቨኒ ጉዳዩ 'የሰርግ እና ምላሽ 'ያክል ነው ቀድመው ጦር ሊልኩ የሚችሉ መሪ እንደሚሆኑ ገምታ ነበር።እንዲህ ይነበባል -
''አሜሪካ ለጊዜው ጉዳዩ ላይ በቀጥታ መግባት ባትችልም የአካባቢው ሃገራትን '' 'ቀኝ እጄን ሰጥቻለሁ' እንደእኔ ሆነህ ይህንን አድርግ'' የምትለው ሀገር የሚታዩዋት ምናልባት ኢትዮጵያ እና ዑጋንዳ ብቻ ናቸው።ኢትዮጵያ ደግሞ በአሜሪካ ፍቃድ ብቻ ላለመሄድ የሚያደርጋት የሱዳን ፊት አለ።ሱዳን ተፅኖ ለመፍጠር በኤርትራ የሚገኙ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኃይሎችን መሸጋገርያ እንዳትሰጥ ያሰጋል።በመሆኑም ኢትዮጵያ በደቡብ ሱዳን ጉዳይ እንደ ሱማሌው ችግር ሙሉ በሙሉ የመግባቷ አዝማምያ እምብዛም አይታይም።ለዑጋንዳው ዩዌሪ ሙሰቨኒ ግን ሰርግ እና ምላሻቸው ነው።'' ሰበር ዜና-በደቡብ ሱዳን የሪክ ማቸር ኃይሎች ውግያ ጀመሩ። ትናንት ምሽት ቁልፏን ከተማ ቦርን ተቆጣጠሩ።ኢትዮጵያና ዑጋንዳ በደቡብ ሱዳን አንፃር (ጉዳያችን አጭር ዘገባ ታህሳስ 10/2006 ዓም)ጉዳያችን ታህሳስ 10/2006 ዓም
የአሁኑ ሁኔታ ደግሞ አሜሪካ በሻብያ እና ህወሓት ላይ የተለየ አዲስ ፖሊሲ ልትከተል እንደምትችል ወይንም እንደምትገደድ እንጠብቅ? ጉዳዩን ከሰሞኑ የምናየው ይሆናል።
ጉዳያችን
የካቲት 6/2006 ዓም

አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሬንፊልድ

No comments:
Post a Comment