ጉዳያችን - በጉዳያችን ሚድያ፣ኮምኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት የሚዘጋጅ ሲሆን ከ2003 ዓም ጀምሮ በድረ-ገፅ ላይ የነበረ በአሁኑ ጊዜ ከአንድ ሚልዮን በላይ ጎብኚዎች ያሉት ገፅ ነው። Gudayachn is prepared by Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant Organization. It has been online since 2011. Currently, Gudayachn is being visited by over One-million readers from all over the world.
Saturday, August 26, 2023
አዲሱ የአማራ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር አቶ አረጋ ከበደ ትናንት ዓርብ ነሐሴ 19/2015 ያደረጉት ሙሉ ንግግር።(ቪድዮ)
Thursday, August 17, 2023
''አንዱ ሲናገር ሌላው አያቋርጥ!'' የሦስተኛ ክፍል ተማሪዎች ክፍል ውስጥ የሚነገራቸው እና የሚያከብሩትን መመርያ ፓርላማው ገና አልተለማመደውም።
የተወካዮች ምክርቤት አባላት የተሰበሰቡት ኢትዮጵያውያንን ወክለው ነው። ኢትዮጵያውያንን መወከል ማለት ደግሞ የተከበረ ባሕል፣መከባበርና አስተዋይነት አብሮ ሊታይበት ይገባ ነበር። አንድ የምክር ቤት አባል ወደ ምክርቤቱ ሲገባ የፓርቲዬን ሃሳብ በእጅም በእግርም ብዬ ማሳለፍ ብቻ በሚል ከሃሳብ ሙግት ውስጥ የሚገኝ አዲስ ለሃገር የሚበጅ በጎ ሃሳብ ፈልቅቆ ለማግኘት የሚይስችል ስብዕና ይዞ ካልገባ ከሚቀመጥበት ወንበር ብዙ አይለይም። የሚባለውን ሁሉ እየተቀበለ ለማሳለፍ እንጂ በሃሳብ ለመሞገት ያልተዘጋጀ የፓርላማ አባል እቤቱ ቢቀመጥ እና በሌላ መገናኛ መንገድ ድምጹን መላክም ይችላል።
Tuesday, August 15, 2023
በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተሰላም ከተማ ላይ የድሮን ጥቃት እንደሆነ የታመነው የመንግስት ጥቃት በጦር ወንጀለኝነት የሚያስጠይቅ ነው።በጉዳዩ ላይ ገለልተኛ አጣሪ ኮሚቴም ካስፈለገ መቋቋም ያለበትና በድርጊቱ የሚጠየቁትን በትክክል ለፍርድ ማቅረብ ይገባል።
የቪኦኤ አማርኛ አገልግሎት ሙሉ ዘገባ ከስር ተያይዞ ያገኛሉ።
=======
Friday, August 11, 2023
ጥያቄው እየመገብን ስናሳድግ የኖርነው ወደፊትም ማሳደግ የምንፈልገው የቱን ነው? የሚለው ነው። መጪው የኢትዮጵያ ዕጣም የሚወሰነው በእዚሁ ነው።
አሁንም ጥያቄው እየመገብን ስናሳድግ የኖርነው ወደፊትም ማሳደግ የምንፈልገው የቱን ነው? የሚለው ነው። መጪው የኢትዮጵያ ዕጣም የሚወሰነው በእዚሁ ነው።ለችግር መፍትሄ ተመሳሳይ ችግር በመድገም አይፈታም።በተቃራኒው በመሄድ ነው ማሸነፍ የሚቻለው። በሌላው በኩል ያለ ጎጠኝነት ጎዳን ተብሎ በተመሳሳይ መንገድ በመሄድ ለጊዜው ስሜትን ያረካ፣ንዴትን ያበርድ ካልሆነ በቀር ዘለቄታዊ መፍትሄ ለሀገር አይሰጥም።ከጎሰኝነት በተቃራኒው በፍጹም ኢትዮጵያዊነት መንገድ በመሄድ እና ስለ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እና ኢትዮጵያ ከልብ በመነጨ የፍቅር ስሜት በመሄድ እና ለእዚህም እስከ የህይወት መስዋዕትነት ድረስ በመክፈል ሀገር ይቆማል።ስለሆነም ስንመግብ የኖርነውን አውቀን፣ወደፊት ለመመገብ የምናስበውን ከአሁኑ በምናቅደው ልክ የነገዋ ኢትዮጵያ ትታወቃለች። መሬት ላይ ያለው ትልቁ የአብዛኛው ህዝብ እውነት ዛሬም የጋራ የሆነች እና ከጎሰኝነት የተጣላች ከፍቅር የታረቀች፣ሁሉንም ወገኔ የምትል ኢትዮጵያን ማየት ነው።
Sunday, August 6, 2023
መሬት ላይ ያለው እውነታ፣ መከላከያ ፋኖ ላይ መተኮስ አይፈልግም።ፋኖም መከላከያ ላይ መተኮስ አይፈልግም።መንግስት ጉዳዩን በሰላም በመፍታት ኢትዮጵያን ከእርስበርስ ጦርነት የማዳን ታሪካዊ ኃላፊነት አለበት።
Wednesday, August 2, 2023
በአማራ ክልል የተነሳው አለመረጋጋትን በፍትሐዊ እና ርቱዕ በሆነ መንገድ ለመፍታት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ማድረግ የሚገባቸው ሦስት ተግባራት።
- የከረረ ብሔርተኝነት ያላቸው ወደ አመራሩ ከመጡ ከኢትዮጵያዊነት ጋር አጣጥሞ ለመሄድ የመቸገር ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል፣
- በህወሓት ሰርገው እንዲገቡ የሚደረጉ ግለሰቦች የሚፈጥሩት አሉታዊ ስዕል በንቅናቄው ላይ የሚሰጠው መልካም ያልሆነ ስዕል እና ከሌሎች ብሔሮች ጋር ለማጋጨት የሚደረጉ ሙከራዎች፣
- እራሱን በቶሎ ወደ ኢትዮጵያዊ ንቅናቄ ካልቀየረ በከረረ ብሔርተኝነት ስሜት የተመሰጡ አባላቱን ወደ ሃገራዊ አጀንዳ ባለቤትነት ለመቀየር የመቸገር ሁኔታ መፈጠር።የእዚህ አይነቱ ችግር አሁን ህወሓት እራሱ ገጥሞት የሚገኘው ችግር ነው።መግብያ ሲዘጋጅ መውጫው አብሮ መታየት አለበት።
- በተሰሩ ግፎች እና ጥፋቶች ላይ ከሚገባው በላይ በመዘከር የይቅርታ እና የአንድነት መንገዶች እንዲከፈቱ ማድረግ ካልቻለ አማራን ብቻ ሳይሆን በብሔራዊ ደረጃ ወደ አደገኛ መንገድ የመሄድ አዝማምያ እንዳይኖር ጥንቃቄ ያስፈልጋል።የሚሉ ነበሩ።
በእዚህ ጽሑፍ መግቢያ ላይ ለማንሳት እንደተሞከረው በዘመነ ኢህአዴግም ሆነ ባለፉት አምስት ዓመታት በጀዋር መሐመድ ''ስልጣን ይዘናል '' ከሚለው ጽሑፍ እስከ አቶ ሽመልስ ''ሰበርናቸው'' የመስቀል አደባባይ ንግግር፣ከመቶ ሺዎች የወለጋ እና የሸገር መፈናቀል እስከ ፍትሕ ያጡ የደቡብ እና ሱማልያ ክልል ነዋሪዎች ጭምር የብሶቱ ጣርያ ከመጠን ያለፈ ነው። ይህንን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይም፣መከላከያም፣ብልጽግናም ካለምንም ማጉረምረ ሊውጡት የሚገባ እውነት ነው። ለእዚህ እውነት እዚህ ላይ መዘርዘር ጊዜ ማጥፋት ነው። አሁን ያለውን ወቅታዊ ጉዳይ ለመተንተን የሚነሳ የመንግስት አካል መነሳት ያለበት ይህንን እውነት ከመቀበል ካልሆነ ቀጣይ የመፍትሄ ሂደቱ ሁሉ የተሳሳተ እና አለባብሶ የመሔድ ከንቱ ድካም ይሆናል። በመሆኑም ይህንን እውነት ጠቅላይ ሚንስትሩም አምነው እና ተቀብለው ወደ መፍትሔ መሄድ ተገቢ ነው።
- መድረኩ ከውይይት በኋላ ለህዝብ መቅረብ ያለበት ለበለጠ ግጭት የማይዳርገው ክፍል ተለይቶ ነገር ግን ዋና ሃሳቡን ያልጣለ የመወቃቀሻ መድረኩ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥንና ራድዮ በቀጥታ መተላለፍ አለበት።
- በመወቃቀሻ መድረኩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ከአማራ ክልል ጋር በተያያዘ እና በኦሮምያ ክልል ለሆነው ሁሉ ያሳዩት ለዘብተኝነት ላይ በግልጽ ይጠየቁ፣እርሳቸውም ከእዚህ በፊት ያልሰማናቸውን ጉዳዮች ጨምረው ለምላሽ ይዘጋጁ።ውይይቱ ስሜት የሚነካ እና ፍጹም ግልጽነት የታየበት መሆን አለበት።
- ሀገር በሆነ ባልሆነው ወደ ግጭት እየገባች የትውልድ ሞት ከሚከተል ለእዚህ ዓይነት መወቃቀስ መዘጋጀት እና ስህተትን ውጦ ለነገ ስህተትን አስተካክሎና መተማመንን በምንም ወጪ ቢሆን ከፍሎ ሀገርን ማስቀጠል ግዴታ ነው።
- ስለሆነም ይህ የመወቃቀሻ መድረክ እጅግ በፈጠነ መንገድ ማድረግ ብዙ ችግሮችን ያስወግዳል።
- አሁን በሁለቱም ክልል ያሉት አመራሮች በሴራ ሹክቻ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በሙስና የተነከሩበት ደረጃ ማንም ወንጀለኛ የሚነዳቸው ስለሆኑ ያከረሩ የጸብና የግጭት መነሻ ናቸው።
- በተለይ በኦሮምያ ክልል ያለው ከጎሳ ፖለቲካ መበስበስ አልፎ ፈጽሞ ለማንኛውም ኃይል ተገዢ ብቻ ሳይሆን የመሰረታዊ የኢትዮጵያ ዕይታቸው ከጥላቻ ባለፈ ወደ ፍጹም ፋሺሽታዊ መንገድ እየሄደ በመሆኑ
- በቀጣይ ኢትዮጵያ እንድትሄድበት ከሚፈለገው የአንድነት መንገድ አንጻር በሁለቱም ክልሎች ያሉ አመራሮች በብሄር ፖለቲካ የተደናበሩ ስለሆነ እና
- ወቅታዊ ችግሩን በአዲስ አሰራር በመቀየር ቁርጠኝነትን የማሳያ አንዱ መንገድ ስለሆነ።
- እዚህ ላይ ህገመንግስቱ ላይ ያሉት መሰረታዊ ችግሮች ማስተካካል። ሀገር በጦርነት ከሚታመስ ህገመንግስትን በማረም ማስተካከል ተገቢ ነው።
- በአማራ ላይ፣በኦሮሞ ላይ እና ሌሎችም ላይ ያሉ ጸብ ጫሪ ትርክቶች በወንጀለኝነት የሚያስጠይቁ ማድረግ፣
- የአኖሌን ሃውልት ከማፍረስ ማናቸውም የጎሳ ቀስቃሽ ንግግር ያደረገ እና የጻፈ በፍጥነት በህግ መቅጣጥ
- ዲጂታል ጎሳ አልባ መታወቂያ ከታቀደው ጊዜ በፈጠነ መልኩ ተግባራዊ ማድረግ
- የክልሎች አከላለል ጎሳን መሰረት ያደረገ እንዳይሆን በፍጥነት ተግባራዊ ማድረግ። እዚህ ላይ በፍጥነት የሚለው ቃል የምጠቀመው ዘመን በማርዘም ችግር ከማባባስ ይልቅ በተግባራዊነቱ የኢትዮጵያን ህዝብ ድጋፍ አግኝቶ ሀገር ማቆም ከሁሉ የተሻለው አማራጭ መሆኑ ቢያንስ ያለፉት አምስት ዓመታት አስተማሪ ስለሆነ ነው።
Saturday, July 29, 2023
ወደብ አልባዋ ኢትዮጵያ እንዴት የቀጥታ ወደብ አገልግሎት ማግኘት ትችላለች? አልጅዚራ ''ኢንሳይድ ስቶሪ'' በእዚህ ሳምንት ያስተላለፈው (ቪድዮ)።How will landlocked Ethiopia get direct access to a port? (video)
Kemal Hashi Mohamoud – Member of the Ethiopian Parliament
Martin Plaut – Journalist specializing in the Horn of Africa and a fellow at the Institute of Commonwealth Studies at the University of London
Kwaku Nuamah – Senior lecturer and chairman of the International Peace and Conflict Resolution Program at American University
Aljazeera English Inside story, July 26,2023
The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church is in turmoil in Athens, Greece.
His Holiness Abune Mathias I, Patriarch of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, met with Greece's Ambassador to Ethiopia, Antonios Sg...
-
በቀሲስ መንግሥቱ ጐበዜ ሉንድ ዩንቨርሲቲ ፣ ስዊድን (ቀሲስ መንግስቱ ጎበዜ በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አርኪኦሎጂ እና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህር እና በሉንድ ዩንቨርስቲ የዶክትሬት...
-
The Ethiopian herald News Paper August 20 , 2020 BY STAFF REPORTER Addis Ababa ************************** (EPA) ADDIS ABABA - Over sixty-mil...
-
አድሚራል ጄምስ ስታርቪድስን =============== ጉዳያችን /Gudayachn =============== ብሉምበርግ የተሰኘው የአሜሪካ ድረገፅ በፖለቲካ እና ፖሊሲ አምድ ስር የአድሚራል ጄምስ ስታርቪድስን አሜሪካ ኢትዮጵ...