ጉዳያችን - በጉዳያችን ሚድያ፣ኮምኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት የሚዘጋጅ ሲሆን ከ2003 ዓም ጀምሮ በድረ-ገፅ ላይ የነበረ በአሁኑ ጊዜ ከአንድ ሚልዮን በላይ ጎብኚዎች ያሉት ገፅ ነው። Gudayachn is prepared by Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant Organization. It has been online since 2011. Currently, Gudayachn is being visited by over One-million readers from all over the world.
Sunday, December 26, 2021
የትግራይ ሕዝብ ከ3 ሺህ ዓመታት በላይ የሚያውቀው እና አብሮት የኖረውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ለ40 ዓመታት በሚያውቀው ህወሓት እንደማይቀየር የሚያስመሰክርበት ጊዜ አሁን ነው።
Thursday, December 23, 2021
የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ሕዝብ ድርጊት በመቀየሙ ወደ መቀሌ ሰራዊቱን ላለመላክ ወስኗል።ውሳኔው መንግስት በተለያየ ጊዜ ወደ ትግራይ እየገባ እርምጃ እንደሚወስድም ገልጧል።የዛሬው የመንግስት ውሳኔ ሲፈተሽ
- ውሳኔው ሲፈተሽ ምን ይመስላል?
- መከላከያ መቀሌ አይገባም ማለትስ ምን ማለት ነው?
- በቀጣይ የመንግስት ሦስት ትኩረቶች ምን መሆን አለባቸው?
- ውሳኔው ሲፈተሽ ምን ይመስላል?
2) የሽብር ቡድኑ የተገደሉበትን ታጣቂዎች ሬሳ የቻለውን ሁሉ ጭኖ በመሸሹና የመንግሥት ኃይል ወደ ትግራይ ሲገባ መንግሥት በትግራይ ጅምላ ጭፍጨፋ ፈፀመ የሚል በአስከሬን የመነገድ እቅድን እንዳሰበ ስለተደረሰበት እና ከእውነት የራቁ ዓለም ዐቀፍ ተቋማት በኢትዮጵያ ላይ የሽብር ቡድኑን ክስ መነሻ በማድረግ የተለያዩ ወሳኔ ለማሳለፍ እንደሚሰሩ ስለታወቀ፡፡
3) መንግሥት የአገሪቱን የግዛት አንድነት የመጠበቅ ሙሉ ኃላፊነቱን ለመወጣት በየትኛውም ጊዜ ወደ ትግራይ ክልል እየገባ እርምጃ መውሰድ እንደሚችል የሚታመን ስለሆነ መሆኑን የዛሬው መግለጫ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ በሰጡት መግለጫ የመንግስትን ውሳኔ አሳውቀዋል
ከእዚህ በተጨማሪ በእዚሁ መግለጫ ላይ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ''መንግሥት አሁን ላይ ምንም የማድረግ አቅም የሌለውን ትሕነግ መልሶ እንዳይነሳ ለማድረግ የሚያስችሉ የተጠኑ እርምጃዎችን በየትኛውም ስፍራ እየገባ ይፈፅማል'' ካሉ በኃላ ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት የአሸባሪውን ትሕነግ ቡድንን ጠራርጎ በማስወጣትና እጁን እንዲሰጥ በማድረግ ስኬታማ እንደነበር ተገልጿል፡፡
ሆኖም ግን የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ መንግሥት በኦሮሚያ ክልል በሸባሪው ሸኔ የሚደርሱ ችግሮችን እንዲሁም በምዕራብ አማራ አካባቢዎች የሚወስዳቸው የተጠኑ እርምጃዎች ይቀጥላል፤ ቀጣይ አቅጣጫዎችንም ያሳውቃል ማለታቸውን ዋልታ ዘግቧል።
ውሳኔው ሲፈተሽ ምን ይመስላል?
የዛሬው የመንግስት ውሳኔ በአንዳንድ ማኅበራዊ ሚድያዎች እንደሚባለው መንግስት ፈጽሞ በትግራይ ያለውን ሁነታ በወታደራዊ የተለያዩ የመቆጣጠርያ መንገዶች አልቆጣጠርም አስፈላጊ ሲሆንም ጥቃት አልፈጽምም አላላለም። ከላይ የመግለጫው ዓረፍተ ነገር ላይ እንደተገለጠው ይልቁንም ከመግለጫው አንዱ ምክንያት መንግስት አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሁሉ ኢርምጃ የመውሰድ አቅም ስላለው መሆኑን ይገልጣል።
የዛሬው የመንግስት ውሳኔ መንግስት ባለበት ሃላፊነት እንደ መንግስት፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ እንደ ህዝብ ለወንድሙ ለትግራይ ህዝብ ያደረገውን እና የሆነውን የትግራይ ህዝብ ከመጤፍ እንዳልቆጠረው እና ይልቁንም ህወሃት ለፈጸመው ክህደት ተብብሮ መገኘቱ እንዳሳዘነው በደንብ ያሳያል።
መከላከያ መቀሌ አይገባም ማለትስ ምን ማለት ነው?
ይህ ማለት የኢትዮጵያ ህዝብ በ1983 ዓም ህወሃት በትግራይ ስም ተደራጅታ ስትመጣ ትግራይ መጣ ወይንም የእገሌ ዘር ሳይል አዲስ አበባ ድረስ አስገብቶ ነበር የኢትዮጵያ ህዝብ ዘረኛ አይደለም ማለትም ነው።
ይህ ማለት የትግራይ ህዝብ የኢሳያስ ጦር ወጋኝ ሲል የኢትዮጵያ ህዝብ ከዳር እስከ ዳር ተነስቶ ባድሜ ላይ ከቶ እስከ 70 ሺህ ሰው የረገፈውን አጥንት ተረስቶ ሰሜን ዕዝ ሲወጋ፣የትግራይ ህዝብ ዝም ማለቱ አሳዝኖናል ከባለፈው ትምህርት ወስደናል ማለት ነው።
ይህ ማለት ከሰሜን ዕዝ የተወሰነ ሜካናይዝድ ጦር ወደ ሌላ የኢትዮጵያ ክፍል ይንቀሳቀስ ሲባል የትግራይ ህዝብ ነጠላ አንጥፎ ህጻናት አሰልፎ እንዳልለመነ በኋላ ህወሃት በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ሲፈጽም መጨፈሩ አሳዝኖናል ማለት ነው።
ይህ ማለት በትግራይ ከ20 ዓመታት በላይ ኖረው እዝያው ተዋልደው የኖሩ፣የህዝቡን ሰብል ከመሰብሰብ እስከ ቤቶች እና ትምህርት ቤቶች ሲገነቡ የነበሩ የሰሜን ዕዝ አባላት ላይ ጥቃት ሲፈጻም ልጆቻችን ናቸው ብሎ ለማስጣል የሞከረ ከትግራይ አለመኖሩ አሳዝኖናል ማለት ነው።
በኋላም መከላከያ መቀሌን ከህውሃት ነጻ ካወጣ በኋላ በቡድን እየሆነ ሲያጠቃው ብቻ ሳይሆን አንዳንዶች ምግቡ ላይ መርዝ እየጨመሩ፣ዓይኑ ላይ በርበሬ እየረጩ ለህዝብ ነጻነት የቆመን ሰራዊት መግፋት አሳዝኖናል ማለት ነው።
በእዚ ሳምንት በትግራይ ቴሌቭዥን አንዳንድ ሲቪል እናቶች ሳይቀሩ የኢትዮጵያ መከላከያ ወደ መቀሌ ከመጣ ቃል በቃል ሲሉት የተሰማው ''ዓይናቸው ላይ በርበሬ እጨምራለሁ፣ለመውጊያ መርፌ አዘጋጅቻለሁ'' የሚሉ ንግግሮች መሰማታቸው አሁንም የጥሞና ጊዜውን በአግባቡ ያልተጠቀመ መኖሩን በመመልከቴ አሳዝኖኛል ማለት ነው።
አንዳንድ የሽብርተኛው ህወሃት ደጋፊዎች መከላከያ መቀሌ አልገባም ነገር ግን አስፈላጊ ሲሆን እርምጃ እወስዳለሁ ማለቱን እንደ ሃይማኖት የሚያመልኩት ህወሃት የተረፈላቸው እየመሰላቸው ሲደሰቱ ይታያሉ።መከላከያ መቀሌ አይገባም ማለት ምን ዓይነት መከራ እንዳለበት የሚረዱት ከህወሃት ሳይሆን ከትግራይ ህዝብ ችግር አንጻር ነገሩ የሚረዱት ግን አይደሰቱም። መከላከያ መቀሌ አይገባም ማለት -
- የመንግስትም ሆነ የግል ድርጅቶች ሥራ አይጀምሩም ማለት ነው።
- ባንኮች ወደ ሥራ አይገቡም፣ከብሄራዊ ባንክ ጋር ያላቸው ግንኙነት አይኖርም ማለት ነው።
- ለትግራይ የሚላክ በጀት የለም ማለት ነው።
- በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ወጣቶች ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ ፈተና አንዳመለጣቸው ሁሉ የስምንተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናም መፈተን አይችሉም ማለት ነው።
- በትግራይ ያሉ ትምህርት ቤቶች፣ሆስፒታሎች እና ሌሎች አካላት ሁሉ ሥራ አይጀምሩም።ሰራተኞችም ደሞዝ አይኖራቸውም ማለት ነው።
- የውጭ ጥቃት በትግራይ ላይ ቢፈፀም ለምሳሌ ከኤርትራ ወይንም ከሱዳን ቢኖር የኢትዮጵያ መከላከያ ህወሓት እያለ ለመከላከል ስለማይችል በቅድምያ የህወሓት መወገድ ቅድመ ሁኔታ ይሆናል ማለት ነው።
- አሁን በትግራይ ያለውን የአስተዳደር መዋቅር ህወሓት በአግባቡ እየመራው አይደለም።በብዙ ቦታዎች ለምሳሌ የአክሱም ከተማን ጨምሮ ህዝቡ በራሱ አለቆች አየመረጠ ይተዳደራል አንጂ ትግራይ በአሁኑ ጊዜ ታጣቂ ሁሉ የሚዘርፍባት አንደሆነች ትቀጥላለች ማለት ነው።
ባጭሩ ህወሓት በቀጣይ ከታሊባን የሽብር ቡድን ጋር ሳይቀር ውል አየገባ ትግራይን ለባዕዳን ለመሸጥ ለማደራደር ይሞከራል ማለት ነው።አስገራሚው ጉዳይ ህወሃትን አንደ ሃይማኖት የሚከተሉት የትግራይ ተወላጆች የትግራይን ወጣት በአፋር አና በአማራ ክልል አስፈጅቶ ቀሪውን አራሱ ረሽኖ አሁንም የቀረውን ለማስጨረስ የሚዘጋጀውን ቅምጥል አመራሩ ግን አሁንም የታሸገ ውሃ ሳይቀር አንዳይጎድልባቸው ሆነው የሚኖሩትን አመራሮች ወንጀል አየሸፈነ ለመኖር የሚሞክር መሆኑ ነው።
መንግስት በቅድምያ ሊያከናውናቸው የሚገቡ ሦስቱ ስራዎች
መንግስት ሀገር የማቆም አና የማፅናት ትልቅ ታሪካዊ ኃላፊነት የተጣለበት ጊዜ ነው።ይህ ኃላፊነት የመንግስት ብቻ አይደለም፣ ግለሰብ አና የሕዝብም ጭምር ኃላፊነት ነው። የህወሓት የሽብር ቡድን በአፋር እና በአማራ በተለይ ወሎ በሰው ልጅ ይፈፀማል የማይባል ግፍ ፈፅሟል።ከ70 ዓመት መነኩሴ መድፈር እስከ የካህን ሚስት መድፈር፣እናቶችን ልጆቻቸው ፊት መድፈር እና ገንዘብ ቀምቶ ከቤት ገብቶ ከበላ ከጠጣ በኃላ ያበላው ያጠጣውን ቤተሰብ ገድሎ የሄደባቸው በርካታ ምስክሮች በመገናኛ ብዙሃን ስንመለከት ነው የሰነበትነው።አሁን በጦርነቱ ሳብያ የተጎዳውን ህዝብም ሆነ ምጣኔ ሃብቱን እንዲያገግም መንግስት ቅድምያ ሊሰጣቸው የሚገባቸው አንገብጋቢ ጉዳዮች አሉ።እነርሱም -
1) በአማራ ክልል በተለይ በዞን እና ወረዳ ደረጃ ሕዝብ ያመነባቸው አና በጦርነቱ ወቅት በነበራቸው ብቃት አመራር እና በችሎታ የሕዝብ ቅቡልነት ያላቸው አመራሮች እንዲመሩ ማድረግ።በአማራ ክልል በታችኛው መዋቅር ላይ ያለው አመራር በጁንታዊ አስተሳሰብ የተበከሉ፣አቅም የሌላቸው እና ሕዝብ በልዩ ልዩ የስነ ምግባር ጉድለት የሚታሙ መኖራቸው ይሰማል።
2) በኦሮምያ ክልል ያለው ሙስና ቅጥ ያጣ መሆኑ ይሰማል።ከፍተኛ የስልጣን ብልግና አና ያለአግባብ መበልጠግ ላይ ብቻ የሚሰሩ አመራሮች ከብልሹ ነጋዴዎች ጋር በመግጠም ከፍተኛ ጥፋት አየፈፀሙ ነው።ይህንን መንግስት በፍጥነት አጣርቶ መፍትሄ አለመስጠቱ አሳሳቢ ነው።
3) ወደ ትግራይ ክልል የሚተላለፍ ሙሉ ደረጃውን የጠበቀ የጤናማ ፕሮፓጋንዳ ራድዮ እና ቲቪ እንዲሁም ከአየር ላይ የሚበተን ወረቀት ጭምር ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ በህወሓት ስር የኖረውን ሕዝብ ላይ ሥራ መስራት ይፈልጋል።አሁን ባለበት ሁኔታ ብዙሃን በትግርኛ የሚተላለፉ የራድዮም ሆነ የቴሌቭዥን ስርጭቶች ቢኖሩም በባለሙያ እና በቂ በጀት ተመድቦ የሚጠበቅ ውጤት ባስቀመጠ መልኩ መስራት ይፈልጋል።
ለማጠቃለል፣በኢትዮጵያ ምድር በሽብርተኛው ህወሓት አማካይነት ደም ሲፈስ፣ሕዝብ ሲሰደድ ግማሽ ክፍለዘመን አስቆጥሯል።ባለፉት አራት ወራት ብቻ በአማራ እና በአፋር ላይ የደረሰው ግፍ በፈጠረው ቁጣ እና ስሜት ወደ መቀሌ ሕዝቡም ሠራዊቱም ቢተም ምን ሊፈጠር አንደሚችል መገመት ይቻላል።በመሆኑም መንግስት የረጅም ጊዜ የኢትዮጵያዊነት አሳቤን ግንዛቤ ባስገባ መልኩ ሰራዊቱ በድንበር ላይ ይዞታውን አስጠብቆ ትዕዛዝ እንዲጠብቅ መደረጉ ለአሸናፊ ሰራዊት ከባድ ውሳኔ ቢሆንም ቆይቶ ግን ኢትዮጵያን በመልካም ይከፍላታል። ሆስፒታላቸው የፈረሰባቸው፣ትምህርት ቤታቸው የተዘረፈባቸው እና ከተሞቻቸው አሁንም በሽብርተኛው ህወሓት የፈረሰባቸው የአፋር እና አማራ ክልል ወጣቶች የፈሰሰውን ሲጠርጉ፣የተሰበረባቸውን ለመጠገን ሲሞክሩ መመልከቱ አንጀት ይበላል።ግፍ ተፈፅሞበት በብዙ ልቀት በልጦ ወደ ሥራ የሚሄድ ወጣት ማየት በራሱ ግፍ ያደረገው በምድር ብቻ ሳይሆን ከፈጣሪም የሚታዘዝ ቅጣት እንደሚያገኝ እማኝ ይሆናል። በአማራም ሆነ በአፋር ክልል ህዝቡ ምግብ ለወራሪዎቹ ሲሰጥ አንድም ቦታ መርዝ ጨምሮ ወይንም ሌላ የተንኮል ሥራ ሰርቶ መስጠቱ አልተሰማም።ከሰኔ፣ 2013 ዓም በፊት በትግራይ ሕግ ማስከበር ሥራ ላይ የነበረው የኢትዮጵያ መከላከያ ላይ ግን አንዳንድ የትግራይ ቦታዎች ብቻ ሳይሆን ጥቅምት 24፣2013 ዓም በሰሜን ዕዝ ላይ ከተፈፀመው ጥቃት ውስጥ አንዱ በመኮንኖች ላይ በራሳቸው የትግራይ ባልደረቦች የሚበሉት ምግብ ላይ መርዝ ተጨምሮ እንደነበር የወቅቱ ዘገባ ነበር።የሽብርተኛው ህወሓት እና አምላክዎቹ ያለባቸው የጥላቻ ጥግ እና የተበደለው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሞራል ልዕልና ሲታይ ያለው እርቀት የትየለሌ የሚያሰኝ ነው።ይህ የሃሳብ ልዕልና የጁንታውን ስነልቦና ላይ የበላይነቱን ተቀዳጅቷል።ቀሪው ስልታዊ አፈፃፀም ብቻ ነው።
==========////============
Tuesday, December 21, 2021
የአንድ ሚልዮን ኢትዮጵያውያን ጉዞ ወደ ሀገር ቤት በቡድን እየሆኑ የሚጎበኙት ቦታ ለማመቻቸት ከወዲሁ ከስር የተያያዘውን ፎርም እንዲሞሉ ጥሪ ቀርቧል።
Friday, December 17, 2021
የተ.መ.ድ 33ኛው ልዩ ሰብዓዊ መብት ምክርቤት የጠራው የዛሬው ስብሰባ አብቅቷል።ከ19 በላይ የሃገሮች ተወካዮች ያሉት ገዢ ሃሳቦች፣ እና የስብሰባው አጠቃላይ አንደምታ እና መንግስት ማየት ያለበት መንገድ
ፈረንሳይ የተጀመረው የኢትዮጵያ እና የተመድ የጋራ ምርመር ይቀጥል ብላለች
ኩባ የካውንስሉ ስብሰባ በአዳጊ ሃገሮች ላይ የተሸረበ ፖለቲካዊ ቃና ያለው ነው።ቅድምያ መስጠት ያለብን ለኢትዮጵያ ብሄራዊ እና አህጉራዊ ጥረቶች ነው ብለዋል።
ፓኪስታን የተመድ ካውንስል በራሱ ያለፈ ታሪኩ የሃያላንን ፖለቲካ ፍላጎት የማስፈጸም ታሪክ አለው ብለውታል።ይህ ስብሰባ ለፓኪስታን ጥያቄ ፈጥሮባታል ብለዋል።
ኤርትራ ይህ ስብሰባ ፍትሃዊ አይደለም፣የኢትዮጵያን ግዛታዊ አንድነት የሚጻረር እና በህወሃት የተሰራውን ወንጀል ለመሸፈን የሞከረ ነው።ወደ ትግራይ ሄደው የቀሩት የእርዳታ መኪናዎችንም አንስተዋል።
ቦሊቭያ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ፖለቲካዊ ሲሆን አይስማማንም ብለዋል።
ፓራጓይ ሁሉም አካላት ለተራቡት ምግብ እንዲደርስ ያድርጉ ብላለች
ናይጄርያ ይህ ስብሰባ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የተጻረረ ነው፣የአፍሪካ ህብረትንም ይሁንታ አላገኘም ብላዋለች ።
ኒውዝላንድ ህወሃት ጦርነቱን ወደ አማራ እና አፋር ማስፋፋቱን ገልጣ ዓለም አቀፍ ምርመራ ኮሚሽኑ ቢያደርግ ብላ ቀላቅላለች
አውስትራልያ የኢትዮጵያ መንግስት ምርመራውን በሚኒስቴር ደረጃ አቋቁሞ ምርመራ ላይ መሆኑን እንደግፋለን ብለዋል።
ስዊድን የጥላቻ ንግግሮች ያሳስቡናል ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግስት በሚንስትር ደረጃ አጣሪ ኮሚቴ ማቋቋሙን አድንቀዋል።
አየርላንድ የአፍሪካ ህብረት ማደራደር እንደሚደግፉ ተናግረዋል።የጥምር ሪፖርቱ በተሰጠው አስተያየት መሰረት ክትትል ይፈልጋል፣መብት የጣሱም ለፍርድ ሊቀርቡ ይገባል ብለዋል።
ኢራን ማናቸውም ጉዳይ የኢትዮጵያን አንድነት በማይነካ መልኩ በአፍሪካ ህብረት በኩል መከናወን ይገባዋል ብለዋል።
ሲሪላንካ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ካለምንም የውጭ ጣልቃ ገብነት ስራውን እንዲሰራ መደረግ አለበት ብለዋል።
አሜሪካ ጉዳዩ ያሳስበናል ብለው ምግብ ወደ ትግራይ አልሄደም፣የትግራይ አማጺዎችም በአማራ እና አፋር ግፍ ፈጽመዋል፣የኤርትራ መንግስትም ጣልቃ ገብነት መቆም አለበት ብለዋል።
ደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ መንግስት የጥምር ምርመራ ውጤት መቀበሉን እናመሰናለን።በእዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋትን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጠዋል።
ሩስያ ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተገዢ ነች። ኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ፖለቲካዊ ተጽኖ ያለበት ማናቸውም ውሳኔ አይሰራም።ኤክስፐርቶችን ከውጭ በመላክ የሚደረግ ስራም ውጤታማ አይሆንም።
ቻይና በኢትዮጵያውያን ችሎታ እና ጥበብ ችግሮችን የመፍታት አቅም ትተማመናለች። የአፍሪካ ህብረት ተሳትፎ ታበረታታለች።ውድ ኢትዮጵያውያን! የዛሬው የተመድ ስብሰባ እንደ ''የውሾች ጉባዔ'' መወገዝ አለበት! የኢትዮጵያ አምላክ ስብሰባውን ይበትነው!
ስብሰባውን የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚጻረር መሆኑን ገልጦ መግለጫ አውጥቷል።
በገለልተኛነቱ የተመሰከረለት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እንደማይስማማ ገልጧል።
የተመድ ሰብዓዊ መብት ካውንስል ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጋር በመሆን በትግራይ ምርመራ አድርገው የዘር ማጥፋት አለመፈጸሙን በአንድ ቀን ማለትም እኣአ ጥቅምት 28/2021 ዓም በጄኔቭ እና አዲስ አበባ መግለጫ ማውጣታቸው ይታወሳል።ይህንን መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት በመሰረተ ሃሳቡ የተስማማበት እና የአውሮፓ እና አሜሪካ መንግስታትን ጨምሮ 15 በላይ ሃገሮች የተቀበሉት ነው።የኢትዮጵያ መንግስትም በትግራይ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የሚያጣራ ቡድን ሁሉ መስርቷል። ስራም ጀምሯል።
በወቅቱ ሁለቱም ማለትም የተመድ ሰብዓዊ መብት ካውንስል እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በጋራ በቀጣይ በአማራ እና አፋር ምርመራ እንደሚያደርጉ እና የጸጥታው ሁኔታ ብቻ እንዳገዳቸው ገልጠው ነበር።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ስብሰባውን አስመልክቶ ያለውም ስጋት የገለጠበት መግለጫ ላይ ያለውም የጀመርነው ፕሮጀክት እያለ የምን ስብሰባ ነው? የሚል ጥያቄ ነው።
የዛሬው የተመድ ሰብዓዊ ካውንስል ስብሰባ የአውሮፓ ህብረት ቢጠራውም የካውንስሉ የአፍሪካ ሃገሮች አንዳቸውም አልፈረሙበትም።
የስብሰባው ዓላማ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ገሶ በተመድ ስም እንደ ኢራን የኒኩሌር መርማሪ ቡድን በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚገቡ ባዕዳን ማሰማራት እና ውጤት በሚሉት ውሳኔ አሳልፎ ኢትዮጵያን እስከመውረር ለመድረስ ነው።Thursday, December 16, 2021
The 17th of December, UNHRC Meeting on Ethiopia's internal issue motive is Colonialism. It is not less than an Open war against Ethiopia and African Sovereignty.
=============
Gudayachn
============
The United Nations Human Rights Council (UNHRC), following the European Union's request, has the plan to have a meeting on the ''grave human rights situation in Ethiopia''on December 17,2021. The Ethiopian Government has called all UN Human Rights Council member countries to reject and vote against this special session.
Ethiopia is in a democratic process. The 2018 reform could run a peaceful and fair election in June 2021 and elect the current Prime Minister and the 2019 Nobel Peace winner, Abiy Ahmed. However, the previous ethnocentric and dictatorial regime led by the minority group Tigray People's Liberation Front (TPLF) declared war on the National Defence Force of Ethiopia, on November 4,2020. Since then Ethiopia is at war with the TPLF which is also categorized under the Terrorist group by Ethiopian Parlament.
Ethiopia's current Human Rights condition, compared to the last 30 years of the TPLF full of atrocities, is much better and in some cases, it is possible to say best. Ethiopian Human Rights Commission is an independent institution. Its neutral investigation by joining the UN Human Rights Commission on the case of the Tigray issue was one of the remarkable jobs that give great credit to the Commission. This particular rereport was accepted by over 15 countries including the European and US Governments.
Regarding the December 17th meeting of the UNHRC on Ethiopia's issue, the Ethiopian Human Rights Commission has expressed its views and concerns on the draft Resolution on the human rights situation of Ethiopia. In a recent press release of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC), the 17th December UNHRC call on Ethiopia is not reasonable and has a great possibility to complicate the situation.
''EHRC has stated its concerns that setting up another body to investigate the same matter covering the same time period could be counterproductive as it could delay criminal investigations and prosecution; it would be detrimental to the right to full redress for victims and survivors of violations identified by the Joint Investigation Team (JIT).'' EHRC, December 15,2021.
Tomorrow's UNHRC Meeting on Ethiopia's internal issue's motive is Colonialism. It is not less than an Open war against Ethiopia and African Sovereignty. The current Ethiopian internal situation can not be a business of any other Government or International Organization's job. Any attempt to transfer the domestic issue of Ethiopia to a global one is to violate the sovereignty of Ethiopia and Africa too. There is no single African Country that reacted positively to the UNHRC call meeting on Ethiopia's internal issue. On October 28,2021, UNHRC participated in the Joint Investigation Team with EHRC, released the JIT report in Geneva and Addis Ababa at the same time. The Joint team was expected to do the same investigation in Amhara and Afar regions in Ethiopia. However, before the joint investigation go further, the UNHRC is calling another annex meeting that seems affiliated with the political approach. So it is valuable to raise the question - what is the purpose of UNHRC's call meeting with some undeclared draft for resolution?
The December 17,2021 meeting of the UNHRC must be boycotted by the member countries or voted against any decision to make any new investigation. Any decision by UNHRC disregarding the started Join Investigation Team (JIT) with Ethiopian Human Rights Commission must not get any acceptance. If the UN Council's meeting decided contrary to Ethiopia's position, it is clear the mission of the meeting is to violate the sovereignty of Ethiopia and Africa too.
===========////=========
Tuesday, December 14, 2021
The Ethiopian government called on member states of the UN rights body to reject and vote against the special session.
Ethiopia has rejected a plan by the UN’s top human rights body to hold a special session on Friday to discuss the human rights situation in the country.
Ethiopia’s foreign ministry said that it was “perplexed and saddened” by the UN Human Rights Council’s decision to hold the session at the request of the European Union.
The Ethiopian government called on member states of the UN rights body to reject and vote against the special session.
“What should have been a priority for the council, instead, was the urgent task of carrying out an investigation into the violations of human rights and atrocities committed by the Tigray People’s Liberation Front, TPLF, terrorist group in Afar and Amhara regional states.” The government said in a statement.
The UN rights council said the session will discuss the “grave human rights situation” in Ethiopia.
Task Force
Ethiopia announced at the end of November that it had set up a task force to deal with human rights violations during the conflict in the north of the country between its military and TPLF rebels.
It said that was in line with the recommendations of a joint report by the Ethiopian Human Rights Commission and the UN human rights office.
-
በቀሲስ መንግሥቱ ጐበዜ ሉንድ ዩንቨርሲቲ ፣ ስዊድን (ቀሲስ መንግስቱ ጎበዜ በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አርኪኦሎጂ እና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህር እና በሉንድ ዩንቨርስቲ የዶክትሬት...
-
አድሚራል ጄምስ ስታርቪድስን =============== ጉዳያችን /Gudayachn =============== ብሉምበርግ የተሰኘው የአሜሪካ ድረገፅ በፖለቲካ እና ፖሊሲ አምድ ስር የአድሚራል ጄምስ ስታርቪድስን አሜሪካ ኢትዮጵ...
-
The Ethiopian herald News Paper August 20 , 2020 BY STAFF REPORTER Addis Ababa ************************** (EPA) ADDIS ABABA - Over sixty-mil...

