Monday, August 9, 2021

የአሸባሪው ህወሓት ስውር የሽብር ወሬዎች የሚመጡበት ሰባት መንገዶች።የሽብር መንዣ ስምንቱ የመጀመርያ ዓረፍተ ነገሮች።


የአሸባሪው ህወሓት ስውር የሽብር ወሬዎች የሚመጡበት ሰባት መንገዶች።

1) ከቤተሰብዎ እራሱ ወይንም እራሷ ባላወቁት መንገድ የውሸት ዜናዎች ይነዛሉ። ዜናውን የነዛላቸው ሰው ዓላማው ለቤተሰብ እንዲያወራ ነው።በተለይ የታወቁ ሰው ከሆኑ ወይንም የህወሓት ተቃዋሚ መሆንዎን ካወቁ ከቤተሰቡ ውስጥ እርስዎን ወይንም ሁሉንም ቤተሰብ ኢላማ ለማድረግ ያቀደ የሽብር ወሬ ነው።

2) የሚወዱት ወዳጅ ወይንም ጥሩ ሰው የሚሉት ሰው በዓላማ ግን የሽብርተኛው ህወሓት ደጋፊ በመሆኑ የሚነዛቸው ወሬዎች።ሽብርተኛው ቡድን አፈቀላጤዎች ከሰማይ አይወርዱም እዛው አጠግብዎ ከሚወዱት ሰው ላይ የተሰራባቸው ሊሆኑ ይችላል።

3) ሼህ ወይንም ካህን ናቸው አይዋሹም በምትሏቸው ሰዎች የውሸት ዜና ይነዛል።ሽብርተኛው ህወሓት ከእነኝህ አካላት ስውር አባላት ነበሩት።አሁንም በገንዘብ በመደለል የውሸት ዜና እንዲያሰራጩ የሚያሰራቸው አሉ።

4) የህዝብ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች።ከተማ በሕዝብ ትራንስፖርት የሚመላለሱ ነገር ግን አንዳንድ ጥርጥር የሚፈጥሩ መንግስትን በማይገባ ጉዳይ በማጥላላት ሕዝብ ጥላቻ እንዲያድርበት ለማድረግ ቀኑን ሙሉ ከታክሲ ታክሲ እየቀያየሩ ሲሄዱ የሚውሉ አሉ።

5) የመንግስት ሰራተኞች እና ኃላፊዎች። እነኝህ በሚሰሩት ሥራ ሕዝብ እንዲመረር በማድረግ ሕዝቡን የማስመረር ሥራ ከመስራት ባለፈ ከሌላው የተሻለ የሚያውቁ በመምሰል ሕዝብ የማያውቀው እኛ በሃላፊነታችን የምናውቀው በማለት ሆን ብለው ወሬ ይነዛሉ።

6) የመንግስት ሚድያ ላይ የሚሰሩ ጋዜጠኞች፣ቪድዮ አቀናባሪዎች እና ድምፅ ኤድተሮች። እነኝህ ለሕዝብ የሚተላለፉ ዜናዎች ላይ ደካማ ዜናዎች በመምረጥ፣በሚያቀናብሩት ቪድዮ ላይ መንግስትን የሚያሳጣ ጉዳይ ላይ በማትኮር እና ጠቃሚውን በመቁረጥ እና ትኩረት እንዳያገኙ በማድረግ 

7) የህዝቡን ማኅበራዊ ግንኙነት የበለጠ እንዲዳከም እና ተስፋ እንዲቆርጥ የሚያደርጉ።የህዝብ ማህበራዊ ግንኙነት ሲጠነክር ይመካከራል፣ በሽብርተኛው ቡድን ላይ የጋራ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ ያግዘዋል።ስለሆነም ጎረቤት ከጎረቤት፣ሰፈር ከሰፈር፣ እንዲጣሉ በማድረግ።በባህር ማዶ ደግሞ ማኅበርሰብ ከማኅበረሰብ እንዲለያይ በማድረግ ሕዝብ በጋራ እንዳይዋጋ ለማድረግ ይጠቀሙበታል።

የሽብር መንዣ ስምንቱ የመጀመርያ ዓረፍተ ነገሮች።
  • ''ወያኔዎች አይቻሉም----'' እነርሱ እኮ '' የፈለገ ቢሆን እነርሱ ----'' 
  • ''ይሄ ሰውዬ (ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይን) እኔ አላመንኩትም ----''
  • ''ይሄ ተረኝነት ----''
  • '' ያው ነው ያም መጣ ያም መጣ ለሕዝብ ጠብ የሚል እንደሆነ የለም ''
  • '' አይምሰልህ/ሽ ፖለቲካ ማለት -----''
  • '' እኔ ምን አገባኝ ----ምን አገባን''
  • ''ዛሬ በህልሜ ----'' ለጁንታው የሚጠቅም ሕልም ያዩ መስለው ያወሩልዎታል።
  • '' ሰራዊቱ ለምን ይህን አያደርግም፣ያንን አይሰራም-----አውቀው ነው እንጂ ''
ከላይ የተጠቀሱት ሁኔታዎች እና አነጋገሮች ሲገጥማችሁ ሳያውቅ በሌላ ሰለባ ሆኖ የመጣ ወይንም የራሱ የሽብርተኛው ህወሓት የሴል አባል ሆኖ በሽብር ሥራ ላይ ተሰማርቶ እንደሚገኝ ቀድማችሁ ንቁ! ሽብር ነዥዎቹ የሚመጡት በአካል፣በስልክ ወይንም በማኅበራዊ ሚድያ ሊሆን ይችላል። ቀድመው ይንቁ! ይጠርጥሩ! እነኝህ የሽብር መንዛት ስራዎች የሚሰሩት በተደራጀ ነገር ግን አንዳንዴ ነዥዎቹም በማያውቁት መንገድ እንዲሰራባቸው ተደርጎ ነው።

==========================
ማስታወቂያ /Advertisement 
===============================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

Saturday, August 7, 2021

ልዩ ዘገባ - ደብረፅዮን ቆስለዋል፣ በጄኔራል ፃድቃን ቡድን ተገደው ቁስላቸውን ደብቀው መግለጫ እንዲሰጡ ዛሬ ተደርገዋል።አሁን ያለው ነባራዊው የጁንታው ሁኔታ።የኢትዮጵያ ደህንነት የጠለፈው የጁንታው ስብሰባ ውሳኔ ሙሉ ይዘት። ኢትዮጵያ በጦርነት ውስጥም ሆና አስደሳች የልማት ስራዎች ዜናዎች እየወጡ ነው።(ሁሉንም በዘገባው ውስጥ ያገኛሉ)



===============================
ጉዳያችን ልዩ ዘገባ  /Gudayachn Special Report
===============================
ደብረፅዮን ቆስለዋል፣ፃድቃን ላይ የደብረፅዮን ቡድን ደጋፊ ሕዝብ ተነስቶባቸዋል

የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት የነበሩት ዶ/ር ደብረፅዮን ክፉኛ መቁሰላቸው ከታማኝ ምንጮች ተሰምቷል።ይህንን ለማስተባበል ደብረ ጽዮንን በማስገደድ መግለጫ ሰጥተው ለማሰራጨት እየተሞከረ ነው። አሁን በትግራይ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ የስልክ እና ሌሎች መገናኛዎች አለመኖራቸው ነው እንጂ የህወሓት ጀሌ እና ሚሊሻ በደረሰበት የሰው እልቂትም ሆነ በምግብ እጥረት  የትግራይን ሕዝብ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ አድቅቆታል። በመሆኑም በቀጣይ የሚዋጋበት አቅም ባለመኖሩ አሁን ጀሌውን ወደ አፋር እና አማራ ሲልኩት ዘርፈህ ብላ፣ ዘርፈህ ተመለስ እየተባለ እንደሆነ የታመኑ ምንጮች ይጠቁማሉ።

በሌላ በኩል በጄኔራል ፃድቃን ቡድን እና በደብረፅዮን መካከል የተነሳው ፀብ እጅግ ከመባባሱ የተነሳ ፃድቃን ከሃዲ ነው ትግራይን አስወደማት፣በድርድር ህዝቡ ሳያልቅ ንብረት ሳይጠፋ ትግራይን ማስቀጠል እንችል ነበር።በፃድቃን እና ጌታቸው ረዳ ድንፋታ ነው ይህን ያህል ጥፋት የደረሰው የሚለው የደብረ ፅዮን ቡድን ደጋፊ አሁን በፃድቃን ቡድን ላይ ተነስቶበታል።ይህ በእንዲህ እያለ ቀደም ባለው ጦርነት ቀኝ እጃቸውን የተመቱ እና ለመታከም የሞከሩ ቢሆንም በኃላ ከፃድቃን ቡድን በተተኮሰ ጥይት እንደገና መመታታቸው ነው የተነገረው።የደብረ ፅዮንን ሃሳብ የሚደግፉት ፈትለወርቅ (ሞንጆሪኖ) እና ዓለም ገብረዋህድ አብረዋቸው መሆናቸው ስሰማ ሆኖም ግን የፃድቃን ቡድን ከጦርነት ውጪ የሚታያቸው መንገድ የለም። 

ይህ በእንዲህ እያለ የደብረ ፅዮን ቡድን እና የፃድቃን ቡድን ለመገዳደል ሁሉ የሚፈላለጉበት ደረጃ እንደደረሱ ነው መረጃዎች የሚያሳዩት።ይህንን ለማብረድ ደብረ ፅዮን እና ፃድቃን አብረው እንዲታዩ ለማሳየት ቢሞከርም በሃሳቡ ልዩነት ግን የፀና እምነት ያላቸው ካድሬዎች እና የጋንታ መሪዎች ሳይቀሩ በተለያዩ ቦታዎች ግጭት እየፈጠሩ ነው ያሉት።ይህን ሁኔታ የሚያውቁት ጥቂት የጁንታውን ዲያስፖራ ክንፍ አባላት ሲሆኑ ሌላው ከሹክሹክታ ባለፈ በግልጥ አያውቁም።

የኢትዮጵያ ወታደራዊ ድህንነት በሚስጥር የጁንታው ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ አመራር እና የዲያስፖራው ክንፍ በዙም ያደረጉት ሙሉ ስብሰባ ጠልፎ አብሮ ተከታትሏል።

የኢትዮጵያ መከላከያ የጥሞና ጊዜ ለመስጠት እና ለትግራይ ገበሬ የሚያርስበት ጊዜ ለመስጠት ሰኔ 21 መቀሌን ለቆ እንደወጣ የተረፈው የህወሓት ጁንታ የፖለቲካ አመራር እና የወታደራዊ አመራር እንዲሁም የዲያስፖራ ክንፍ በጋር ስብሰባ ተቀምጠው ነበር።ስብሰባውን የኢትዮጵያ ወታደራዊ ደህንነት ክፍል ጠልፎ ገብቶ አብሮ ሙሉውን ተከታትሏል።በእዚህ መሰረት የስብሰባው ውጤት የሚከተሉት እንደነበሩ የፍትህ መፅሄት ዛሬ በሶስተኛ ዓመት፣ ቁጥር 144 ነሐሴ 2013 ዕትም እንደሚከተለው ዘግባለች።

ህወሀት መከላከያ መቀሌን ጥሎ ከወጣ በኋላና ወደ ከተማዋ እንደገባ የጦር መሪዎቹና ፖለቲከኞቹ ለ6ቀናት የzoom ስብሰባ (ውጭ ያሉት ጋርም) አድርገው ነበር። የኢትዮጵያ መከላከያ ሙሉ መረጃውን አብሮ (በሚስጥር) ተከታትሏል።
በ6ቀኑ ቆይታቸው ከተስማሙባቸው ጉዳዮች ውስጥ
1. ትግራይን ለመገንጠል ኢትዮጵያ ውስጥ 3አብዮቶች የግድ ያስፈልጋሉ፣
2. የኦሮሞ ብሔር ምንም የጋራ አገራዊ ማንነት ስለሌላቸው የአአን ጉዳይ "ፊንፊኔ ኬኛ"ብለው እንዲነሱ ማድረግ፣ ለዚህም ተጋሩ የሚከፈለውን ዋጋ ከፍለው የኦነግን ሃይል መደገፍና ፊንፊኔ ኬኛን ማጦዝ አለባቸው፣
3. በአፋርና ሶማሌ ግጭት መፍጠርና አፍር ላይ የተወሰኑ መሬቶችን በኛ በኩል በመውረር አፋር existential threat እንዲሠማው በማድረግ ጅቡቲ ካሉ አፋሮች ጋር እንዲተባበርና ግጭቱ እንዲሠፋ ማድረግ፣
እኛ በምንወጋው ጊዜም ስነልቦናዊ ውድቀት ደርሶበት በኢትዮጵያ ተስፋ እንዲቆርጥ ማድረግ፣
4. የአፋርና ሶማሌ ጦርነት ሰፍቶ የታላቋ ሶማሊያን ፕሮጀክት ማስጀመርና የጂቡቲ አፋሮችና የሶማሊያ ሶማሌዎች ኢትዮጵያ ውስጥ የproxy (የውክልና ጦርነት) ጦርነት ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲከሰት ማድረግ፣
5. ባድመ በግድ እንደተወሰደች አድርጎ በኤርትራ ጦርነት መክፈትና የኤርትራን ተጋሩ ማነሳሳት፣ ለዚህም የኤርትራ ዲያስፖራን መጠቀም፣
6. ኢሳያስ በሚሞትበት ጊዜ የትግራይን ብሔርተኝነት በማቀንቀን ለኤርትራ ትግሬዎች የመጨረሻ እድል መስጠት፣
7. ኤርትራ ውስጥ ያሉ አፋሮች ኢትዮጵያና ጅቡቲ ካሉት ጋር ተባብረው አገር እንዲመሠርቱ ማድረግና መደገፍ፣
8. በኢትዮጵያ በሶማሊያና በጅቡቲ ያሉ ሶማሌዎች ወደ ዋናው አገር ሶማሊያ እንዲቀላቀሉ መስራት፣
9. ባጠቃላይ የታላቋን ትግራይ ለመመስረት ያሁኖቹ ኢትዮጵያ ፣ ጅቡቲ፣ኤርትራና ሶማሊያ የግድ ቅርጻቸውን መቀየር አለባቸው፣
10. ለትግራይ አገር መሆን 4አገሮች የግድ ያስፈልጉናል፣ ግብጽ፣ አሜሪካ ፣ እንግሊዝና እስራኤል፣
👉 ግብጽ ትግራይን የምትደግፍ ከሆነ ግድቡን በትግራይ ወታደሮች እንዲፈርስ እንደምናደርግ ማሳወቅ፣
👉ለእስራኤል እኛም የነሱን መንገድ እንደምንከተል መናገርና ሁሌም ከነሡ ጋር እንደምንሆን ማሣመን፣
👉ከእንግሊዝና አሜሪካ ጋር በሚደረገው ውይይት የምትመሠረተው ትግራይ የኒዮ-ሊብራሊዝም ተከታይ እንደምትሆንና ትግራይ ውስጥ ያሉ ማዕድናት በሙሉ ለUSና USA ባለሀብቶችና ድርጅቶች እንደምንሰጥ ቃል መግባት፣
👉USናUK የሚያቀርቧቸውንም ማናቸውንም ነገሮች ያለቅድመ ሁኔታ መቀበል፣
11. ለምዕራቡ አለም(USAና UKን ጨምሮ) በኤርትራ እየተስፋፋ ያለውን እስልምና እንደሚያሠጋንና ይሄንን ለማጥፋትም አብረን ከነሱ ጋ እንደምንሰራ ማሳመን" የሚሉ ናቸው።

አሁን ያለው ነባራዊው የጁንታው ሁኔታ 

አሁን ያለው የህወሓት ጁንታው እና ትግራይ ውስጥ ያለው ነባራዊ ሁኔታ ፈፅሞ የተዳከመበት እንደሆነ ነው የውጭ የሎጀስቲክ ጥናት ባለሙያዎችም ሆኑ ውስጣዊ የጁንታውን ሁኔታ የሚያውቁ የውጭ ወኪሎቻቸው የሚናገሩት። ለእዚህ ደግሞ የሚሰጡት በቂ ምክንያቶች አሉ። እነርሱም -
  • ከጥቅምት 24ቱ በኢትዮጵያ ሰራዊት ላይ ካደረሱት ጥቃት ጀምሮ የኢትዮጵያ መከላከያ እና የኤርትራ ሰራዊት በጥምር በወሰዱት እርምጃ ዋናው የልዩ ኃይላቸው አስክዋል እና ንዑሱ ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል።
  • በቀጣይ ወደ አማራ እና አፋር ለመግባት ባደረጉት ጥረት በምዕራብ ግንባር ብቻ 12 ጊዜ በብዙ የሰው ኃይል ጥቃት ባለፉት ሶስት ሳምንታት ብቻ ቢሞክሩም ቀድሞ ቆልፍ ቦታዎች የያዘው የአማራ ልዩ ኃይል እና የመከላከያ ሰራዊት ለወሬ ነጋሪ አላስቀረም።በሰሜን ወሎ እና አፋር በአንድ ቀን እስከ ሰላሳ ሺህ ሚሊሻ ነው ያለቀው።ወደ አፋር የተደረገው ሙከራ ላይ በተለይ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ሄሊኮፍተሮች የጁንታው ኃይል በተዘናጋበት ሰዓት ከቀትር በኃላ 11 ሰዓት ገደማ እስከ ምሽት 2 ሰዓት ድረስ በፓውዛ በተደረገ ጥቃት የተረፈ የህወሓት ጀሌ የለም።
  • ከእዚህ በኃላ የተበታተነው የህወሓት ጀሌ የተሰጠው መመርያ በቻለው እየተገናኘ በወልድያ በኩል አድርጎ ወደ ደቡብ ጎንደር በጋይንት በኩል አድርጎ እንዲገባ ያስገድዱት ገቡ።ይህንን የሚያዙት የተቆራረጠ ጀሌ ከኃላው ብዙ ደጋፊ ኃይል እንደሚላክ በውሸት እየተነገረው ነው። ስለሆነም የተበታተነው ጀሌ አንዴ አላማጣ፣አንዴ ላሊበላ ገባ ወጣ የሚል ጀሌ መታየት ጀመረ።
  • በትግራይ ውስጥ ያለው የነዳጅ እና ምግብ ነክ ያልሆነ ያዋጋል ብሎ ጁንታው ያሰበው እስከ ነሐሴ መጀመርያ የሁመራ መንገድን ስለምናስከፍት ከነሐሴ በኃላ  ሎጀስቲክ ከሱዳን ይመጣል በሚል እሳቤ ነበር።ሆኖም ግን ይህ ባለመሆኑ አሁን ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ገብቷል።
  • ላለፉት ስምንት ወራት ለማረስ ጊዜ ያላገኘው ገበሬ (ቀድሞ ከነበረው 2 ነጥብ 5 ሚልዮን ሕዝብ በላይ እርዳታ ላይ ነበር) አሁንም በክረምት ባለማረሱ ምክንያት ለዘር የቀረውን ሳይቀር በመጨረሱ አሁን ረሃብ ሕዝብ ውስጥ ገብቶ ተጨማሪ ወታደር የማግኘት ሕልም ከሳምንታት በኃላ  የሚታይ አይሆንም።
  • በቀጣይ ኤርትራን እንዲወሩ ከውጭ መንግሥታት በተሰጣቸው መመርያ መሰረት አስመራን ለመውጋት ማቀዳቸው ግልጥ ሆኗል።በመሆኑም ኤርትራ ተመልሳ እንደምትመጣ፣የኢትዮጵያ መከላከያም የተኩስ አቁሙ ሲያበቃ ተመልሶ እንደሚመጣ ሕዝቡም ጁንታውም ያውቀዋል።ስለሆነም የውጭ መንግስታት በቶሎ ወደ ድርድር እንዲመጡ እንዲገፉላቸው እየጠየቁ ነው።
  • ነባራዊው ሁኔታ ሲጠቃለል ጁንታው ከውጫዊው ኃይል ባላነሰ የውስጣዊው ቅራኔ እና የችጋር ቆፈን በከፍተኛ ደረጃ ወጥሮ ይዞታል።
የህወሓት ጁንታ ወረራ ውጤቱ ምን ይሆናል?

ባጭሩ አሁን ያለው ሁኔታ እንደ 1983 ዓም የኢትዮጵያ ሕዝብ ተሰላችቶ የሚተወው ጦርነት የሚመስላቸው የጁንታው ደጋፊዎች ብዙ ናቸው።አሁን ሁኔታው እንደዛ አይደለም።ጊዜ በፈጀ ቁጥር የእነፃድቃን የትዕቢት መንገድ ትግራይን ሙሉ በሙሉ ያወድማታል።የመሰረተ ልማት ጉዳይ አይታሰብም።ሕዝብ ግን በከፍተኛ መንገድ መሰደዱ ይቀጥላል።አሁንም ነጭ ጨርቅ እያውለበለቡ ወደ ኤርትራ እና የቀረው የኢትዮጵያ ክፍል እየተሰደደ ያለው ሕዝብ ቁጥሩ እየጨመረ ነው።በቀጣይ የህወሓት ጁንታ የወረራ ውጤት የትግራይ ክልል በክልልነት ላትቀጥል ትችላለች። ከሰሞኑ የተቆራረጠው የጁንታው ጀሌ አንዳንድ የአማራ፣የአፋር እና የኤርትራ ቦታዎች ዘረፋ ይጨምር ይሆናል።በሳምንታት ውስጥ ግን ከማሰልጠኛ የሚወጣው ብቻ ሳይሆን አሁን እየቆረጠ የተነሳው ሕዝብ ሙሉ በሙሉ እንደሚያፀዳው ምንም ጥርጥር የለውም።የእዚህ ጊዜ የፃድቃን ትዕቢት ምን ያህል እንዳልሰራ ቆይቶ ከደነዘዙበት የሚነቁት እራስ በራስ መመታታት መጀመሩ አይቀርም።

የጁንታው ወረራ ለትግራይ የሚል አጀንዳ የለውም።ዋና ዓላማው ''ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እስከ ሲኦል እንወርዳለን'' በማለት በአደባባይ እንደተናገሩት ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እና የባዕዳንን ተልኮ ማስፈፀም ነው።የኢትዮጵያ ሕዝብም የሚዋጋው ለኢትዮጵያ ሕልውና ነው።ለኢትዮጵያ ህልውና ደግሞ ከመቶ ሚልዮን በላይ የሚሆን ሕዝብ ሕልውናውን የማስከበር ግዴታ ስለሆነ ውጤቱ የሚሆነው በጁንታው መቃብር ላይ ኢትዮጵያን በሁለት እግሮቿ ማቆም ነው።

ኢትዮጵያን ላለፉት 50 ዓመታት ከባእዳን ጋር ሆኖ ሕዝብ ወደ ድህነት የመራው የህወሓት ሽብርተኛ ቡድን ያደረሰው ጥፋት ቀላል የሚባል አይደለም።በኮ/ል መንግስቱ ጊዜ አንድ ወቅት እንደጠቀሱት የወያኔ ጦርነት ኢትዮጵያን ድሃ እንዳደረጋት ሲገልጡ ጦርነቱ ባይኖር ኖሮ ኢትዮጵያ ከሰሜን ጫፍ እስከ ደቡብ፣ከምዕራብ እስከ ምስራቅ ድረስ የባቡር ሐዲድ መዘርጋት ትችል እንደነበር ገልጠዋል። ይህ ሳይበቃቸው ላለፉት 27 ዓመታት ያህል በቤተ መንግስት ውስጥ ሆነው ኢትዮጵያን በእርዳታ እና በብድር ያገንገችውን ሁሉ ሲዘርፉ እንደኖሩ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ጥናት ዘገባዎች ሳይቀሩ ከ11 ቢልዮን ዶላር በላይ በሕገ ወጥ መንገድ እንዳወጡ ተጠቅሷል።ዛሬም ጠግበውባት ''ኢትዮጵያን ለማፍረስ እስከ ሲኦል ድረስ መሄድ ካለብን እንሄዳለን'' ብለው በኢትዮጵያ ላይ ካራ ስለውባታል። አሁን የኢትዮጵያ ሕዝብ ካለፈው ተምሯል።እየተዋጋ ሃገሩን ያለማል።

ኢትዮጵያ በጦርነት ውስጥም ሆና አስደሳች የልማት ስራዎች ዜናዎች እየወጡ ነው።

ሰሞኑን ኢትዮጵያ በጦርነት ላይም ሆና የልማት መልካም ዜናዎች ተሰምትወባታል። ከእዚህ በታች በአጭር በአጭሩ ለማቅረብ እሞክራለሁ።የእዚህ ዓይነቱ ዜና አስፈላጊ የሚሆነው ሁሉም ስለማይዘምት እና በመሃል የምጣኔ ሃብቱን እና የልማት ሥራውም አንዱ ግንባር በመሆኑ ከግንዛቤ ውስጥ ለማስገባት ነው።ከእዚህ በታች ያሉት የልማት ስራዎች ባለፈው አንድ ሳምንት ውስጥ በኢትዮጵያ የተዘገቡ ናቸው።

  • በአዲስ አበባ መብራት መቆራረጥ ለማስቀረት የመብትራት ኃይል አመርቂ ሥራ ሰርቷል 
ከ600 ሚልዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለመስመሮች መቆራረጥ ምክንያት የሆኑ 625 ኪሎ ሜትር የምረዝሙ  አሮጌ መስመሮችን በአዲስ የመቀየር ሥራ  መፈፀሙ የተነገረ በእዚህ ሳምንት ነው።በቀጥያ የ400 ኪሎ ሜትር ገመዶች መቀየር ይቀጥላል።ይህ በከተማዋ የመብራት መቆራረጥ እንደሚያቃልል ተነግሯል።
  • በኢትዮጵያ የመኪና ላይ እና የእግር ጉዞ ጂ ፒ ኤስ አገልግሎት በኢትዮጵያውያን ኩባንያዎች ሥራ ላይ ውሏል።
በኢትዮጵያ ያሉ ከተሞች እና ገጠር ለቅሞ የሚያሳይ እና በድምፅም በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ የሚመራ ጂፒኤስ አዲስ አበባ ላይ የተመረቀው በእዚህ ሳምንት ነበር።ጂ ፒ ኤሱ ከኢትዮጵያ ድንበሮች ዙርያ ሁሉ የሚያመላክት መሆኑን እና የቤት ቁጥር እና መንገድ ቁጥር የሌላቸው ቦታዎች ከመብዛታቸው አንፃር ጂፒኤሱ ሁሉም ቦታዎች አመላካች ገፅታን የሚያሳይ መሆኑን እና እየተሻሻለ እንደሚሄድ ተነግሯል።በሌላ በኩል ጂ ፒ ኤሱ አንዴ ሞባይል ላይ ዳውንድ ሎድ ከተደረገ በኃላ ካለ ኢንተርኔት ሊጠቀሙበት እንዲችሉ ተደርጎ መሰራቱ ነው የተነገረው።
  • የከፍተኛ ትምህርት ጥራት ተቆጣጣሪ መስርያቤት ተጠሪነቱ ለፓርላማ እንዲሆን ተወሰነ 
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ጥራት ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ በከፍተኛ ትምህርት ኮሚሽን ስር ሆኖ በተለይ የመንግስት ዩንቨርስቲዎች ጥራት መቆጣጠር ላይ ስሽኮረመም የነበረው ኤጀንሲ ተጠሪነቱ ለፓርላማ እንዲሆን እና ሁሉንም የግል እና የመንግስት ዩንቨርስቲዎች እኩል እንዲቆጣጠር እና ሪፖርት ለፓርላማ ከመስከረም ጀምሮ እንዲያቀርብ ተወስኖ በራሱ እንዲደራጅ መወሰኑ ለማወቅ ተችሏል።
  • የትምህርት ሚኒስቴር ለአንደኛ እና ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የመማርያ መፃህፍት አስረጂ ባለ ቪድዮ ድረ ገፅ አስመረቀ 
ድረ ገፁ በያንዳንዱ ክፍል ያሉ መፃህፍት በቪድዮ የሚሰጥ ገለጣ ተማሪዎች የሚማሩበት ድረ ገጽ ለተማሪዎች በጣም የሚያግዝ እንደሚሆን ተስፋ ተጥሎበታል።ተማሪዎች በትምህርት ቤታቸው መግቢያ በቀላሉ ገብተው የሚያጠኑበት መንገድ አሁን ተመቻችቷል።
  •   የአድዋ ዜሮ ፕሮጀክት መስከረም ላይ እንዲመረቅ ጥድፍያ ላይ ነው።67% ተፈፅሟል።
ኢትዮጵያ አድዋ በዓል በየዓመቱ ይከበር እንጂ ሁነኛ የሆነ የመታሰብያ ቦታም ሆነ ከውጭ ለሚመጣ ጎብኝም የምናሳየው ደረጃውን የጠበቀ ሙዜም የለም።በቅርብ መንግስት በአዲስ አበባ መሃል አራዳ አድዋ ዜሮ ፕሮጀክት በውስጡ ሙዜም፣መፃህፍት ቤት እና ሌሎች ድንቅ የአገልግሎት ክፍሎች እየተሰሩ መሆኑ ተነግሯል።ፕሮጀክቱ በመጪው መስከረም ለመጨረስ ጥድፍያ ቢኖርም ምናልባት በወራት ሊቀጥል ይችላል የሚል ግምት አለ።አሁን ግን 67% ተፈፅሟል።
  • 3ነጥብ 6 ቢልዮን ዶላር ገቢ 
ኢትዮጵያ ከእዚህ በፊት አግኝታ ከምታውቀው በላይ ከውጭ ንግድ ማግኘቷ የተሰማው በእዚህ ሳምንት ነው።በእዚህ መሰረት በያዝነው ዓመት 3 ነጥብ 6 ቢልዮን ዶላር ማግኘቷ ለማወቅ ተችሏል።
  • 90 ሚልዮን ዶላር 
ኢትዮጵያ ከኤሌክትሪክ ሽያጭ 90 ሚልዮን ዶላር ማግኘቷ የተጠቀሰውም በእዚህ ሳምንት ነው።ይህ ገቢ ለጅቡቲ እና ሱዳን ብቻ ከተሸጠው የተገኘ ገቢ ሲሆን የሱዳን መንግስት አሁን የሚያገኘው 200 ሜጋ ዋት ሲሆን በቅርቡ ኢትዮጵያ 1000 ሜጋ ዋት እንድትሸጥላት  እንደጠየቀች በእዚህ ሳምንት ተነግሯል።መንግስት አሁን ካለው የሱዳን እና የኢትዮጵያ ግንኙነት አንፃር የሚያየው እንደሚሆን የብዙዎች ግምት ነው።
  • የአዲስ አበባ ማዘጋጃ እድሳት (አንድኛው ክንፍ) መስከረም መጨረሻ ይመረቃል።
የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ከተሰራ ጀምሮ እንደ አሁኑ ሙሉ እድሳት ተደርጎለት አይታወቅም።አሁን ታሪካዊ ይዘቱን ሳይለቅ ነገር ግን እጅግ ዘመናዊ በሆነ መልኩ እድሳቱ ተጀምሯል።እድሳቱ በተራ በሁለቱ ክንፍ እየተሰራ ሲሆን የአንደኛው ክንፍ በ62 ሚልዮን ብር እድሳት ከመስከረም መጨረሻ በፊት ይመረቃል። አሁን የሚመረቀው የልጆች መጫወቻ እና 150 መኪናዎች ማቆምያ ሁሉ ያካተተ እንደሆነ ለማወቅ ይቻላል።
===================///================= 

================
 ማስታወቂያ / Advertisment
====================
የጓደኞችዎን ወይም የቤተሰብዎን የሞባይል አየር ጊዜ ለማሳደግ ከዚህ በታች ያለውን አገናኝ ጠቅ ያድርጉ።
በአንድ ሁኔታ ውስጥ በሚመገብ ቤት የሚኖር የቤተሰብ እውነተኛ የወዳጅነት ስልክዎ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን የሚመለከት ከስር ሊ መረጃን ይጫኑ - 
Open the link to mobile top up at home







Friday, August 6, 2021

ልዩ ጥንቃቄ - በምዕራብ ኢትዮጵያ አዲስ ስጋት አለ።




  • በማይካድራ የዘር ጭፍጨፋ የፈፀመው የህወሓት ኃይል ሲሰለጥን ቆይቶ ኢትዮጵያ ላይ ለመዝመት  አሁን ሱዳን ብሉናይል ግዛት ገብቷል።

ጉዳያችን ዜና / Gudayachn News
========================== 
የማይ ካድራን ጭፍጨፋ ፈጽሞ ወደ ሱዳን የሸሸው ኃይል ተጨማሪ ስደተኞችን አክሎ ወታደራዊ ሥልጠና በኒውዮርክ የኢትዮጵያ ወታደራዊ አታሼ በነበረ ሰው ስልጠና እየወሰደ እንደነበር ከእዚህ በፊት መገለጡ ይታወቃል። ይህ ኃ ኃይል በአሁኑ ጊዜ ወደ ብሉ ናይል ግዛት የገባ ሲሆን በቋራ እና በቤኒሻንጉል በኩል ለመምጣት ዝግጅት ላይ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። በተለይም በቋራ ከቅማንት ታጣቂ፣ በቤኒሻንጉል ከጉምዝ ታጣቂ ጋር በመሆን ትንኮሳ ለመፈጸም ማሰቡን የመረጃ ምንጮች ገልጠዋል።  ጉዳዩን የሱዳን መንግሥት  ቢክድም የሳተላይት ፎቶዎች ግን እንቅስቃሴውን አጋልጠዋል።

በሌላ በኩል ይህንን ስራዋን የምታውቀው ሱዳን በአብዬ ግዛት የሚገኘው በተባበሩት መንግሥታት ስር የሚገኘው የኢትዮጵያ ጦር ከተለያዩ ሀገሮች በተውጣጣ ኃይል እንዲቀየርላት ከእዚህ በፊት የጠየቀችው ሱዳን ዛሬ እንደ አዲስ ጥያቄዋን አንስታለች።ሚድል ኢስት ሞኒተር ዛሬ እንደገለጠው ሱዳን ባለፈው ሚያዝያ ወር ላይ የጠየቀችውን ጥያቄ መልሳ አሁን ማንሳቷን ገልጧል።በሱዳን 4ሺህ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል የሚገኝ ሲሆን ሰራዊቱ የደቡብ እና ሰሜን ሱዳን መገናኛ በሆነችው እና በነዳጅ ሀብት በበለፀገው የአብዬ ግዛት ላይ የሚገኙ ሲሆን በቦታው የሚገኙ ሲቪሎች እና የእርዳታ ሰራተኞች ጥበቃ እና ቁጥጥር ላይ ተሰማርተዋል።ሱዳን ይህንን ጥያቄ ያነሳቸው አንዱ ምክንያት በኢትዮጵያ ላይ የሚዘምቱ በማይካድራ ጭፍጨፋ የተሳተፉ ወንጀለኞችን እያሰለተነች እና ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት እየሞከረች ከመሆኑ አንፃር ከኢትዮጵያ ጋር የበለጠ ፍጥጫ ውስጥ እንደምትገባ በመረዳት እንደሆነ መገመት ይቻላል።

Thursday, August 5, 2021

የኢትዮጵያ እናቶች እና ድንግል ማርያም ምስጢረኞች ናቸው።በምስጢር ያወራሉ፣በምስጢር ስለ ኢትዮጵያ ይመክራሉ።



ሐመረ ኖህ እንጦጦ ኪዳነ ምሕረት 

- ባለፈው ሰሞን ብዙ ታውቃለች የምላት አንዲት እህት የኢትዮጵያ ሰራዊት በ21 መቀሌ ገብቶ በ21 ወጣ የሚል ፅፋ ልክ ድንግል ማርያም የህወሓትን ደም አፍሳሽ ወንጀለኛ ሰራዊት የምትደግፍ አድርጋ በውስጠ ወይራ በማኅበራዊ ሚድያ ላይ ስትፅፍ አይቼ፣አዬ! የራስን ክፋት ቅዱሳን እንዲያግዙ የመመኘት የዘመኑ ድፍረት! ብዬ ገርሞኝ ነው የሰነበተው።

- የኢትዮጵያ እናቶች በምስጢር የሚያማክሯት እናት አለቻቸው።ጎረቤት ቢያስከፋቸው፣መንግስት ቢበድላቸው፣የቤቱ ጣጣ ከገበያው አልጣጣም  ብሏቸው ልጆቻቸው እንዳይራቡ ሲሰጉ፣ሀገር ላይ ረሃብ እና ጦርነት ሲመጣ ወደ የምስጢር እናታቸው ድንግል ማርያም ስዕል ጠጋ ብለው ያወሯታል። 

================
ኢትዮጵያ ተአምር የሆነች ሀገር ነች።ብፁዕ አቡነ ኤልያስ በስካንድንቭያን ሀገሮች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ የኢትዮጵያን ጉዳይ ሲያነሱ '' ልጆቼ አይምሰላችሁ።እኔ በሕይወቴ ሁሉ የተረዳሁት ሃገሩን እንዲሁ የሚጠብቀው የእግዚአብሔር መንፈስ አለ።ይህ መንፈስ ማዕበል ሲመጣ እንዴት አድርጎ እንደሚያጠፋ፣ሃገሩን እንደነበረ መልሶ ስገጣጥም ነው የሚታየው። ኢትዮጵያ የምትጠበቅበት ልዩ መንፈስ አላት'' ይላሉ።ከሰማንያ ዓመታት በላይ ያስቆጠሩት አባት ይህንን የሚሉበትን ምክንያት ሲያስረዱ ዝም ብለው ሳይሆን ከልጅነታቸው በኢትዮጵያ ላይ የተመለከቱትን እያንዳንዱን ክስተት እያስታወሱ ነው።

 ከ1933 ዓም እስከ 1982 ዓም የኖሩት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በቀድሞ አጠራር የሸዋ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ኢትዮጵያን ሲገልፁ '' የእግዚአብሔር የምስጢር ሀገር'' ብለው ነው።እግዚአብሔር በዓለም እንዲቀመጡ ያልተዋቸው፣ዓለም የተዋቸውን ውድ የአምላክነቱ መገለጫ የአምልኮ ስርዓቶች የምስጢር ኪሱ የሆነችው ኢትዮጵያ ውስጥ አስቅምጧል።ዓለም የሌለው ያሬዳዊ ዜማ፣ታቦተ ፅዮን፣ግማደ መስቀሉ እና ገና ጊዜያቸው ደርሶ ያልወጡ ምስጢራት ሁሉ በኢትዮጵያ አሉ።በአስር ዓመታት የጵጵስና አገልግሎታቸው ብዙ ፍሬ ያፈሩት አቡነ ጎርጎርዮስ ዕብራይስጥ፣ እንግሊዝኛ፣ ፈረንሳይኛ እና አረብኛ ቋንቋዎችን የሚችሉ ሲሆን የወታደራዊው መንግስት ከመውደቁ አንድ ዓመት ቀደም ብለው ብፁዕነታቸው ሚያዚያ 23/1982 ዓ.ም፣ ሻሸመኔ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ያስተማሩት ትምህርት ላይ የኢትዮጵያውያንን አንድነት ሲናገሩ ''ምንም ብትሉ ምንም ብትሉ ይሄ ሕዝብ አንድ ነው'' ብለዋል።በወቅቱ ኢትዮጵያ ገና በህወሓት የጎሳ ክልል ሳትከለል እና የጎሳ እሳት ሳይጣድባት ነበር ይህንን የተናገሩት።

ከላይ የአረጋዊውን እና አሁንም በሕይወት ያሉትን አቡነ ኤልያስን እና በአካለ ሥጋ የተለዩን አቡነ ጎርጎርዮስ (ቡራኬያቸው ይደርብንና) ከተናገሩት መነሻ ላድርግ እንጂ የዛሬ ማጠንጠኛ ሃሳቤ የኢትዮጵያ እናቶች እና ድንግል ማርያም በምስጢር ከድንግል ማርያም ጋር እንዴት እንደሚያወሩ ለማውሳት ነው። ነገ ነሐሴ 1/2013 ዓም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ስርዓት መሰረት ከሰባቱ የአዋጅ አፅዋማት ውስጥ የሚመደበው የፍልሰታ ፆም ነው።ይህ ፆም በኢትዮጵያውያን የሃይማኖቱ ተከታዮች ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ከህፃን እስከ አዋቂ የምፆመው፣አብያተ ክርስቲያናት በምእመናን የሚሞሉበት፣ካሕናት ሌሊት በሰዓታት፣ቀን በቅዳሴ እና የአንደምታ ትርጉም የሚያገለግሉበት ነው።ወሩ ክረምት እንደመሆኑ ሕፃናቱም ሆኑ ወጣቶች የትምህርት ጊዜያቸው ስላልሆነ ወደ አብያተ ክርስቲያናት ለመሄድ አመቺ ጊዜ ነው።

የዘንድሮው የፍልሰታ ፆም ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያን ፈተና እንዲቀል የሚጸልዩበት ልዩ ዓመት ነው።''ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲዖልም ቢሆን እንወርዳለን'' እያለ የሚደነፋ ባላጋራ ተነስቶባታል።ልጆቿን በጎሳ ከፋፍለው እያናከሱ ''የበቀል እጃችሁን አንሱ''  የሚል ግልጥ መልዕክት ከህወሓት አመራሮች ተሰጥቶባታል።ጦርነት በሀገሪቱ ሰሜን እየተደረገ ነው።በእዚሁ ጦርነት በህወሓት የአማራ እና የአፋር ሕዝብ ላይ በተከፈተው ጦርነት ከ200 ሺህ በላይ ሕዝብ ተፈናቅሏል።በትግራይም ላለፉት 9 ወራት በመቶ ሺዎች ለረሃብ በአስር ሺዎች ለመፈናቀል በአስር ሺዎች ደግሞ ለሞት ተዳርገዋል።በእዚህ ሁሉ መሃል ግን የእናቶች ለቅሶ እና ጭንቀት አለ።

የኢትዮጵያ እናቶች በምስጢር የሚያማክሯት እናት አለቻቸው።ጎረቤት ቢያስከፋቸው፣መንግስት ቢበድላቸው፣የቤቱ ጣጣ ከገበያው አልጣጣም  ብሏቸው ልጆቻቸው እንዳይራቡ ሲሰጉ፣ሀገር ላይ ረሃብ እና ጦርነት ሲመጣ ወደ የምስጢር እናታቸው ድንግል ማርያም ስዕል ጠጋ ብለው ያወሯታል። ወደ ድንግል ማርያም ስዕል (ስዕለ አድህኖ) ሲጠጉ ልጇን ክርስቶስን አብረው ያገኙታል።እናትና ልጁን የሚነግሯቸው በእምነት ነው።እንደ ዘመኑ ጥቅስ ተቃሽ፣ቁጥር እና ምዕራፍ ሳይሆን በሕይወታቸው ከአምላክ እናት ጋር በምስጢር በማውራት ምን እንደሚገኝ በሕይወታቸው ሁሉ ያውቁታል።ብዙ መከራ በቤታቸው እየጨረፈ ሲጠጋ እንዴት በምስጢር ከድንግል ማርያም ጋር አውርተው እንዳለፈ የሚጠቅሱት አፍ የሚያስይዙ ታሪኮች አሏቸው።ብዙውን አይናገሩትም።እንደነሱ ምስጢሩን ለሚያውቁ እናቶች ካገኙ አብረው ያወጉታል።በሀገር የመጣ ፈተና እንዴት በጸሎት እንደሚያልፍ፣ኢትዮጵያን የነካ እንዴት በፀሎታቸው የውሃ ላይ ኩበት እንደሚያደርጉት ያውቃሉ።ብዙ አያወሩም።ፈተና ሲመጣ አይርበተበቱም።ብቻ መጣሁ ብለው ወደ የመኝታ  ክፍላቸው ወይንም ወደ አቅራቢያቸው ወዳለው ቤተክርስቲያን ሄደው ''የጭንቅ አማላጇ፣የአምላክ እናት'' ብለው ከልጅሽ ከወዳጅሽ አማልጅን ብለው በለቅሶ ይጠሯታል።በወንጌሉም በሰርግ ቤት ወይኑ ሲያልቅ መላ በይን ብለው ወደ ድንግል ማርያም ቀርበው የምልጃ ፍሬ ካዩት በላይ እነርሱ ብዙ የሚተርኩት እውነተኛ ታሪኮች አሏቸው።

በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ እናቶች ማዶ ከትግራይ ወዲህ ከቀረው የኢትዮጵያ ክፍል ሆነው ''ቅድስት ሆይ ልምኝልን'' እያሉ የሚማፀኑበት ጊዜ ነው። ድንግል ማርያም የማንንም ፖለቲካ አታይም።ኢትዮጵያን ለመበተን እስከ ሲኦል እወርዳለሁ ብሎ በድፍረት በተናገረው ግን ትደሰታለች ማለት አይደለም።ባለፈው ሰሞን ብዙ ታውቃለች የምላት የኢትዮጵያ ሰራዊት በ21 መቀሌ ገብቶ በ21 ወጣ የሚል ፅፋ ልክ ድንግል ማርያም የህወሓትን ደም አፍሳሽ ወንጀለኛ ሰራዊት የምትደግፍ አድርጋ በውስጠ ወይራ በማኅበራዊ ሚድያ ላይ ስትፅፍ አይቼ፣አዬ! የራስን ክፋት ቅዱሳን እንዲያግዙ የመመኘት የዘመኑ ድፍረት! ብዬ ገርሞኝ ነው የሰነበተው።የምድር የዘር አንቡላችንን እኛው ጋር እንደቀረፋ ይቀመጥ እንጂ በኃጢአት ለላሸቀ ከሰይጣን ለከፋ ክፋታችን ቅዱሳንን እንዲያግዙን  የማድረግ ድፍረታችንን ይቅር ይበለን።የኢትዮጵያ እናቶች እንዲህ አይደሉም።እነርሱ ክፉ ላደረገ ክፉ አታድርግ የሚል ብሂላቸው ሁሌም መመርያቸው ነው።ይህ ማለት ግን የግፍ ፅዋ የሚቀበሉበት የውሃ ልክ የለም ማለት አይደለም።እንደ ጣይቱ በሀገራቸው እና በሕዝብ ላይ የመጣን ከፊት የሚመሩበት ጊዜ አለ።የግፍ ፅዋው ሞልቶ ሲተርፍ።

ከእዚህ ሁሉ በፊት ግን ወደ ምስጢረኛዋ ድንግል ማርያም ቀርበው ስለሀገር፣ስለልጆቻቸው እና ስለ መንደራቸው ሁሉ እያለቀሱ ከልጅሽ አማልጅን ብለው መፀለያቸው ይቀድማል። ፀሎታቸው ደግሞ መሬት ወድቆ አያውቅም።ኢትዮጵያን እዚህ ያደረሳት የእናቶቻችን ፀሎትም ነው።ጠቅላይ ሚንስትር ዓቢይ  የኢትዮጵያ እናቶች ፀሎት ነው የሚጠብቀኝ ሲሉ ዝም ብለው አይደለም።በክርስትናም ሆነ በእስልምና ያሉ እናቶች እንዴት እንደየየሚያመልኩት አምላክ እንደሚፀልዩ ስለሚያውቁ ነው።ዘንድሮም በፆመ ፍልሰታ በትግራይ ያለች እናትም በጎንደር እና ጎጃም፣ገሞጎፋ እና ከፋ፣ሐረር እና ጅጅጋም ያለች እናት ስለ ኢትዮጵያ ስለልጆቿ እና ስለ ሁሉም ወደ የምስጢር ወዳጇ ድንግል ማርያም ጠጋ ብላ በሃዘን ፀሎቷን ታደርሳለች። በእዚህ የትግራይ እናት ከጅጅጋው፣የግምበላዋ እና ከደብረብርሃን፣የአምቦዋ ከጎንደር በፀሎት በእንባ ትገናኛለች።የእናቶቻችን ፀሎት ጎርፍ ነው።ኢትዮጵያን የሚጠላ ''ኢትዮጵያን ለመበተን እስከ ሲኦል እደርሳለሁ'' እያለ የደነፋውን ጎርፍ አድርጎ ይወስዳል።ድንግል ማርያምም የኢትዮጵያ ነገር አይሆንላትም እና ለምልጃ ከልጇ ፊት ትቆማለች።ስትቆም ደግሞ ፍርድ ከዙፋኑ ይወጣል። በእዚህ እናምናለን።

የኢትዮጵያ እናቶች እና ድንግል ማርያም ምስጢረኞች ናቸው።በምስጢር ያወራሉ፣ስለ ኢትዮጵያ ይመክራሉ።
ከፆሙ በረከት ይክፈለን! የኢትዮጵያን ጠላቶች ከእግሮቿ በታች ይጣልላት!
========================///===========

==========================
ማስታወቂያ /Advertisement 
===============================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 


Wednesday, August 4, 2021

The current US Government is complicating the Horn of Africa problems. The three huge mistakes in today’s US Secretary of State Antony J. Blinken spoke with Sudan Prime Minister Abdalla Hamdok.

 

Department of State

The Nine lines press release from the US Secretary of state Antony J. Blinken states as the Secretary spoke today with the Sudanese Prime Minister Abdalla Hamdok. It also mentioned ‘’the discussion was shared concerns over the expansion of armed confrontation in the Amhara and Afar regions of Ethiopia, the deteriorating humanitarian situation in the Tigray region, and reports of Eritrean troops re-entering Ethiopia…impact regional stability.’’

Here is the full statement of the Press release –

‘’Secretary of State Antony J. Blinken spoke today with Sudanese Prime Minister Abdalla Hamdok to discuss shared concerns over the expansion of armed confrontation in the Amhara and Afar regions of Ethiopia, the deteriorating humanitarian situation in the Tigray region, and reports of Eritrean troops re-entering Ethiopia, all of which impact regional stability. Secretary Blinken and PM Hamdok agreed to encourage all parties to enter negotiations toward a ceasefire, to engage in an inclusive political dialogue to preserve the unity and integrity of the Ethiopian state, and to allow full humanitarian access to those in need.  The Secretary and the Prime Minister also discussed progress in Sudan’s democratic transition and ways to expand U.S.-Sudanese relations.’’


According to this press release US Secretary of state makes the following huge mistakes that are clearly visible from the press release.

These are: -

Mistake I

 The US Secretary of state is not speaking with the perfect actor of the situation. Why he did not discussed with the Ethiopian Foreign Minister or PM Abiy who have the first hand capacity to handle the situation? Why he prefer to talk with Sudan PM on Ethiopia internal issue. It is quite clear the US current Government is pushing the Sudan Government and Military to make some sort of interference in Ethiopian internal case. The US Government never released a press condemning the Sudan invasion of the territory of Ethiopia for the last 8 months. This is not by chance. It is a clear indicator that the US Government is at the back of Sudan (the immediate back Egypt is there also) in her all 'touches the red line' of invading  Ethiopian territory.

Egypt military is almost fully dependant on the US military assistance and personal trainings. Egypt and Sudan were on three round military trainings for the last 12 months. The last military training was titled ‘The Nile Guard’. All these situations were part of the provokes against Ethiopia. Today US Secretary of state talks with the Sudan PM instead of discussing and looking for solutions with Ethiopian authorities means a lot in diplomatic words since Ethiopia and US over a Century official diplomatic relation is alive.

Mistake II

 The recent press releases, speeches and articles came out from the US Government are not curious for its political words, diplomatic relations, even the integrity and Sovereignty of Ethiopia. Using Tigray region militia as ‘’Tigray Defence Force’’ and counting the regional militia of Amhara and other regions of Ethiopia local militias as if they are an independent army of certain nations are a common but seems intentional flashes seen from Washington side. This is a dangerous outlook and not less than from provoking and interfering in a very internal issue of Ethiopia.

In today’s press release also the US Secretary of State mentioned the local militia of Amhara and Afar putting in the level of other country national army. For example, when US talks about the withdrawal of the Eritrean army from Tigray, the Amhara and Afar militias withdrawal  issue is also mentioned together. This is as if the Amhara and Afar local militias have equal status to other country’s army, like Eritrea, US mentioned to leave from their own land of country. This is nothing but to say the California state police can not make any law enforcement in Washington D.C.

Both Amhara and Afar region militias, whether they go to Tigray or Oromia, they are moving within their own land and territory. But United States attempt in her press releases and officials’ opinion shares to Journalists, they try to dictate where Ethiopian army and militia suppose to go and back. This is a very dangerous motive that some US officials are developing the outdated ‘colonial mind’. It will not also bring peace to the Horn of Africa. Other than more complication.

Mistake III

The third mistake of the Secretary of State’s today press release, on the talks with the Sudan PM and the previous press releases regarding the security condition of the Amhara and Afar regions in Ethiopia, is that US is trying to hide the origin of the  security problem for the two regions. Before three weeks, there was not a single security problem in Amhara and Afar regions in the level of today. The TPLF militia invasion to Amhara and Afar region is the main source, cause and origin of the security problem in the two regions. However, US press releases and officials’ speeches ‘go around the bush’. No one heard that as the US government criticize the TPLF invade to the two regions is the main cause of security problem. In today’s particular press release, nothing is mentioned as the TPLF is the cause for displacements of Hundred thousands from both Amhara and Afar regions.

In general, the current US Government is complicating the Horn of Africa problems rather than looking for the necessary solutions. It is biased and seems to repeat the same mistakes that the former US Government’s made in Syria, Libya and Afghanistan. As far as I understand my own birth country, Ethiopia, all previous wrong strategies applied in Libya, Syria and Afghanistan can never be applicable in Ethiopia. Supporting faction groups and undermining the legally elected Governments might have been applied in those countries. But it can not be in Ethiopia. This is quite a different land, over 3000 years non-interrupted statehood history and unique deep-rooted culture with resilience unity that is not easily visible,penetrate and predictable. History in the future will show us all.

Getachew Bekele Damtew

Gudayachn Editor 

 ============////===============

 

 


Tuesday, August 3, 2021

ዘግናኝ ነው።በለንደን፣ዴንቨር እና ካርቱም በጅብ የተበላ አስከሬን ከበው ጨፈሩ!?

Picture credit to buzzfeed.com


እህል እንዴት በጉሮሯቸው ወረደላቸው? ተኩሎ መውጣት፣የክት ልብስ አውጥቶ መልበስ፣ማሽካካት እና መደለቁ እንዴት ከሰውነታቸው ጋር ተስማማላቸው? የትግራይ እናቶች ልጆቻቸው በመሶበ የሲብንቶ ፋብሪካ መኪና እየተጫኑ ወደ አፋር እና የአማራ አዋሳኝ  ወረዳዎች እየተወሰዱ ተደፍተው፣የአፋር እና የቆቦ ጅቦች የምሽቱ አልበቃ ብሏቸው በቀን እየወጡ የትግራይ ልጆችን ታፋ፣እግር እና አንገት እየቦጠቦጡ ሲዘነጥሉ፣የአፋር አርብቶ አደር እና የአማራ ገበሬ የትግራይ ወጣቶችን አስከሬን ለመቅበር ሳምንታንት አይበቁኝም እያለ በደቦ ወጥቶ እየቀበረ፣ የሽብርተኛው ህወሓት ቅምጥሎች በአሜሪካ ዴንቨር፣በእንግሊዝ ለንደን እና በሱዳን ካርቱም ድግስ ደግሰው እየበሉ እየጠጡ እና ከበሮ እየደለቁ ሲጨፍሩ አደሩ።

''ትግራይ መከራ የሚመጣው ከበሮ ሲበዛ ነው።ሀገሩ የእግዚኦታ ጸሎት እንጂ ጭፈራ ሲበዛ አይወድም'' የሚለው አባባል የትግራይ እናቶች እና አባቶች የሚናገሩት ነው።እነርሱ እንደሚሉት ድሮ አያቶቻችን ነገሩን ነው።ይህ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ አነጋገር እንደሆነ ይታመናል።ሀገሩ የገዳማውያን የእነ አባ ጴንጤሌዎን፣የእነ አባ ገሪማ፣የእነ አቡነ አረጋዊ የጸሎት  ቦታ እንጂ በዘመኑ እንደተነሱት 'ጉግ ማንጉጎች' የእነ ጌታቸው ረዳ፣ ደብረፅዮን እና ፃድቃን አጉራ ዘለል የጥፋት መልዕክተኞች አይደለም።

በሀገር ውስጥ የትግራይ እናቶችን በአንዲት አንባሻ መጋገርያ እፍኝ ስንዴ አንሰጥሽም ማስፈራርያ (እርሱም ገና በአፋር በኩል በሚገባ የእርዳት እህል ነው) የትግራይ እናት ልጇን ብቻ ሳይሆን በቤቷ ያለውን የሚላስ የሚቀመስ ለህወሓት ካልሰጠች ሞት ይጠብቃታል።ይህ ያስመረራቸው የመቀሌ እናቶች ባለፈው ሳምንት ''ልጆቻችንን አምጡ!'' ብለው ለመሰለፍ ቢሞክሩ በጌታቸው ረዳ የእርዳታ እህል በጠገቡ ቅልቦች ተይዘው በሚያሰቅቅ ሁኔታ ተገርፈው ወደ እስር ቤት ተወርውረዋል።በልጆቻቸው መታፈስ ያዘኑ እና መጠየቅ የሚያስከትለውን መከራ የተረዱ እናት እራሳቸውን በራሳቸው ማጥፋታቸው ያለፈው ሳምንት የመቀሌ ዜና ነበር።

በእዚህ ሁሉ የመከራ ዶፍ ላይ ግን በለንደን፣ዴንቨር እና ካርቱም ቀደም ብለው የህወሓት ጥቅም ተጋሪዎች የሰፋ ሰውነታቸውን እያገላበጡ በትግራይ ወጣቶች እና እናቶች አስከሬን ዙርያ ጨፈሩ።አዳራሹን ክብ ሰርተው ሲዞሩ በመሃል የሚጮህ በጅብ እየተዘነጠለ  ያለ የምስኪን የትግራይ ታዳጊ ሕፃን አስከሬን አለ።የጅቡ ጥርስ ስጋውን አልፎ አጥንቱን ሲሰነጥቅ የሚያሰማው የሲቃ ድምፅ እንዳይሰማቸው ሙዚቃውን ጨምረው!ጨምረው! ይባባላሉ።የአስከሬኑ ሽታ እንዳይሸታቸው እና የአራዊቱ የሰው ስጋ ዝንጠላ የሰቆቃ ድምፅ እንዳይረብሻቸው  አስከሬን ከቦ ከሚጨፍረው ሕዝብ ከፍ ያለ መድረክ ላይ የሚታዩት የድሮ የኪነ ጥበብ ሰዎች እየተባሉ ይጠሩ የነበሩ ናቸው።ኪነ ጥበብ የሁሉም ነች።የኪነ ጥበብ ሰው የሰው ልጅ ሁሉ የሆነ ጥበብን ይዟልና በዘሩ ተጠራርቶ አስከሬን በሞላባት፣የእናቶች ሰቆቃ በጆሮ በሚያቃጭልበት ሰዓት ሕዝብ አያስጨፍርም።

ለመሆኑ ከምን ተፈጥረው ነው? ቆመንለታል የሚሉት የትግራይ ሕዝብ ታዳጊዎቹን እያነቀ ወደ ግንባር የምልከው የህወሓት የሽብር ቡድን እያሞገሱ በትግራይ ልጆች አስከሬን ዙርያ የሚደንሱት? የዴንቨር፣ለንደን እና ካርቱም የህወሓት ቅምጥሎች ጨፋሪዎች ፊት መሽካካት የሚታይበት የደለበ ሰውነታቸው ቅንጣት ታህል በአስር ሺዎች እንደቅጠል የረገፈበት ከትግራይ ማኅበረሰብ የወጡ አይመስሉም።እነርሱ ሞት አይደለም ጠንከር ያለ ፀሐይ እንዳይነካቸው መኪናቸው ውስጥ የአየር ማቀዝቀዣ እየተጠቀሙ የሚሄዱ ቅምጥሎች ናቸው። እራሳቸው ቀስቅሰው በተነሳ ጦርነት ሺዎች እረግፈው እና ጅብ ሰውነታቸውን እየበላው፣ህፃናቱ አድኑን እያሉ እየጮሁ፣ እናቶች ልጆቻቸውን የሚያስገቡበት አጥተው እያለቀሱ፣ቅምጥሎቹ ዴንቨራውያን እና ለንደናውያን በራሱ በጅብ በሚበላው ሕዝብ ስም ድግስ ጠርተው እየበሉ ያወካሉ፣'ትግራይ!' እያሉ ይዘባበታሉ።

በእነርሱ ቤት የእናቶች ለቅሶ የእንባቸው ወላፈን እነርሱን አይነካም፣በእነርሱ ቅንጭር የአስተሳሰብ ልክ ጅብ የሚዘነጥላቸው የትግራይ ታዳጊ ልጆች እና ወጣቶች አስከሬን ዕጣ እነርሱ ቤት እና በልጆቻቸው አይደርስም፣ በእነርሱ ቤት የእነርሱ ልጆች ከምግብ ምግብ አማርጠው የአይስክሬም ቀለም ዓይነት ላይ የሚጣሉ ቅምጥሎች ላይ የትግራይ ልጆች ዕጣ አይደርስም። ፈጣሪ ፍርዱ ከስር ነው።ለሞቱት ሲፈርድ ማን አነሳሳው፣ማን ወጠነው፣ማን እንዴት እና በምን ምክንያት የትግራይ ልጆችን ለጅብ እንዲሰጡ አደረሳቸው የሚለውን ሁሉ መርምሮ ነው።ያን ጊዜ ዛሬ አስከሬን ዙርያ ከቦ የመጨፈር ስነ ልቦና የእብደት እና የአዕምሮ መሰለብ እንጂ የጤነኛ ሰው ሥራ እንዳልሆነ የዛሬ ጨፋሪዎች  ርቱዕ በሆነች ፍርድ እንዲረዱት ይደረጋል። ያኔ ''ትግራይ መከራ የሚመጣው ከበሮ ሲበዛ ነው።ሀገሩ የእግዚኦታ ጸሎት እንጂ ጭፈራ ሲበዛ አይወድም'' የሚለው የትግራይ አያቶች አባባል ዕውነት መሆኑ ይገለጥላችኃል።ለካ ቆመንለታል የምትሉትን ሕዝብ እንዴት ትወዱታላችሁ? ጃል! በሞተበት፣እናቶች እራሳቸውን በሚያጠፉበት ልጆች አስከሬናቸው በጅብ በሚዘነጠልበት ጊዜ መርጣችሁ መጨፈራችሁ።በጭፈራው የታደማችሁ ሁሉ ህሊና ካላችሁ ብቻ መልሳችሁ የሰራችሁትን አስቡት።

በመጨረሻ የናንተ የቅምጥሎቹ የሰሞኑ የጥጋብ ስራ መቼ  በትግራይ እናቶች እና ወጣቶች አስከሬን ዙርያ እየዞራችሁ መጨፈር ብቻ  ሆነ? ኢትዮጵያን አናውቃትም ብላችሁ ሁሉ አቅራርታችሁ ነበር።የአሉላን ስም እየጠራችሁ የምትነግዱ የራስ አሉላ ደመኞች፣በንጉሥ ዮሐንስ ስም ይምትነግዱ እናንት የዮሐንስ አንገት ቆርጣችሁ በካርቱም አድባባይ ገበያ ለገበያ ካዞሩት ጋር የተዋዋላችሁ ባንዳዎች ናችሁ።ኢትዮጵያ ይህንን ሰምታ እኔም አላውቃችሁም የእናንተ ዓይነት አስከሬን ከቦ የሚጨፍር ልጅ የለኝም ብላ መልሳለች።በነገራችን ላይ ኢትዮጵያን አናውቅም ያሉት እና በአዳራሹ የነበሩት ፎቶ እና ቪድዮ በሙሉ አዲስ አበባ ኢሚግሬሽን ቢሮ ገብቷል።ሀገር ቤት ያላቸውም ንብረት ኢትዮጵያን አናውቃትም ላሏት የምትጠብቅላቸው አይመስልም።እናት አላውቅሽም ያላትን ልጅ ንብረት የመጠበቅ ግዴታም የለባትም።እውነታው ይሄው ነው።እየጨፈራችሁ!?

 ================
 ማስታወቂያ / Advertisment
====================
የጓደኞችዎን ወይም የቤተሰብዎን የሞባይል አየር ጊዜ ለማሳደግ ከዚህ በታች ያለውን አገናኝ ጠቅ ያድርጉ።
በአንድ ሁኔታ ውስጥ በሚመገብ ቤት የሚኖር የቤተሰብ እውነተኛ የወዳጅነት ስልክዎ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን የሚመለከት ከስር ሊ መረጃን ይጫኑ - 
Open the link to mobile top up at home


Monday, August 2, 2021

ከየትኛውም የዓለማችን ክፍል ሆነው የታላቁን ዓባይ ግድብ ሥራ ማጠናቀቂያ ገንዘብ በስልክዎ በቀጥታ ወደግድቡ የባንክ ሂሳብ ማስገባት የሚችል አዲስ ድረ ገጽ እና አፕ ተዘጋጅቶ ባሳለፍነው ሳምንት ተመረቀ። የኢትዮጵያ መብራት ኃይል የአፑ ባለቤት ሲሆን ንግድ ባንክ የገንዘብ ፍሰቱን ያከናውላል ።ይጠቀሙበት! ለሌላውም ያስተዋውቁ!


===================
የኢትዮጵያ ዓባይ ግድብ 80% መጠናቀቁ ይታወቃል።አሁን የቀረው ወሳኝ ሥራ በገንዘብ እጥረት እንዳይዘገይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል።
ይህንን ሥራ ለማቀላጠፍ ከቪዛ፣ማስተር ካርድ በመጠቀም በእጅ ስልክዎ በቀላሉ በአፕ ወይንም ገፁን በመክፈት መደገፍ የሚችሉበት የቴክኖሎጂ መንገድ ተዘጋጅቷል።አፑ የተዘጋጀው በከፍተኛ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች እና ባለድርሻ አካላት ሲሆን በእዚህ መሰረት በዝግጅቱ የተሳተፉት:- 
  • ከኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ድጋፍ ለዓባይ  (Ethiopia International Professional Support for Abay) 
  • ከኢትዮጵያ የሰላም እና እርቅ ኅብረት (United Ethiopia for Peace and Reconciliation) 
  • የኢትዮጵያ መብራት ኃይል፣
  • የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና 
  • ኤግሌ ቴክኖሎጂ ሲስተም (Eaglelion Technology System) የተሳተፉ ሲሆን በተጨማሪም 
  • የኢትዮጵያ ኢምባሲ በለንደን
  • የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ
  • የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስተር
  • በአሜርካ እና አውሮፓ የሚገኙ የሕግ ባለሞያዎች
  • የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበርያ  የተሳተፉበት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
አጠቃላይ ሥራውን ከጅምሩ አንስቶ ዶ/ር በላቸው ጨከነ፣ዶ/ር ዓለማየሁ ገብረየስ፣አቶ ሲራክ ሙሴ እና ዶ/ር ልዑልሰገድ አበበ ከእንግሊዝ ላለፉት አራት ወራት ያህል ከላይ የተዘረዘሩትን ባለድርሻ አካላት በማስተባበር መርተውታል።

ድረ ገጹን እና አፑን ለመክፈት እንዲሁም በቀጥታ በድረ ገፆቹ ለመጠቀም የሚከተሉትን ማስፈንጠርያ (ሊንኮች) መክፈት ይችላሉ።


በተያያዘ ዜና ከአንድ ሳምንት በፊት የኢትዮጵያ መብራት ኃይል የገንዘብ መለገሻ mygerd ድረ ገጽ 
www.mygerd.com  መልቀቁ ይታወቃል። 




=============================
ከእዚህ በታች ያለው ማስታወቂያ ከላይ ከተፃፈው ጽሁፍ ጋር አይገናኝም።የጉዳያችን ማስታወቂያ ነው።
==========================
ማስታወቂያ /Advertisement 
===============================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

የመስቀል ደመራ በዓል በንግስት ዕሌኒ ሀገር በግሪክ ቅዳሜ መስከረም 16፣2019 ዓም በከፍተኛ ድምቀት ተከብሮ ዋለ።በግሪክ የምትገንኘው የአቴንስ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን ምእመናን ለቅዱስ ሲኖዶስ አቤቱታቸውን ደግመው አቀረቡ።

======== ልዩ ሪፖርታዥ ======== በእዚህ ርዕስ ስር የሚከተሉትን ንዑስ ርዕሶች ያገኛሉ።እነርሱም ፡  የመስቀል ደመራ ለምን ይከበራል? ግማደ መስቀሉ  ወደ  ኢትዮጵያ እንዴት መጣ? የዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል...