ጉዳያችን - በጉዳያችን ሚድያ፣ኮምኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት የሚዘጋጅ ሲሆን ከ2003 ዓም ጀምሮ በድረ-ገፅ ላይ የነበረ በአሁኑ ጊዜ ከአንድ ሚልዮን በላይ ጎብኚዎች ያሉት ገፅ ነው። Gudayachn is prepared by Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant Organization. It has been online since 2011. Currently, Gudayachn is being visited by over One-million readers from all over the world.
Sunday, March 20, 2022
የትግራይ ተወላጅ የኢንጅነር እምብዛ ታደሰ አስከሬን ከተቀበረበት ቤተክርስቲያን አውጥቶ መልሶ ለጅብ የሰጠው ማን ነው?
Saturday, March 19, 2022
የአቡነ ማትያስ ንግግር ግልጽ የሆነ ፖለቲካዊ ተልዕኮ እንጂ ሃይማኖታዊ አይደለም። ''እውነት አርነት ያወጣችኋል'' የሚለው ቃል ተዘቅዝቆ ተጻፈ።ህወሃትም ለማለት ያልደፈረውን ማለታቸው ደግሞ አስተዛዛቢ ነው።
Wednesday, March 16, 2022
በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ባለፉት 9 ወራት ውስጥ ብቻ ወደ 1.2 ሚልዮን የኖርዌይ ክሮነር ወይንም ከ7 ሚልዮን ብር በላይ በማዋጣት ለዓባይ ግድብ ማሰርያ፣በጦርነት ለተጎዱ ወገኖች የሚሆን ለአማራ ክልል፣ለአፋር ክልል እና ለአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ልከዋል።ተቀባዮቹም የምስጋና እና ማረጋገጫ ልከዋል።(የምስጋና ደብዳቤዎቹን ይዘናል)
Monday, March 14, 2022
አስቸኳይ! የተፈናቃዮችን ችግር ለመፍታት እና በከተሞች የሰራተኛው ኑሮ ለማሻሻል መንግስት ቀላል የሆኑ 3 ቁልፍ ሥራዎችን በፍጥነት ይስራ!
- ተፈናቃዮች እየገጠማቸው ያለው ችግር የዕለት ተደራሽ እርዳታ ብቻ አይደለም።ጉዳያቸውን ከሌላ የመንግስት ሥራ በተለየ የሚመለከት ባለስልጣን እና ቢሮ የማጣት ግዙፍ ችግርም ጭምር ነው። ይህ ትልቅ ስብራት ነው።ጎዳና የወጣ ዜጋ ቢያንስ የሚያደምጠው ሰው ሊያጣ አይገባም።ለእዚህ በቅርቡ ከወለጋ የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን ከአዲስ አበባ እስከ አርሲ እና ደብረብርሃን የተንከረታተቱበት ሂደት በሃገር ውስጥ መገናኛ ሁሉ የተዘገበውን መመልከት ይቻላል። የሚያደምጣቸው የለም።ሃላፊነት የሚወስድ የለም።
- በመሆኑም ይህ ብሔራዊ ኮሚቴ የማስፈጸም አቅሙ በቶሎ በህግ ተሰጥቶት ሊንቀሳቀስ እና በሁሉም ክልሎች ከትግራይ የመጡትን ጨምሮ የአጭር ጊዜ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ወደ ሥራ መግባት አለበት።
- ኮሚቴው ከሙሰኝነት የጸዱ እና ብሄራዊ ሃብት በማዕከል የሚያሰባስቡ ታማኝ ሰዎች መያዝ አለበት።
- በስራው ላይ የመከላከያ አባላት መሳተፋቸው የሰው ኃይል እንቅስቃሴው ፈጣን ያደርገዋል።በህዝቡ እና በመከላከያ መሃል ያለውን ግንኙነትም ያጠነክራል።
Sunday, March 13, 2022
የብልፅግና ፓርቲ የሦስት ቀን ጉባዔውን ፈጽሟል።አርባ አምስት የስራ አስፈፃሚ አባላት መርጧል።የተመረጡ የሥራ አስፈፃሚ ዝርዝሩን ይዘናል።
- ብልፅግና ፓርቲ ከብሔር ተኮር የፖለቲካ ፓርቲነት ይልቅ ሕብረ ብሔራዊ ፌድራል የፖለቲካ ፓርቲ እንደሚሆን ገልጿል።
- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን በተመለከተ መንግስት በቤተክርስቲያን ጉዳይ እንደማይገባ በሕገ መንግስቱ የተደነገገ መሆኑን አንቀጽ ጠቅሰው የገለጡት የፓርቲው ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ነገር ግን መንግስት ሲወጣ ተቃዋሚዎች ይግቡ ማለት አይደለም ብለዋል።
- የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ሰኞ መጋቢት 5፣2014 ዓም የመጀመርያ ስብሰባውን ያደርጋል።
በዚሁ መሰረት የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት የሚከተሉት ናቸው፦
1. ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ
2. አቶ አደም ፋራህ
3. አቶ ደመቀ መኮንን
4. አቶ ደስታ ሌዳሞ
5. ዶ/ር ፍጹም አሰፋ
6. አቶ አብርሃም ማርሻሎ
7. አቶ አሻድሊ ሀሰን
8. አቶ ጌታሁን አብዲሳ
9. አቶ ኡሙድ ኡጁሉ
10. አቶ ተንኳይ ጆክ
11. አቶ ኦርዲን በድሪ
12. አቶ አሪፍ መሃመድ
13. ዶ/ር አብርሃም በላይ
14. ዶ/ር ሊያ ታደሰ
15. ሀጂ አወል አርባ
16. ሀጅሊሴ አደም
17. አቶ ኤሌማ አቡበከር
18. ወ/ሮ ሀሊማ ሀሰን
19. አቶ ሙስጠፌ መሀመድ
20. አቶ አህመድ ሽዴ
21. ዶ/ር ነጋሽ ዋጌሾ
22. አቶ ፀጋዬ ማሞ
23. ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል
24. አቶ ተስፋዬ በልጅጌ
25. አቶ ርስቱ ይርዳው
26. አቶ ተስፋዬ ይገዙ
27. አቶ ሞገስ ባልቻ
28. አቶ ጥላሁን ከበደ
29. አቶ መለሰ ዓለሙ
30. አቶ ሽመልስ አብዲሳ
31. አቶ ፍቃዱ ተሰማ
32. ዶ/ር አለሙ ስሜ
33. ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ
34. አቶ አወሉ አብዲ
35. አቶ ሳዳት ነሻ
36. ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
37. ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ
38. ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ
39. ዶ/ር ይልቃል ከፍያለ
40. ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ
41. አቶ ተመስገን ጥሩነህ
42. አቶ መላኩ አለበል
43. ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ
44. ዶ/ር ሰማ ጥሩነህ
45. አቶ ግርማ የሺጥላ ናቸው።
Tuesday, March 8, 2022
የሴቶች ቀን ማርች 8 በሚከበርበት በዛሬዋ ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ ዩንቨርስቲዎች የሚማሩ ሴት ተማሪዎች ዩንቨርስቲዎቻቸው እጅግ አስፈሪ እንደሆኑባቸው ስንቶቻችን እናውቃለን?
- ለክብርት ፕሪዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ፣
- የትምሕርት ሚንስትር ፕሮፌሰር ብርሓኑ ነጋ፣
- የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣
- ክብርት የፌድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት መዓዛ አሸናፊ እና ሌሎች
ዛሬ ማርች 8 የሴቶች ቀን ነው።ቀኑ በኢትዮጵያ እየተከበረ ነው።የአከባበሩ ታሪክ የሚነሳው ወደኋላ 100 ዓመታት ይጓዛል።እንደ አውሮፓውያኑ 1908ዓም በኒውዮርክ ከተማ ነዋሪ የሆኑ 15,000 ሴቶች የተሻሻለ የሥራ ሰዓትና የደመወዝ ክፍያን እንዲሁም የመምረጥ መብታቸው እንዲከበር ጠይቀው አደባባይ ወጡ። ከአንድ ዓመት በኋላ በአሜሪካ በብሔራዊ ቀንነት አወጀ።በዓሉ ዓለምአቀፋዊ ሆኖ እንዲከበር ክላራ ዚክተን የተባለች ሴት በ1910 ዓም እአአ በዴንማርክ ዋና ከተማ ኮፐንሃገን በተደረገ ዓለምአቀፍ ስብሰባ ላይ ሃሳቡ ቀረበ። በእዚህም ከ17 ሃገራት የተውጣጡ 100 ተሳታፊ ሴቶች በሃሳቡ ተስማሙ። በመቀጠል በ1911 ዓም እአቆጣጠር በዓሉ በኦስትርያ፣ዴንማርክ፣ጀርመንና ስዊዘርላንድ በዓሉ መከበር ጀመረ።በዓሉ በተሟላ ደረጀ ዓለምአቀፋዊ መልኩን የያዘው እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ1975 ዓም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሴቶች ቀንን ሲያከብር ነበር።
በኢትዮጵያ በወታደራዊ መንግስት ጊዜ ከሶሻሊዝም ርዕዮት ጋር እየትጠቀሰ መከበር ጀመረ።በወቅቱ የአብዮታዊት ኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበር (አኢሴማ) በሚል በብሔራዊ ደረጃ ኢስከ ቀበሌ ድረስ መዋቅር ያለው ነበር።ይህ አደረጃጀት ግን ነጻ አደረጃጀት ባለመሆኑ እና የመንግስት ውሳኔ አስፈጻሚ ብቻ ሳይሆን የካድሬነት ተግባሩ ማመዘኑ እንደማኅበር ጸንቶ መቀጠል አልቻለም።
- በአንድ የታወቀ ዩንቨርስቲ ውስጥ ሴቶች መጻሕፍት ቤት አምሽተው ፈጽሞ ወደ ዶርማቸው መምጣት አይችሉም።ዩንቨርስቲው ግቢ እና ጥበቃ ባለው በእዚህ ዩንቨርስቲ ውስጥ ሴት ተማሪዎቹ የሚፈሩት ከተማሪዎች በላይ የዩንቨርስቲው ጥበቃዎችን እና የምግብ ቤት ሰራተኞችን ነው።በአንድ ዩንቨርስቲ ውስጥ የዩንቨርስቲው ጥበቃዎች ተማሪዎችን መድፈራቸው በተማሪውም በዩንቨርስቲው ሰራተኞችም ዘንድ የታወቀ ነው።
- በአንድ ዩንቨርስቲ ውስጥ የተማሪዎች የምግብ ቤት ኃላፊ የሴት ተማሪዎችን የመመገብያ ካርድ ቀምቶ በግል ስልካቸው ላይ እየደወለ ከስነምግባር የወጣ ጥያቄ አቅርቧል። በእዚህ ተግባር የተጨነቁ ተማሪዎች የሆነውን በዶርማቸው ላሉ ተማሪዎች ሳይናገሩ እንደሚደብቁ ታውቋል።
- በብዙ ዩንቨርስቲዎች ውስጥ ሴት ተማሪዎች ኮምፕዩተር ይዘው ግቢው ውስጥ መታየት ይፈራሉ።በግቢ ውስጥ ብቻ ሳይሆን ዶርማቸው ውስጥ ኮምፕዩተራቸውን ይዘው ቢገቡ ጥበቃ የሚያደርግላቸው የለም።የሴቶች ዶርሞች ምሽት ላይ ተሰብረው ኮምፕዩተር እና ሞባይሎች ይወሰዳል። አንዳንዶቹ ጋር ፊታቸውን ሸፍነው በሚመጡ ሌቦች ነው የሚዘረፉት።
- በብዙ ዩንቨርስቲዎች ውስጥ መምሕራን ተማሪዎችን በጾታቸው ብቻ በውጤቶቻቸው እና የመመረቅያ ጽሁፎቻቸው ላይ ተጽዕኖ ያደርሱባቸዋል።
- ተማሪዎቹ ወደ ዩንቨርስቲ ቢሮዎች የሚፈልጉትን አገልግሎት ለማግኘት ሲሄዱ በብዙ ቦታዎች ሴቶች ተማሪዎችን በንቀት እና ሥርዓት አልባ በሆነ መንገድ የሚያስተናግዱ በርካታ ሰራተኞች አሉ።
- ለሃይማኖታዊ ስርዓት አካባቢያቸው ወደሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ወይንም መስጊድ ለመሄድ በአለባበሳቸው ምክንያት አንዳንድ ዩንቨርስቲዎች ያሉ የጥበቃ ሰራተኞች የወጣውንም ያልወጣውንም ሕግ እንደፈለጉ እየተረጎሙ ሴቶች ተማሪዎችን ያጉላላሉ።
- ሴቶች ተማሪዎች ዩንቨርስቲ አካባቢ ወደየሚገኙ ሱቆች ወጥተው ዕቃ ለመግዛት በጣም ይሳቀቃሉ።ምክንያቱም በሱቆቹ አካባቢ ያሉ ለደህንነታቸው ስጋት የሆኑ ወጣቶች አሉ።
- አንዳንድ ዩንቨርስቲ የሚገኙባቸው ክልሎች የጸጥታ ኃይሎች ዋና የጥቃት ኢላማዎቻቸው ወደ ከተማው የሚመጡ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ሲሆኑ ይህ ሁኔታ ደግሞ በከተማዎቹ አስተዳደሮች እና የዩንቨርስቲ አመራሮች ጭምር የሚታወቅ ግን ምንም እርምጃ ያልተወሰደባቸው ናቸው።
- የዩንቨርስቲ ከባቢያዊ የትምህርት ሁኔታ አስጨናቂ ሆኖባቸዋል።በእዚህ ሳብያ የትምህርት ውጤታቸው የሚቀንስ ብቻ ሳይሆን የሚያቋርጡ እንደሚኖሩ መገመት ቀላል ነው። ለመኖሩ መገመት ቀላል ነው።
- አንገታቸውን ደፍተው በዩንቨርስቲው ውስጥ መቆየት እንደ ብልሃት እየተወሰደ ነው።
- አዳዲስ ሃሳቦችን የማፍለቅ እና ለመብት የመቆም ቆራጥ ስሜት እንዳይኖራቸው አድርጓቸዋል።
- ችግሩ በዩንቨርስቲዎቹ ውስጥ በሲስተም የተሳሰረ ስለሆነ ብሶታቸውን የሚያሰሙበት እና የሚከሱበት አካል ዩንቨርስቲው ውስጥ የለም።
- ከእዚህ በፊት በደረሰባቸው በደል ለመክሰስ የሞከሩ በእዚሁ የተሳሰረ ሲስተም ሳብያ የበለጠ መሸማቀቅ ስለደረሰባቸው ሌሎች መብታቸውን እንዳይጠይቁ አድርጓል።
Thursday, March 3, 2022
ዩክሬን፣ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ እና ወቅቱ የሚጠይቀው ኢትዮጵያን እና መንግስትን የማገዝ ሃገራዊ ፋይዳው
-
በቀሲስ መንግሥቱ ጐበዜ ሉንድ ዩንቨርሲቲ ፣ ስዊድን (ቀሲስ መንግስቱ ጎበዜ በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አርኪኦሎጂ እና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህር እና በሉንድ ዩንቨርስቲ የዶክትሬት...
-
አድሚራል ጄምስ ስታርቪድስን =============== ጉዳያችን /Gudayachn =============== ብሉምበርግ የተሰኘው የአሜሪካ ድረገፅ በፖለቲካ እና ፖሊሲ አምድ ስር የአድሚራል ጄምስ ስታርቪድስን አሜሪካ ኢትዮጵ...
-
The Ethiopian herald News Paper August 20 , 2020 BY STAFF REPORTER Addis Ababa ************************** (EPA) ADDIS ABABA - Over sixty-mil...