ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, September 21, 2016

ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ በኢትዮጵያ ታሪክ የት-መጣነት(origin) ጉዳይ ባደረጉት ጥናት ላይ የተደረገ ቃለ መጠይቅ (ኦድዮ)

ከእዚህ በታች ያለው ጽሁፍ እና የዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ (ኦድዮ) በጉዳያችን ገፅ ላይ ከሶስት አመታት በፊት ማለትም በ2005 ዓም  ተለጥፎ ነበር። ዛሬ እንደገና ቃለ መጠይቁን ማውጣቱ አስፈላጊ ሆኗል።በአሁኑ ወቅት የዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ በእዚህ ቃለ መጠይቅ ላይ ያነሳቸውን ነጥቦች በመጽሐፍ አትሟቸዋል።
=======================================
  
''እኛ ኢትዮጵያውያን ታላቅ ሕዝብ ነን።እራሳችንን ዝቅ ማድረግ አይገባንም።ለምን ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር አለች አሁን? ይህ ማለት ኢትዮጵያን ያስጠሩ ሰዎች ቀድመው ነበሩ ማለት ነው።......ቀድሞ 'ኢትዮጵ' የሚባል ሰው ስለነበረ ነው።ለሀገር ሲሆን 'ኢትዮጵያ' አሰኛት እናም ከእርሱ ዘር የተወለድነው ሁሉ ኢትዮጵያውያን እንባላለን።እኔ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም ጃማይካ ነኝ ወዘተ ብልም ሃቁ እንዳፈጠጠ አለ።ይህ ሰው የኢትዮጵ ልጅ ስለሆንኩ እኔ ሁላችንም ብታምኑም ባታምኑም፣ብትክዱትም ባትክዱትም  ሁላችንም የእርሱ ልጅ ነን።እርሱ ከየት መጣ ለሚለው በሚወጣው መፅሐፌ ላይ ተዘርዝሯል። እኛ ኢትዮጵያውያን ከየት እንደመጣን ከስር መሠረታችን የሚታወቅ እንጂ ሜዳ ላይ የተልን አይደለንም።ማንነታችን በትክክል የተመዘገበ እና የታወቀ ከማንም በላይ በእዚህ ምድር ላይ ከአይሁዳውያንም ቀዳሚ ነን።''

በመቀጠል ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ስለ ኩሽ፣ሴም፣ሰለሞናውያን ስርወ-መንግስት፣ስለ የኦሮሞ ሕዝብ ከጥንት ጀምሮ በኢትዮጵያ ንግስና ታሪክም ሆነ የፖለቲካ ሕይወት ውስጥ የነበረውን ታሪክ ሁሉ በሰፊው ተንትነዋል።''ለእዚህ ሁሉ ታሪክ ማስረጃ ምንድነው?'' ተብለው ሲጠየቁ እንዲህ መልሰዋል- 

''ታሪኩ እስከ ዛሬ አንድ ሺህ አመት ድረስ  በደንብ ይታወቅ ነበር።ዮዲት ጉዲት ስትነሳ መፃህፍትን ሁሉ ስታጠፋ እና  የአክሱም መንግስት ሲፈርስ 'አክሱማይ ሲራክ'  የተባለ ሰው  ፅሁፉን ይዞ ወደ ኑብያ(የአሁኗ ሱዳን) ተሰዶ እዝያው ሞተ።በኃላ ንጉስ ላሊበላ ከኢየሩሳሌም ስደት ሲመለስ መፅሐፉን ከኑብያ ወስዶ አፃፈው።በኃላ ግን የግብፅ ጳጳሳት ታሪኩን ለማስጠፋት ብዙ ሰሩ።አንዱ ምክንያታቸው መፅሐፉ ከጥንት የኢትዮጵያ ታሪክ ጀምሮ እስከ ዮዲት መነሳት ጊዜ ብቻ የሚናገር ሳይሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአይሁድ ማስተማር ሳይጀምር ለኢትዮጵያውያን ለሶስት አመት ያክል ቀ 22 ዓመቱ እስከ 25 አመቱ ድረስ ማስተማሩን በትክክል ይናገር ነበርና ነው።በእዚሁ መሳደድ ዳግም መፅሐፉን ይዘው አባቶች ወደ ኑብያ ተሰደዱ። ......መፅሐፉ የዛሬ 50 አመት ገደማ አንድ መነኩሴ ኑብያ ከፈራረሱ ህንፃዎች መካከል ሱዳናውያን የጥንት መፃህፍት መኖራቸውን ነገረዋቸው አግኝተው ወደ ኢትዮጵያ አመጡት።ከእዛ ወዲህ በተቆራረጠ መልክ መፅሐፉ ታትሟል።'' ብለዋል።
የታሪክ ምርምር ቀጣይ ነው። ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ በማስረጃ የተደገፈ የምርምር ውጤታቸውን አቅርበዋል።በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ እራሱን የቻለ መረር ያለ ምርምር ማስፈለጉን የሚያመላክት ነው።ቃለ ምልልሱ ሙሉውን በአንክሮ ሊሰሙት የሚገባ ነው።ያዳምጡት።
 የቀድሞው የኢቲቪ ዝነኛ ጋዜጠኛ ብዙ ወንድማገኘሁ  በፓልቶክ ስሟ (ሙያዬ) አወያይነት ይህ ዶ/ር ፍቅሬ ያደረጉት ቃለ መጠይቅ የተካሂደው  ኢትዮጵያ የመወያያ መድረክ ፓልቶክ (ECADF)  ነው። 
በቃለ መጠይቁ መጀመርያ ላይ የሚሰማው ፉከራ እና የእንግሊዝኛ ንግግር  የዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ነው የቃለ መጠይቁ አካል ስለሆነ በትዕግስት ማዳመጡን ይቀጥሉ።

ጉዳያችን GUDAYACHNgetachewb221@gmail.com

No comments:

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...