ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, September 15, 2016

በተራራማ መሬት ላይ የእርከን ሥራ ለትግራይ ያስተማረ ኮንሶ እየተገደለ፣እየተሰደደ ነው እንድረስለት!


የኮንሶ ሕዝብ በደቡብ ከሚገኙት በታሪክ፣በጠንካራ ሰራተኝነት እና ከሁሉም ጋር ተግባብቶ በመኖር ከሚታወቁት ሕዝብ መካከል ኮንሶ አንዱ እና ዋናው ነው። ኮንሶ ከኢትዮጵያ ውጭ በዓለም አቀፍ ደረጃም ኢትዮጵያን ስመ ጥር ካደረጉ የአገራችን ክፍሎች አንዷ ነች።የጀርመን ድምፅ ራድዮ የአማርኛው አገልግሎት እኤአቆጣጠር ሰኔ 30፣2011 ዓም ኮንሶን አስመልክቶ ´የኮንሶ ባህላዊ ይዞታ በአለም የቅርሥ ማህደር´´በሚል ርዕስ ስር ባስተላለፈው ፕሮግራም ላይ ስለ ኮንሶ ቅርሶች በዓለም አቀፍ ደረጃ በዩኔስኮ መመዝገብ እንዲህ ብሎ ነበር። 

´´የተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት UNESCO ከትናንት በስትያ የኮንሶ ህዝብ ባህላዊ የመኖርያን አካባቢ በተባበሩት መንግስታት ስር እንደተመዘገበ ይፋ አድርጎአል። ድርጅቱ ከሰኔ አስራ ሁለት እስከ ሰኔ ሃያ ሁለት አመታዊዉን እና ሰላሳ አምስተኛዉን ጉባኤ በዋና ጽፈት ቤቱ ፓሪስ ላይ ያደረገ ሲሆን ከአለም አገራት የተሰባሰቡ የባህልና ቅርጽ ጥበቃ ባለሞያዎችም ተካፋይ ነበሩ። ድርጅቱ ከአፍሪቃ ዘንድሮ በአለም ቅርሥነት የመዘገባቸዉ ነገሮች በአምስት አገራት የሚገኙ ሲሆኑ፣ ከእነዚህ ውስጥ ከኢትዮጵያ፣ የ400 አመት እድሜ እንዳለዉ የተነገረለት የኮንሶ ማህበረሰብ ባህላዊ የመኖርያ ስፍራ አንዱ ነው´´ (http://www.dw.com/am/የኮንሶ-ባህላዊ-ይዞታ-በአለም-የቅርሥ-ማህደር/a-6560771) ይላል።

ኮንሶ በእርከን ሥራ በዓለም ላይ ቀደምት ተሞክሮ ካላቸው ቦታዎች ውስጥ ትጠቀሳለች።ብዙ የድህረ ምረቃ ጥናቶች በኮንሶ ዙርያ ተሰርተዋል።ዛሬ የቅርስ እና የታሪክ እንዲሁም የህዝብ በሰላም መኖር የሚያባንነው የህወሓት ስርዓት የደቡብ ህዝቦች አስተዳደርን በጀርባ እየገፋ የኮንሶን ሕዝብ እየገደለ ነው። ኢሳት በሰሞኑ ዘገባው በኮንሶ ከ9 መንደሮች በላይ ወድመዋል።ከ3ሺህ ሕዝብ በላይ ተሰዷል። በትናንትናው እለት ብቻ 26 ሰዎች አንዲት ነፍሰ ጡር ጨምሮ በጥይት ተገድለዋል። የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ አማርኛው አገልግሎት እኤአ መስከረም 14፣2016 ባስተላለፈው ዘገባ ላይ እንዲህ ይላል -

´´ከጳጉሜ 5, 2008 ዓ.ም. ምሽት ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ የመከላከያ ሰራዊት ኮንሶ በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች ነዋሪዎች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን በጥቃቱም ቁጥሩ ያልታወቀ ሰው ሕይወት መጥፋቱን፤ በዞኑ ፖሊስ ጣቢያም የዐስራ አራት ሰው አስክሬን እንደሚገኝ እንደተናገራቸው ገልጸው በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውን ፣ ወደ 1000 ሺህ የሚጠጉ አባወራዎች ቀያቸውን ጥለው መጥፋታቸውን በሕዝብ እንደተመረጡ ከሚነገረው የኮሚቴ አባላት አንዱ አቶ ገመቹ ገንሴ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል። እሳቸው በተጨማሪ ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው የደቡብ ክልል መንግሥት ነው ይላሉ።´´ (http://amharic.voanews.com/a/konso-resident-representative-claim-14-dead-where-regional-government-admit-for-6-dead/3509332.html?nocache=1)

ይህ ሁሉ መከራ ኮንሶ ላይ የወረደው ለምን በዞን ደረጃ እራሴን ላስተዳድር ብሎ በመጠየቁ ብቻ ነው።ይህንን ጥያቄሕጉ 15 ሺህ ሰው ብቻ እንዲጠይቅ ቢያዝም ኮሚቴው ግን ከ50 ሺህ ሕዝብ በላይ አስፈርሞ በወረዳው ምክር ቤት አፀድቆ እና ሕጋዊ መስመርን ተከትሎ ከክልሉ እስከ ፈድሬሽን ምክር ቤት ድረስ እንደጠየቀ  12 አባላት ያሉት  የኮሚቴው አባል አቶ ገመቹ ደንፌ ለአሜሪካ ድምፅ ራድዮ የካቲት 7፣2016 እኤአ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ላይ አብራርተዋል።የተሰጣቸው ምላሽ ግን ´´ይህ የሚሆነው በኢህአዴግ መቃብር ላይ ብቻ ነው´´ የሚል እንደነበር የኮሚቴው አባል ይገልፃሉ።
(http://av.voanews.com/clips/VAM/2016/02/06/9c0f1a2f-006e-4f3f-b61c-41eb67eab7fe.mp3)

በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ላይ ያለው ኮኮብ የብሔር ብሄረሰብ መብት ማሳያ ነው እያለ የምመፃደቀው ስርዓት ለእዚህ አይነቱን  ቀላል የህዝብ ጥያቄ ተደፈርኩ በሚል ጀብደኝነት እና ታሪካዊ ህዝብን በማጥፋት የኢትዮጵያን መልክ ማጥፋት እና የእራሱን አዲስ ታሪክ መፃፍ  የሚፈልገው ሕወሓት የኮንሶን ሕዝብ ከደቡብ ህዝቦች አስተዳደር ጀርባ ሆኖ እርስ በርስ እያጫረሰው ነው።ኮንሶ የኢትዮጵያ ክብር ነው። ኮንሶ የኢትዮጵያ አንዱ ፊት ነው።ይህ ሕዝብ የሕወሓት ህገ መንግስት አይጠብቀውም። እኛ ኢትዮጵያውያውያን ብቻ ነን  የምንደርስለት።የእርከን እርሻ ትግራይን ያስተማረ ኮንሶ ሕዝብ እየተገደለ ነው።እንድረስለት።
ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

No comments:

ወቅታዊ የዓለም ሁኔታ እንድንነታረክ ዕድል የሚሰጥ አይደለም።ብንነቃ መልካም ነው።

========== ጉዳያችን ወቅታዊ ========== የዓለም ታሪክ እንደሚያስተምረን ዓለም በወሳኝ የእጥፋት(turning point) ታሪኮች ውስጥ አልፋለች። እነኝህ የእጥፋት ጊዜዎች የዋዛና የፈዛዛ ጊዜ አይደሉም።መላው ዓለ...