አቡነ አብርሃም የምዕራብ ጎጃም ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
አቡነ አብርሃም የምዕራብ ጎጃም ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ዛሬ መስከረም 16፣2009 ዓም በባህርዳር በተከበረው የደመራ መስቀል በዓል ላይ ለተሰበሰበው ምዕመን ስለ እውነት በአደባባይ መስክረዋል። በአሜሪካ የዲሲ እና አካባቢው ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስም የነበሩት አቡነ አብርሃም በእዚሁ አገልግሎታቸው በምእመናን በተለይ በወጣቶች ዘንድ ከፍተኛ ፍቅርን አትርፈው እንደነበር ብዙዎች ይመሰክራሉ። በተለይ በምእመናን መካከል የሚነሱ ግጭቶችን በማስታረቅ እና መናገር እና መስማት የማይችሉ ወጣቶች መንፈሳዊ አገልግሎት በምልክት እንዲማሩ ያደረጉት ጥረት ተጠቃሽ ነው።ከአሜሪካ አገልግሎታቸው በመቀጠል የምስራቅ ሐረርጌ እና የጅጅጋ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው አገልግለዋል።በአሁኑ ወቅት የምዕራብ ጎጃም ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናችው።
አቡነ አብርሃም በዛሬው የባህር ዳር ደመራ ላይ ከመሰከሩት እውነት ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል።
´´
´´ችግሩ ያለው ከመሪዎች እንጅ ከተመሪ አይደለም ....መንግስትን ና የራሱን ሚድያ ገስጹ የህዝብ ጥያቄ መመለስ አለበት ....እኔ ከመፍራቴ አንጻር በዓሉ ባይከበር ደስተኛ ነበርሁ ነገር ግን አባቶቼን ሳይ በየሳምንቱ ቢከበርም አይቆጨኝም።ትናንት አስከሬን እያወጣ አልቅሱ ሲለን ነበር።.....የህዝቡ ጥያቄ መመለስ አለበት። .....ወታደር ከዚህ በኋላ የሰላምን ምላጭ እንጅ የመሳሪያን ምላጭ መሳብህን አቁም።....በየሀገሩ በስደት ያለው ወገናችን መመለስ አለብት ። ......እኛ አባቶች የምናገረውን በተገቢው መልኩ ለህዝብ የማታቀርቡ የመንግስት ሚድያ ካላስተካከላችሁ ከዚህ በኋላ አደባባዩ አትገቡም።እኛ የተናገርነውን ትቆራርጡ ታቀርቡ እና ምእመኑ ምን አባት አለን እንዲል ታደርጋላችሁ። ክርስቲያን እውነት ይናገራል።.......ለእዚች አገር መጠበቅ ቤተ ክርስቲያን አስተዋፅኦ ትልቅ ነው።ቤተ ክርስቲያን ስለ ወታደርም ትፀልያለች።ሕዝብ የሚጠብቁትን ጠብቅ እያለች የምትፀልይ ይህች ቤተ ክርስቲያን ነች።ስለዚህ ልትደመጥ ይገባታል።አንድ ሰው ባልሰራው ከታሰረ፣እግዚአብሔርስ እንዴት ዝም ይላል።ሁላችንም እንደወንድምነት እንተባበር። ስንት ወገናችን በበረሃ አለቀ።........ዛሬ ስጋት ነው።አሁን የመጣው ሕዝብ ለሃይማኖቴ ልምጣ ብሎ የመጣ እንጂ ማንም ይጠብቀናል ብሎ አይደለም የመጣው።......
........ያለ በደላቸው የታሰሩት ወንድሞቻችን መፈታት አለባቸው። .....ጠላትን እንዳላንበረከኩ አባቶቻችን ፤ዛሬ ለምን እርስ በእርስ ተከፋፈልን? የተሸከምነው መሳሪያ ከክርስቶስ መስቀል አይበልጥም። .....ወታደሮችና ድንበር ጠባቂዎች ስለ እናንተ ቤተክርስቲያን ስለምትጸልይ የሷ ልጆች ናችሁና ደም አታፍሱ። ´´ የሚሉ ይገኙበታል።
........ያለ በደላቸው የታሰሩት ወንድሞቻችን መፈታት አለባቸው። .....ጠላትን እንዳላንበረከኩ አባቶቻችን ፤ዛሬ ለምን እርስ በእርስ ተከፋፈልን? የተሸከምነው መሳሪያ ከክርስቶስ መስቀል አይበልጥም። .....ወታደሮችና ድንበር ጠባቂዎች ስለ እናንተ ቤተክርስቲያን ስለምትጸልይ የሷ ልጆች ናችሁና ደም አታፍሱ። ´´ የሚሉ ይገኙበታል።
አቡነ አብርሃም ይህንን ሲናገሩ ምእመናን በእልልታ እና በእንባ ስሜታቸውን ይገልፁ ነበር።ከዛሬው የባህርዳር ደመራ በኃላ አቡነ አብርሃም ሕዝብ ወደ ቤቱ ሳይገባ እኔ አልገባም በማለት ህዝቡ ከሄደ በኃላ በእግራቸው ወደ ቤታቸው በፖሊስ ታጅበው ሄደዋል።
በቅዱስ ሲኖዶስ አባል ደረጃ በመስቀል ደመራ ላይ አሁን በስልጣን ላይ የሚገኘው የሕወሓትን መንግስት በግልጽ ስገሰፅ የአቡነ አብርሃም የመጀመርያው ይሆናል። አቡነ አብርሃም እናከብርዎታለን።በእዚህ የመከራ ዘመን ለኢትዮጵያ እንደ አቡነ ጴጥሮስ በአደባባይ ስለ እውነት የመሰከሩ ምስክር ሆነዋልና።እርስዎ የተጋረደውን አዚም ገፈውታል።ፈለግዎን ተከትለው ሌሎች አባቶችን ድምፅ አሁንም በብዛት መስማት እንፈልጋለን። ድምፅ ብቻ አይደለም ምእመኑን በመከራው ሰዓት አብረው እየተንገላቱ የሚያፀኑ ካህናት መብዛት አለባቸው።
ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com
No comments:
Post a Comment