ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Thursday, November 30, 2017

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በሰላሳ ቀናት ውስጥ በሶስት የአውሮፓ ከተሞች ሶስት አብያተ ክርስቲያናት ገዛች፣ የኦስሎ ቤተክርስቲያን ህንፃ ኮሚቴ ትውልድ አኩሪ እንቅስቃሴ ማድረጉ አስመስግኖታል።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እና ምእመናን የተመለከተ የፔው ምርምር ማዕከል አዲስ ዓለም አቀፍ ጥናት ይፋ አደረገ (የጥናቱን ሙሉ ይዘት ይዘናል)



ኦስሎ፣ኖርዌይ ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አቡነ ሕርያቆስ ቀሲስ ካሳሁን እና ዲያቆናት እሁድ ህዳር 17/ 2010 ዓም  ቅዳሴ ሲያሳርጉ 

ጉዳያችን / Gudayachn

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በሰላሳ ቀናት ውስጥ  በሶስት የአውሮፓ ከተሞች ሶስት አብያተ ክርስቲያናትን ገዛች

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በሶስት የአውሮፓ ታላላቅ ከተሞች  ሶስት አብያተ ክርስቲያናትን ገዝታለች።እነርሱም በፍራንክፈርት ጀርመን የመድሃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን፣ኦስሎ ኖርዌይ ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለ ሃይማኖት እና ለንደን እንግሊዝ የደብረ ገነት ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ናቸው።አውሮፓ ውስጥ ሃይማኖተኛ ሳይሆን በእግዚአብሔር ማመን እና አምልኮት መፈፀም ብርቅ እየሆነ የመጣበት አህጉር ሆኗል።በመካከለኛው ዘመን በአውሮፓ ድንቅ ጥበብ የታዩባቸው በርካታ ህንፃ አብያተ ክርስቲያን ይገኛሉ። እነኝህ አብያተ ክርስቲያናት ግን በሰንበት ቀኖችም ሆነ በበአላት ቀናት በውስጣቸው አምልኮተ እግዚአብሔር የሚፈፅም ምእመናን አይገኙም።በእርግጥ ለአውሮፓውያን የልደት በዓል ዋዜማ አመታዊ ኮንሰርት የሚደረግባቸው አብያተ ክርስቲያናት በዋና ዋና ከተሞች ውስጥ አሉ። 

አሁን አውሮፓ ውስጥ እየሆነ ያለው ከእዚህ የከፋም ነው። አብያተ ክርስቲያናት ለምሽት ክበቦች የመሸጥ እና የመከራየት ዕጣ እየደረሰባቸው ነው።ይህ እየሆነ ባለበት ሰዓት ነው እንግዲህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በሚልዮን የሚቆጠር ዶላር እያወጣች እየገዛች ያለው።ግዥዎቹ የተፈፀሙት በአውሮፓ የሚኖሩ ምእመናን በሚያዋጡት እና ከባንክ በሚገኝ የእረጅም ጊዜ ክፍያ ብድር ነው።
አዲስ የተገዛው  የለንደን እንግሊዝ የደብረ ገነት ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን 
አዲስ የተገዛው የኦስሎ ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን 
ጀርመን ፍራንክፈር የመድሃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ግዢ ሲፈፀም የደብሩ አስተዳዳሪ መላከ መዊ ልሳነ ወርቅ ሲፈርሙ 

የኦስሎ ቤተክርስቲያን ህንፃ ኮሚቴ ትውልድ አኩሪ እንቅስቃሴ ማድረጉ አስመስግኖታል
ኦስሎ ቅዱስ ገብርኤል አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የህንፃ ጨረታ ሂደት እና ለግዥ የሚሆን የገንዘብ ማሰባሰብ (አብዛኛውን ገንዘብ) ስራውን በአንድ ወር ውስጥ ማሰባሰብ መቻሉ እና ምእመናንን በሚገባ ማንቀሳቀሱ ከፍተኛ አድናቆትን አስገኝቶለታል።የህንፃ ኮሚቴ በቅርብ አመታት ውስጥ በአዲስ መልክ ከተመሰረተ በኃላ መሬት ገዝቶ ቤተ ክርስቲያን የመገንባት፣ አብያተ ክርስቲያናትን መግዛት ወይንም የባህል ማዕከል ገዝቶ ወደ ቤተ ክርስቲያን መቀየር የሚሉ አማራጮችን ይዞ ወደ ሥራ ገብቷል።

ይህ በወጣቶች የተገነባው የህንፃ ኮሚቴ በተለይ ባሳለፍነው ወር ውስጥ የህንፃ ጨረታ ግዢ ሂደት ላይ ኮሚቴው በበቂ መልኩ ያደረገው የአሰራር ብቃት፣ከምእመናን ጋር የነበረው የግንኙነት መስመር እና ሁሉንም ምእመን የማስተባበር ሥራ መሰራቱ ከእግዚአብሔር ፍቃድ ጋር ተጨምሮ ለፍሬ ሊበቃ ችሏል።የህንፃ ኮሚቴው አባላት እንቅልፍ አጥተው ያደሩባቸው ሌሊቶች፣ ከስራ ለበርካታ ቀኖች የቀሩባቸው ጊዜዎች እና በታማኝነት የምመናንን አስተዋፅኦ ጠብቀው ለቤተ ክርስቲያን ጨረታ መልካም ውጤት ቤተ ክርስቲያንን አድርሰዋታል።ከእነኝህ ውስጥ ሁለቱን ክስተቶች ብቻ መጥቀሱ የነበረውን ውጣ ውረድ ሊያሳይ ይችላል።

የእሁዱ ለቅሶ 

የኦስሎ ቅዱስ ገብርኤል አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ህንፃ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ተክሉ ጨረታው በተሰማበት የመጀመርያ እሁድ ከቅዳሴ በኃላ ስለ ጨረታው ምንነት፣ ቤተ ክርስቲያን ያላት ገንዘብ መጠን እና ከባንክ ሊገኝ የሚችለው ገንዘብ እና  ኮሚቴው ሊሰራ ያሰባቸውን ስራዎች አብራሩ።ይህች እሁድ ምእመናን በቤተ ክርስቲያን በስሜት ያለቀሱበት፣ ሁሉም በአንድነት በተሰበረ ልብ ሆነው ምን እናድርግ እያሉ የተመካከሩበት ሰንበት ነበር። በእዚህ ሁሉ መሃል የህንፃ ኮሚቴ አባል ወ/ሮ ሶስና ሳግ በቀላቀለው እና ከውስጧ ፍልቅል ብሎ በወጣ የለቅሶ ድምፅ  እያሰማች ቆመች እና መናገር ጀመረች: -
" እኔ በጣም ይቅርታ አድርጉልኝ ይህንን ነገር ሳልናገረው ማለፍ አልችልም። ትናንት ምሽት ላይ ከአረብ ሀገር ቤተ ክርስቲያን ጨረታ ላይ መሆናችንን የሰማች እህት እያለቀሰች ያወራችኝን ልንገራችሁ።ልጅቷ ከአሳዳርዎቿ ተደብቃ መንገድ ላይ ወጥታ እንደምትደውል ስትነግረኝ እያለቀሰች ያለችኝ 200 ዶላር አለች ከሰራሁት እሷኑ እልካለሁ አለችኝ''  ብላ ወ/ሮ ሶስና ስትናገር ምእመናን ስሜት ይብሱን ተነካ።ለጥቂት ሰኮንዶች ፀጥታ ሰፈነ።በአረብ ሀገር በጉልበት ሥራ የምትሰራ እህት አውሮፓ ላለ ቤተ ክርስቲያን ልቧ ተነክቶ እንቅልፍ አጥታ አምሽታ ምሽት ላይ መንገድ ዳር ወጥታ ስልክ ደውላ ከሰራቻት የወር ክፍያ ላይ 200 ዶላር ለመክፈል ያውም ከእንባ ጋር ለሕንፃ ኮሚቴ አባል ደውላ ጠይቃለች።ጉዳዩ እራስን ለመመልከት እና እኔ ምን አደረኩ? የሚያስብል ልዩ ድባብ የፈጠረ ሰንበት ነበር።

ወ/ሮ ሶስና  ሃብተ ማርያም የቤተ ክርስቲያን ህንፃ ኮሚቴ  ገቢ አሰባሳቢ ክፍል ኃላፊ ባለፈው ዓመት ኮሚቴው ባዘጋጀው ዝግጅት ላይ  ስታስተባብር  
(ቀኑ ቅዳሴ ያለበት  ቀን ሳይሆን ድራማ እና ልዩ ልዩ የገቢ ማስገኛ ዝግጅቶች የቀረቡበት ከኖርዌይ የፍቅር እስከ መቃብር መፅሐፍ ወደ ኖርዌይ የመለሰው ደራሲ እና ልዩ  ልዩ እንግዶች የተገኙበት የምእመናን የጋራ መገናኛ ቀን ነበር። ከጀርባ  ያሉት ያን ጊዜ መላክ ብስራት አባ ሀብተየሱስ  አሁን አቡነ ሕርያቆስ ለልጆች መማርያ የሰንበት ትምህርት ቤቱ ያዘጋጀውን መፅሐፍ ሲያስተዋውቁ ነው)

 ለሁለተኛ ጊዜ የተራዘመው እና የመጨረሻው ጨረታ ሊጀመር 24 ሰዓታት ሲቀሩት  

የቤተ ክርስቲያኑ የጨረታ ጊዜ ሁለት ጊዜ ተራዝሟል።ለእዚህም ምክንያቱ አዳዲስ አመልካቾች በመምጣታቸው ነበር።የኦስሎ ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለ ሃይማኖት ጨረታ ልዩ የሚያደርገው አንዱ ምክንያት በኖርዌይ ውስጥ ቤተ ክርስቲያን ለጨረታ ብቻ ሳይሆን ለሽያጭ ማቅረብ ከቆመ አመታት ሆኖታል ሆኖም ግን የእግዚአብሔር ፍቃድ ሆኖ ይህ የተገኘው ቤተ ክርስቲያን ቀደም ብሎ በግለሰብ ተይዞ በመኖሩ ለሽያጭ ሊቀርብ ችሏል።ይህ ምናልባት ከብዙ አመታት በኃላ የሚያጋጥም ዕድል ነው።

በጨረታው ላይ ከአምስት በላይ ድርጅቶች ከመሳተፋቸው በላይ ለሁለት ቀናት ያህል የቆየ እልህ አስጨራሽ ነበር።ከጨረታው ከመጀመሩ 24 ሰዓታት በፊት በሕንፃ ኮሚቴው ውስጥ በወሳኝ አገልግሎት ላይ ከሚገኙት ውስጥ የኮሚቴው ሰብሳቢ ዶ/ር ተክሉ በድቁና ከሚያገልግሉት አንዱ ልጁ እንዳመመው ይሰማል።ይህ ሲሆን ሁለት ቀናት በጨረታ በጋራ ከሚከታተልበት ከአቡነ ሕርያቆስ ቤት ነበር።ሆኖም ግን ልጁን ሄዶ ለማየት አልቻለም።ልጁ ሆስፒታል ደርሶ ሲመለስ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ እዚህ እየጠበቀው ነበር እና አሁንም ሄዶ ማየት አልቻለም።

ዶ/ር ተክሉ አባተ የኦስሎ ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ህንፃ ኮሚቴ ሰብሳቢ

በሌላ በኩል የኮምቴው የሂሳብ ሹም ዶ/ር ዳዊት ሻወል ጨረታው ሊጀመር ሀያ አራት ሰዓታት ሲቀሩት ለስራ ከኖርዌይ ውጭ ወደ እንግሊዝ እንዲሄድ መስርያቤቱ ያዘዋል።ሁኔታው በወቅቱ ሁሉም የኮሚቴ አባላት የመገኘታቸው አስፈላጊነት አንፃር እራሱን የቻለ ድባብ ይዞ መጥቶ ነበር።


ዶ/ር ዳዊት ሻወል የህንፃ ኮሚቴ ሂሳብ ሹም 

በሌላ በኩል ከህንፃ ኮሚቴው ጭንቀት እና ውጥረት በተጨማሪ በኖርዌይ እና በመላው ዓለም የሚኖሩ ዜናውን የሰሙ ኢትዮጵያውያን ውጤቱን በጭንቀት ይከታተሉ ነበር።በመቶዎች የሚቆጠሩ ምእመናን በቫይበር ግሩፕ የተሰባሰቡበት የምእመናን ስብስብ እራሱ የቻለ የጨረታው ገፅታ ነበር።ለሁለት ሳምንታት ከጨረታው በፊት በነበሩ እያንዳንዱ ምሽቶች የሚገናኘው ይህ የምእመናን ግሩፕ በጎፈንድ የተከፈተው ሂሳብ ከመቶ ሺህ የኖርዌይ ገንዘብ በላይ እንዲሰበሰብ አግዟል።

ባጠቃላይ የኦስሎ ቅዱስ ገብርኤል ወአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ህንፃ ኮሚቴ አባላት ከሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ እና ከቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ እና የአቡነ ኤልያስ ረዳት አቡነ ሕርያቆስ ጋር በተቀናጀ መልኩ የሰሩት ሥራ ምእመናንን በጣም ያስደሰተ ታሪካዊ ሥራ ነው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እና ምእመናን የተመለከተ የፔው ምርምር ማዕከል አዲስ ዓለም አቀፍ ጥናት ይፋ አደረገ

ፔው የምርምር ማዕከል በዓለም ላይ ባሉ የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት አዲስ ጥናት አውጥቷል።በጥናቱ በዓለም ላይ ከሩስያ ቀጥሎ ከፍተኛ የኦርቶዶክስ አማኞች ያሉባት ሀገር ኢትዮጵያ መሆኗን እና በሰንበት እለት ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ ኢትዮጵያ ከፍተኛውን ቁጥር እንደያዘች ይገልጣል። የጥናቱ ውጤት ከእዚህ በታች ይመልከቱ።

Ethiopia is an outlier in the Orthodox Christian world









An Orthodox priest at Nakuto Lab Rock Church, outside Lalibela, Ethiopia. About three-quarters of Orthodox Ethiopians say they attend church every week. (Eric Lafforgue/Art in All of Us/Corbis via Getty Images)
An Orthodox priest at Nakuto Lab Rock Church, outside Lalibela, Ethiopia. About three-quarters of Orthodox Ethiopians say they attend church every week. (Eric Lafforgue/Art in All of Us/Corbis via Getty Images)

Ethiopia has the largest Orthodox Christian population outside Europe, and, by many measures, Orthodox Ethiopians have much higher levels of religious commitment than do Orthodox Christians in the faith’s heartland of Central and Eastern Europe.

The country in the Horn of Africa has 36 million Orthodox Christians, the world’s second-largest Orthodox population after Russia.

Nearly all Orthodox Ethiopians (98%) say religion is very important to them, compared with a median of 34% of Orthodox saying this across 13 countries surveyed in Central and Eastern Europe. About three-quarters of Orthodox Ethiopians say they attend church every week (78%), compared with a median of 10% in Central and Eastern Europe and just 6% in Russia.
Orthodox Ethiopians are more likely than Orthodox Christians in Central and Eastern Europe to wear religious symbols (93% vs. median of 64%), to say they believe in God with absolute certainty (89% vs. 56%), to fast during holy times such as Lent (87% vs. 27%), and to tithe (57% vs. 14%). Indeed, these gaps between Orthodox Christians in Ethiopia and Europe mirror broader differences in religious commitment between people living in sub-Saharan Africa, where religious observance is relatively high among all major religious groups, and those in more secular societies in Central and Eastern Europe.
Orthodox Ethiopians also tend to be more conservative on social issues than are other Orthodox Christians surveyed; they express higher levels of moral opposition to homosexuality, prostitution, abortion, divorce and drinking alcohol. For instance, Orthodox Ethiopians are much more likely to say that having an abortion is morally wrong than are Orthodox Christians in Central and Eastern Europe (83% vs. median of 46%).

Orthodox Christians do not make up a majority of Ethiopia’s overall population: 43% of Ethiopians are Orthodox, while approximately 19% are Protestant and 35% are Muslim. Still, in 2010, the 36 million Orthodox Christians in Ethiopia made up about 14% of the world’s total Orthodox population (compared with a 76% share in Central and Eastern Europe), up from about 3 million in 1910, when Orthodox Ethiopians made up 3% of the Orthodox total. This increase is owed mainly to natural growth in Ethiopia’s population, which rose from 9 million to 83 million between 1910 and 2010.
Ethiopian Orthodoxy is part of the Oriental branch of Orthodoxy, which accounts for approximately 20% of the global Orthodox population and is not in communion with Eastern Orthodoxy, the larger branch, largely due to theological and doctrinal differences.
Note: Read more about the history of Ethiopia’s Orthodox Christians.
Source: - Pewresearch 

ጉዳያችን GUDAYACHN 

 www.gudayachn.com

No comments: