ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, November 22, 2017

ማኅበረ ቅዱሳን በውጭ ለሚኖሩ ሕፃናት እና ታዳጊዎች ማስተማርያ እና መማርያ ሥርዓተ ትምህርት አዘጋጅቶ አስመረቀ።



  • የሥርዓተ ትምህርት ዝግጅቱ ከሁለት ዓመት በላይ ወስዷል፣
  • ዝግጅቱ ከመጀመሩ አስቀድሞ ከሶስት መቶ በላይ የሚሆኑ በእንግሊዝ የሚኖሩ ምእመና  ተሳትፈውበታል፣
  • ከሰላሳ ያላነሱ የቤተ ክርስቲያን ወጣት ምሁራን ተሳትፈውበታል፣
  • ጥናቱ የአብያተ ክርስቲያናት ተሞክሮ፣የልጆች የቋንቋ ክህሎት እና የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ደረጃ፣ እንደዚሁም ወላጆች የተሳተፉበት በችግሮች እና የመፍትሔ አቅጠጫዎች ዙሪያ ያተኮረ የመነሻ ጥናት ተደርጎበታል።
በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አንዱ እና ፈታኙ ጉዳይ ልጆቻቸውን በሚፈልጉት ሃይማኖት እና ኢትዮጵያዊ ባህል አሳድጎ ለቁምነገር ማብቃት ነው።ይህንን ችግር ለመፍታት የሚያጋጥመው ችግር ደግሞ በባለሙያ የተዘጋጁ ልጆችን የማስተማርያ በቂ ስርዓተ ትምህርት አለመኖር ተጠቃሽ ነው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምርያ ስር የሚገኘው ማኅበረ ቅዱሳን የአውሮፓ ማዕከል ስር የሚገኘው የተተኪ ትውልድ ሥልጠና ክፍል ይህንን ችግር ለመፍታት ጥረት ሲያደርግ ነበር።

በእዚህም መሰረት ማኅበሩ ላለፉት ሁለት ዓመታት በላይ ለሆነ ጊዜ ወስዶ የሥርዓተ ትምህርቱን አዘጋጅቷል።በእዚህ ከሶስት መቶ በላይ የሚሆኑ በእንግሊዝ አገር የሚኖሩ ምእመናን እንደተሳተፉበት የተገለጠው ጥናት አሁን ለውጤት በቅቶ በያዝነው ወር ህዳር 3/2010 ዓም እንግሊዝ ዋና ከተማ ለንደን ከተማ በምትገኘው ደብረ ገነት ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን መመረቁ ተሰምቷል። 

በስርዓተ ትምህርቱ ምረቃ ላይ ከእዚህ በፊት ሕፃናትን እንዴት እናስተምራቸው በሚል ርዕስ መፅሐፍ ያሳተሙት የዚህ ስርዓተ ትምህርት ዝግጅት አስተባባሪ እና የማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማዕከል ምክትል ሰብሳቢ ዶ/ር ጨከነ በላቸው የሥርዓተ ትምህርቱ ዝግጅት ላይ አስተዋፅኦ ያደረጉ ከሰላሳ በላይ የቤተ ክርስቲያኒቱ ምሁራን ወጣቶች መሳተፋቸውን ገልፀዋል።

ከአምስት እስከ ዘጠኝ ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ሕፃናትና ታዳጊዎች ታስቦ የተዘጋጀው ይህ ሥርዓተ ትምህርት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን፣ የአማርኛ ቋንቋ እና የመዝሙር ጥናት የተሰኙ አምስት የትምህርት ዘርፎችን ያካተተ ሲኾን፣ የትምህርቶቹ አርእስትና ይዘቶችም በቤተ ክርስቲያን የሚከበሩ በዓላትንና ወቅቶችን መሠረት በማድረግ የተዘጋጁ ናቸው፡፡

የዜናው ምንጭ = ማኅበረ ቅዱሳን ድረ ገፅ (www.eotcmk.org)
ማን እንደርሱ (መዝሙር) በማኅበረ ቅዱሳን የመዝሙር ልዑክ 


ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

No comments:

የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...