Friday, July 23, 2021

በዘንድሮው የጃፓን ኦሎምፒክ የሚሳተፉ አትሌቶች በጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ልዩ ክትትል ከእዚህ በፊት ከነበረው በተሻለ መልኩ ከስምት ወራት በፊት ሆቴል እንዲገቡ ተደርጎ ነበር።በበጀትም ከእዚህ በፊት ያልተያዘ 150 ሚልዮን ብር እንዲያገኝ ሆኗል።ዛሬ በቶክዮ ኦሎምፒክ ስታድዮም ለምን ሁለት ሰው ብቻ ኢትዮጵያን ወክሎ እንዲያልፍ ተደረገ?


የዛሬ የቶክዮ ኦሎምፒክ መክፈቻ ስነስርዓት
Photo= © Getty Images 2021

በእዚህ ፅሁፍ ውስጥ - 
  • ኢትዮጵያ እና ኦሎምፒክ
  • በዘንድሮው ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን ወክለው በመክፈቻው ስነስርዓት ላይ ለምን ሁለት ሰው ብቻ ታየ?
  • የዶ/ር አሸብር እና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሁኔታዎችን አለመከታተል እና አለማመቻቸት የፈጠረው ክፍተት ምንድነው?
  • አሁን ውድድሩ ላይ ይተኮር!  
  

ኢትዮጵያ እና ኦሎምፒክ 

ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ መሳተፍ የጀመረችው ሜልቦርን፣አውስትራልያ እኤአ 1956 ዓም ጀምሮ ሲሆን እስከ እኤአ 2016 ዓም በሪዮ እስከተደረገው የኦሎምፒክ ውድድር ድረስ በተከታታይ ተሳትፋለች።በእነኝህ ውድድሮች ውስጥ ከሜልቦርን ውጪ በሁሉም ውድድሮች ቢያንስ አንድ ሜዳልያ አግኝተናል።ከፍተኛ የሜዳልያ ቁጥር ያስመዘገብንባቸው ውድድሮች ሞስኮ ኦሎምፒክ 4 መዳልያዎች፣ባርሴሎና እና አትላንታ በያንዳንዳቸው 3 ሜዳልያዎች አግኝተናል።በመቀጠል በሲድኔ ኦሎምፒክ 8 ሜዳልያዎች ያገኘን ሲሆን በቀጣይ የተደረጉት በአቴንስ እና በቤጂንግ በእያንዳንዳቸው 7 ሜዳልያዎችን አግኝተናል።በለንደን 2016 ዓም  እኤአ  እና  በ2016 ዓም በሪዮ በድምር 16 ሜዳልያዎች አግኝተናል።

 በ2020 ዓም እኤአ በቶክዮ፣ጃፓን መደረግ የነበረበት የኦሎምፒክ ውድድር በኮቪድ 19 ምክንያት ውድድሩ ዘግይቶ ዛሬ ሐምሌ 16/2013 ዓም  ተጀምሯል።በዛሬው ደማቅ የመክፈቻ ስነሥርዓት ላይ አንድ ሺህ እንግዶች ቢገኙም ስታድዮሙ ግን በሰው ሳይሞላ ስነ ስርዓቱ በቀጥታ ለመላው ዓለም እንዲታይ ሆኗል።በእዚህ የመክፈቻ ስነስርዓት ላይ የኢትዮጵያ ልዑክ በስታድዮሙ መሃል ሲያልፍ በሁለት ሰው ብቻ መታየቱ በርካታ ኢትዮጵያውያንን አበሳጭቷል።

በዘንድሮው ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን ወክለው በመክፈቻው ስነስርዓት ላይ ለምን ሁለት ሰው ብቻ ታየ?

ኢትዮጵያ ዘንድሮ ለኦሎምፒክ ውድድር ዝግጅት ቀደም ብላ ነበር ዝግጅቷን የጀመረችው።በተለይ ለልምምዱ ተብሎ ከእዚህ በፊት አትሌቶች ወደ ሆቴል የሚገቡበት ጊዜ አጭር መሆኑ ኢንዲቀርና  በጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ልዩ ክትትል ጭምር የአትሌቶች የሆቴል ቆይታ ከስምንት ወራት ቀድሞ እንዲሆን ተደርጎ ቆይቷል።በበጀትም በኩል 150 ሚልዮን ብር ተበጅቶለታል።በልምምዱ መሃከል ክብርት ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ተገኝተው አበረታተዋል።በኃላም አትሌቶቹ እና የኦሎምፒክ ኮሚቴ አባላት በቤተመንግሥት ተጠርተው ሽኝት ተደርጎላቸዋል።ባጭሩ በመንግስት በኩል የነበረው ክትትልም ሆነ ማበረታቻ በኢትዮጵያ ልክ አቅም ብቻ ሳይሆን ከእዚህ በፊት ከነበረው በተሻለ መልኩ ድጋፍ ነበር።

ይህ በእንዲህ  እያለ በዛሬው የኦሎምፒክ መክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ በርካታ አትሌቶች በስታድዮሙ ይታያሉ ተብሎ ሲጠበቅ ሁለት ብቻ ታይተዋል።ምክንያቱን አስመልክተው አንዳንዶች በማኅበራዊ ሚድያ የተለያዩ ምክንያቶችን ቢሰጡም፣ሰይፉ ፋንታሁን የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሸብርን እና ኮማንደር ደራርቱን ወደ ጃፓን ደውሎ አነጋግሯል።በቃለ መጠይቆቹ ላይ በርካታ ነጥቦች ተነስተዋል።ለምሳሌ ለምን ሁለት ብቻ ገቡ ለሚለው ጥያቄ ዶ/ር አሸብር ጧት የስድስት ሰው መግብያ ካርድ ለደራርቱ አስረክብያለሁ በሰዓቱ ስላልደረሱ ነው፣እኔም ዘግይቼ ስሰማ ደነገጥኩ  ሲሉ ደራርቱ በበኩሏ በቦታው ለመድረስ ሞክረው ነገር ግን በመረጃ ክፍተት በመጡበት በኩል መግባት እንደማይቻል እንደተነገራቸው ገልጣለች። በሌላ በኩል በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ላይ ቀርቦ የተጠየቀው አትሌት ገዛሐኝ አበራ ጉዳዩ እንዳሳዘነው ገልጦ ምክንያቱን በተመለከተ ብዙም መረጃ እንደሌለው በሚገልጥ መልኩ ምላሽ ሰጥቷል።አለባበስን በተመለከተ የተጠየቁት ዶ/ር አሸብር ከአዲዳስ ኩባንያ ጋር በገባነው የማስተዋወቅ ውል መሰረት ነው ካሉ በኃላ መልሰው የሱፍ ልብሶች ተሰፍተው እንደነበር ይገልጣሉ።ኮማንደር ደራርቱ በሌላ በኩል የሀገር ልብስ ተዘጋጅቶ እንደነበር ገልጣለች።

በቃለ መጠይቁ ላይ የአትሌቶች መንደር የመግባት ፍቃድ በተመለከተ ኮማንደር ደራርቱ መረጃ እንደሌላት በሚገልጥ መልኩ መግባት አለመቻሉን ስትጠቅስ ዶ/ር አሸብር ደግሞ ለሁሉም የመግባት መብት አለው ካሉ በኃላ ለማደር ግን አትሌቶች ብቻ ናቸው የሚችሉት ብለዋል።ሌላው ለዶ/ር አሸብር የተጠየቁት የሚወዳደሩ አትሌቶች 31 ሆነው እያለ ለምን 101 ልዑክ ሄደ? የሚል ነበር።እርሳቸውም ሲመልሱ ሌላው አሰልጣኝ የቦርድ አባል እያለ ቁጥሩ እንደጨመረ ገልጠዋል።ኮማንደር ደራርቱ በሌላ በኩል የቡድን መሪ ዶ/ር በዛብህ በቂ መረጃ ባላገኘበት ሁኔታ ለእዚህም በትውልድ እንግሊዛዊ የሆኑ ትውልደ ኢትዮጵያዊት ለመረጃ ክፍተት አስተዋፅኦ እንዳደረጉ እና በእሳቸው ተሳትፎ ከእዚህ በፊት ቅሬታ እንዳቀረበች አስታውቃለች።ዶ/ር አሸብር ግን ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ በርካታ ሥራ የሰራች እና ልትመሰገን የሚገባት ነች ብለዋል።

የዶ/ር አሸብር እና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሁኔታዎችን አለመከታተል እና አለማመቻቸት የፈጠረው ክፍተት ምንድነው?

ከላይ በቃለ መጠይቆቹ ላይ በግልጥ እንደሚታየው በዶ/ር አሸብር እና በኮማንደር ደራርቱ መሃል በሀገር ቤትም ቀደም ብሎ እንደተሰማው የተናበበ አሰራር እንዳልነበረ በግልጥ ይታያል። ደራርቱ እያለቀሰች እንደተናገረችው የአትሌቲክ መንደር መግባት የማይቻል እንደሆነ ነው የምታውቀው ዶ/ር አሸብር ደግሞ የመግቢያ ካርድ ሰጥቻቸዋለሁ የታክሲ ቫውቸር ነው የሰጧቸው በርሱ  ተጠቅመው መድረስ ነበረባቸው። እኔም ዘግይቼ ነው አለመድረሳቸውን ያወኩት ብለዋል።ይህ በራሱ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነው  ካርድ መስጠታቸውን ብቻ እንደ ኃላፊነት መወጣት መውሰዳቸው በራሱ አስገራሚ ነው።ካርዱን ሲሰጡ ያሉትን መረጃዎች በትክክል ለእነደራርቱ ነግረዋቸዋል? አዳዲስ መረጃዎችስ ተከታትለው በሞባይል የትደረሳችሁ እያሉ ጠይቀዋል? 

በሌላ በኩል አለባበስን በተመለከተ በመክፈቻው ስነ ስርዓት ላይ የአዲዳስን ልብስ ለብሳችሁ ግቡ የሚል ሕግ አለ ወይ? ሁሉም ሀገር ባህላዊ ልብሱን ለብሶ ሲገባ (ከእዚህ በፊትም ኢትዮጵያ እንደምታደርገው) ኢትዮጵያ ያውም 150 ሚልዮን ብር የተመደበለት ኦሎምፒክ ምን ያህል ገንዘብ አስፈልጎት ነው የመክፈቻው ላይ የአዲዳስን  ልብስ ማስተዋወቅ አስፈላጊ ስለነበር ነው ብለው ዶ/ር አሸብር የሞገቱት? ከእዚህ በተለየ ሱፍም ተሰፍቶ ነበር ያሉት በአዲዳስ ልብስ እንደሚገባ እየታወቀ ለሱፍ ማሰፍያ ወጪ ወጥቷል ማለት ነው? በደራርቱ በኩል የሀገር ልብስ መዘጋጀቱን ገልጣለች። 

ኢነኝህ ሁኔታዎች የሚያሳዩት የኢትዮጵያ ስፖርትን ለዘመናት ያቀጨጨው የተዝረከረከ አሰራር፣ቅንነት የሌላቸው ሰዎች አመራር እና ሙስናም ነው። በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ውስጥ ያለው ዝርዝር ችግር ይህ ነው ብሎ ለመደምደም ቀረብ ብሎ መመርመር ቢያስፈልግም በዛሬው  የቶክዮ ኦሎምፒክ ጉዳይ ግን ዋናው ምክንያት የተናበበ አሰራር አለመኖሩ እና አንዱ አንዱን ለማሳጣት የሚደረግ ሩጫ ውጤት ይመስላል። እዚህ ላይ በዋናነት የኢትዮጵያ ኤምባሲ በጃፓን ምን የማመቻቸት ሥራ ሰርቷል።እነደራርቱ በተለያዩ ሀገሮች  ለውድድር ቢሄዱም  ቶክዮን ያህል ውስብስብ ከተማ ውስጥ በቡድን ታክሲ ተሳፍረው እንዲመጡ በሚል ያለምንም ድጋፍ መጠበቅ ይከብዳል። ያውም በኮቪድ ምክንያት ከታክሲ ውጪ ወደ ስታድዮሙ ለሎች መኪናዎች ባልተፈቀዱበት ሁኔታ ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሚሆን መገመት ይቻላል። ኢትዮጵያ ኤምባሲ በየሀገሩ የምትከፍተው እንዲህ ላለ ጊዜ ካልሆነ ለመቼ ሊሆን ነው? እዚህ ላይ የኢምባሲው ድጋፍ ምን እንደነበር የታወቀ ነገር የለም።ሆኖም ግን ይህንን የመረጃ ክፍተት የመሙላት እና የኢትዮጵያውያንን ልዑክ በቦታው መግባቱን የመከታተል እና ድጋፍ የመስጠት ስራ ከኤምባሲው በተጨማሪ የኮሚቴው ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሸብር ግን የማይተካ ሚና እንዳላቸው ጥያቄ ውስጥ አይገባም።

አሁን ውድድሩ ላይ ይተኮር!  

አሁን ባለው መረጃ ተወዳዳሪዎቹ አትሌቶች፣ተኩአንዶ ተወዳዳሪዎች እና ሌሎችም ገና ሀገር ቤት ነው ያሉት።ወደ ጃፓን የሚገቡት ከነገ ቅዳሜ ጀምሮ ነው። ለእዚህም ምክንያቱ አሁን በጃፓን ባለው ከፍተኛ ሙቀት ምክንያት በጉልበታቸው ላይ የመዛል ስሜት ስለሚያመጣ በቀዝቃዛዋ  በኢትዮጵያ መቆየታቸው አስፈላጊ ስለሆነ ነው ሲሉ ዶ/ር አሸብር ተናግረዋል።አሁን ጊዜው የመነታረክያ አይደለም።ኢትዮጵያ ታላላቅ ውድድሮች ከፊቷ ይጠብቃታል።የዛሬውን የመክፈቻ ስነ ስርዓት በተመለከተ የመገምገምያ እና የማረምያ ጊዜው ከውድድሩ በኃላ ይደርሳል።አሁን ሙሉ ትኩረት መሆን ያለበት ወደ ውድድሩ ነው። ተወዳዳሪዎቹንም የመወዳደር ስነ ልቦናቸውን ከፍ እንዲያደርጉ በኮማንደር ደራርቱም ሆነ በዶ/ር አሸብር በኩል መስራት  ስራዎች ከመኖራቸውም በላይ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናትም ሆኑ የንግድ ማኅበረሰቡ ተወዳዳሪዎቹ የተለያዩ ሽልማቶች እንደሚጠብቃቸው ተስፋ መስጠት ይገባል።
ተወዳዳሪዎች በእርግጠኝነት የማሸነፍ ስነ ልቦናቸው ከፍ ያለ እንደሆነ ካደረጉት ዝግጅት መረዳት ይቻላል።

ለማጠቃለል የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ጨምሮ ለኢትዮጵያ ስፖርት መጫጨት ምክንያቶቹ ውስጥ አንዱ አስተዳደራዊ ችግር መሆኑን መንግስት ተመልክቶ ወደፊት ለውጥ ለውጥ በሚያመጣ መልኩ መሰራት እንዳለበት የኦሎምፒክ ኮሚቴው ሁኔታ አመላካች ነው።የኢትዮጵያ ስፖርት በፌድረሽን ደረጃ ብቻ ሳይሆን  በተለያዩ የመንግስት እና የግል ድርጅቶች ውስጥ የሚገኙ የስፖርት ኮሚቴዎች  ለረጅም ጊዜ ሳይቀየሩ የቆዩ፣የገንዘብ አጠቃቀማቸው ግልጥነት የሌለው እና ተጫዋቾች የኮሚቴ አመራሮችን የሚፈሩበት ሁኔታ በራሱ የግንኙነቱ ችግርም ወደፊት መታየት እንዳለበት የሚያመላክት ነው። 
ኢትዮጵያን ወክለው በቶክዮ የሚወዳደሩ አትሌቶቻችን ሁሉ በድል እንዲመለሱ እንመኛለን።

ድል ለኢትዮጵያ!

==========================
ማስታወቂያ /Advertisement 
===============================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

Wednesday, July 21, 2021

What the Media isn't Telling You About the Ethiopia situation in Tigray region.A Very informative New video that you must not miss it.

Source - Break Through News (BT)
July 21/2021

==========================
ማስታወቂያ /Advertisement 
===============================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

Tuesday, July 20, 2021

መንግስት ጁንታውን ትክክለኛ ቀለበት ውስጥ አስገብቶታል።ጁንታው የትግራይ ሕዝብን እያሰቃየ ነው።



  • በጁንታው በግድ የተሰለፉ ታዳጊ ሕፃናት ወደ ኃላ ከዞራችሁ ትገደላላችሁ ስለተባሉ ሕፃናቱ በአማራ ክልል ያሉ መንደሮች ሲደርሱ ደብቁን እያሉ እያለቀሱ መሳርያቸውን እየጣሉ ወደ መንደሮች ሲገቡ ታይተዋል።

ጁንታው በሶስቱም ግንባሮች ክፉኛ ተመትቷል።

የተረፈው የህወሓት አመራር ግራ ተጋብቷል።ትግራይ ከውስጥም ከውጪም ሲኦል ሆናበታለች።ከውስጥ የተፈጠረው ቀውስ ከባድ ነው።ከትግራይ ውጪ ለማዝመት በግዳጅ የሰበሰባቸውን ጀሌዎች በላከበት ሁሉም ግንባሮች ክፉኛ እየተመታ መላወስ አልቻለም።በምዕራብ በኩል የላከው ጀሌ በፀለምት ማይጠብሪ በኩል የመጣው ሙሉ በሙሉ ተደምስሶ ተመልሷል።በራያ በኩል የተከፈተው ከፍተኛ ኪሳራ አስከትሎበታል በተለይ በእዚህ ግንባር በጁንታው በግድ የተሰለፉ ታዳጊ ሕፃናት ወደ ኃላ ከዞራችሁ ትገደላላችሁ ስለተባሉ ሕፃናቱ በአማራ ክልል ያሉ መንደሮች ሲደርሱ ደብቁን እያሉ እያለቀሱ መሳርያቸውን እየጣሉ ወደ ሕዝቡ መንደር ውስጥ ሲገቡ ታይተዋል።


ሦስተኛው የጁንታው ጥቃት የነበረው በአፋር ግንባር ነበር።በእዚህ ግንባር ያለ የሌለ ጉልበቱን አሰባስቦ ተኩስ የከፈተው ጁንታ ዋና ዓላማው የአፋር አርብቶ አደሮችን መዝረፍ እና መግደል የሚችለውን ገድሎ የጅቡቲ አዲስ አበባ መንገድ ለመቁረጥ ነበር።ይህ ትናንት እና ዛሬ የተደረገው ውጊያ የአፋር፣የኦሮሞ እና የአማራ ልዩ ኃይሎች የተሳተፉበት ሲሆን በውጊያው ከአስር ሺህ በላይ በግድ እና በውድ የተሰለፉ የጁንታው ጀለዎች ማለቃቸው ነው የተሰማው።ቁስለኞቹ በብዛት ወደ አማራ እና አፋር ክልል ተወስደው እየታከሙ ሲሆን፣የአስከሬን መቅበሩ ሥራ እስከ መጪዎቹ አስር ቀናት እንደማይጠናቀቅ ነው የተሰማው።የሰው እልቂቱ በእዚህ ደረጃ ላይ እያለ ነው በውጪ እና በሀገር ውስጥ ያሉ ነገር ግን እነርሱ እና ቤተሰቦቻቸው በምቾት እየኖሩ ምስኪኑ የትግራይ ወጣት ግን እንዲሞት ግፋ ይሉታል።

መንግስት ጁንታውን ትክክለኛ ቀለበት ውስጥ አስገብቶታል።ጁንታው የትግራይ ሕዝብን እያሰቃየ ነው።

መቀሌ ኑሮ ሲኦል ሆኗል።የንግድ እንቅስቃሴ የለም።ገንዘብ ሳይኖር እንዴት እና ምን ትነግዳለህ? መብራት የለም።አንዳንድ ቦታዎች ያሉ ጀነረተሮች የሚሰሩበት ነዳጅ እየተሟጠጠ ነው።ለመክናዎች አንዳንድ ነዋሪዎች በችርቻሮ በሃይላንድ ከሚሸጡ ሰዎች እየገዙ ሲጠቀሙ ቪኦኤ ትግርኛ በፊልም አስደግፎ ከትናንት በስትያ አሳይቷል።በትግራይ ከተሞች እና ገጠር ቦታዎች ላይ የሚገኙ የጁንታው ታጣቂዎችን ማጅራት እየመታ መሳርያ የሚወስደው ወጣት በዝቷል።ለሚጣሱ ሕጎች ዳኛ የለም።የመንግስት መዋቅር ባለመኖሩ የመንግስት ሰራተኛው ደሞዝ ከተከፈለው አንድ ወር ሆነው። በኢትዮጵያ ኑሮ የመንግስት ሰራተኛ ከአንድ ወር የበለጠ አስቤዛ መግዛት አይታሰብም። 

ከእዚህ ሁሉ በላይ ሌላ አዲስ ፈተና ደግሞ የትግራይ ወጣት ላይ ተደቅኗል።ጁንታው ከተማ እና ገጠር የተገኘውን ወጣት ማፈስ እና ለሶስት ቀናት ተኩስ እያለማመደ ወደ ግንባር መላክ ጀምሯል። እናት ልጇን ለማዳን የማትችልበት ደረጃ ላይ ደርሳለች።እናቶች ልጆቻቸውን ለማዳን መቻል ቀርቶ ጁንታው በጅምላ ህዝቡ ገንዘብ እና ምግብ እንዲያዋጣ ጥሎበታል።ለራሱ ተረጂ የሆነ ሕዝብ መግብ አምጣ ይባላል። የእናቶች ሃሳብ ይህ ብቻ አይደለም።ልጆቻቸው ክትምህርታቸው ቀርተዋል።ይህ ማለት ዘንድሮ ሁሉም ባሉበት ክፍል መድገም የግድ ይሆንባቸዋል። በመጪው ጥቅምት ወር ላይ በመላ ኢትዮጵያ የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ይሰጣል። የትግራይ ተማሪዎች ግን ዘንድሮ ለፈተናው መቀመጥ አይችሉም።

ይህ ሁሉ የትግራይ ወጣቶች ፈተና፣የእናቶች ሰቆቃ እና የተማሪዎች ቢያንስ በአንድ ዓመት ወደኃላ መቅረት እንዲሁም በሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶች በከንቱ ጦርነትን መርገፍ ዋናው ምክንያት ለዶ/ር ደብረፅዮን፣ጌታቸው ረዳ እና ፃድቃን ስልጣን ጥበቃ ሲባል የሚደረገው ከንቱ ልፋት ነው።ጁንታው የትግራይን ሕዝብ ከጉሮሮው መንጠቁ ሳይበቃው በተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ዕርዳታ በኩል ወደ ትግራይ በአፋር መስመር በኩል እህል ጭነው ሊገቡ የነበሩ 169 ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች የጫኑ የጭነት መኪናዎች ከጁንታው በአስሩ ላይ በመተኮሱ 169ኙም መኪናዎች ወደትግራይ ከመግባት ተገትተዋል።የዕርዳታ መኪናዎቹ ወደትግራይ የማይገቡት በተደረገባቸው ተኩስ መሆኑን እራሱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባወጣው መግለጫም አምኗል።ቢቢሲ አማርኛም ይህንኑ ጠቅሶ ነገር ግን ማን ተኮሰ የሚለውን ቢቢሲ አማርኛ አለመናገሩ ብዙዎች ዘንድ ግርምት ፈጥሯል። ምክንያቱም ሮይተርስ ብቻ ሳይሆን እራሱ የጁንታው ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳም አፋር አርብቶ አደር ላይ ተኩስ መክፈታቸውን አምነው እያለ ቢቢሲ በዕርዳታ መኪናዎቹ ላይ ማን እንደተኮሰ ለመፃፍ ስሽኮረመም ታይቷል።

ባጠቃላይ የተረፈው የጁንታው አመራር የትግራይን ሕዝብ ወደ ጦርነት መማገድ ብቻ ሳይሆን ለዕርዳታ የመጣለትን ምግብ እንዳይገባ ተኩስ ከፍቶበታል። በአማራ እና አፋር ያሉ  የትግራይ አዋሳኝ ወረዳዎች እና ከተሞች  ያሉትን ነዋሪዎች እንዲፈናቀሉ እያደረጉ ነው። መንግስት  የመከላከያ ኃይልን በሙሉ ኃይል ገና አላንቀሳቀሰም።እስካሁን በሶስቱም ግንባሮች የተመታው የጁንታ ኃይል ባብዛኛው በአማራ ልዩ ኃይል እና ከሁሉም ክልሎች በተውጣጡ ልዩ ኃይሎች ነው።የሱማሌ ልዩ ኃይልም በምክትል አዛዥ ኮለነል እየተማራ ዛሬ አዲስ አበባ መግባቱ እና ወደ ግንባር መንቀሳቀሱ ተሰምቷል።የደቡብ፣የሲዳማ፣የኦሮሞ፣የሐረር እና የሌሎች ክልሎች ልዩ ኃይሎች ወደ ግንባር ቀደም ብለው ተንቀሳቅሰዋል።መንግስት ግን ባቀደው መልክ የጁንታውን ኃይል በትክክለኛ ቀለበት ውስጥ አስገብቶታል። በእዚህም የኢትዮጵያ የቅርብ እና የሩቅ ጠላቶችም በጭንቀት ሁኔታውን እየተከታተሉ ነው።በተለይ ጁንታው ኢትዮጵያን ለመበተን የመነሳቱን ሂደት በከፍተኛ ደረጃ የሚደግፉት የውጭ የጠላት ኃይሎች ለጁንታው ምናልባት በሳተላይት የተደገፈ መረጃ ከመስጠት እና  እንደ ግብፅ ያሉት ደግሞ የወታደራዊ አማካሪዎቻቸው በምክር ለመርዳት ከመሞከር ውጪ ምንም ሊያደርጉ አይችሉም።የሰሞኑ ጁንታው በአፋር አርብቶ አደሮች ላይ ተኩስ ከፍቶ የጅቡቲ አዲስ አበባ መንገድን እንዲዘጋ የሚለው ምክረ ሃሳብ ከኢትዮጵያ ጠላቶች የተገኘች እንደሆነች መገመቱ ቀላል ነው።እርሱም ቢሆን ተመትቷል።የትግራይ ሕዝብ ኢትዮጵያን ለመበተን በግልጥ እየነገረ ከሚያዘምተው የራሱም ሆነ የኢትዮጵያ ጠላትን እየደገፉ ከመሄድ ከጁንታው ጋር አጭር ትግል አድርገው ቀሪዎን ጊዜ ብሩህ ዘመን ማድረግ በእዚህ የፅሞና ጊዜ ለትግራይ ሕዝብ የቀረበ ታሪካዊ ጥሪ እና ዕድል ነው።

==========================
ማስታወቂያ /Advertisement 
===============================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

Monday, July 19, 2021

''ጥፊ ያላት ከተማ ነጋሪት ቢጎሰምባት አትሰማም''



  • ''በአማራ ላይ ሂሳብ እናወራርዳለን'' ለሚለው የተረፈ ህወሓት አመራሮችን አደገኛ የዘረኝነት ንግግር የተቃወመ የተጋሩ የፖለቲካም ሆነ ማኅበራዊ  ድርጅት ወይንም ስብስብ አለ?

 ''ጥፊ ያላት ከተማ ነጋሪት ብጎሰምባት አትሰማም'' እንዲሉ ህወሓት የሽብር ተግባሩን በመቀጠሉ  ከጥሞና ጊዜ በኃላ መንግስት የጠነከረ እርምጃ እንደሚወስድ ግልጥ እየሆነ መጥቷል።የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሰኔ 21፣2013 ዓም  በተናጥል የተኩስ አቁም ውሳኔ የእርሻው ወቅትን ገበሬው እንዲጠቀምበት በማሰብ ትግራይን ለቆ ሲወጣ የህወሓት ሽብር ተግባር በትግራይ ከተሞች እና ገጠር ደጋፊ ያልሆኑ ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጋር የነበሩ በሚል ቁጥሩ ከፍ ያለ ሕዝብ በመግደል ነበር የጀመረው።

ከግድያው ተከትሎ ተከታታይ የድንፋታ መግለጫዎች በህወሓት የሽብር ቡድን ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ መሰጠት ተጀመረ።በእዚሁ መግለጫ ላይ ጦርነቱን ወደ አማራ እና ኤርትራ እንደሚያስፋፉት መዛት ጀመረ።ቀደም ብሎየህወሓት የተረፉ አመራሮች በግልጥ በአማራ ሕዝብ ላይ ጦርነት አውጀዋል።ይህንንም ደጋግመው እየተቀባበሉ ''በአማራ ላይ ሂሳብ እናወራርዳለን'' በማለት ተናግረዋል።

 ህወሓት በአማራ ላይ ያላት ጥላቻ በ1967 ዓም ባወጣችው ማኔፈስቶ በግልጥ አስቀምጣለች።ይህ የናዚያዊ ትርክቷ አድጎ ዛሬ ሂሳብ አወራርዳለሁ ወደማለት አሳድጋዋለች።ይህ ንግግር በሀኪም ማስረጃ አይሰጣቸው እንጂ የአዕምሮ ህመም ላይ ባሉ የህወሓት ሽብርተኞች መነገሩ ባይገርምም።ይህንን ንግግር ያወገዘ የተጋሩ የፖለቲካም ሆነ ማኅበራዊ ድርጅት ወይንም ስብስብ አለመኖሩ ግን ሌላው ከባድ ጥያቄ ነው።ከአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ እብደታቸውን በልክ ማድረግ የማይችሉ ግለሰቦች መፈጠራቸው አይደንቅም።የሚደንቀው ግን ከእዛው ማኅበረሰብ ውስጥ በምንም ዓይነት መልክ የሚገኝ ስብስብ አለማውገዙ ግን ሌላ አደገኛ ጉዳይ ነው።

አሁን ያለንበትን ጊዜ በሚገባ ማወቅ ክምር መረዳት ያስፈልጋል።የተረፈው የህወሓት ስብስብም ሆነ አብረውት የቆሙት ጀሌዎቹ ጥያቄያቸው ግልጥ ነው።እኩልነት አንፈልግም።በቅኝ ገዢነት እንግዛችሁ ነው።ይህን ቅኝ ገዢነት ካልተቀበላችሁ ደግሞ ኢትዮጵያን እናፈርሳታለን የሚል ዛቻ ተደጋግሞ ተሰምቷል።አሁን ጉዳዩ ቁርጥ ነው።ይህ ቀላል ጉዳይ አይደለም።ኢትዮጵያን አጠፋለሁ ብሎ በአደባባይ የዛተ  እንዴት እንደሚጠፋ በቅርብ ዘመን ላልተመለከተ ታዳጊ ወጣት ታሪክ የሚሆን እርምጃ በተረፈ ህወሓት ላይ እንደሚወሰድ አትጠራጠሩ። 

ጥሞና ጊዜው ጥሩ አጋጣሚ ነበር።ወደ ሰላም መጥቶ ቆሜለታለሁ የሚሉትን ሕዝብ ማዳን አንዱ አማራጭ ነበር። ከእዚህ አልፎ ዛቻ፣ንፁሃንን መግደል እና መዝረፍ ግን እጅግ የመረረ ምላሽ ከኢትዮጵያ መከላከያ እንደሚኖር አለመጠበቅ የዋህነት ነው። የመከላከያ እታማዥር ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ዛሬ  በግልጥ ተናግረዋል።እኛ በትዕዛዝ ውጡ ስንባል እንወጣለን። መልሶ ግቡ ስንባል እንገባለን ብለዋል።መንግስት ለህሊናም ያልተሞከረ መንገድ እንዳለ በኃላ ይህ ቀርቶ ነበር ከመባል በሚል ከባድ ውሳኔ የሆነውን ለቆ መውጣት እና በተናጥል የተኩስ ማቆም አውጆ ሞክሮታል።ነገር ግን ይህ ለውጥ አላመጣም ይልቁንም ጦርነት የተጠሙት የተረፉት የህወሓት አመራሮች በመቀሌ እና ሌሎች ከተሞች ወጣቱን እያፈሱ የሦስት ቀኖች ስልጠና እየሰጡ ወደግንባር ወንድምህን ግደል ብለው እያዘመቱት ነው። መንግስት ዝቅ ብሎ ይህንን ያህል ሲያስተናግደው በትዕቢት የተወጠረው ተረፈ ህወሓት ከእንግዲህ ወዲህ የሚወሰድበት እርምጃ  የከፋ ነው።በእርምጃው ደግሞ የልማት አውታሮች አይፈርሱም ማለት አይቻልም።አሁንም ትምህርት ቤቶች ሳይቀሩ የእሳት ማንደጃ ማዕድቤት ያደረገ ያለው የሽብር ቡድን ለሚፈርሱ የልማት አውታሮች ቅንጣት ታህል አያስብም።

ባጠቃላይ  አሁን ሁኔታው  ''ጥፊ ያላት ከተማ ነጋሪት ቢጎሰምባት አትሰማም'' እየሆነ ነው። ይህ ሲባል አንዳንዶች ተራ ሟርት ይመስላቸዋል።ይህ ግን ፈፅሞ አይደለም።ምክንያቱም  ኢትዮጵያ ማበዳቸውን ለማረጋገጥ የሃኪም ማስረጃ ብቻ በቀራቸው ሽብርተኞች ሰላሟ አይታወክም። በእርግጥ አንድ እና ብቸኛው መስመር የትግራይ ማኅበረሰብ ህወሓትን በቃኝ ከህዝብ እያጋጨህ የወደፊት የመኖር ተስፋዬን አታጨልምምብኝ  ማለት ነው።ይህንን እንደማኅበረሰብ  በማድረግ ድምፁን ያሰማበት ሁኔታ ደግሞ እስካሁን አልተሰማም።በእርግጥ በግለሰቦች ደረጃ  ህወሓትን ሲታገሉ የኖሩ አሉ።ለእነርሱ ክብር ይገባቸዋል።ቢያንስ ከአማራ ጋር እንደህዝብ ለማጋጨት ሂሳብ እናወራርዳለን ንግግርን  አለመቃወም ግን የማስተዋል መጉደል ውጤት ነው።

==========================
ማስታወቂያ /Advertisement 
===============================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

Wednesday, July 14, 2021

Ethiopian National Defence Force (ENDF) is one of the top disciplined and well trained armies in our globe. Its law enforcement in Tigray was with higher level of humanity

  • Ethiopian army ranks 60th out of 138 armies around the world


 Ethiopian National Defence Force guarding the GERD



By Getachew Bekele Damtew,
Gudayachn Editor

The end of the year 2020 and the last six months of 2021 were one of the very crucial times for Ethiopians. The political, economic and social reforms,started in 2018, were at a very important stage; both the ruling and opposition parties were preparing for the June 21,2021 election; a number of urban based Government projects were at final stages and the impact of Covid-19 was starting to decline relatively to Summer 2020.

 

All these situations were suddenly shifted with the new political and military incidence in Tigray province of Ethiopia. On November 4/2020 Tigray People's Liberation Front (TPLF) attacked the Ethiopian National Defence Force (ENDF) command quarters in  Mekelle, Dansha, Adigrat, Aguila and Sero. On the same evening, Prime Minister Abiy Ahmed announced, on a live transmission broadcast of TV and Radio, Ethiopian National Defence Force was ordered to take all necessary actions of law enforcement.

 

It was only three weeks that the Ethiopian National Defence Force needed to disarm the TPLF army which was estimated at over 250 thousands highly armed soldiers.On the coming weeks and months the diaspora wing of TPLF started to distribute disinformation and false news through social media mainly on Twitter. Even Though, some US, European Union and International Organizations officials have well know-what on the real situation in Tigray, they preferred to distribute the false information on Ethiopian National Defence Force (ENDF) in their meetings,speeches and press releases.

 

Ethiopian National Defence Force is one of the top disciplined armies in Africa. This not only originated from its well cultured society but  it is due to its training and leaders on different levels ability to shape the army on International Military Standards. The army has a long history of law enforcement. Its founders were UN Peacekeeping force members in Korean and Congo war in the 1940s and 1950s. In recent years the army provided exemplary International Peacekeeping service in Rwanda, Sudan Darfur and even currently serving in Somalia. In all these services there is not a single complaint raised from any communities and individuals of the host countries. Therefore, it is not possible to say an army with sound service abroad has a problem of human rights violation in its own community in Tigray province in Ethiopia.

 

Disinformation and spreading fake news was not only opened on Ethiopian National Defence Force. The Eritrean army was also under the target.The international media  talked as if civilians were killed in a large number in different cities of Tigray. Here it is not possible to say that there are no casualties. This is not vacation.It is law enforcement with ten thousands fighting with another ten thousands. So it could not be free from any count of dead bodies, which is the ugly side of ‘war’.However, we need to note that In any measurement Ethiopian National Defence Force do not have any ethical and discipline problem. 

 

To conclude, the Ethiopian army ranks 60th out of 138 armies around the world, according to the Jerusalem post June 15,2021 issue. And it is top among Saharan countries in having highly educated and well trained officers. The army is not a treat for all immediate neighbouring countries. Moreover, it is proud of their security guarantee. Therefore, it is not acceptable and justifiable to criticize the Ethiopian National Defence Force in its ethical standard and the level of responsibility for both its own community in Tigray and any other country's citizens.

==========================

ማስታወቂያ /Advertisement 
===============================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

Tuesday, July 13, 2021

ጉዳያችን ምዕራፍ ሁለት ተመልሳለች - ብዙ ጊዜ እንደ ዋዛ ያያቸውን ዓማራ አሁን ቀስቅሰውታል።

 ጉዳያችን ምዕራፍ ሁለት ተመልሳለች።በእዚህ ምዕራፍ የተለያዩ ጉዳዮች ይዳሰሳሉ።በእዚህኛው የጉዳያችን ገፅ ላይ ፅሁፉን ወደፈለጉት የዓለም ቋንቋ የሚቀይሩበት ማስፈንጠርያ ከእያንዳዱ ፅሁፍ አናት ላይ ያገኛሉ።በተጨማሪም ለጉዳያችን የሚፅፉበት ቦታም በቀኝ በኩል ተቀምጧል።

ወደ ወቅታዊው ጉዳይ ስንመለስ፣የምዕራቡ እና የምስራቁ ውጥረት በአዲስ መልክ እየመጣ ነው።ኢትዮጵያን ከግራ እና ከቀኝ ወጥሮ በውስጥ ጉዳይ ሁሉ ሳይቀር በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የተነሱትን ጎሰኞች አይዞአችሁ ብሎ ኢትዮጵያን ለመከፋፈል ብሎም አፍሪካን ለማዳከም እና የማትነጥፍ 'የጥገት ላም' ለማድረግ እሩጫው በርትቷል።

በእዚህ ሁሉ መሃል የምድያው ሚና ቀላል አይደለም።ሚድያው የማነስ እና የመተለቁ ቁምነገር ሳይሆን የሚመነጨው ሃሳብ ምን ያህል የተቀባዩን ወዳጅ ከሆነ የሞራል ስንቅ የሀገር ጠላት ከሆነ ደግሞ የተንኮል ድሩን የመበተን ኃይል ያለው አዲስ ሃሳብ ያመነጫል? ነው ጥያቄው።በአዲስ ሃሳብ ዓለም እንደገና ተቦክቶ ይሰራል።በማይቀየር ሃሳብ ደግሞ ዓለም ባለበት ይረግጣል።

ወደ እዚህ ሁለተኛ ምዕራፍ ጉዳያችን ስትገባ በኢትዮጵያ አንድ ግልጥ ሆኖ የመጣ ጉዳይ አለ። ህወሓት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ጦርነት ከፍቷል።ቃል አቀባዩ አቶ ጌታቸው ረዳ ቃል በቃል ''ኢትዮጵያን እናፈርሳታለን'' ብሏል።ኢትዮጵያ ባንዳ እና ለሆዱ ያደረ አሰር ገሰስ ስታፈራ ህወሓት የመጀመርያዋ አይደለም።ከእዚህ በፊት በታሪክ ተነስተውባታል።ነገር ግን ሁሉንም አይቀጡ ቅጣት ቀጥታ አባራቸዋለች።የህወሓት ዕጣም ካለፉት የተለየ አይሆንም።

ይህንን ጽሁፍ ስፅፍ ህወሓት በሁለት ግንባሮች ማለትም በወልቃይት ሁመራ እና በራያ በኩል ቃል በቃል የተረፈ ህወሓት ሰዎች  ጀነራል ፃድቃን እና አቶ ጌታቸው እንዳሉት  ''ከአማራ ጋር ያላቸውን ሂሳብ ለማወራረድ'' በንፁሃን ላይ ግድያ ጀምረዋል።የአማራ ክልልም የክተት አዋጅ አውጇል። ብዙ ጊዜ እንደ ዋዛ ያያቸውን ዓማራ አሁን ቀስቅሰውታል።

የዛሬ 46 ዓመት የተዘፈነው ዘፈን (ከጉዳያችን ዩቱብ ድምፅ ክምችት) 





የመስቀል ደመራ በዓል በንግስት ዕሌኒ ሀገር በግሪክ ቅዳሜ መስከረም 16፣2019 ዓም በከፍተኛ ድምቀት ተከብሮ ዋለ።በግሪክ የምትገንኘው የአቴንስ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን ምእመናን ለቅዱስ ሲኖዶስ አቤቱታቸውን ደግመው አቀረቡ።

======== ልዩ ሪፖርታዥ ======== በእዚህ ርዕስ ስር የሚከተሉትን ንዑስ ርዕሶች ያገኛሉ።እነርሱም ፡  የመስቀል ደመራ ለምን ይከበራል? ግማደ መስቀሉ  ወደ  ኢትዮጵያ እንዴት መጣ? የዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል...