Tuesday, March 30, 2021

የኢትዮጵያን ፀጥታ ለማረጋገጥ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ራሳቸውን እና ቤተሰባቸውን ከሽ.ነ.ድ. መጠበቅ አለባቸው።

  • የውጪ ባዕዳን እና በውስጥ ያኮረፉ ከሊቅ እስከደቂቅ ያለው ኢትዮጵያዊ ላይ ሊዘምቱበት የሚዘጋጁት በሽነድ ነው።

ኢትዮጵያ በጥገናዊ ለውጥ ውስጥ ከገባች ነገ መጋቢት 24/2013 ዓም ሦስተኛ ዓመቷን ትይዛለች።በእነኝህ ሦስት ዓመታት ውስጥ በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል።ይህ ለውጥ ባይመጣ ኖሮ ኢትዮጵያ ዛሬ እጅግ አደገኛ ብቻ ሳይሆን ሕልውናዋም ጥያቄ ውስጥ የማይገባበት ምክንያት አይኖርም።ምክንያቱም የነበረው የውስጥ ቅራኔ ውስብስብ ከመሆኑ አንፃር በቀጥታ የእርስ በርስ ጦርነት አይኖርም ማለት አይቻልም።አንዳንዶች ይህ ሲባል ዛሬ ያለችው ኢትዮጵያ ከሦስት ዓመት ከነበረችው የባሰ ነው ብለው የሚናገሩ በማኅበራዊ ሚድያ የሚገልጡ ከአጠቃላይ ኢትዮጵያ የነበረችበት የችግር ጥልቀት ያልተረዱ ናቸው።ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች በሙሉ ወደ ሀገር ቤት ገብተዋል፣ስደተኞች ወደ ሀገራቸው በነፃ መግባት መውጣት ችለዋል፣በሺህ የሚቆጠሩ እስረኞች ተፈትተዋል፣የመገናኛ ብዙሃን ነፃነት በአንፃራዊ መልኩ የተሻለ ነው፣የትምህርት ፖሊሲ በአዲስ መልክ ተዘጋጅቷል፣የኢትዮጵያ ምድር ኃይል እና አየር ኃይል መዋቅር ማሻሻያ ተሰርቷል፣የፍትሕ፣የፖሊስ እና ሌሎች መዋቅሮች ማሻሻያ ተጀምሯል፣የዓባይ ግድብ ፕሮጀክት በአዲስ መልክ ተከልሷል፣በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መሃከል ሰላም ተፈጥሯል ሌላም ስራዎች ተሰርተዋል።እነኝህ እያንዳንዳቸው ቢተነተኑ ብዙ ገፅ ማብራርያ የሚፈልጉ ናቸው።

ከላይ በመጠኑ የተጠቀሱት ስራዎች እና ሌሎች ያልተጠቀሱት ተግባራት የተሰሩ እና እየተሰሩ ቢሆኑም በሌላ በኩል ደግሞ የሕዝብ መፈናቀል፣የጎሳ ግጭቶች እና የእምነት ቦታዎች መቃጠል የተፈፀሙ አሳዛኝ ድርጊቶች ናቸው።ይህ ሁሉ ሆኖ ግን አጠቃላይ ሂደቱን ስንመለከት ኢትዮጵያ ከግዙፍ ችግሮቿ ለመውጣት ከትናንቱ እጅግ በላቀ መስመር ላይ እንዳለች መረዳት ይቻላል።ሆኖም ግን በቀጣይ ወራት ኢትዮጵያ ከምትተገብራቸው ሁለት ግዙፍ ስራዎች ማለትም የአባይ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ መሙላት ተግባር እና የብሔራዊ ምርጫ አንፃር የኢትዮጵያን መነሳት የሚያሰጋቸው ባዕዳን እና በውስጥ ያኮረፉ በውጭ እና በሀገር ውስጥ ያለውን ኢትዮጵያ ከሊቅ እስከደቂቅ ሊዘምቱበት የሚዘጋጁት በሽነድ ነው።

ሽ.ነ.ድ ኢትዮጵያን ለማጥቃት የኢትዮጵያ ጠላቶች ቀደም ባሉ ዓመታት ሲጠቀሙበት የነበረ ድርጅት ነው።ቃሉ ለመጀመርያ ጊዜ የሰማሁት የአንድ ዓመት የኮሌጅ ተማሪ ሳለሁ የዛሬ 30 ዓመት የኢትዮጵያ ኮሌጆች እና ዩንቨርስቲዎች ወደ ብላቴ የአየርወለድ ማሰልጠኛ ሲዘምቱ በሄድኩበት ወቅት ወደ አስር ሺህ የሚቆጠሩ ተማሪዎች ውስጥ ተማሪዎቹን ለማሸበር የሚወሩ ወሬዎችን ተማሪው የሰጠው ስም ነበር።ሽነድዎች በጣም ጥቂት ሲሆኑ የጠላት ተልዕኮ ይዘው በወቅቱ የነበሩት ሽምቅ ተዋጊዎች ለማግነን የታሰበ  የውሸት ወሬ እየፈጠሩ የሚያወሩ ናቸው።እነኝህን ኃይሎች ተማሪው ወድያው ስለነቃባቸው በግዙፉ የብላቴ ተራራ ላይ አስር ሺህ ተማሪ በተሰበሰበበት ነው ሽነድ የሚለው ስም በይፋ የተሰጣቸው።ሽ.ነ.ድ ማለት ሽብር ነዥ ድርጅት ማለት ነው።

ሽ.ነ.ድዎች ዛሬ የት ናቸው ?

ሽነድዎች በብላቴ ተማሪውን በተለያየ ወሬ ለመረበሽ ሞክረው እንደነበር ሁሉ ዛሬ ሽነድዎች የኢትዮጵያን ሕዝብ ከታች ሊስትሮ እስከ ጠጅ ቤት፣ከገጠር ጠላ ቤት እስከ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል፣ከታክሲ ተሳፋሪ እስከ ቦይንግ 767፣ከቤተ መቅደስ እስከ መስጊድ፣ከዩንቨርስቲ እስከ ቀበሌ ፅህፈት ቤት፣በውጭ ደግሞ በዩቱብ መስኮት ላይ ተንጠላጥለው ይገኛሉ።

ዛሬ ሽነድዎች ሸነድ መሆናቸውን የሚያውቁ እና የማያውቁ ተብለው በሁለት ይከፈላሉ።  
 
ሽነድዎች እንዲሆኑ የሰለጠኑ እና መሆናቸውን የሚያውቁ የመኖራቸውን ያህል ሽነድ መሆናቸውን ሳያውቁ የሽነድን ሥራ የሚሰሩ አሉ።ሽነድ መሆናቸውን የሚያውቁ ሆን ብለው ህዝቡ መሃል ሆነው ከቤተሰባቸው ጀምሮ በቀን ውሏቸው ያገኙአቸውን ሁሉ በተሰጣቸው የውሸት ወሬ ሁሉ ላገኙት ሲያሰራጩ የሚውሉ ናቸው።ጧት ከባላቸው ወይንም ከሚስታቸው ቀጥሎ ጎረቤቶቻቸውን ሁሉ  ኢትዮጵያ እንዲህ ልትሆን ነው፣አዲስ አበባ ልትጠፋ ነው፣አንድ ሰው ሞተ ሲባሉ አንድ መቶ ሰው ሞተ እያሉ የሚያወሩ ናቸው። ሽነድ መሆናቸውን የሚይውቁ ሰዎች እንዳይታወቁ የሚጠነቀቁ ናቸው።የውሸት ወሬ አከፋፋይ እና አመንጪ ስለሆኑ እነርሱ የውሸቱን ወሬ የመለኮስ ሚና እንጂ ማቀጣጠሉን እራሳቸው ሽነድ መሆናቸውን ለማያውቁ ማቀበሉ ላይ ነው የሚተጉት።

ሽነድዎች አንዱ ተግባራቸው ሕዝብ ተስፋ እንዲቆርጥ የሚያደርጉ ማናቸውንም ወሬዎች ማውራት ነው።በጣም አሰቃቂ ነገር ሲፈፀም ይፈነጥዛሉ።ሕዝብ በመንግስት እና በመሪዎቹ ላይ ተስፋ እንዲቆርጥ በዋናነት በጠቅላይ ሚኒስትሩ እና በሌሎች ኢትዮጵያን ብለው በሚሰሩ ባለሙያዎች ላይ ሁሉ የውሸት ወሬ ይከፍቱባቸዋል።በእዚህም ሕዝብ ውሸት ሲደጋገምለት ያምናል በሚል ስራዬ ብለው ሕዝቡን ማሸበር ላይ በመስራት ላይ ናቸው።ሌላው ቀርቶ ዛሬ ኢትዮጵያ በመጪው ዓመት ካሜሮን ላይ ለሚደረገው የአፍሪካ ዋንጫ ማለፍዋ አናዷቸዋል።በማኅበራዊ ሚድያ ሰሞኑን በሚያወሩት ወሬ እና በጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ላይ በከፈቱት የውሸት ዘመቻ ሕዝቡን ያስተከዙት እና ተስፋ ያስቆረጡት መስሏቸው ባለበት ሰዓት ከመቅፅበት ከአይቨሪኮስት የተሰማው የኢትዮጵያ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ማለፍ ሕዝብ አውራ ጎዳና ላይ ወጥቶ ማስጨፈሩ ሽነድ የደከመበትን ሕዝቡን የማስተከዝ ሥራ ገደል መክተቱ አናደዳቸው።

ሸነድዎች በቀጣይ ሊሄዱበት ያሰቡበት መንገድ ያልላካቸውን እግዚአብሔር እንደላካቸው እያደረጉ በክርስትናውም ሆነ በእስልምናው መምህራንን በገንዘብ እየገዙ ትንቢት ተገለጠልን እያሉ ማውራት ነው።ዘመኑ ደግሞ የዩቱብ ዘመን ስለሆነ በቀላሉ ህዝቡ ጋር እንደሚደርሱ ያስባሉ።ሽነድዎች ጥቂት በመሆናቸው በወሬ የኢትዮጵያን ሕዝብ ለማሸበር አቅም የላቸውም። ነገር ግን ሽነድ መሆናቸውን ሳያውቁ የሽነድዎችን የሐሰት ወሬ የሚያሰራጩ መብዛታቸው ወሬው እንደፈለገ እንዲዞር እረድቷቸዋል።

በውጭ ሀገርም ሆነ በሀገር ቤት እጅግ ቅኖች፣ለሀገር አሳቢዎች እና የኢትዮጵያን ከፍ ማለት የሚፈልጉ ብቻ ሳይሆን በተጠሩበት ሁሉ ቀድመው ለሀገራቸው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስለ ኢትዮጵያ ከሽነድዎች በሚሰሙት የውሸት እና የተጋነነ ወሬ ተጨንቀው ሌሎችን በማስጨነቅ ሳያውቁት የሽነድ ቫይረስ ያስተላልፋሉ።ሽነድዎች ዋና ዓላማቸው ይህ ነው።ሕዝብ እንዳይረጋጋ፣እንዳይደሰት እና ተስፋ እንዳይታየው ማድረግ ስለሆነ ሽነድ መሆናቸውን ሳያውቁ የሽነድን ሥራ የሚሰሩትን ከቤተሰብነት እስከ መልካም ወዳጅ ቀርበው የውሸቱን ወሬ ይነዙባቸዋል።

ባጠቃላይ በቀጣይ ወራት ኢትዮጵያን ለመረበሽ በጦር ሜዳ ያልተሳካለት የውስጥም ሆነ የባዕዳን ኃይሎች የቀራቸው ብቸኛ መንገድ ሽነድ ( ሽብር ነዥ ድርጅት) ነው።መንግስትም ሆነ ሕዝብ ከጠጅ ቤት እስከ ሸራተን ባር፣በሞባይል ልስክ ከሚለቀቅ የውሸት ወሬ እስከ የዩቱብ የውሸት ወሬ ነዥ ተናበው ነው የሚሰሩት።ሸነድ በተራ መንደር ውስጥ ብቻ የሚገኙ አይደሉም።በመንግስት መስርያቤት እና በመንግስት መገናኛ ብዙሃንም ሳይቀሩ የሚዘጋጁ ፕሮግራሞች ላይ የረቀቁ የስነ ልቦና ዘመቻ የምትከፍት ቃላት በመሰንቀር ወይንም መልካሙን ዜና በመደበቅ ካልተቻለ ቆርጦ በማስተላለፍ ሁሉ ሸነድ ኢትዮጵያን ለማተራመስ ይሰራል።ስለሆነም ከሀገር ቤት እስከ ባሕር ማዶ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከቤተሰብ እስከ ጎረቤት፣የቅርብ እና የሩቅ ወዳጅ ሁሉ ሳያውቀው የሸነድ አስተላላፊ እንዳይሆን ነቅተው እና ተግተው እራሳቸውንም ቤተሰባቸውንም መጠበቅ አለባቸው። 

========================//////================

 ********************************
ማስታወቂያ /Advertisement 
====================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 
  

Sunday, March 28, 2021

በሙ/ጥ/ዲ/ ዳንኤል ክብረት ለኢትዮጵያ እንደራሴዎች ምክርቤት ምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመርያ መርሐግብር ላይ የመሐመድ ካሳ ምስክርነት ፣የዶ/ር ዳኛቸው ንግግር እና የዕጩ ተወዳዳሪው ሙ/ጥ/ዲ/ ዳንኤል ክብረት ንግግር (ቢመለከቷቸው ብዙ የሚያተርፉባቸው 3 ቪድዮዎች)

ሙ/ጥ/ዲ/ ዳንኤል ክብረት በያዝነው ዓመት 2013 ዓም በሚደረገው ብሔራዊ እንደራሴዎች ምርጫ የግል ዕጩ ተወዳዳሪ ናቸው።ትናንት መጋቢት 18/2013 ዓም በአዲስ አበባ ካፒታል ሆቴል የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመርያ መርሐግብራቸው ላይ የተደረጉ ሦስት ድንቅ ንግግሮች ቪድዮዎች ከእዚህ በታች ቀርበዋል።

የመሐመድ ካሳ ምስክርነት  

የዶክተር ዳኛቸው አሰፋ ንግግር 

የሙ/ጥ/ዲ/ ዳንኤል ክብረት ንግግር 


********************************
ማስታወቂያ /Advertisement 
====================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

Thursday, March 25, 2021

رئيس الوزراء سد النهضة مصدر إزدهار وليس مصدر قلق لدول The Renaissance Dam is a source of prosperity not a source of concern for downstream countries

رئيس الوزراء سد النهضة مصدر إزدهار وليس مصدر قلق لدول المصب
''The Renaissance Dam is a source of prosperity not a source of concern for downstream countries'' The PM of Ethiopia,Abiy Ahmed.
Watch full video in Arabic version.

********************************
ማስታወቂያ /Advertisement 
====================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

Monday, March 22, 2021

በአዲሱ የኢትዮጵያ የትምህርት ፖሊሲ እና ፍኖተ ካርታ አማራጮችና አተገባበሮቻቸው ላይ ከትምህርት ሚኒስትሩ ከዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩርያ ማብራርያ (ቪድዮ)

ቪድዮ = ኢቲቪ መጋቢት 13/2013 ዓም (ማርች 22/2021 ዓም)

********************************
ማስታወቂያ /Advertisement 
====================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

Sunday, March 21, 2021

አቶ ሽመልስ እና የክልሉ አስተዳደር ኦሮምያን ማስተዳደር እንዳቃተው በግልጥ መናገር አለበት።ብልጥግና በፍጥነት ተሰብስቦ በኦሮምያ ክልል ላይ ውሳኔ ማሳለፍ አለበት።



የኦሮምያ ክልል፣ላለፉት ሦስት ዓመታት በተለየ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ክልሎች  ውስጥ የፀጥታ  ችግር ሆኖ ቀጥሏል። ክልሉ በመጀመርያ ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ የገባው ከሱማልያ ክልል ጋር ነበር።በእዚሁ በተነሳው የክልል መስመር ጭቅጭቅ ወደ አንድ ሚልዮን የሚጠጋ ሕዝብ ተፈናቀለ።በመቀጠል በስም ኦነግ ሸኔ እየተባለ ነገር ግን የክልል ሚሊሻ መሆናቸው የተነገረ በጌድዮን ሕዝብ ላይ ጥቃት ፈፀሙ።መቶ ሺዎች ተፈናቀሉ።እናቶች እና ሕፃናት በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ።በእዚህ ብቻ አላበቃም።በምዕራብ ወለጋ በተደጋጋሚ፣በሐረር ደጋማ ቦታዎች፣በአርሲ እና ሻሸመኔ ላይ የተፈፀሙት ጥቃቶች በሙሉ ከኦሮምያ ክልል ሚሊሻ እና ቢሮክራሲ የታገዘ ነው።ጥቃቶቹ በእዚህ ብቻ አላቆሙም።በመተከል እና በአጣዬ ሰሜን ሸዋ የተፈፀሙት ጥቃቶች በሙሉ በንፁሃን ላይ የተፈፀሙ የሽብር ጥቃቶች ናቸው።

ከላይ የተፈፀሙት ጥቃቶች በሙሉ በጅምላ በእናቶች እና ሕፃናት ላይ መፈፀማቸው ብቻ ሳይሆን በተደጋጋሚ በዙር የተደረጉ ከመሆናቸው በላይ ፈፃሚዎቹ ላይ በአርሲ እና የሻሸመኔ እንዲሁም ሐረር ላይ ወንጀል የፈፀሙት ታስረዋል፣ምዕራብ ወለጋ ላይ ባለው ሽብርተኛ ቡድን ላይም እርምጃ ተወስዷል እየተባለ ቢነገርም የኦሮምያ ክልልም ሆነ የፈድራል መንግስት ላይ ያሉት ባለስልጣናት ቁርጥ የሆነ እርምጃም ሆነ ጉዳዩን በተገቢው  ሲኮንኑት አይታዩም።ለምሳሌ በያዝነው ሳምንት መጨረሻ በሰሜን ሸዋ አጣዬ  ከተማ ላይ የኦሮምያ ክልል ሚልሻ በሕዝቡ ላይ በቀጥታ በፈፀመው ጥቃት ከ20 በላይ ንፁሃን መገደላቸው መነገሩ ይታወቃል። የሚገርመው ጥቃቱን ያደረሰው የኦሮምያ ክልል መግለጫ ሳይሰጥ እና ክልሉ ምን ዓይነት እርምጃ እንደወሰደ ሳይገልጥ የተጠቃው የአማራ ክልል ነው መግለጫ የሚሰጠው። በተለይ የሰሜን ሸዋው  ጥቃት የብልጥግና ፓርቲ በቶሎ ተሰብስቦ ወሳኝ እርምጃ እንዲወሰድ ካላደረገ የሀገሪቱ ትልቅ የፀጥታ ችግር  እንደሚሆን መረዳት ቀላል ነው። 

አሁን ብልጥግና ጊዜ የለውም።ብልጥግና ብቻ ሳይሆን የመከላከያ ሰራዊቱም በኦሮምያ ክልል ሽብርተኛ አስተሳሰብ የተሟሸ ነው የሚል ስሜት በከፍተኛ ደረጃ በሕዝቡ ውስጥ እየተደመጠ ነው።ይህ አደገኛ የፀጥታ አደጋ ነው። በትናንትናው የአጣዬ ጥቃት ላይ የፌድራል ጦር ከመጣ በኃላ አጥቂውን የኦሮምያ ክልል ሚሊሻ የመውጫ መንገድ መስጠቱ እና ሕግን ከማስከበር ይልቅ የሚዘርፉትን ''የያዛችሁትን ይዛችሁ ሂዱ'' ሲሉ ተመለከትን ያሉ የሰሜን ሸዋ ነዋሪዎች በመንግስት ላይ ከፍተኛ ቅሬታ ተሰምቷቸዋል።

ለማጠቃለል የአማራ ክልል ሕዝብ  እንደሌላው ኢትዮጵያዊ በሕግ እና በመንግስት ላይ ከጥንት የመጣ መተማመን ያለው ሕዝብ ነው። ሕግ ያከብራል፣መንግሥትንም ያከብራል።ለእያንዳንዱ ጉዳይ ምክንያታዊ እና አሳማኝ ነገሮች ይፈልጋል።''በሕግ ከሄደው በሬዬ ያለፍትሕ የሄደችው ዶሮዬ ትቆጨኛለች'' የሚል ሕዝብ የፍትህ እና የመንግስት ሰራዊት አድሎ በእዚህ ደረጃ መገለጡን ከተመለከተ ይወስናል።ውሳኔውን ለማስቀየር ሌላ አንድ መቶ ዓመታት አይበቁም።መንግስት በጊዜው ማሰብ አለበት። የኦሮምያ ክልል ሚሊሻ እና ቢሮክራሲ ውስጥ የተደበቀው የኦነግ መዋቅር እና አስተሳሰብ ለአማራ  ክልል ብቻ ሳይሆን ለአፋር፣ለሱማሌ፣ለደቡብ እና ለትግራይም አደጋ እንደሆነ ሁሉም ያውቃሉ።ስለሆነም በተሰበሰቡበት የብልጥግና ፓርቲ ውስጥ በቶሎ ተሰብስበው መሬት የወረደ ለውጥ ማምጣት አለባቸው።ይህ ካልሆነ የኦሮምያ ክልል ላይ  ሌሎች የብልጥግና ፓርቲ አባላት ግንባር ገጥመው በክልሉ  ውስጥ የበቀለውን የሽብር ቡድን ስርዓት ሊያስይዙት ይገባል። አቶ ሽመልስ እና የክልሉ አስተዳደር ኦሮምያን ማስተዳደር እንዳቃተው በግልጥ መናገር አለበት።ብልጥግና በፍጥነት ተሰብስቦ በኦሮምያ ክልል ላይ ውሳኔ ማሳለፍ አለበት።
********************************
ማስታወቂያ /Advertisement 
====================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

Wednesday, March 17, 2021

ልብ የሚሰብር ዜና - የለውጥ ሐዋርያው የታንዛንያው ፕሬዝደንት ጆን ማጉፉሊ በ61 ዓመታቸው አረፉ።ሙስናን ለመዋጋት ተዓምር ሰርተዋል።፣ታንዛንያ ከምዕራብ ኩባንያዎች ጋር የገባችውን የማዕድን ውል ሀገሪቱን በሚጠቅም መልክ እንዲቀየር እየተጋደሉ ነው ያረፉት።አፍሪካዊ መሪዎቻችንን እናክብር! እንጠብቅ!



ለምዕራባውያን የማዕድን ኩባንያዎች የራስ ምታት ነበሩ።ለታንዛንያ መድሃኒት ነበሩ።በአጭር ጊዜ ተአምራዊ የተሰኘ ለውጥ አምጥተዋል።የስም ማጥፋት ዘመቻ በውጭ ሚድያዎች ተካሂዶባቸዋል።የ''ዎል ስትሪት'' ድረ-ገፅ ከሰዓታት በፊት የዕረፍት ዜናቸውን የዘገበበት ርዕስ አነጋጋሪ ነው።''ከማዕድን ኩባንያዎች ጋር ውዝግብ የገቡት የታንዛንያው ፕሬዝዳንት በ61 አመታቸው አረፉ'' ይላል። ይህ ርዕስ በራሱ የታንዛንያው ፕሬዝዳንት ምን ያህል ለምዕራብ ኩባንያዎች የራስ ምታት እንደነበሩ፣ለታንዛንያ ደግሞ ሩቅ አሳቢ እንደነበሩ አመላካች ነው። 

ፕሬዝደንት ጆን ማጉፉሊ ካለፈው የካቲት ጀምሮ ለሕዝብ አልታዩም ነበር።ፕሬዝዳንቱ ያረፉት በዳሬሰላም ሆስፒታል ሲሆን ለሞታቸው ምክንያት የልብ ህመም መሆኑን የሚናገሩ አሉ።በሌላ በኩል በኮቪድ ምክንያት እንዳረፉም የሚወጡ ዘገባዎች አሉ።የታንዛንያው ምክትል ፕሬዝዳንት በመንግስት ቴሌቭዥን ለሕዝባቸው መርዶውን ካረዱ በኃላ በቀጣይ 14 ቀናት በታንዛንያ የሐዘን ቀን እንደሚሆን እና የሀገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ እንደሚውለበለብ ተወስኗል።
ስለ ፕሬዝዳንቱ ሸገር ራድዮ የዛሬ ሶስት ዓመት በመቆያ ፕሮግራም ያቀረበውን እስከመጨረሻ ያድምጡ።


ከምሥራቅ አፍሪካ መሪዎች የታንዛንያውን ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ ማረፍ በተመለከተ ከተባሉት 








********************************
ማስታወቂያ /Advertisement 
====================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

Monday, March 15, 2021

በ1952 ዓም ኢትዮጵያዊቷ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ብዙአየሁ አጎናፍር ''በጭፍን ጥላቻ (Prejudice)'' ላይ ከህንድ፣እንግሊዝ፣አሜሪካ እና ኖርዌይ ተማሪዎች ጋር በአሜሪካ ያደረገችው ድንቅ ውይይት።(ቪድዮ)1959 High School Students from Ethiopia,Norway,UK,India and USA discussion on Prejudice.

ውይይቱ - 
- በወቅቱ የነበረውን የዓለምንም ሆነ የኢትዮጵያዊ ትውልድ ስሜት  ያሳያል፣
- በወቅቱ የነበረው የሁለተኛ ደረጃ  ኢትዮጵያዊ ተማሪ ብስለት እና ችሎታ ያሳያል።
- የኢትዮጵያን የወቅቱ የትምህርት ደረጃ ያሳያል።
********************************
ማስታወቂያ /Advertisement 
====================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church is in turmoil in Athens, Greece.

His Holiness Abune Mathias I, Patriarch of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, met with Greece's Ambassador to Ethiopia, Antonios Sg...