ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Sunday, March 21, 2021

አቶ ሽመልስ እና የክልሉ አስተዳደር ኦሮምያን ማስተዳደር እንዳቃተው በግልጥ መናገር አለበት።ብልጥግና በፍጥነት ተሰብስቦ በኦሮምያ ክልል ላይ ውሳኔ ማሳለፍ አለበት።



የኦሮምያ ክልል፣ላለፉት ሦስት ዓመታት በተለየ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ክልሎች  ውስጥ የፀጥታ  ችግር ሆኖ ቀጥሏል። ክልሉ በመጀመርያ ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ የገባው ከሱማልያ ክልል ጋር ነበር።በእዚሁ በተነሳው የክልል መስመር ጭቅጭቅ ወደ አንድ ሚልዮን የሚጠጋ ሕዝብ ተፈናቀለ።በመቀጠል በስም ኦነግ ሸኔ እየተባለ ነገር ግን የክልል ሚሊሻ መሆናቸው የተነገረ በጌድዮን ሕዝብ ላይ ጥቃት ፈፀሙ።መቶ ሺዎች ተፈናቀሉ።እናቶች እና ሕፃናት በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ።በእዚህ ብቻ አላበቃም።በምዕራብ ወለጋ በተደጋጋሚ፣በሐረር ደጋማ ቦታዎች፣በአርሲ እና ሻሸመኔ ላይ የተፈፀሙት ጥቃቶች በሙሉ ከኦሮምያ ክልል ሚሊሻ እና ቢሮክራሲ የታገዘ ነው።ጥቃቶቹ በእዚህ ብቻ አላቆሙም።በመተከል እና በአጣዬ ሰሜን ሸዋ የተፈፀሙት ጥቃቶች በሙሉ በንፁሃን ላይ የተፈፀሙ የሽብር ጥቃቶች ናቸው።

ከላይ የተፈፀሙት ጥቃቶች በሙሉ በጅምላ በእናቶች እና ሕፃናት ላይ መፈፀማቸው ብቻ ሳይሆን በተደጋጋሚ በዙር የተደረጉ ከመሆናቸው በላይ ፈፃሚዎቹ ላይ በአርሲ እና የሻሸመኔ እንዲሁም ሐረር ላይ ወንጀል የፈፀሙት ታስረዋል፣ምዕራብ ወለጋ ላይ ባለው ሽብርተኛ ቡድን ላይም እርምጃ ተወስዷል እየተባለ ቢነገርም የኦሮምያ ክልልም ሆነ የፈድራል መንግስት ላይ ያሉት ባለስልጣናት ቁርጥ የሆነ እርምጃም ሆነ ጉዳዩን በተገቢው  ሲኮንኑት አይታዩም።ለምሳሌ በያዝነው ሳምንት መጨረሻ በሰሜን ሸዋ አጣዬ  ከተማ ላይ የኦሮምያ ክልል ሚልሻ በሕዝቡ ላይ በቀጥታ በፈፀመው ጥቃት ከ20 በላይ ንፁሃን መገደላቸው መነገሩ ይታወቃል። የሚገርመው ጥቃቱን ያደረሰው የኦሮምያ ክልል መግለጫ ሳይሰጥ እና ክልሉ ምን ዓይነት እርምጃ እንደወሰደ ሳይገልጥ የተጠቃው የአማራ ክልል ነው መግለጫ የሚሰጠው። በተለይ የሰሜን ሸዋው  ጥቃት የብልጥግና ፓርቲ በቶሎ ተሰብስቦ ወሳኝ እርምጃ እንዲወሰድ ካላደረገ የሀገሪቱ ትልቅ የፀጥታ ችግር  እንደሚሆን መረዳት ቀላል ነው። 

አሁን ብልጥግና ጊዜ የለውም።ብልጥግና ብቻ ሳይሆን የመከላከያ ሰራዊቱም በኦሮምያ ክልል ሽብርተኛ አስተሳሰብ የተሟሸ ነው የሚል ስሜት በከፍተኛ ደረጃ በሕዝቡ ውስጥ እየተደመጠ ነው።ይህ አደገኛ የፀጥታ አደጋ ነው። በትናንትናው የአጣዬ ጥቃት ላይ የፌድራል ጦር ከመጣ በኃላ አጥቂውን የኦሮምያ ክልል ሚሊሻ የመውጫ መንገድ መስጠቱ እና ሕግን ከማስከበር ይልቅ የሚዘርፉትን ''የያዛችሁትን ይዛችሁ ሂዱ'' ሲሉ ተመለከትን ያሉ የሰሜን ሸዋ ነዋሪዎች በመንግስት ላይ ከፍተኛ ቅሬታ ተሰምቷቸዋል።

ለማጠቃለል የአማራ ክልል ሕዝብ  እንደሌላው ኢትዮጵያዊ በሕግ እና በመንግስት ላይ ከጥንት የመጣ መተማመን ያለው ሕዝብ ነው። ሕግ ያከብራል፣መንግሥትንም ያከብራል።ለእያንዳንዱ ጉዳይ ምክንያታዊ እና አሳማኝ ነገሮች ይፈልጋል።''በሕግ ከሄደው በሬዬ ያለፍትሕ የሄደችው ዶሮዬ ትቆጨኛለች'' የሚል ሕዝብ የፍትህ እና የመንግስት ሰራዊት አድሎ በእዚህ ደረጃ መገለጡን ከተመለከተ ይወስናል።ውሳኔውን ለማስቀየር ሌላ አንድ መቶ ዓመታት አይበቁም።መንግስት በጊዜው ማሰብ አለበት። የኦሮምያ ክልል ሚሊሻ እና ቢሮክራሲ ውስጥ የተደበቀው የኦነግ መዋቅር እና አስተሳሰብ ለአማራ  ክልል ብቻ ሳይሆን ለአፋር፣ለሱማሌ፣ለደቡብ እና ለትግራይም አደጋ እንደሆነ ሁሉም ያውቃሉ።ስለሆነም በተሰበሰቡበት የብልጥግና ፓርቲ ውስጥ በቶሎ ተሰብስበው መሬት የወረደ ለውጥ ማምጣት አለባቸው።ይህ ካልሆነ የኦሮምያ ክልል ላይ  ሌሎች የብልጥግና ፓርቲ አባላት ግንባር ገጥመው በክልሉ  ውስጥ የበቀለውን የሽብር ቡድን ስርዓት ሊያስይዙት ይገባል። አቶ ሽመልስ እና የክልሉ አስተዳደር ኦሮምያን ማስተዳደር እንዳቃተው በግልጥ መናገር አለበት።ብልጥግና በፍጥነት ተሰብስቦ በኦሮምያ ክልል ላይ ውሳኔ ማሳለፍ አለበት።
********************************
ማስታወቂያ /Advertisement 
====================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

No comments:

የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...