ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, March 2, 2021

ሰበር ዜና - ግብፅ እና ሱዳን እርስ በርስ የመደጋገፍ ወታደራዊ ውል ዛሬ ተፈራረሙ።የአፍሪካ ቀንድን እና ቀይባሕርን ለመጠበቅ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግንኙነታቸውን ወደ የጋራ ወታደራዊ፣ምጣኔ ሃብታዊ እና የውጪ ፖሊሲ ውል ማሳደግ ይገባቸዋል።


የግብፅ ወታደራዊ የጦር ቺፍ ኦፍ ስታፍ  ሞሃመድ ፋሪድ እና የግብፁ አቻቸው መሐመድ ኦትማን አል-ሁሴን በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ከስምምነቱ በኃላ ሲጨባበጡ (Photo-AFP)

ግብፅ እና ሱዳን ወታደራዊ የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ ፡፡ዛሬ ማክሰኞ የካቲት 23/2013 ዓም ግብፅ እና ሱዳን የመከላከያ ትብብር ስምምነት የተፈራረሙ ሲሆን የሁለቱ አገሮች ስምምነት ለኢትዮጵያ በተለይ በዓባይ ግድብ አንፃር ሁለቱም ባላቸው ስልታዊ ግንኙነት አንፃር ይህ ስምምነት ትልቅ ማስጠንቀቅያ እንደሆነ አያጠራጥርም።

የሱዳኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ማርያም አል-ሳዲቅ አልማሃድ  ማክሰኞ  ከግብፅ አቻቸው ሽክሪ ጋር በካይሮ ተገናኝተው የተመለሱ ሲሆን ሁለቱም ሀገሮች በኢትዮጵያ የዓባይ ግድብ ውይይት ላይ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንዲገባበት ለማድረግ ጥረታቸውን ለማጠናከር ተስማምተዋል።የግብፁ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትርም በጣም በቅርቡ ወደ ሱዳን እንደሚመጡ ተሰምቷል።የሱዳን እና የግብፅ ወታደራዊ ውል የተፈፀመው ሁለቱ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች በዓባይ ጉዳይ ላይ በጋራ ከመከሩ በኃላ መሆኑን የግብፅ ዜና አውታሮች ዘግበዋል። በሁለቱ ሀገሮች የጦር ኃይል እታማዥር ሹም (ቺፍ ኦፍ ስታፍ) ስምምነቱ ከተፈረመ በኃላ የሱዳኑ እታማዥኦር ሹም ጀነራል መሐመድ ኡትማን አል ሁሴን ሲናገሩ ''የግብፅ ጦር ኃይል ወንድሞቻችን ላደረጉልን የልግስና ስጦታ እና አሁን የገጠሙንን ችግሮች ለመጋፈጥ ላደረጉልን ድጋፍ ሁሉ እናመሰግናቸዋለን''ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እያለ የሱዳን እና የግብፅ ወታደራዊ ስምምነት ኢትዮጵያ እና ኤርትራም በቶሎ ግልጥ ወደ ሆነ ወታደራዊ ስምምነት ውስጥ መግባት እንዳለባቸው የሚያሳስቡ ብዙዎች ናቸው።የግብፅ እና የሱዳን ስምምነት ጀርባ ያሉ የቅርብም ሆኑ የሩቅ ሀገሮች እንደሚኖሩ መገመቱ ቀላል ነው።የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ የህዝብ ብዛት ያላት ማለትም ከአንድ መቶ ሚልዮን በላይ ሕዝብ ያላት ኢትዮጵያ በቀይባሕር ዙርያ የሚደረገው የውጪ ጣልቃ ገብነት አያሳስባትም ማለት አይቻልም።ኤርትራም በሱዳን እና በግብፅ ጥምረት አንፃር ፈጥኖም ይሁን ዘግይቶ የጥቃቱ ኢላማ እንደሆነች የታወቀ ነው።ለእዚህ አላማ ግን መጀመርያ ሁለቱን ሀገሮች በተናጥል ላማጥቃት ቀዳሚ ስልት ሊሆን ይችላል።በትግራይ የተደረገው የሕግ ማስከበር ሂደት በስኬት መጠናቀቁ እና የኢትዮጵያ እና የኤርትራ የእርስ በርስ መናበብ በፍርሃት ያራዳቸው ግብፅ እና ሱዳን ቀደም ብለው የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ሲያደርጉ ነበር የሰነበቱት።

ኢትዮጵያ ለዓመታት በእርስ በርስ ግጭት ከመዳከም ቀና የምትልባቸው ጊዜዎች እንደመጡ የተረዱ ጠላቶቿ ከአሁኑ ለመኮርኮም ሽር ጉድ ላይ ያሉ ይመስላል።ኢትዮጵያ በዓባይ ግድብ ሙሌት ብቻ አይደለም የፈሯት።የጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ መንግስት ከ250 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት በመስኖ ዘንድሮ ማልማቱ የሃገራቱ እራስ ምታት ሆኗል።ይህ ብቻ አይደለም ኢትዮጵያ የመጪው የአፍሪካ ቱሪዝም ተደራሽ መሆኗ ግብፅ ምጣኔ ሀብቷን  የሚደጉመው ቱሪዝም ወደ ኢትዮጵያ ይፈሳል ብላ ስጋት አላት።ኢትዮጵያ በዓባይ ግድብ ላይ የሚኖራት በርካታ ደሴቶች፣የጎርጎራ፣ኮይሻ እና ወንጪ ልማቶች ከፍተኛ ቱሪስት ወደ ኢትዮጵያ እንዲፈስ እንደሚያደርግ ግብፆች ገብቷቸዋል።ቱሪስት ደግሞ ከደረቃማ ቦታዎች የኢትዮጵያን በአእዋፋት እና ደኖች የተከበበ ስፍራዎችን እንደሚመርጡ የታወቀ ነው። 

ከአንድ ሺህ ኪሎሜትር በላይ የሚሆን ክልል የሚያካልለው የቀይ ባሕር ካለው እጅግ ስልታዊ የንግድ መተላለፍያ መስመርነቱ አንፃር ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በወታደራዊ መስክ ከተስማሙ ባዕዳን የመግባት ዕድላቸው ስለሚጠፋ ኢትዮጵያን ሳትነሳ ለማድከም ይታሰባል።ኢትዮጵያን የማድከም ሙከራው በተለይ በግብፅ በኩል ከግማሽ ክፍለ ዝመን በላይ የዘለቀ ሲሆን የእስካሁኑ ሙከራ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ በመግባት ኢትዮጵያን እርስ በርስ ማጋጨት ነበር። አሁን ኢትዮጵያ የውስጥ ግጭቷን ቢያንስ በታጠቀ ኃይል እየጠፋ ሲሄድ እራሳቸው ለመምጣት የሚያስቡ ይመስላል።የኢትዮጵያ ሕዝብ አይደለም እንደዛሬ በአጭር መገናኛ እየተገናኘ ቀርቶ ቀድሞም በእግሩ እየሄደ ሃገሩን ለባዕዳን አሳልፎ ሰጥቶ አያውቅም።አሁን ግን ከጀግንነት ባለፈ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መሪዎች በጊዜ ግልጥነት ያለበት የእርስ በርስ ወታደራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ግንኙነት እና ጥምረት በፍጥነት መፈፀም አለባቸው።በኢትዮጵያ ያለው የፀጥታ ችግር ኤርትራን የማይመለከት፣በኤርትራ እና ቀይባህር ያለው የባዕዳን ጣልቃ ገብነት ኢትዮጵያን የማይመለከት አድርጎ ማሰብ አይቻልም።ይህንን ሁኔታ ለመረዳት የኢትዮጵያን ያለፉትን አንድ መቶ ዓመታት ታሪክ መመልከት ብቻ በቂ ነው።ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በፍጥነት በግንኙነታቸው ላይ በተለይ በወታደራዊ፣ምጣኔ ሃብታዊ እና የውጪ ፖሊስ ላይ የተናበበ ስምምነት ማድረጋቸው የጋራ ህልውናቸው መሰረት ነው።ኢትዮጵያም በባህር ኃይል በኩል አመርቂ ስራዎች እየሰራች እንደሆነ ይሰማል።የባህር ኃይል አዛዥ፣ምክትል አዛዥ እና የአስተዳደር አካል ሙሉ በሙሉ ሥራ የጀመረ ሲሆን የማዘዣ ጣብያውንም በጊዜያዊነት አደራጅቷል።ከእዚህ በተጨማሪ  በአሁኑ ጊዜ በሩስያ፣ቻይና እና ፈረንሳይ ውስጥ ቁጥራቸው ከፍ ያለ ኢትዮጵያውያን የባህር ኃይል ባለሙያዎች በመሰልጠን ላይ እንዳሉ  የኢትዮጵያ ጦር ኃይል ኢታማዥኦር ሹም ጄኔራል ባጫ ደበሌ ለባላገሩ ቴሌቭዥን የቀድሞ ጦር ሰራዊት ሚድያ ዝግጅት በቅርቡ በሰጡት ቃለ ምልልስ ገልጠዋል።  

*******************
ማስታወቂያ /Advertisement 
====================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ? 
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ - 

No comments:

ሐያ ገዳማት የሚገኙበት በግሪክ የሚገኘው የአቶስ ተራራ ገዳማውያን አኗኗር (ቪድዮ)

ገዳሙ ከሰርብያ፣ሮማንያ፣ቡልጋርያና ሩስያ የመጡ ዓለምን የናቁ መነኮሳት ገድመውበታል።