ለምዕራባውያን የማዕድን ኩባንያዎች የራስ ምታት ነበሩ።ለታንዛንያ መድሃኒት ነበሩ።በአጭር ጊዜ ተአምራዊ የተሰኘ ለውጥ አምጥተዋል።የስም ማጥፋት ዘመቻ በውጭ ሚድያዎች ተካሂዶባቸዋል።የ''ዎል ስትሪት'' ድረ-ገፅ ከሰዓታት በፊት የዕረፍት ዜናቸውን የዘገበበት ርዕስ አነጋጋሪ ነው።''ከማዕድን ኩባንያዎች ጋር ውዝግብ የገቡት የታንዛንያው ፕሬዝዳንት በ61 አመታቸው አረፉ'' ይላል። ይህ ርዕስ በራሱ የታንዛንያው ፕሬዝዳንት ምን ያህል ለምዕራብ ኩባንያዎች የራስ ምታት እንደነበሩ፣ለታንዛንያ ደግሞ ሩቅ አሳቢ እንደነበሩ አመላካች ነው።
ፕሬዝደንት ጆን ማጉፉሊ ካለፈው የካቲት ጀምሮ ለሕዝብ አልታዩም ነበር።ፕሬዝዳንቱ ያረፉት በዳሬሰላም ሆስፒታል ሲሆን ለሞታቸው ምክንያት የልብ ህመም መሆኑን የሚናገሩ አሉ።በሌላ በኩል በኮቪድ ምክንያት እንዳረፉም የሚወጡ ዘገባዎች አሉ።የታንዛንያው ምክትል ፕሬዝዳንት በመንግስት ቴሌቭዥን ለሕዝባቸው መርዶውን ካረዱ በኃላ በቀጣይ 14 ቀናት በታንዛንያ የሐዘን ቀን እንደሚሆን እና የሀገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ እንደሚውለበለብ ተወስኗል።
ስለ ፕሬዝዳንቱ ሸገር ራድዮ የዛሬ ሶስት ዓመት በመቆያ ፕሮግራም ያቀረበውን እስከመጨረሻ ያድምጡ።
ከምሥራቅ አፍሪካ መሪዎች የታንዛንያውን ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ ማረፍ በተመለከተ ከተባሉት
********************************
ማስታወቂያ /Advertisement
====================
Click the link below to Top-up your friends or family's mobile air time.
በአንድ ደቂቃ ውስጥ በሀገር ቤት የሚኖር የቤተሰብ ወይንም የወዳጅዎን ስልክ ሂሳብ ሊሞሉ እንደሚችሉ ያውቃሉ?
አገልግሎቱን ለማግኘት ከስር ሊንኩን ይጫኑ -
No comments:
Post a Comment