Friday, February 28, 2020

በፋሽሽት ጣልያን ወረራ ወቅት የሴት አያቷን የጦር ግንባር ታሪክ የፃፈችው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አሜሪካዊት መዓዛ መንግሥቴ መፅሐፍ ''ዘ ሻዶው ኪንግ '' (The Shadow King) አድናቆት አትርፏል።

ጉዳያችን ሚድያ፣ኮሚኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት 
Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant

ደራሲ መዓዛ መንግሥቴ (Photo New York Times, Nina Subin)

መዓዛ መንግሥቴ ትባላለች።አያቷ ጣልያን ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት ያደረጉትን ተጋድሎ ኢትዮጵያ ድረስ መጥታ የጦርነቱን ቦታዎች ተመልክታለች።እናቷ ከአያቷ የሰሙትን እያንዳንዱን መራር ተጋድሎ ከትባዋለች።መትሽፉ የወጣው በእዚህ ዓመት መስከረም ወር ነው።

''ታሪኩ ለራሴ የመሰጠኝ፣ያስገረመኝ ነው።አያቴ ወደ አርበኝነት ስትሄድ የአባቷን ጠበንጃ ይዛ ነበር።'' ያለችው መዓዛ መፅሐፉ የአፍሪካውያን ሴቶች ተጋድሎ ኩራት ማሳያ መሆኑን ያስመሰከረ ተብሏል።መዓዛ ከእዚህ በፊት በጥር 2010 ዓም እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር  ''Beneath the Lion's Gaze'' የተሰኘ መፅሐፍ በ1966 ዓም በነበረው የኢትዮጵያ አብዮት ወቅት የሚተርክ መፅሐፍ ፅፋ ነበር።

''ዘሻዶው ክንግ'' የተሰኘው መፅሐፍ በአሁኑ ጊዜ በአማዞንም ጭምር እየተሸጠ ሲሆን አማዞን መፅሐፉን ሲያስተዋውቅ ስለመፅሐፉ የለጠፈው ፣ስለመፅሐፉ ይዘት በሚገባ ያስረዳል።

A gripping novel set during Mussolini’s 1935 invasion of Ethiopia, The Shadow King takes us back to the first real conflict of World War II, casting light on the women soldiers who were left out of the historical record.
With the threat of Mussolini’s army looming, recently orphaned Hirut struggles to adapt to her new life as a maid in Kidane and his wife Aster’s household. Kidane, an officer in Emperor Haile Selassie’s army, rushes to mobilize his strongest men before the Italians invade. His initial kindness to Hirut shifts into a flinty cruelty when she resists his advances, and Hirut finds herself tumbling into a new world of thefts and violations, of betrayals and overwhelming rage. Meanwhile, Mussolini’s technologically advanced army prepares for an easy victory. Hundreds of thousands of Italians―Jewish photographer Ettore among them―march on Ethiopia seeking adventure.
As the war begins in earnest, Hirut, Aster, and the other women long to do more than care for the wounded and bury the dead. When Emperor Haile Selassie goes into exile and Ethiopia quickly loses hope, it is Hirut who offers a plan to maintain morale. She helps disguise a gentle peasant as the emperor and soon becomes his guard, inspiring other women to take up arms against the Italians. But how could she have predicted her own personal war as a prisoner of one of Italy’s most vicious officers, who will force her to pose before Ettore’s camera?
What follows is a gorgeously crafted and unputdownable exploration of female power, with Hirut as the fierce, original, and brilliant voice at its heart. In incandescent, lyrical prose, Maaza Mengiste breathes life into complicated characters on both sides of the battle line, shaping a heartrending, indelible exploration of what it means to be a woman at war.



ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

Wednesday, February 26, 2020

Gudayachn replied to David Pilling's opinion, issued in Financial Times, under the title of ''Why Abiy Ahmed is more popular in Norway than in Ethiopia'', Feb.26, 2020.



David Pilling (picture FT)

ጉዳያችን ሚድያ፣ኮሚኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት
Gudayachn Multimedia, 
Communication and Consultant 


To: David Pilling
david.pilling@ft.com
      Financial Times


Dear Sir, David, first of all, I would like to thank you for your opinion on Financial Times, under the title of Why Abiy Ahmed is more popular in Norway than in Ethiopia, posted two hours back as of today February 26,2020. 

Fortunately, my origin is from Ethiopia and follows the day to day political situation of the country. On the other hand, I am also living in Oslo and got the chance to attend the recent remarkable Nobel Prize ceremony of the Prime Minister Abiy  in Oslo city hall.

As far as I understand the situation in Ethiopia is quite different from your mentioned sources. In fact the nation is in a real change. But the change process is not so spontaneous like that had happened in 1974 of the  mass revolution and the rebel control of the capital Addis Ababa in 1991. The current political change is big reform but going so slow without dropping the vital political,economic and social values of the ancient and historical nation, Ethiopia. Africa has a good experience in losing valuable assets of social, peace and stability. That is through running a political change process that could abolish all human and capital resources, just through categorizing all former political actors  under the name of ''former regime''. As far as I understand the current political movement of Abiy is attempting a new path of political thinking called MEDEMER.

Abiy’s  introduction of MEDEMER is quite a new phenomena to Africa.In the last two years, since the reform was launched, all political parties could get into the country and move freely. In fact, before them,all political prisoners were released and all media who had been  exiled could be functional in Ethiopia’s territory which was unthinkable even three years ago.

Here I can realize that your source of information is from the extremist group like you mentioned, Jawar Mohamed as a commentator. I think you need to dig a little bit, at least, to visit google about such a person's negative contribution for the security and social cost of the current generation of Ethiopia both at home and abroad. I think also, it is quite a good indicator to know the reason why over One-Hundred fifty thousand people signed a petition against Jawar Mohamed, that is only for the past 18 months. I am not feeling comfortable, when a political commentator like you quote, Jawar, as a reference source of the peace and security of the nation with over one-hundred million people. That is Ethiopia. 

Ethiopia’s current immediate problem is ethnocentric politics running by individuals and activists like you have mentioned, Jawar Mohamed. This politics is not only dangerous to Ethiopia but also for the horn of Africa. It is not even a week since Jawar's idea of ethnocentric politics was seriously criticized by a senior political advisor of Eritrea, Yemane G.Meskel. Yemane, on his reply to Jawar’s tweeter, just three days back on February 22,2020 reads as -

"Our position is not ambivalent.  We strongly believe that the policy of institutionalized ethnicity is toxic & obsolete.  In our view, eradication of this malaise will serve the best interests of Ethiopia. Furthermore, Eritrea & the whole region will benefit from this."

That is why I am saying there is a big information gap between you and the real political situation in Ethiopia. In addition to that, I need to remind you that  your opinion has totally disregarded the recent three consecutive weeks Pro-Abiy demonstrations in over Eight major cities in Ethiopia. 

In general, your opinion needs a big update in the current political situation of Ethiopia. Rather it is based on one sided view of the country. I think you need to see the other side too.

With Best Regards

Getachew Bekele Damtew
E-mail = getachewb221@gmail.com

Editor ጉዳያችን ሚድያ፣ኮሚኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት
Gudayachn Multimedia, 
Communication and Consultant 

Tuesday, February 25, 2020

ሰበር ዜና - የጣልያን መከላከያ ሚኒስትር ሎረንዞ ጐርኒ፣ ፋሺሽት ጣልያን በደብረሊባኖስ መነኮሳት ላይ ለፈፀመችው ጭፍጨፋ አገራቸው ታሪካዊ ተጠያቂነቷን ማመን አለባት አሉ። ቦታውን ሄጄ ለማየት ወስኛለሁ ብለዋል።


====================
ጉዳያችን ሚድያ፣ኮሚኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት 
Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant
=====================


የጣልያን መከላከያ ሚኒስትር ሎረንዞ ጎርኒ  Lorenzo Guerini 

የጣልያን መከላከያ ሚኒስትር ሎረንዞ ጎርኒ  Lorenzo Guerini ዛሬ የካቲት 17/2012 ዓም ጣልያን ውስጥ በሰጡት መግለጫ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1937 ዓም ከግንቦት 21 እስከ 29 በኢትዮጵያ ደብረ ሊባኖስ ገዳም የፋሺሽት ወታደሮች የፈፀሙትን አሰቃቂ ጭፍጨፋ ጣልያን በታሪክ ተጠያቂ የሆነችበት መሆኑን ማመን እንዳለባት ገልጠዋል።


ሚኒስትሩ የጳውሎ ቦሩሶ Paolo Borruso ''ደብረ ሊባኖስ በ1937'' የተሰኘውን መፅሐፍ ጠቅሰው ጣልያን በዘመኑ ከሰራችው ከባዱ የጦር ወንጀል ውስጥ የደብረ ሊባኖሱ እልቂት መሆኑን አብራርተዋል።ዜናውን የዘገበው የጣልያን ዜና አገልግሎት አንሳ (ANSA) እንደገለጠው በደብረ ልባኖሱ እልቂት ሰማዕትነት የተቀበሉት የገዳሙ መነኮሳት 449 ናቸው ቢባልም እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1990 ዓም በተገኘ አዲስ ጥናት የተገደሉት ሰማዕታት መነኮሳት ቁጥር ከ1500 እስከ 2000 እንደሚደርስ ዛሬ ማምሻው ባወጣው ዘገባ ለመረዳት ተችሏል። 


ጉዳያችን GUDAYACHN 

 www.gudayachn.com

የድንግል ማርያምን ዘላለማዊ ድንግልና እና የስላሴን ምስጢር የሚነቅፍ አስተያየት በፌስ ቡክ ገፁ ከሶስት ዓመት በፊት የፃፈው ስፔናዊ አርቲስት በስፔን ክርስቲያን ጠበቆች ማኅበር በያዝነው ወር ፍርድ ቤት ተከሰሰ።

====================
ጉዳያችን ሚድያ፣ኮሚኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት 
Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant
=====================
ዊሊ  ታሌዶ (Willy Toledo)


ዊሊ  ታሌዶ (Willy Toledo) ይባላል።49 ዓመቱ ነው።ስፔን ውስጥ ታዋቂ አክተር እና አክቲቪስት ነው።በፌስ ቡክ ገፁ የፈለገውን ሲጥል ሲያነሳ አንድ ቀን የማይገባ ስድብ በድንግል ማርያም ላይ እና በሥላሴ ሶስትነት እና አንድነት ላይ  ይፅፋል። ከእዚህ በፊት የስፔን ፍርድ ቤት ተከሶ ሁለት ጊዜ ችላ ብሎት ሳይቀርብ ቀርቷል።ይህንንም ተከትሎ  ታዋቂ አክተር እና አክቲቪስት በመሆኑ ከፍርድ በላይ ሊሆን አይገባም፣የኅብረተሰባችንን ስነ ልቦና የሚቃረን እና እምነታችንን የሚያጥላላ ፅሁፍ ፅፏል፣በአንደበቱም ተናግሯል በማለት የስፔን ክርስቲያኖች ጠበቃ ማኅበር በያዝነው የካቲት/2012 ዓም መልሶ ፍርድ ቤት ከሶታል።

ተከሳሹ ''የመናገር እና ሃሳብን የመግለጥ መብቴን ተጠቅሜ ነው የፃፍኩት፣ልከሰስ አይገባም'' ቢልም በማድሪድ ከተማ በሚገኘው 26ኛው የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ክሱ እየታየ ነው።እአአቆጣጠር ሐምሌ 5፣2017ዓም በፌስ ቡክ ገፁ በፃፈው አስተያየት በወቅቱ ክስ ተመስርቶበት አንዳንዶች ታዋቂ አክተር እና አክትቪስትነቱን ተጠቅሞ ፍርድ ቤት ለመቅረብ ያንገራገረው ዊሊ  ታሌዶ፣ የስፔን ክርስቲያን ጠበቆች ማኅበር እንደገና በያዝነው ወር ክሱን ስላንቀሳቀሰው ጭንቀት ላይ ነው።

''ወንጀል የሚባለው የወንጀል ተግባር ነው እንጂ እንዴት ቃላትን ወንጀል ብላችሁ ትከሱኛላችሁ?'' በማለት ለፍርድቤቱ ከጠበቃው  አንዲካ ዙሉታ (Endika Zulueta) ለተነሳለት ጥያቄ መልስ የሰጠው አክተር፣ ፅሁፉን መፃፉን አምኖ ጉዳዩን ከስፔን የዲሞክራሲ አገር መሆን አለመሆን ጋር ለማያይዝ ሞክሯል።ፍርድ ቤቱ ግን ስሞታውን አልተቀበለውም።በሕግ ጉዳይ የእዚህ ዓይነት የክስ ጉዳዮች እና ሂደታቸው አስተማሪ ብቻ ሳይሆኑ ተመሳሳይ ሕጎች መውጣት እንዳለባቸው አስተማሪ እንደሚሆኑ ይታመናል።

በነገራችን ላይ ፣አውሮፓ የሃይማኖት ዶግማ ነቅፈው የሚፅፉ እንዲህ ይከሰሳሉ።ገዳማትን እየነቀፉ የምርጫ ቅስቀሳ የሚያደርጉት ያልተከሰሱባት የኢትዮጵያ ጉዳይስ? በቅርቡ በሰሜን ሸዋ የኦሮሞ ፌድራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) የደብረ ሊባኖስን ገዳም አስመልክቶ የተነገሩት አገር ከፋፋይ ዘረኛ ንግግሮች እንዴት ታለፉ?በእርግጥ የኢትዮጵይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ የሐሰት ዜና የሚነዙ ሚድያዎች ላይ ክስ መስርቷል።ይህ እንዳለ ሆኖ ግለሰቦችም በተለይ በእምነት ጉዳይ እያስታከኩ የሌላውን እምነት የሚያጥላሉ ለሕግ መቅረብ እንዳለባቸው የአውሮፓው ተሞክሮ ያመላክተናል።

ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

Monday, February 24, 2020

በታላቁ የዓድዋ በዓል አከባበር ላይ በሰውኛ ፕሮዳክሽንና ኢንተርቴይንመንት ውስጥ ሕይወት የዘሩ አርቲስቶች - ሚካኤል ሚልዮን እና ባለቤቱ መዓዛ ታከለ

ጉዳያችን ሚድያ፣ኮሚኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት 
Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant

  • በእዚህ ፅሁፍ ስር የሳምንቱን የዝክረ ዓድዋ በዓል መርሐግብር ያገኛሉ 

ፎቶ -አርቲስት ሚካኤል ሚልዮን እና መዓዛ ታከለ በጣይቱ ሆቴል ስለ ዝክረ ዓድዋ መግለጫ ሲሰጡ።
(ከአርት ቲቪ የተወሰደ )

''የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የመላው ዓለም ድል ነው።ድሉ የሰውን ልክ ያገኝ፣ ቅኝ ገዢዎች ከአላስፈላጊ ትዕቢት ዝቅ ብለው በሰው መጠን እንዲኖሩ፣ለጥቁሮች ደግሞ ራስን ዝቅ አድርጎ ከመመልከት ወጥተው በሰው እኩል መሆናቸውን ያሳዩበት ታላቅ ድል ነው።ይህ ማለት ሁሉንም የሰው ማዕረግ ያስተካከለ ድል ነው''
ይህንን የተናገረችው የአርቲስት ሚካኤል ሚልዮን ባለቤት አርቲስት መዓዛ ታከለ ነች።አርቲስት መዓዛ፣ አርቲስት ሚካኤል ሚልዮን እና ሌሎች አጋሮች ጋር ሆነው ''ሰውኛ ኢንተርቴይመንት'' የተባለ ድርጅት መስርተዋል።ሰውኛ ከሚሰራቸው የኪነጥበብ ፈጠራዎች በተጨማሪ የዓድዋ በዓል መልክ ባለው እና ዘመኑን በሚዘክር ደረጃ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ማክበር ነው።ላለፉት አራት ዓመታት በተከታታይ የዓድዋ በዓልን ድምቀት በመስጠት ብቻ ሳይሆን ለትውልዱ ከአዕምሮ በማይጠፋ ደረጃ ለማስቀረት አርቲስቶቹ ትልቅ አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ ናቸው።

ከወንዶች ጉዳይ አዝናኝ ፊልም ጀምሮ በልዩ ልዩ የፊልም እና የመድረክ ስራዎቻቸው  የምናውቃቸው አርቲስት  ሚካኤል ሚልዮን እና መዓዛ ታከለ በሰውኛ  ፕሮዳክሽንና ኢንተርቴይመንት ለአራተኛ ጊዜ በሚከበረው የዓድዋ በዓል ላይ ዛሬ በወመዘክር የመክፈቻ መርሃግብሩን በርካታ ታዳሚ በተገኘበት ያስጀመሩ ሲሆን በቀጣይ ቀናት እስከ በዓሉ ማለትም የካቲት 23/2012 ዓም ድረስ የተለያዩ መርሃግብሮች አሏቸው።ከመርሃግብሩ ውስጥ የአድዋ በዓል ዕለት ከምኒልክ አደባባይ እስከ አድዋ ድልድይ ድረስ የሚኖረው የባዶ እግር ጉዞ እና የአድዋ ዘማቾች የሚያስታውስ የጎዳና ትዕይንት እና በእዚሁ እለት ቀትር ላይ በእንጦጦ የዳግማዊ ምንሊክ ቤተ መንግስት የንጉሱን የግብር ማብላት ስነስርዓት በጠበቀ መልኩ የሚዘጋጅ የምሳ ፕሮግራም የብዙዎችን ትኩረት የሳበ እና በአዲስ ትውልድ ውስጥም የማይጠፋ አሻራ የሚያኖር ነው።

ሰውኛ ፕሮዳክሽንና ኢንተርቴይንመንት በእዚህ ሳምንት እና እስከ በዓሉ ድረስ በአዲስ አበባ ያዘጋጃቸውን መርሐግብሮች ከእዚህ በታች ይመልከቱ።
የአርት ቲቪ ዝግጅቶቹን አስመልክቶ ያወጣው ማስታወቂያ 
ምንጭ - አርት ቲቪ ቪድዮ 




ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

Friday, February 21, 2020

Eastern part of Ethiopia, Harar christians need protection.


ጉዳያችን ሚድያ፣ኮሚኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት 
Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant

Abune Mekarios, Member of Ethiopian Orthodox Tewahedo church Holy Synod and Archbishop of Ethiopian-Somali region and East Hararge, Amharic press release on January 29,2020 explained the situation in Eastern Ethiopia, Hararge. Here under is the main content of the press release.


Abune Mekarios


Abune Mekarios Press release 
In the name of the Father, and of the Son, and of the Holy Spirit, Amen. 
Between January 19 and January 22, 2020,  Christians were physically attacked, properties of four Christians were destroyed, 17 Christians were unfairly arrested; 246 Christians are displaced from their homeland and fled to Debre Adhano St Gabriel Church in Harar after being physically attacked, robbed and received  death threats. We want all human beings to stand up for justice. Harrar is not a city that belongs to only a small group of people, but it is for all Ethiopians. 


For those who were attacked by the police that were supposed to serve everyone without prejudice, those who were arrested even after being attacked by people who are now walking free - we want you to remain strong for your sufferings shall be counted as good deeds in the eyes of the Lord. Like our forefathers passed through times of hardships by keeping their faith, we are certain that nothing will stop you from doing the same. Christianity is always about victory over challenges, not a guarantee to a temporary satisfaction. The latest attack on Christians is no different from what the wicked emperors had done against our forefathers. You undeniably have more to gain by enduring challenges like our forefathers did. 


Even though organized mobsters with irresponsible security police officers attempted to incite you to engage in violence and chaos, you remained patient and strong. By so doing, you have proved how strong Christians are, even during trying times. And be happy for what you did (for your patience and restraint).


It is not possible to live a peaceful life while publicly discriminating Christians. Bearing this in mind, we want the government to evaluate its system once again and stop these irresponsible government officials, who are attempting to advance their hate filled agenda and are attempting to impose their belief (on Christians), from committing such acts. 

The police must serve all citizens despite their background and religion and impartially, without prejudice. However, the latest attacks targeted against our church reveals that the reality on the ground is different. Since it is challenging to live a peaceful life while persecuting others (Christians), we want the government to ensure such acts (of terror) won’t happen again and to take the necessary preventive measures before it gets worse.

We request the government bring to justice the groups and individuals that are trying to incite violence between communities that are living in harmony and peace. The fact is that the perpetrators of these heinous attacks are being released, while Christians who were victims of these atrocities are still being arrested. We call for the end of such (blatant) acts.

Even though some commendable actions have been taken by the regional government which announced it has arrested the mobsters who were behind the recent attacks, such acts (arresting the innocent and releasing the perpetrators) however is nothing different from arresting Christ while releasing Barabbas. 

We were happy that the United Nations Educational Scientific and Cultural Organization (UNESCO) passed a resolution to add Ethiopian Epiphany to the list of World Intangible Cultural Heritages. On the other hand, the attempt to take over a place of religious festivals of Orthodox followers and replace it with another one is very depressing. We call for the end of such actions.  

Like other religions that celebrate their sacred festivals peacefully without being attacked, we want to urge the government to do the same to all Christians without prejudice. As long as followers of Christians are being victims to violence and attacks... we will continue demanding for the respect of our rights. We also want to make it clear that we will hold a demonstration to denounce the recent attacks soon. 

We once again denounce the acts of the regional government’s actions of arresting innocent Christians, while releasing mobsters. And, we call upon the Christian youth to be organized and defend their faith from anymore attack and collect the necessary evidence if any additional acts are committed by mobsters against churches to bring those perpetrators to justice. 


God Bless Ethiopia, God Bless the World.








Wednesday, February 12, 2020

የኢትዮጵያ ወቅታዊ ፖለቲካ ድምፅ የሚሰማባቸው ሰፈሮች ወቅታዊ ገፅታ

ጉዳያችን/ Gudayachn
የካቲት 5፣2012 ዓም (ፈብሯሪ 13/2020 ዓም)
================
በእዚህ ፅሁፍ ውስጥ በሚከተሉት ርዕሶች ስር ፅሁፎች ያገኛሉ። እነርሱም - 

- የካቲት ወር በ1909 ዓም ፣
-  የካቲት ወር በ2012 ዓም፣
- ኢትዮጵያና ዓለም አቀፍ ኮርፖሬሽኖች፣
- ብልፅግና  ፓርቲ የጀዋርን ቡድን የማቅጠን ሂደቱን  አጠናክሮ በግልጥም በስውርም ቀጥሏል፣
- የብልፅግና ፓርቲ የገጠመው ትልቁ ተግዳሮት ፣
-  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ለኢትዮጵያ ፀጥታ ወሳኝ ጉዳይ ነው፣
- እግዚአብሔርን የማይፈሩ፣ሰውን የማያፍሩት የህወሓት አመራሮች ጉዳይ፣
- ቴዲ አፍሮ በመጪው ሳምንት በመስቀል አደባባይ
 ===============================
የካቲት ወር በ1909 ዓም

በ1909 ዓም የዳግማዊ ምንሊክ ሴት ልጅ ንግስት ዘውዲቱ በየካቲት 4 ቀን ዘውድ ደፉ።በእዚሁ ዓመት ራስ ተፈሪ የንግስትቱ ሞግዚትና አልጋ ወራሽ እንዲሆኑ ተሾሙ።የንግሥት ዘውዲቱ ወደ ንግስና መምጣት በልጅ ኢያሱ ዘመን የነበረው ሹክቻ እና ብጥብጥ የሚቆምበት በመሆኑ ህዝቡ መደሰቱ ይነገራል።ከንግስት ዘውዲቱ ንግስና በኃላም የኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ በአንፃሩ የተረጋጋ መልክ ቢያሳይም በመሬት ባላባቱ የጦር አበጋዞች እና ትምህርት ቀመስ በሆኑ ወጣት የሹማምንቱ ልጆች መሃል ልዩነት ፈጥሮ ነበር።በወቅቱ በዘመናዊ ትምህርት የተሻሉ የነበሩት እና የውጪውን ዓለም በተለይ ስለ አውሮፓ ስልጣኔ የተሻለ ግንዛቤ የነበራቸው የቀድሞው ራስ ተፈሪ (የኃላው ቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ) ይደገፉ የነበሩት በወቅቱ በነበሩ ጥቂት ዘመናዊ ትምህርት ቀመስ ወጣቶች  ሲሆኑ እነኝህ ወጣቶች ንግስት ዘውዲቱ ከነገሱም በኃላ የኢትዮጵያ ጉዳይ ያስጨንቃቸው ነበር።

በወቅቱ የሚጨነቁት ወጣቶች ዋና ምክንያታቸው 20ኛው ክፍለዘመን ከመግባቱ ጋር በአውሮፓ የነበረውን እንቅስቃሴ ከሌላው ባላባት በተሻለ ማወቃቸው ነበር።በንግሥት ዘውዲቱ ዘመን ያለው የአውሮፓ ቅኝ ገዢዎች አመጣጥ በአድዋ እንደነበረው ዓይነት አይደለም።በንግሥት ዘውዲቱ ዘመን ዓለም ተቀይሯል።ወቅቱን የመጠነ ዘመናዊ ዲፕሎማሲ የሚጠይቅ እና ለእዚህም የመሬት ባለቤት በመሆን እና አገሬን እወዳለሁ ብሎ በመፎከር ብቻ የሚገኝ ሳይሆን ዘመናዊ ትምህርት እንደሚያስፈልግ ያውቁ ስለነበር የንግሥት ዘውዲቱ መምጣት ብቻ ኢትዮጵያን የ20ኛውን ክ/ዘመንን እንደማያሻግራት ገብቷቸዋል።ስለሆነም ከንግስት ዘውዲቱ ንግስና ቀን ጀምሮ የራስ ተፈሪ ቡድን ራስ ተፈሪ ኢትዮጵያን እንዲመሩ ለማድረግ ጥረታቸውን ቀጠሉ።

የካቲት ወር በ2012 ዓም

የየካቲት ወር የኢትዮጵያ ፖለቲካ ድምፅ የሚሰማበት ወር ነው።2012 ዓም ከገባ ስድስተኛ ወር ሆነ።ከየካቲት ወር  ቀደም ብሎ በነበሩት ወራት ከሶስት ያላነሱ የአደባባይ የህዝብ በዓላት እና የአፍሪካ ሕብረት መሪዎች ስብሰባ የመንግስት የፀጥታ አካልንም ሆነ ሕዝብን በተወጠረ ስሜት የያዘ ጉዳይ ነበር።በተለይ በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ወቅት የውስጥ ወይንም የውጭ ያልታወቀ ኃይል አንዳች አደጋ እንዳይፈጥር ማስጨነቁ አልቀረም።ይህንንም ተከትሎ ነው የዘንድሮው የመሪዎች ስብሰባ ከመጀመሩ በፊት ጥበቃው በሄሊኮፍተር በታገዙ ኮማንዶዎች ጭምር መሆኑን የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በዜና ላይ ሳይቀር ሁሉ ሲያሳይ ነበር።ትልቁ ቁምነገር ግን ስብሰባው በሰላም ተፈፅሟል።

በዘንድሮው የካቲት ላይ ሆነን ከመቶ ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ጉዳይ የተጨነቁት ወጣት ምሑራን ተመሳሳይ ስሜት ዛሬም ይታያል።ኢትዮጵያ በወሳኝ የ21ኛው ክ/ዘመን በብቃት የመሻገር እና ያለመሻገር ድልድይ ላይ ትገኛለች።ጊዜው ወሳኝ ለመሆኑ ከእኔ አባባል በላይ በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ በፓርላማ ቀርበው እንደተናገሩት ''ጊዜው የሞትሽረት ወቅት'' መሆኑን ተናግረዋል።ይህ ማለት ከሩቅ ተመልካች ብቻ ሳይሆን እራሱ መንግስትም ያመነው ነው ማለት ነው።

ኢትዮጵያ እና ዓለም አቀፍ ኮርፖሬሽኖች 

ኢትዮጵያ ባሳለፍነው ክ/ዘመን በርዕዮተ ዓለም ስትንገላታ ነው የኖረችው።የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ በአገር ውስጥ ፖለቲካ ብቻ የተያዘ አይደለም።የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ሂደት በጉጉት ከሚጠብቁት ውስጥ ዓለም ዓቀፍ ቱጃር ኩባንያዎች ናቸው።እነኝህ ኩባንያዎች ከቻይና ጋር በአፍሪካ ቅርምት የድርሻቸውን የገበያ ድርሻ ለመውሰድ በከፍተኛ ጉጉት ላይ ናቸው።የግሉን የኢኮኖሚ ዘርፍ ማሳደግ ላይ ከቻይና እስከ ኒውዮርክ ያሉ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች የሚስማሙበት ነው።ነገር ግን መጠኑ በምን ያህል ይሁን?መንግስት እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች ውስጥ በምን ያህል ደረጃ ራሱን ከምጣኔ ሃብቱ ማርቅ አለበት? የግል ዘርፉንስ የውጭ ኩባንያዎች ናቸው ወይንስ የአገር ውስጥ ኩባንያዎች እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ቅድምይ ሊሰጣቸው የሚገባው? በሚሉት ዙርያ ጥያቄዎች መነሳታቸው  የሂደቱን ወሳኝ አፈፃፀም  ይወስነዋል።

የውጪ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ መጉረፍ በተለይ በቁልፉ የምጣኔ ሀብት ዘርፍ ለምሳሌ እንደ ባንክ፣ቴሌ እና የኃይል ማመንጫ ዘርፍ  መምጣት በራሱ መጥፎ ነው የሚል አመለካከት የመኖሩን ያህል መምጣታቸው ተገቢ ነው የሚሉ ምሁራን አሉ። ይህንን ክርክር ለጊዜው እናቆየው እና ጉዳዩ ግን በኢትዮጵያ መጪ ፖለቲካ ላይ የውጪው በተለይ የምዕራባውያን  የድጋፍ ዋና መሰረት ከጅኦ-ፖለቲካው በተጨማሪ ይሄው  የኢትዮጵያን የገበያ እና ጥሬ ዕቃ የማግኘት ጉጉት  የአገሪቱን መጪ ፖለቲካንም እንደሚወዘወዝ መገንዘብ ይገባል።

ብልፅግና  ፓርቲ የጀዋር ቡድንን የማቅጠን ሂደቱን  አጠናክሮ በግልጥም በስውርም ቀጥሏል።

ጀዋር በአንድ ቀጭን መንገድ መሄድ ጀምሮ መንገዱ መሃል ላይ ሲደርስ የኃላ በር በኃይል ሲዘጋ ዘወር ብሎ የተደናገጠ እና ያለው አማራጭ የፊቱ ምን እንደሚሆን ሳያውቅ የሚሄድ ሰው ይመስላል።ብዙ ስልት አውቃለሁ የሚል ብቻ ሳይሆን በአንድ ወቅት የዕድምያቸውን አብዛኛውን ጊዜ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ሲንገላቱ የኖሩት አቶ አንዳርጋቸውን ስልት አለዎት ወይ? እያለ መመፃደቅ ደረጃ የደረሰው ጀዋር አሁን የአሜሪካ ዜግነቱን ለመተው አመልክቶ አዲስ አበባ ላይ ያንን ስንቀው የነበረውን ኢትዮጵያዊነት ስጡኝ እያለ እየተማፀነ ነው።

የምርጫ ቦርድም የካቲት 2/2012 ዓም ለኢሚግሬሽን እና ዜግነት ጉዳይ በፃፈው ደብዳቤ ጀዋር ዜግነት በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጠው መጠየቁ ለማወቅ ተችሏል።በሌላ በኩል የጀዋር ቡድን እና የብልፅግና ቡድን በኦሮምያ ውስጥ ከፍተኛ ፍጥጫ ላይ መሆናቸው ግልጥ ሆኗል።በእዚህም ምክንያት ብልፅግና የአመራር ሚናውን ቢይዝም በወረዳ እና በዞን ደረጃ እንዲሁም በሌላው ቢሮክራሲ ውስጥ የጀዋር ቡድን የሚደግፉ ፅንፈኞች  ላይ ርምጃ መውሰድ ተጀምሯል።ርምጃው በያዝነው ወር በበለጠ እንደሚጠናከር ይጠበቃል። በእዚህ ሂደት ብልፅግና ቀድሞ የሰራቸው ስራዎች የጀዋርን አከርካሪ ብቻ ሳይሆን ጥርሱን ያነቃነቀ ሥራ ሰርቷል።ይሄውም በታች ደረጃ ያሉትን የእርሱ አድናቂዎች በተለያየ የስራ እና የብድር ዕድል እየሰጡ ከጀዋር የመለየቱ ሂደት በብዙ ቦታ ተሳክቷል።ለምሳሌ በአምቦ ውጥረት ለመፍጠር የሚሞክሩ ወጣቶች ላይ መንግስት  በቀጥታ ማሰር መጀመሩ እና በትናንትናው እለትም በጅማ ጀዋር ሊያደርግ ያሰበው ስብሰባ ህዝቡ የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይን ፎቶ ይዞ በመውጣቱ  ከፍተኛ መሸማቀቅ በጀዋር ላይ ደርሷል። ይህ ብቻ አይደለም።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ከጅማ በተጨማሪ የቦረና እና ባሌ የኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን ልብም በድማቅ ንግግራቸው እና በልማት ፕሮጀክቶች መግዛት ችሏል።በእዚህም ጀዋር ከፍተኛ ክስራት ደርሶባታል። በእዚህ አይነት ጊዜ ላይ ጀዋር የለመዳት አንድ አይነት አካሄድ አለ።እርሱም እየተነነበት ያለውን የደጋፊ ኃይል ለማንቃት አንድ የማንቂያ እና የመሞከርያ ጉዳይ አንስቶ አንድ አይነት ግጭት ለመፍጠር እንደሚያስብ  እና አለሁ ለማለት እንደሚፈልግ የታወቀ ነው።ባለፈው ተከበብኩ የሚለውን ጉዳይ ለግጭት የተጠቀመበት ለእንደዚህ ዓይነት የመሞከር ሥራ እንደሆነ ማወቅ ይቻላል።የጀዋርን መኖር እንደ መጠባበቂያ ኃይል የሚመለከቱት ሶስተኛ ረድፈኞች በሌላ በኩል የጀዋርን ደጋፊ መሳሳት ተከትለው ራሳቸውን ወደ መቅበር እያዘነበሉ እንደሆነ ይታያል።

የብልፅግና ፓርቲ የገጠመው ትልቁ ተግዳሮት

ኢህአዴግ በመፍረሱ (መፍረስ የሚለው በራሱ ፈርሷል ወይንስ? የሚል ጥያቄ እንዳለ ሆኖ) የማይደሰት የለም።አንዱ እና ዋናው ጥላቻ አደረጃጀቱ በጎሳ ላይ መሆኑ ሲሆን ብልፅግና ቢያንስ እንደ ሱማሌ፣አፋር እና ቤንሻንጉል ያሉ ክልሎችን ፖሊሲ አውጪው አካል ውስጥ መግባታቸው እንጂ አሁንም ብልፅግና አደረጃጀቱ ከኢህአዴግ የጎሳ አደረጃጀት ለመውጣት የሚውተረተር  ምንልባት ከምርጫው በኃላ የሚሳካለት ሊሆን ይችላል።

ይህ በእንዲህ እያለ ግን የብልፅግና ፓርቲ መሰረታዊ እና ትልቁ ተግዳሮት ከፍተኛ የአድርባይነት እና የአቅም ችግር ያለባቸውን የኢህአዴግ ካድሬ እና አመራር ይዞ ለመሄድ የሚያደርገው ደካማ አካሄድ ዋጋ እንዳያስከፍለው ያስፈራል።ብልፅግና በአዲስ አካሄድ ነው የምሄደው ካለ አቅም ያላቸው እና ከነበረው የአድርባይነት ባህል የለሉበት አዲስ የሰው ኃይል ማካተት እና ወደ አመራር ማምጣት እንጂ የነበረውን አድር ባይ ካድሬ አስራ ሰባት ቀን አይደለም ከዛ በላይ ቢሰለጥንም የተሻለ መንገድ ከማምጣት ይልቅ ወደ ኃላ እንዳይጎተት ያስፈራል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ለኢትዮጵያ ፀጥታ ወሳኝ ጉዳይ ነው።

በኢትዮጵያ ላይ የሚመጡ ለውጦች በሙሉ ማዕከል የሚያደርጉት የፖለቲካውን አውድ ብቻ ሳይሆን የማኅበራዊ በተለይ የሃይማንቱን አውድም ጭምር ነው።በተለይ ከኢትዮጵያ ሕዝብ አብዛኛው የምከተላት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ዋናዋ የፖለቲካ ስሜት ማብረጃ ስትሆን ኖራለች።ይህ የደርግ መንግስትም ሆነ የህወሓት መራሹ መንግስት ሲመጣ  በስጋት የሚመለከታት  እና በሚፈልገው መልክ ለመቆጣጠር በቤተክርስቲያኒቱ ላይ ትልቅ ጉዳት አድርሰዋል።በአሁኑ ጊዜም የኦዴፓ እና የፅንፍ አካል ተጠግተው ከእዚህ በፊት በቤተክርስቲያኒቱ ላይ የማዳከም ሥራ ሲሰሩ የነበሩ እንደ እነ ቀሲስ በላይ ያሉትን በገንዘብ በማባበል ቤተክርስቲያንቱን ለመክፈል ከሁለት አካላት  ድጋፍ እየተደረገለት መሆኑ ይሰማል።እነርሱም የመጀመርያው ከፅንፈኛው የጀዋር ቡድን ሲሆን ሁለተኛው ከፅንፈኛ የተሃድሶ እንቅስቃሴ ነው።ሁለቱም አካላት የምታከኩት ሃይምኖትን ይምሰል እንጂ ግቡ ፖለቲካዊ እና ኢትዮጵያን ለመከፋፈል የሚደረግ ትልቁ አጀንዳ አካል ነው።

ይህ በእንዲህ እያለ በመንግስት በኩል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚፈፀመውን ጉዳይ በቀላሉ እየተመለከተው ነው።የደህንነት መስርያቤቱም ሆነ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን ለመክፈል የሚደረገው ሙከራ ትልቁ እና ቀዳሚው የኢትዮጵያ የፀጥታ ጉዳይ እንደሆነ ያሰቡበት አይመስልም። አጀንዳው አገርን የመክፈል እንጂ ቤተክርስቲያኗን ብቻ አይደለም።ከጀርባ የሚንቀሳቀሰው የበጀት እና ሃይማኖቱ የማይመለከታቸው የሰው ኃይል ሁሉ የሚያሳየው ጉዳዩ ፖለቲካዊ ብቻ ሳይሆን አገራዊም መሆኑን ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ድንገተኛ ስብሰባ ለመጪው ሰኞ ጠርቷል።የስብሰባው ዋና አጀንዳ በወቅታዊው በቤተክርስቲያኗ ላይ እየደረሰ ባለው ጉዳት ላይ እና በተለይ በኦሮምያ ቤተ ክህነት በሚል በቀሲስ በላይ የሚመራው ቡድን ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ ተወያይቶ ቀኖናዊ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል።

እግዚአብሔርን የማይፈሩ፣ሰውን የማያፍሩት የህወሓት አመራሮች ጉዳይ  

በቅዱስ መፅሐፍ የሚገኝ አንድን ሰው ክርስቶስ እራሱ ሲጠቅሰው ''ሰውን የማያፍር፣እግዚአብሔርን የማይፈራ'' አንድ ሰው ነበር በማለት ነው።አንድ ሰው እግዚአብሔርን ባያፍር የሰፈሩን ሰዎች ያፍራል።ሰውን ባያፍር እግዚአብሔርን ይፈራል።ሲሆን ሁለቱም ቢሆን ጥሩ ነበር።የህወሓት አመራር ግን ሁለቱንም አጥተውታል። በከዘራ እና በሰው እየተደገፉ የሚሄዱት ፣አቶ ኃይለማርያም  በአንድ ወቅት ሲመራቸው ''እንደ ጆፌ አሞራ ቢሮዬ ቁጭ ብዬ ይዞረኛል'' ያሏቸው አቦይ ስብሐት ሲሆን አክሱም ፅዮን ተቀምጠው ካልሆነ ወደ አድዋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ጥግ ይዘው ዳዊት በመድገሚያቸው  እና የህወሃትን አመራር በመምከርያቸው ጊዜ በአገር አማን መቀሌ ላይ ዛሬም ክላሽ ወጣቱን እያስያዙ ሲፎክሩ ማየት ያስገርማል። ኢትዮጵያን ከባንክ እስከ ግድብ ፕሮጀክት፣ከስኩአር ፕሮጀክት እስከ የኮንትሮባንድ መዳኒት ማስመታት ድረስ ከዝያም በላይ ከ11 ቢልዮን ዶላር በላይ ግጠው ወስደውባት እና ራቁቷን ቆማ ዛሬም ሰውን ሳያፍሩ፣እግዚአብሔርን ሳይፈሩ የካቲት 11 በዓል ለመጨፈር የህወሓት አመራር እየተዘጋጀ ነው።መቸም ረስተነው ይሆናል እንጂ ህወሓት በዓሏን ዱባይ ላይ ሁሉ ድል አድርጋ በድሃው የኢትዮጵያ ሕዝብ ደግሳ እንደነበር መቸም አይረሳም መቀሌ ላይ የውሃ ፕሮጀክቱ ገንዘብ ተበልቶ ዱባይ ላይ ውስኪ ሲወራረድ ነበር። በ21ኛው ክ/ዘመን ሕዝቡን ለስራ ከማስነሳት ይልቅ ወንድምህን ግደል ብሎ ያውም አንድ እግራቸው መቃብር በገባ አዛውንት ሲቀሰቀስ መመልከት ምንኛ ያሳዝናል።ህወሓት የካቲት 11 ለማክበር ምን ዓይነት ሞራል አላት? ቢያንስ ራሱ  ተራው የህወሓት ታጋዮች የተነሱበት የመነሻ መፈክርን የአሁኖቹ የህወሓት አመራሮች አንግበውታል? የኤፈርትን ገንዘብ በማን እጅ ነው? የትግራይ ከተሞች ንፁህ ውሃ ማግኘት ተስኗቸው የኤፈርት ብር ኝን በማን እጅ ነው? የካቲት 11 ሲከበር በየትኛው የሞራል ልዕልና ነው?

ቴዲ አፍሮ በመጪው ሳምንት በመስቀል አደባባይ  

ኪነ ጥበብ ኢትዮጵያዊነትን በተለይ ላለፉት ሰላሳ ዓመታት ትውልዱን ለማስተማር ምን ያህል ሰርቷል? ቢባል ይህንን ያህል የጎላ ሥራ አልታየም ማለቱ ይቀላል። የኢትዮጵያን ነገር ትቶ ያልተወው ቴዎድሮስ ካሳሁን ግን በትውልዱ ውስጥ ኢትዮጵያን ለማጉላት ትልቅ ሚና ተጫውቷል። ቴዲ በያዝነው ሳምንት መጨረሻ በመስቀል አደባባይ ለሕዝብ ስራዎቹን ያቀርባል።በእዚህ ላይ ብዙ ባልልም፣ቴዲ የፍቅር ጉዞ ብሎ ገና በጧቱ ትውልዱን ለመምከር ሥራ ሲጀምር እነ ጀዋር በከፈቱበት የማኅበራዊ ሚድያ ዘመቻ ተሰናክሎ ነበር።ዛሬ ጀዋር የኢትዮጵያዊነት ዜግነት ስጡኝ እያለ በሚለምንበት ሰዓት ቴዲ ኢትዮጵያ የሚለውን ዜማ በመስቀል አደባባይ ጮክ ብሎ በመጪው ሳምንት መጨረሻ ያዜማል።ግሩም ነው። ኢትዮጵያ!

=====================//////================


የቴዲ አፍሮ ኢትዮጵያ! ቪድዮ 




ጉዳያችን / Gudayachn



ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com