====================
ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com
ጉዳያችን ሚድያ፣ኮሚኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት
Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant
=====================
ዊሊ ታሌዶ (Willy Toledo)
ዊሊ ታሌዶ (Willy Toledo) ይባላል።49 ዓመቱ ነው።ስፔን ውስጥ ታዋቂ አክተር እና አክቲቪስት ነው።በፌስ ቡክ ገፁ የፈለገውን ሲጥል ሲያነሳ አንድ ቀን የማይገባ ስድብ በድንግል ማርያም ላይ እና በሥላሴ ሶስትነት እና አንድነት ላይ ይፅፋል። ከእዚህ በፊት የስፔን ፍርድ ቤት ተከሶ ሁለት ጊዜ ችላ ብሎት ሳይቀርብ ቀርቷል።ይህንንም ተከትሎ ታዋቂ አክተር እና አክቲቪስት በመሆኑ ከፍርድ በላይ ሊሆን አይገባም፣የኅብረተሰባችንን ስነ ልቦና የሚቃረን እና እምነታችንን የሚያጥላላ ፅሁፍ ፅፏል፣በአንደበቱም ተናግሯል በማለት የስፔን ክርስቲያኖች ጠበቃ ማኅበር በያዝነው የካቲት/2012 ዓም መልሶ ፍርድ ቤት ከሶታል።
ተከሳሹ ''የመናገር እና ሃሳብን የመግለጥ መብቴን ተጠቅሜ ነው የፃፍኩት፣ልከሰስ አይገባም'' ቢልም በማድሪድ ከተማ በሚገኘው 26ኛው የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ክሱ እየታየ ነው።እአአቆጣጠር ሐምሌ 5፣2017ዓም በፌስ ቡክ ገፁ በፃፈው አስተያየት በወቅቱ ክስ ተመስርቶበት አንዳንዶች ታዋቂ አክተር እና አክትቪስትነቱን ተጠቅሞ ፍርድ ቤት ለመቅረብ ያንገራገረው ዊሊ ታሌዶ፣ የስፔን ክርስቲያን ጠበቆች ማኅበር እንደገና በያዝነው ወር ክሱን ስላንቀሳቀሰው ጭንቀት ላይ ነው።
''ወንጀል የሚባለው የወንጀል ተግባር ነው እንጂ እንዴት ቃላትን ወንጀል ብላችሁ ትከሱኛላችሁ?'' በማለት ለፍርድቤቱ ከጠበቃው አንዲካ ዙሉታ (Endika Zulueta) ለተነሳለት ጥያቄ መልስ የሰጠው አክተር፣ ፅሁፉን መፃፉን አምኖ ጉዳዩን ከስፔን የዲሞክራሲ አገር መሆን አለመሆን ጋር ለማያይዝ ሞክሯል።ፍርድ ቤቱ ግን ስሞታውን አልተቀበለውም።በሕግ ጉዳይ የእዚህ ዓይነት የክስ ጉዳዮች እና ሂደታቸው አስተማሪ ብቻ ሳይሆኑ ተመሳሳይ ሕጎች መውጣት እንዳለባቸው አስተማሪ እንደሚሆኑ ይታመናል።
በነገራችን ላይ ፣አውሮፓ የሃይማኖት ዶግማ ነቅፈው የሚፅፉ እንዲህ ይከሰሳሉ።ገዳማትን እየነቀፉ የምርጫ ቅስቀሳ የሚያደርጉት ያልተከሰሱባት የኢትዮጵያ ጉዳይስ? በቅርቡ በሰሜን ሸዋ የኦሮሞ ፌድራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) የደብረ ሊባኖስን ገዳም አስመልክቶ የተነገሩት አገር ከፋፋይ ዘረኛ ንግግሮች እንዴት ታለፉ?በእርግጥ የኢትዮጵይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ የሐሰት ዜና የሚነዙ ሚድያዎች ላይ ክስ መስርቷል።ይህ እንዳለ ሆኖ ግለሰቦችም በተለይ በእምነት ጉዳይ እያስታከኩ የሌላውን እምነት የሚያጥላሉ ለሕግ መቅረብ እንዳለባቸው የአውሮፓው ተሞክሮ ያመላክተናል።
www.gudayachn.com
No comments:
Post a Comment