ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Sunday, February 9, 2020

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ሊቀመንበር አቶ የሸዋስ አሰፋ በኦስሎ ኖርዌይ ተገኝተው ከኢዜማ ድጋፍ ማኅበር አባላት ጋር ተወያዩ።

 አቶ የሸዋስ አሰፋ የኢዜማ ሊቀመንበር 
Please Note - Under Amharic version (here below) you can see the video of Ethiopian Prominent Opposition partyEthiopian Citizens for Social Justice Party latest brief for the Diplomatic Community in Addis Ababa.

ጉዳያችን ምጥን ዜና 
የካቲት 1/2012 ዓም (ፈብሯሪ 9/2020 ዓም)

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ሊቀመንበር አቶ የሸዋስ አሰፋ ዛሬ ዕሁድ የካቲት 1/2012 ዓም በኦስሎ፣ኖርዌይ ከኢዜማ ድጋፍ ማኅበር ጋር ስብሰባ ማድረጋቸውን ጉዳያችን በቦታው ተገኝታ ለመረዳት ችላለች።በስብሰባው ላይ አቶ የሸዋስ ኢዜማ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ እያደረገ ያለው የምርጫ ዝግጅት፣የአባላት ተሳትፎ እና በወቅታዊ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ማብራርያ ከሰጡ በኃላ ከተሳታፊዎች ጥያቄዎች ተነስተው  ለተነሱት ጥያቄዎች አጥጋቢ ምላሾች ሰጥተዋል። 

በተለይ ኢዜማ በአንዳንድ ከተሞች ያደረጋቸው የስብሰባ ጥሪዎች በአንዳንድ ህገ ወጦች መሰረዙን አስመልክቶ ሲናገሩ። የማኅበራዊው ሚድያ ባብዛኛው የሚያወራው ኢዜማ  ኢትዮጵያ ውስጥ ካደረጋቸው በርካታ የተሳኩ ስብሰባዎች  ይልቅ በሕገወጦች ምክንያት ያልተደረጉት አራት የሚደርሱ ስብሰባዎች ላይ የሚያተኩር መሆኑን ጠቅሰው። እነኝህ ቦታዎችም ቢሆን ለመረበሽ የሞከሩት ቁጥር ከኢዜማ ደጋፊ ቁጥር ጋር ሲተያይ እጅግ ያነሰ ቢሆንም  ኃላፊነት በተሰማው መንገድ ሰዎች እንዳይጋጩ የፀጥታ ማስከበር ሰራውን መንግስት መስራት አለበት ከሚል ፅኑ ዓላማ አንፃር  የሰረዝናቸው ስብሰባዎች ነበሩ በማለት አብራርተዋል።

በእዚሁ ስብሰባ ላይ አቶ የሸዋስ የኢዜማ የፖሊሲ ጥናቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ በከፍተኛ ባለሙያዎች የተዘጋጀ ሲሆን ባለሙያዎቹ የግድ የኢዜማ አባል መሆን አይጠበቅባቸውም ነበር ብለዋል።በሌላ በኩል በመላው ኢትዮጵያ በተመሰረቱት በ400 የምርጫ  ወረዳ ጣቢያዎች ላይ በእያንዳንዱ ጣቢያ ቢያንስ ከሶስትመቶ ሰው አባል እና አስራአምስት የስራ አስፈፃሚ እንዳለው ገልጠው።ከእዚህ በተጨማሪ በእነኝሁ ወረዳዎች ደረጃ የፖሊሲ ጥናት ቡድን እንዳለ አስታውቀዋል።በመጨረሻ ላይ ኢዜማ በኢትዮጵያ ከገዢው ፓርቲ የቀድሞው ኢህአዴግ የአሁኑ ብልፅግና ፓርቲ ጋር በሚወዳደርበት ጣብያ ብዛት በተገዳዳሪ ደረጃ  ከመቀሌ እስከ ሞያሌ፣ከወለጋ እስከ ከሚሴ ከ400 በላይ የምርጫ ጣቢያ መስርቶ ለመጪው ምርጫ በበቂ ደረጃ የተዘጋጀ መሆኑ በአቶ የሸዋስ ተብራርቷል።

Ethiopian Citizens for Social Justice Party latest brief for the Diplomatic Community. (video)

ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

No comments:

ኢትዮጵያ በዘመናዊ ታሪኳ ታላቅ ተልዕኮ የሚኖረው ሀገራዊ የምምክር ኮሚሽን በተመለከተ ምን ያህል እናውቃለን?

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ኮሚሽን አማካሪ ኮሚቴ አባላትን ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል ባካተተ መልኩ አዋቅሯል። በእዚህ ጽሑፍ ስር የሚከተሉት ነጥቦች ምላሽ ያገኛሉ፡  ኮሚሽኑ እንዴት ተመሰረተ?  የኮሚሽኑ 11 ኮሚሽነሮች እንዴት ተመ...