ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Monday, February 24, 2020

በታላቁ የዓድዋ በዓል አከባበር ላይ በሰውኛ ፕሮዳክሽንና ኢንተርቴይንመንት ውስጥ ሕይወት የዘሩ አርቲስቶች - ሚካኤል ሚልዮን እና ባለቤቱ መዓዛ ታከለ

ጉዳያችን ሚድያ፣ኮሚኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት 
Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant

  • በእዚህ ፅሁፍ ስር የሳምንቱን የዝክረ ዓድዋ በዓል መርሐግብር ያገኛሉ 

ፎቶ -አርቲስት ሚካኤል ሚልዮን እና መዓዛ ታከለ በጣይቱ ሆቴል ስለ ዝክረ ዓድዋ መግለጫ ሲሰጡ።
(ከአርት ቲቪ የተወሰደ )

''የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የመላው ዓለም ድል ነው።ድሉ የሰውን ልክ ያገኝ፣ ቅኝ ገዢዎች ከአላስፈላጊ ትዕቢት ዝቅ ብለው በሰው መጠን እንዲኖሩ፣ለጥቁሮች ደግሞ ራስን ዝቅ አድርጎ ከመመልከት ወጥተው በሰው እኩል መሆናቸውን ያሳዩበት ታላቅ ድል ነው።ይህ ማለት ሁሉንም የሰው ማዕረግ ያስተካከለ ድል ነው''
ይህንን የተናገረችው የአርቲስት ሚካኤል ሚልዮን ባለቤት አርቲስት መዓዛ ታከለ ነች።አርቲስት መዓዛ፣ አርቲስት ሚካኤል ሚልዮን እና ሌሎች አጋሮች ጋር ሆነው ''ሰውኛ ኢንተርቴይመንት'' የተባለ ድርጅት መስርተዋል።ሰውኛ ከሚሰራቸው የኪነጥበብ ፈጠራዎች በተጨማሪ የዓድዋ በዓል መልክ ባለው እና ዘመኑን በሚዘክር ደረጃ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ማክበር ነው።ላለፉት አራት ዓመታት በተከታታይ የዓድዋ በዓልን ድምቀት በመስጠት ብቻ ሳይሆን ለትውልዱ ከአዕምሮ በማይጠፋ ደረጃ ለማስቀረት አርቲስቶቹ ትልቅ አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ ናቸው።

ከወንዶች ጉዳይ አዝናኝ ፊልም ጀምሮ በልዩ ልዩ የፊልም እና የመድረክ ስራዎቻቸው  የምናውቃቸው አርቲስት  ሚካኤል ሚልዮን እና መዓዛ ታከለ በሰውኛ  ፕሮዳክሽንና ኢንተርቴይመንት ለአራተኛ ጊዜ በሚከበረው የዓድዋ በዓል ላይ ዛሬ በወመዘክር የመክፈቻ መርሃግብሩን በርካታ ታዳሚ በተገኘበት ያስጀመሩ ሲሆን በቀጣይ ቀናት እስከ በዓሉ ማለትም የካቲት 23/2012 ዓም ድረስ የተለያዩ መርሃግብሮች አሏቸው።ከመርሃግብሩ ውስጥ የአድዋ በዓል ዕለት ከምኒልክ አደባባይ እስከ አድዋ ድልድይ ድረስ የሚኖረው የባዶ እግር ጉዞ እና የአድዋ ዘማቾች የሚያስታውስ የጎዳና ትዕይንት እና በእዚሁ እለት ቀትር ላይ በእንጦጦ የዳግማዊ ምንሊክ ቤተ መንግስት የንጉሱን የግብር ማብላት ስነስርዓት በጠበቀ መልኩ የሚዘጋጅ የምሳ ፕሮግራም የብዙዎችን ትኩረት የሳበ እና በአዲስ ትውልድ ውስጥም የማይጠፋ አሻራ የሚያኖር ነው።

ሰውኛ ፕሮዳክሽንና ኢንተርቴይንመንት በእዚህ ሳምንት እና እስከ በዓሉ ድረስ በአዲስ አበባ ያዘጋጃቸውን መርሐግብሮች ከእዚህ በታች ይመልከቱ።
የአርት ቲቪ ዝግጅቶቹን አስመልክቶ ያወጣው ማስታወቂያ 
ምንጭ - አርት ቲቪ ቪድዮ 




ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com

No comments: