====================
ጉዳያችን ሚድያ፣ኮሚኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት
Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant
=====================
የጣልያን መከላከያ ሚኒስትር ሎረንዞ ጎርኒ Lorenzo Guerini
የጣልያን መከላከያ ሚኒስትር ሎረንዞ ጎርኒ Lorenzo Guerini ዛሬ የካቲት 17/2012 ዓም ጣልያን ውስጥ በሰጡት መግለጫ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1937 ዓም ከግንቦት 21 እስከ 29 በኢትዮጵያ ደብረ ሊባኖስ ገዳም የፋሺሽት ወታደሮች የፈፀሙትን አሰቃቂ ጭፍጨፋ ጣልያን በታሪክ ተጠያቂ የሆነችበት መሆኑን ማመን እንዳለባት ገልጠዋል።
ሚኒስትሩ የጳውሎ ቦሩሶ Paolo Borruso ''ደብረ ሊባኖስ በ1937'' የተሰኘውን መፅሐፍ ጠቅሰው ጣልያን በዘመኑ ከሰራችው ከባዱ የጦር ወንጀል ውስጥ የደብረ ሊባኖሱ እልቂት መሆኑን አብራርተዋል።ዜናውን የዘገበው የጣልያን ዜና አገልግሎት አንሳ (ANSA) እንደገለጠው በደብረ ልባኖሱ እልቂት ሰማዕትነት የተቀበሉት የገዳሙ መነኮሳት 449 ናቸው ቢባልም እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1990 ዓም በተገኘ አዲስ ጥናት የተገደሉት ሰማዕታት መነኮሳት ቁጥር ከ1500 እስከ 2000 እንደሚደርስ ዛሬ ማምሻው ባወጣው ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።
ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com
No comments:
Post a Comment