Friday, December 23, 2016

ዛሬ ኢትዮጵያ የምትሄድበትን መንገድ እያየን የነገ መውጫውን ካሁኑ መተለም የግድ ይላል።ለእዚህም የመፍትሄ ሃሳብ መውለድ ያስፈልጋል (የጉዳያችን ማስታወሻ ክፍል አንድ)


አሁንም ስለ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዳይ በጣም በጥልቅ አስባለሁ።የችግሩ ብቻ ሳይሆን የመፍትሄው አካልም እኔ እራሴ እንደሆንኩ አስባለሁ።የብዙዎቻችን ችግር ችግሩን የማንሳት እንጂ የመፍትሄው አካል ለመሆን ምን ላድርግ የሚል ኃላፊነት አለመውሰድ ነው።በእዚች እድሜዬ በቻልኩት ሁሉ ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዳይ ከመከታተል የቦዘንኩበት ወቅት የለም።መጨረሻ ላይ ግን አንጀቴን የሚባለኝ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው።ሕዝብ ስል በፖለቲካው ዙርያ ተዋናይ የሆኑትን ብቻ አደሉም።ፖለቲካ ውስጥ ገብተው የሚሰሩ ከየትም አቅጣጫ እንበለው እነርሱም ፍቅር  የሚሉት የእራሳቸው ነጥብ ይኖራል።ፖለቲካ ላይ ለጥቅም እና ለዝና ከገቡት ውጭ ሌሎች የህዝብ ፍቅር አስገድዷቸው የገቡ ናቸው ብዬ አምናለሁ።ይህንን መካድ አይቻልም። 

አሁን በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ላይ  የሚታዩኝ አራት  ችግሮች በደንብ እይተንፀባረቁ ነው።

1/ የኢትዮጵያ ዘለቄታ የፖለቲካ መፍትሄ ላይ አቅዶ አለመስራት፣

2/ ኢትዮጵያዊነትን ከማጠንከር ይልቅ ኢትዮጵያዊነትን የሚያላሉ ተግባራት ላይ መሰማራት፣

3/ አሁን ያሉት ልዩነቶች አልበቃ ብሎ ለነገ ሌላ፣አዲስ እና ትኩስ ልዩነት ለመፍጠር መሞከር፣

4/ የነገዋ ኢትዮጵያ አሁን ካለባት የአምባገነን እና የጎሳ ፖለቲካ ወጥታ በትክክለኛ ፍትህ፣ዲሞክራሲ እና ሁሉን ያሳተፈ እንድትሆን ከመጣር ይልቅ አሁን ጀምሮ የእራስን ጎሳ እያገነኑ የነገ መሪ እኔ ነኝ ማለት፣

እነኝህ አራት ችግሮች የኢትዮጵያ የወቅቱ ችግሮች ናቸው።ችግሮቹ አሁን በስልጣን ላይ ባለው ስርዓት ብቻ የሚቀነቀኑ ሳይሆኑ በነገዋ ኢትዮጵያ ላይም ተመሳሳይ ችግር እንዲፈጠር ሕልም እና ምኞት እንዳላቸው  ከማኅበራዊ ድረ-ገፅ አንስቶ እስከ መድረክ ንግግሮች ድረስ የሚያንፀባርቁ አካላት በትክክል እየታዩ ነው።ከአሁኑ ይልቅ በነገው ላይ የሚሰራው ሥራ ነው አሳሳቢው።¨ከትናንት ብንዘገይ ከነገ እንቀድማለን¨ የምትለው አባባል ልትዘነጋ አይገባም።የኢትዮጵያ ነገር ውስጣችንን የሚያቆስለን በድፍረት ልንጋፈጣቸው የሚገቡ ብዙ ሺህ ጉዳዮች ከፊታችን እንዳሉ መዘንጋት የለብንም። የፌስ ቡክ ንትርኩ አንዳች ጉዳይ አይፈይድም።ይልቁንም ለነገዋ ኢትዮጵያ ሁሉንም ከሊቅ እስከ ደቂቅ ሳይል የሚበክል የጎሳ ማግነን ሃሳቦች አሁን ያለነውን ብቻ ሳይሆን መጪውን ትውልድ እንዳይበክል መስራቱ ነው ቁም ነገሩ።

የኢትዮጵያ ሕዝብ የነገ መጪ እጣ ግን አንገብጋቢ ነው።መፍትሄ የሌለን ሕዝብ ልንሆን ፈፅሞ አንችልም።ነገን አሻግረን ከተመለከተን የመፍትሄው አካል የሆነው የዛሬ የተግባር ግዴታችን ይገባናል።እውነትን፣ፍቅርን እና ፅናትን አለመያዝ ብቻ ነው የመፍትሄ ድሃ የሚያደርገን።ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግር ስናወራ የነገውን የሚያስብ እንጂ አሁን ላለው ስሜት ማስታገሻ ብቻ መሆን የለበትም። 

አንድ ማወቅ የሚገባን ጉዳይ የሥርዓት ለውጥ አይቀርም።በባሌም በቦሌም ብሎ አይቀርም።ለለውጥ የሚሰራው ይስራ።ለለውጥ የሚሰራው በኃላ ይደርሳል ያላቸው ተግባራት ግን  መስራት የሚገባቸው ብዙ ሺዎች ቁጭ ብለው ኢትዮጵያን አይን አይኗን ማየታቸው ነው ጥፋቱ።ለውጥ እንደሚመጣ እያወቅን ከአሁኑ ኢትዮጵያችን ነገ ብቻ ሳይሆን ከእዝያ በኃላም ደምቃ እንድትገኝ በእዚህም ሂደት ሁሉም ኢትዮጵያን ያለ ሁሉ እርስ በርሱ ሳይናከስ እና ማኅበራዊ ሰላሙ ከአሁኑ በባሰ መልኩ ሳይደፈረስ  እንደ ሀገር መቀጠሉ ነው ወሳኙ ቁም ነገር። ይህ ደግሞ ከአሁኑ እየተገነባ ካልመጣ እና ሁሉም ወገን በጋራ የሚያምንባቸው ሃሳቦችን እያጎላን ካልመጣን ነገ በይድረስ ይድረስ የሚሰራ አይደለም። የኢትዮጵያ ሕዝብ በእውነትም ያሳዝናል (ከእራሴ ጨምሮ)። ምሁራኑ አዲስ ሃሳቦች አፍልቆ፣ ከስልጣን ጥማት እና ከማታለል ፈፅሞ በራቀ መልኩ የሕዝቡን ደካማ አስተሳሰቦች እያበረቱ፣እይታውን እያጠነከሩ እና ከክፍለ ዘመን ወደ ክፍለዘመን በቀላሉ የምትሸጋገር ኢትዮጵያን ለማምጣት አሁን ላይ የመፍትሄ ሃሳብ አምጠው መውለድ እና ወደ ሥራ መግባት የምሁራኑ የውዴታ ግዴታ ነው።የኢትዮጵያ ምሁራን ከሀገር ቤት እስከ ባህር ማዶ ያላችሁ ለነገዋ ኢትዮጵያ የሚሰራ የመፍትሄ ሃሳብ በቶሎ  ውለዱ እንጂ የእኔ ጎሳ ነገ ኢትዮጵያን ይገዛል ብላችሁ ያለፈ ችግር የሚደገምባት ኢትዮጵያን እንድናይ አታድርጉ።ይህንን ሃሳብ በሚገባ ተንጠርጥሮ መቅረብ እንዳለበት አምናለሁ።ወደፊትም በጊዜው ጊዜ ለማቅረብ እሞክራለሁ።

ኢትዮጵያን መውደድ ማለት፣ህዝብን መውደድ ማለት የእራስን ጎሳ ብቻ ማምለክ አይደለም።የምንኖረው 21ኛው ክ/ዘመን ነው።ይህ የዘመን ቁጥሩ ብቻውን ከጎሳ የፀዳ ዓለም እንደማያሳየን የታወቀ ነው።ዓለም የፈለገውን ሊዘፍን ይችላል።እኛ ኢትዮጵያውያን ግን ከጥንት ጀምሮ አለምን ያስተማርነው ብዙ የፍቅር ታሪኮች አሉን።በወቅቱ የተለየ እምነት ይዘው ከመካ የመጡትን የመሐመድ ቤተሰቦች ጀምሮ እስከ ከዓለም ዳር በክርስትናቸው ምክንያት የተሰደዱትን ዘጠኙን ቅዱሳን የተቀበልን እስከ አሁን ድረስም አሻራቸውን በኢትዮጵያ እንዲያሳርፉ እና አካላችን እንዲሆኑ ያደረግን ድንቅ ህዝቦች ነን።ዓለም በጎሳ ስላበደ አሜሪካን ሀገር የጥቁር እና የነጭ ችግር ስላለ፣በኢትዮጵያ ታሪክ ያልታየ የጎሳ መንግስት አራት ኪሎ ላይ ስልጣን ስለያዘ መሰረታዊ የአስተሳሰባችን መጠን ሊዛነፍ አይገባም።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ከትግራይ እስከ ሞያሌ፣ከአኮቦ እስከ ፈርፈር ግራ ተጋብቷል።የሚሰማው ሁሉ ጆሮውን እየጠለዘው ልክ አሁን ያየውን ችግር ያህል ነገም እንዳይደገም የመፍትሄ ሃሳብ የሚሰጠው ወገን እየጠበቀ ነው።አጫጭር ስሜት የሚኮረኩሩ፣ የእኔ ጎሳ የበለጠ ጀግናው የሚሉ ፉከራዎች ለነገ አብሮ የመኖር ሕልውናችን ዋስትናዎች አይደሉም።ዛሬ ኢትዮጵያ የምትሄድበትን መንገድ እያየን የነገ መውጫውን ካሁኑ መተለም የግድ ይላል። ለእዚህም የመፍትሄ ሃሳብ መውለድ  ያስፈልጋል ።


ጉዳያችን GUDAYACHN

 www.gudayachn.com

ከአበበ ቢቂላ ቀጥሎ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሩጫ ነፍስ መዝራት ምክንያት የሆነው ምሩፅ ይፍጠር አረፈ።

The 1980s Ethiopian famous Athlete Miruts Yifter has died.
ኃይሌ ገብረ ስላሴ ወደ ሩጫው ዓለም እንዲገባ ምሩፅ ይፍጠር ምክንያት እንደሆነው ደጋግሞ ተናግሯል።ምሩፅ ይፍጠር በሞስኮ ኦሎምፒክ ማሸነፉ የወቅቱ ድል ብቻ ሳይሆን ዛሬ ላሉን አትሌቶች ልባቸው ወደ አትሌቲክስ እንዲሸፍት ያደረገ አኩሪ የኢትዮጵያ አትሌት ነው። ኃይሌ ገብረ ስላሴ ምሩፅ ኦሎምፒክ ያሸነውን በዜና ስሰማ ውስጡ ለአትሌቲክስ ሩጫ መነሳቱን እና እንደ እርሱ በሆንኩ የሚል ምኞት እንዳደረበት በተለያየ ጊዜ በሰጠው ቃለ መጠይቅ ገልጦ ነበር።
ምሩፅ ይፍጠር በተለይ በሞስኮ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ካደረገ በኃላ ስሙ በመላው ኢትዮጵያ እና በዓለም ተናኝቶ ነበር። የሞስኮ ኦሎምፒክ አሸንፎ ሲመጣ ከአየር መንገድ ጀምሮ በግልፅ መኪና ሲገባ በሺህ የሚቆጠር የአዲስ አበባ ነዋሪ በሆታ እና በእልልታ ተቀብሎት ነበር።በወቅቱ ኮለኔል መንግስቱ ቤተ መንግስት ድረስ አስጠርተው ሽልማት አድርገውለታል። ምሩፅ በወቅቱ ከመንግስት ካገኘው ሽልማት ውስጥ የታርጋ ቁጥሯ 00001 የነበረ አዲስ መኪና እና በቦሌ መንገድ ኦሎምፒያ አጠገብ ዘመናዊ የመኖርያ ቪላ ነበሩ። 
ምሩፅ በህክምና ሲረዳ ከቆየ በኃላ ማረፉ ተነግሯል። የምሩፅ ይፍጠርን ነፍስ በገነት ያኑርልን።

ቪድዮ: ምሩፅ ይፍጠር በሞስኮ ኦሎምፒክ 1980 እኤአቆጣጠር  1974 ዓም


ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Thursday, December 22, 2016

Ethnic tensions in Gondar reflect the toxic nature of Ethiopian politics.

A coach torched by anti-government protesters in Gondar, Ethiopia. 
All photographs  by William Davison

The guardian
Thursday 22 December 2016 12.17 GMT

From uneven development to authoritarian government, the morass of issues facing the city of Gondar offer a snapshot of Ethiopia’s wider problems
¨¨ሀገራችን እንዳለን አይሰማንም።ጣልያን በወረረችን ዘመን ላይ ያለን ሆኖ ይሰማናል።ለሀገሪቱ ሁለተኛ ዜጋ ሆነናል።¨ የጎንደር ከተማ ነዋሪ ለእንግሊዙ ዘጋርዳይን የተናገረው። “We don’t feel like it is our country. We feel like it is the time when the Italians invaded. We are like second-class citizens,” says a prosperous local businessman

In Gondar, a city in Ethiopia’s northern highlands, a lone tourist pauses to take a photo of a fortress built more than two centuries ago. Nearby, past a row of gift shops, lies the wreck of a coach torched during unrest in August.

Gondar, known as “Africa’s Camelot”, was once the centre of the Ethiopian empire – at a time when that empire was defined mainly by Amhara traditions. 
Today, the city is facing new tensions that have a complex history. A territorial dispute between elites here in the Amhara region and those in neighbouring Tigray has been simmering for at least 25 years.

Analysis State of emergency likely to ramp up repression in fractured Ethiopia

Protests by the Oromo ethnic group have led to spiralling violence and a crackdown on dissent that risks long-term instability. Tigrayans have been accused by opponents of wielding undue influence over Ethiopia’s government and security agencies since 1991. In recent months, these and other grievances have led to protests, strikes, vandalism and killings in Gondar, causing a drastic reduction in foreign visitors to the tourism-dependent city and an exodus of fearful Tigrayans.

Shops and schools have reopened in Gondar, after the authorities reasserted control in urban areas by declaring a state of emergency on 8 October. But sporadic clashes with the military continue in the countryside.
“We don’t feel like it is our country. We feel like it is the time when the Italians invaded. We are like second-class citizens,” says a prosperous local businessman. Like all interviewees, he requested anonymity due to fear of reprisals from the authorities. Europeans never colonised Ethiopia, but Mussolini’s army occupied the country from 1936 to 1941.

Gondar’s predicament is a microcosm of Ethiopia’s: a toxic brew of uneven development, polarised debate amid a virtual media vacuum, contested history, ethnic tensions, a fragmented opposition and an authoritarian government. Ethiopia’s rulers show few signs of being able to solve the morass of problems, which many believe the government itself caused.

Trouble began in Gondar in July 2015, when word went around that the authorities intended to arrest Col Demeke Zewdu, a former rebel and retired military officer.When security forces tried to arrest Zewdu, who is a member of a committee campaigning over the contested Wolkait territory, armed Amharas protected him and several people, including security officers, were killed.

Wolkait is an administrative district in Tigray that borders Amhara. The committee says Wolkait and others areas were taken out of Gondar’s control by the Tigrayan People’s Liberation Front in 1992, when Ethiopia was divided into a federation along ethno-linguistic lines. Allied rebels led by the TPLF, who unseated a military regime in 1991, introduced the system and still monopolise power.

Critics of the committee point out that a 1994 census found more than 96% of the people of Wolkait were Tigrayan , and that the complaints of annexation stem from the town of Gondar, not the district itself. The activists say the TPLF moved Tigrayans into the area during the rebellion.

The issue struck a chord in Gondar. After Demeke’s arrest, rural militiamen paraded through the city on 31 July, firing bullets into the air during a large, peaceful demonstration. It is thought that the demonstration was facilitated by the Amhara wing of the TPLF-founded Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) – a four-party coalition that, along with allied organisations, controls all the country’s legislative seats.

A Tigrayan lecturer at Gondar University said he abhors Ethiopia’s ethnicised politics and believes jostling between the Amhara and Tigrayan EPRDF wings lay behind the Gondar violence. The TPLF is the predominant party in the EPRDF, and Amhara National Democratic Movement politicians are seeking greater power, he said. “I don’t believe in parties which are organised on ethnicity. I prefer it to be based on the individual.” An end to ethnic politics would make a resolution of the Wolkait issue possible, he believes.

Among activists from Amhara, disavowal of the ethnicity-based system is at the crux of disagreements over how to oppose the EPRDF. Because federalism formally protects the rights of communities marginalised during previous eras, when Ethiopia was a unitary state, promoting national unity at the expense of ethnic autonomy is often cast as regressive.

Groups promoting Amhara identity within a democratised federation are therefore at odds with those focused on national cohesion, according to Wondwesen Tafesse, a commentator on Amhara issues. “Since most diaspora Amharas support Ethiopianist political parties, they seem to have this fear in the back of their mind that a resurgent Amhara nationalism, and the possible emergence of a strong Amhara political organisation, might undermine their political designs,” said Wondwesen.

In the weeks after Demeke’s detainment, there was more unrest, amid allegations that Tigrayan businesses were being targeted and Tigrayans attacked. People in Gondar say the companies were targeted because of their connections with the regime, rather than the owners’ ethnicity.

Amba Giorgis town in the North Gondar district of Ethiopia’s Amhara region

Facebook Twitter Pinterest. Amba Giorgis town in the North Gondar district of Ethiopia’s Amhara region. A territorial dispute has recently caused clashes between farmers and the military
Unrest in Amhara was preceded by protests by the Oromo, Ethiopia’s largest ethnic group, who also complain of marginalisation and repression. In response, the government has reshuffled officials – and intensified repression. During the state of emergency, the government has sent at least 24,000 people to camps for indoctrination under rules that allow the suspension of due process. According to the Association for Human Rights in Ethiopia, security forces killed some 600 demonstrators over the past year.

Since the beginning of November, a new federal cabinet has been announced and similar changes made in the Amhara government. But while maladministration and corruption were tagged as the pre-eminent problems, there is little evidence of officials being punished, or of policy reforms. An Amhara government spokesman said systemic changes were not required.

In August, on the outskirts of Gondar near Demeke’s neighbourhood, a crowd looted Baher Selam hotel. It was targeted following a rumour that the Tigrayan security officers allegedly involved in the operation to arrest the colonel were staying there.

Near the wrecked hotel, an elderly lady was roasting coffee beans. On the morning of the incident she was coming home from church when she heard gunshots.Business has since declined and large numbers of unemployed young people have been mobilised against the government, she said.

People here believe Wolkait was part of Gondar throughout history. “If they take that place, where else are they going to take?” the woman asked. “The situation is not going to go back to normal. If you light a match, it’s small – but it can burn a whole area.”

Source : The guardian (https://www.theguardian.com/global-development/2016/dec/22/gondar-ethiopia-ethnic-tensions-toxic-politics?CMP=share_btn_fb )

ጉዳያችን GUDAYACHN

 www.gudayachn.com

Will Russia take military action against Saudi? (Gudayachn reader´s comment and reply)


Please Note: the below comment and reply were posted on US based web site zehabesha.com  
The comment was give for an article  written in Amharic on gudayachn.com  under the title of  ¨የአንካራው የሩስያው አምባሳደር ግድያ ምን አዲስ የፖለቲካ ትኩሳት ሊያስነሳ ይችላል? meaning ¨ What will be the political consequence for the assassination of Russian Ambassador to Turkey? ¨  (http://www.gudayachn.com/2016/12/blog-post_19.html )
==========================================


Dear Gudayachin,there is one important point that you missed that would actually make your frustration (የጉዳያችን ስጋት ግን ገዳዩ ማንም ሆነ ማን ሩስያ በሳውዲ አረብያ ላይ የአየር ጥቃት ለመፈፀም ከእዚህ ጊዜ የተሻለ የማታገኝ መሆኑን ልታስብ ብትችል እና ብታደርገውስ የሚል ነው)the impossible nightmare.

I don’t think that you have the clue what kind of agreement Saudi Arabia has with United States since 1973. It is a deep politics but I will try to put it as short as possible. At the final days of the second world war three international organizations have been established UN, IMF and World Bank. While IMF was established at the Bretton-wood Conference all participant countries agreed that the US dollar to be a world reserve currency. And they fixed 35 America dollar worth 1 ounce of gold. Which means if any country wants to change its dollar reserve to gold, it can go to US Federal Reserve Bank and change the equivalent amount of gold.And because of that every country used dollar as transaction currency between countries. And dollar demand skyrocketed. At this point the United States government starts to print dollar without having equivalent amount of gold reserve. And France and Germany started suspicious that the US government is printing and distributing just a fiat money with no back of gold. So, they asked the US Federal reserve to change their excess dollar reserve into gold. By then the US government did one funny thing. All this happened in 1973 while Richard Nixon was on power. Just one morning Nixon come to TV screen and told the world that the US closed the gold window. Which means, the US government never change your dollar into gold. “Might is Right” worked at this point. But the Americans were not stupid. They know that unless and otherwise they do something, no body needs to have dollar or use dollar as an international transaction currency. So, before they closed the gold window, the then national security adviser (later Secretary of State) to President Nixon, Henry Kissinger went to Saudi Arabia to cut the infamous “Petro-Dollar-Security Pact.” The crux of the pact was just the Saudi-Arabian Government at the start and later all the gulf monarchies will sale their oil with US DOLLAR ONLY and in return United States will give protection for the monarchies. And since then every country needs the US dollar to buy oil. For example, Euro is stronger than US Dollar but Germany must have the US Dollar to buy oil from middle east. No country will sale it by euro. So, the US Simply print a bunch of green paper and distribute to the world. Any gulf nation that would try to challenge the deal will face the fate of Saddam Hussien.

So, Dear Editor-in-Chief of Gudayachin, it is not as simple as you imagined to carpet bomb Saudi Arabia by any force including putin unless he gets the green light from US. It will be a nuclear confrontation. The power of united states lies on the power of dollar. And any earthly power that challenge the status quo is a deadly threat to US. And Putin knows this better than anybody else. Frankly speaking, there is near to zero probability that the Saudi security apparatus has a significant role to kill the ambassador. Of course the assassin is not just a nut lone assassin. There would be strong hand. Who has interest in Syria? Russia, Iran on one camp; and Israel, Turkey, Qatar, Saudi Arabia and United States on the other camp. So, we can predict that the masters of the planet (either CIA or the Mossad or Jointly could be the the real architects). May be that is a trap by these two intelligence apparatuses to drag putin to deploy boots in Syria then they will let him bleed white like the red army faced in Afghan (1979-1989). I have no time to list here what interest each of those countries have on Syria. But all of them have a strategic interest which is a game-changer both Geo-politically and Geo-economically.


Dawit F. Mestesahil
December 20, 2016 at 5:24 pm


Gudayachn Reply to the above comment


Thank you Dawit for your comment.

You explained well how strong the Saudi security is protected by US both militarily and economically. However, I think the 1970s and 80s situation has started to be changed since 9/11 incidence. An official investigation result of the 9/11 terrorist action on New York city,  finger to Saudi Arabia. Saudi Arabia means may not mentioned as state but the terrorists family and economic  base is in Saudi Arabia. United States criticised both directly and indirectly  as Saudi money was using to fund terrorism. However, due to strong economic and strategic interest,  US government could not push the issue officially.

Since 2010, Saudi movement in middle east is quite changing. Saudi began to make her self as ¨regional supper power ¨ country.  This was made together with UAE and Qatar. Since March, 2015, Saudi involved in Yemen civil war. Recently it began to build  military camps in the Horn of Africa (Eritrea and Djibouti on process). Many international terrorists root of fund was found from Saudi side. In all this situation still US lost her courageous to control the  Saudi move. On the other hand US is attracted with Saudi purchasing power of armaments and sophisticated military jets from her own market. Therefore even US knows Saudi is moving to ¨the wrong direction¨,  it focuses only on her current interest. However, it does not mean US do not have fear on Saudi moves. That is why the US strategic interest in middle east is started to change.  The good example is the US agreement with Iran on Iranian Nuclear power installation. 

Currently US do not feel safe from Saudi money funded terrorists act in different factional groups in middle east. Because US know such a kind of gup will creat an  ideological challenge to west with antagonistic situation between the west and middle east in future. 

Regarding Russia, Saudi means one of the source of fund to Syria and Yemen conflict.In fact Iran involvement, on the other side, should not be forgotten. So even if Syria war has stopped, Russia may think as  there is no guarantee unless Saudi and Quatar are obliged to collect their hands from any form of involvement in supporting opposition groups particularly in Syria. 

Therefore if Russia took some military action on Saudi,  I think no body should  be surprised . In fact Russia decision  to take some military action against Saudi may not lead to full scale war. Because Russia may not be ready to do in such a way. But it may plan to give some lesson through bombarding some strategic military places in Saudi. Here in all move US might be consulted at the back door. The question that should be raised here is that what is the gain that US and Russia  will get from Russia military act against Saudi? I think  to Russia; one, it will show her shadow on middle east. Two, it will help to increase oil price which gives market benefit to Russia Oil production (in fact other producers will be benefited also). Three, it will give guarantee to Syria and Yemen peace by giving strong warning to Saudi.  Incase of US; it will increase the importance of US army presence in Saudi. So US will increase her price on Saudi. US can say, if US is not present in Saudi, Saudi security is nothing but exposed to foreign powers. 

Generally Russia action on Saudi has bilateral interest for both US and Russia from different perspectives. It is quite clear also US did not plan to clash directly with Saudi. But a lesson given by Russia may help US to speak louder and boost as its presence help Saudi not to go Russia to full scale war. Saudi will reflect the same motto.  Then life continues as usual. 


GUDAYACHN 
December 22, 2016 at 3:23 am
Reply


ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Monday, December 19, 2016

የአንካራው የሩስያው አምባሳደር ግድያ ምን አዲስ የፖለቲካ ትኩሳት ሊያስነሳ ይችላል? (የጉዳያችን ልዩ ዘገባ)

በቱርክ የሩስያ አምባሳደር አንድሬ ካርሎቭ ከመገደላቸው ጥቂት ደቂቃዎች በፊት ንግግር ሲያደርጉ  (photo: Reuters)

ጉዳያችን /Gudayachn

ታህሳስ 11፣2009 ዓም  (ዴሴምበር 19፣2016)



የሰኞው ምሽት ግድያ 


ሰኞ ምሽት በቱርክ ዋና ከተማ አንካራ የሚገኘውን የስዕል ኤግዚብሽን መክፈቻ ላይ የተገኙት ሩስያን እኤአ 2013 ዓም ጀምሮ በቱርክ የወከሏት አምባሳደር  አንድሬይ ካርሎቭ (Andrey Karlov) ከጀርባቸው በተተኮሰ የሽጉጥ ጥይት ተገደሉ።ግድያው በቀጣዩ ቀን የሶርያን ጉዳይ በተለይ ሩስያ፣ኢራን እና ቱርክ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው ደረጃ ውይይት ለማድረግ ሞስኮ ላይ ቀጠሮ ነበራቸው። ግድያውን ተከትሎ ከተሰጡት ሁለት መላ ምቶች ውስጥ አንዱ የሩስያ እና የቱርክ ግንኙነት ይሻክራል የሚለው ሲሆን ሌላው ደግሞ በሶስቱ ሀገሮች ማለትም በሩስያ፣ቱርክ እና ኢራን መካከል  ሶርያን አስመልክቶ የሚደረገውን ውይይት ለማደናቀፍ የታሰበ ነው የሚል ነው። ሆኖም ግን የሩስያው ፕሬዝዳንት ፑቲንም ሆኑ አደጋውን ወደ ሞስኮ እየበረሩ ሳለ አይሮፕላን ውስጥ የተነገራቸው የሩስያው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰርገይ ላቭሮቭ (Sergey Lavrov) አደጋው በቱርክ እና በሩስያ መካከል ያለውን ግጭት የሚያባብስ አይሆንም ብለዋል።እንደ እውነቱም ከሆነ ቱርክ ከወራት በፊት የሩስያ አይሮፕላንን መትታ ከጣለችበት እና ግንኙነቷ ከሩስያ ጋር ከሻከረ ወዲህ ባሉት ጊዚያት ከሩስያ ጋር በሶርያ ጉዳይ እየተቀራረበች እና ሞስኮ ላይ ጉባኤ ለመቀመጥ ቀጠሮ እስከመያዝ መድረሷ በሁለቱ ሃገራት መካከል የከፋ ግንኙነት ተፈጥሯል ለማለት አያስደፍርም።ሆኖም ግን በሶርያ ጉዳይ ሩስያ እና ቱርክ የጋራ መስመር ለመያዝ አልተቸገሩም ማለት አይቻልም።ቱርክ የኩርድ ተገንጣይ እንቅስቃሴ በሶርያ መሰረት እንዳያገኙ ታስባለች።ከእዚህ በተለየ የቱርክ ከሩስያ ጋር መቀራረብ ጉዳዩን የምያወሳስበት መንገድ የቱርክ የናቶ ጦር ቃል ኪዳን ሀገሮች አባል መሆኗ ነው።ናቶ ደግሞ ከምሥራቅ በኩል ቀዳሚ ስጋቴ የሚላት ሩስያ ነች።ሩስያ እና ቱርክ ደግሞ የሶርያ ጉዳይ አገናኛቸው።ይህ ሁኔታ ምዕራባውያንን ያስደስታል ብሎ ማሰብ አይቻልም። 

ፑቲን ቅጭም ባለ ፊት 


የሩስያው ፕሬዝዳንት ፕሬዝዳንት ፑቲን ፊታቸውን ቅጭም አድርገው በ¨ሩስያ ቱዴይ¨ ቴሌቭዥን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሟቹን አምባሳደር አንድሬይ ካርሎቭን በቅርብ እንደሚያውቁ እና ትጉህ፣ታታሪ አምባሳደር መሆናቸውን ከገለፁ በኃላ ልዩ መታሰቢያ እንደሚደረግላቸው ገልፀዋል።ፑቲን ስሜታዊ ላለመሆን በሞከረ መልኩ በሰጡት በእዚሁ መግለጫ ላይ  በተለይ ጉዳዩን አስመልክተው ሲናገሩ የሶርያ ሰላም እየተሻሻለ መምጣት ያሳሰባቸው ወገኖች ድርጊቱን የፈፀሙ መሆናቸውን እንደሚገመት እና ልዩ የምርመራ ቡድን ወደ ቱርክ መላኩን ገልፀዋል። የቱርክ እንግሊዝኛ ጋዜጣ ¨ደይሊ ሳባህ¨በበኩሉ  በሩስያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ የአደጋ ኮሚቴ ከግድያው ጋር በተያያዘ መመስረቱን ከመግለፁም በላይ የሩስያ ፓርላማ (ዱማ) የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ኮሚቴ ሊቀመንበር ሌኦንድ ስሉትስኪ (Leonid Slutsky)
     ¨ በአንካራ እና በምዕራብ ያሉ ስልታዊ ጠላቶቻችን በአንካራ እና በሞስኮ መካከል አዲስ የግንኙነት መቀዛቀዝ  እንዲኖር እንደሚሰሩ ብናውቅም   ምንም አይነት አዲስ ውጥረት ግን አይኖርም¨ ማለታቸውን ጠቅሷል።

መንገዶች ሁሉ ወደ ሳውዲ አረብያ ያመራሉ 


በግንቦት ወር 2016 እኤአ  ¨ናሽናል ኢንተረስት ዶት ኦርግ¨  ¨ሩስያ እና ሳውዲ አረብያ ወደ ለየለት ፀብ እያመሩ ነው¨ (Russia and Saudi Arabia Are Headed for a Showdown) በሚል ርዕስ በወጣ ዘገባ ላይ በሩስያ እና ሳውዲ አረብያ መካከል ያለው ውጥረት በነዳጅ ገበያ ዙርያ የማይታጠፍ ነው ካለ በኃላ።ሳውዲ አረብያ በርካታ ነዳጅ ከአጋሮቿ ጋር ወደገበያ በመልቀቅ ተዋዳዳርዎቿን ለመጉዳት እንደምትሞክር ያትታል።ሩስያ በአንፃሩ የነዳጅ አምራች ሀገሮች ማህበር በምህፃሩ ¨ኦፔክ¨ በመባል የሚታወቀውን ድርጅት በተለየ ¨የጋዝ ላኪ ሀገሮች ፎረም¨ የሚል መስርታ ውጤታማ የሆነ ሥራ ላለፉት አስር አመታት መስራቷን ይገልፃል። የሩስያ እና የሳውዲ ችግር የቅርብ ጊዜ ክስተት ብቻ አይደለም። ሩስያ በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት ወታደሮቿ አፍጋኒስታን ዘምተው በነበረበት ወቅት ከፕሮፓጋንዳ እስከ ቀጥታ እርዳታ ከአሜሪካ ጋር ሆና ሩስያን ያጠቃች ሳውዲ አረብያ ነበረች። ¨አል ሞኒተር ¨  ¨What Russia's Syria shift means for Moscow-Riyadh ties¨ በሚል ርዕስ እኤአ መጋቢት 18፣2016 ዓም ባሰፈረው ፅሁፍ ላይ ይህንኑ የቆየ የሩስያ እና የሳውዲ አረብያ ፀብ እንዲህ በማለት ገልፆታል።
  ¨የሩስያ እና የሳውዲ ግንኙነት አሁን የተጀመረ ሳይሆን በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት ሳውዲ አረብያ ፀረ-ሶቪየት ድጋፍ በአፍጋኒስታን በማድረግ ይገለፃል።በተጨማሪም የሩስያ መሪዎች በቼቼንያ ተገንጣዮች እንቅስቃሴ ሳውዲ አረብያን ይጠረጥራሉ¨ ይላል።

በሌላ በኩል ሩስያ በሳውዲ አረብያ ድርጊት ከተበሳጨችበት ጉዳይ አንዱ ሳውዲ አረብያ በየመን ላይ ከመጋቢት ወር 2015 እኤአ ጀምሮ የከፈተችው የአየር ጥቃት ጉዳይ ነው። ሳውዲ አረብያ በእዚህ ድርጊት በዓለም አቀፍ ወንጀል መጠየቅ እንደሚገባት ሩስያ ደጋግማ ተናግራለች።በእዚህ ድርጊትም ተባባሪ በመሆን መሳርያ ለሳውዲ አረብያ በመሸጥ የሚታወቁት እና የየመኑን እልቂት ሳውዲ አረብያን ከመውቀስ የታቀቡት ምዕራባውያንን ሩስያ ኮንናለች።ከእዚህ አልፋ የሩስያ መገናኛ ብዙሃን ሳውዲ አረብያ በየመን ፈፀመችው ያሉትን የህዝብ ፍጅት በቀጥታ በቴሌቭዥን በማስተላለፍ ከምዕራብ ዜና አውታሮች በተሻለ መንገድ ተቀምጣለች። 

¨የገዳዩን እጅ የዘወረው ማን እንደሆነ ማግኘት አለብን¨ ፕሬዝዳንት ፑቲን 
“We must know who directed the killer’s hand.” President Putin 

ይህ ሁሉ ጉዳይ በሩስያ እና ሳውዲ አረብያ መካከል እያለ ነው እንግዲህ የሶርያው የእርስ በርስ ጦርነት ሲነሳ ሩስያ በፕሬዝዳንት በሺር አል-አሳድ  የሚመራውን የሶርያን መንግስት ደግፋ ስትቆም ምዕራባውያን፣ሳውዲ አረብያ እና ኩአታር ከሶርያ አማፅያን ጎን የቆሙት።

ጦርነቱ እንደተጀመረ ሰሞን ፕሬዝዳንት ፑቲን በተለይ ፕሬዝዳንት ኦባማን የሶርያ አማፅያን የአሸባሪው ¨አይኤስ ኤስ¨ ውላጅ እና አካል መሆናቸውን ብቻ ሳይሆን ለአካባቢው ጠንቅ መሆናቸውን ባስረዱበት የቡድን ስምንት ስብሰባ ላይ አማፅያኑ የሰው ስጋ ሲበሉ የሚያሳይ ቪድዮ እስከማሳየት ደርሰዋል።በወቅቱ ፑቲን ሰሚ አላገኙም።ጦርነቱ በተለይ ሳውዲ አረብያ እና ኩአታር በአንድ በኩል በኢራን የሚደገፈው ¨ሄዝቦላ¨ እና የሶርያ መንግስት በሌላ በኩል ሆነው ሩስያ የሶርያን መንግስት በመደገፍ ጦርነቱ ቀጠለ።ጦርነቱ በያዝነው ወር ግን አዲስ ቅርፅ ያዘ።የሶርያ መንግስት ወታደሮች ቁልፍ በአማፅያን የተያዙ ከተሞችን ያዙ።አማፅያኑ የመውጫ ኮሪደር እንዲሰጣቸው ሩስያን እና የሶርያን መንግስት መማፀን ከጀመሩ ገና ሳምንታት መሆኑ ነው።የሶርያ ጦርነት በሶርያ መንግስት ሲጠናቀቅ የሳውዲ አረብያ እና ኩአታር እንዲሁም የምዕራባውያን እጅ አዙር እርጥባን የሚደርሳቸው አማፅያን ከገበያው መውጣት ደጋፊ አገሮችን ከሶርያ ጉዳይ የሚያሽቀነጥር ሆነ።የሶርያን ጉዳይ የሚወስኑት ባለጉዳዮቹ አሸናፊዎቹ ሊሆኑ ሳምንታት ቀሩት። ሩስያ ሞስኮ ላይ በመጭዋ የሶርያ ጉዳይ ላይ ለመነጋገር ዛሬ ታህሳስ 11፣2009 ዓም ከቱርክ እና ኢራን ጋር ቀጠሮ ያዘች። 

ይህ በእንዲህ እያለ ነው የሩስያው አምባሳደር በአንካራ የስዕል ኤግዚቢሽን ላይ የተገኙት እና የቱርክ ፖሊስ ባልደረባ መሆኑ  በተነገረው ሰው ከጀርባቸው ተተኩሶ የተገደሉት።ግድያውን ማን ፈፀመው? ፕሬዝዳንት ፑቲን እንዳሉት የገዳዩን እጅ የዘወረው ማን እንደሆነ ያገኙት ይሆን? የጉዳያችን ስጋት ግን ገዳዩ ማንም ሆነ ማን ሩስያ በሳውዲ አረብያ ላይ የአየር ጥቃት ለመፈፀም ከእዚህ ጊዜ የተሻለ የማታገኝ መሆኑን ልታስብ ብትችል እና  ብታደርገውስ የሚል ነው።አንድ ቀን ማለዳ ስንነሳ በጭስ የታፈኑ የሳውዲ ሰማዮችን ከማየት ይሰውረን።በእዚህ ማን ያተርፋል? ማን ይጎዳል? ወደፊት የምናየው ይሆናል።ዓለማችንን ሰላም ያድርግልን።  


ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

Friday, December 16, 2016

ባንኪሙንን የሚተኩት ፖርቹጋላዊው አዲሱ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ አንቶንዮ ጉተሬስ (Antonio Guterres) ማን ናቸው?

ጉዳያችን/ Gudayachn
ታህሳስ 8/ 2009 ዓም ( December 16,2016)
==============================
አንቶንዮ ጉተሬስ (Antonio Guterres) በፈረንጆቹ አቆጣጠር ጥር 1/2017ዓም  ሥራ ይጀምራሉ።

የመንግሥታቱ ድርጅት ባለፈው ጥቅምት/ 2009 ዓም ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ አዲስ ዋና ፀሐፊ መርጧል። አዲሱ ዋና ፀሐፊ ፖርቱጋላዊው አንቶንዮ ጉተሬስ በማስፈፀም አቅሙ እየተዳከመ የመጣውን ድርጅት ያነቃቁታል ተብሎ ይታሰባል።የተባበሩት መንግሥታት አዲስ የመዋቅር ለውጥ እንደሚያስፈልገው የምወተውቱ ብዙዎች ናቸው።አሁን ባለው የዓለም ሰላም መታወክ በተለይ በመካከለኛው ምስራቅ የሶርያውን ግጭት ጨምሮ እንደ ሀገር መቆም ያቃታቸው የሊብያ እና የየመን ጉዳይ፣የደቡብ ሱዳን ግጭት እና የሩስያ እና አሜሪካ ውጥረት ሁሉ ድርጅቱን አንቶንዮ ጉተሬስን በስልጣን በሚቆዩባቸው በመጪዎቹ አምስት አመታት ውስጥ ወጥረው የሚይዙ ጉዳዮች ናቸው።ይህ ማለት በእነኝህ አመታት የሚፈጠሩት አዳዲስ ክስተቶች እና ድርጅቱ የገባበት ከፍተኛ የሙስና እና የተዝረከረከ አሰራር ማስተካከልን ጨምሮ ማለት ነው።

አንቶንዮ ጉተርዮስ ማን ናቸው? 


- አንቶንዮ ጐርዮስ  ሚያዝያ 30፣1949 እኤአ በፖርቹጋሏ ከተማ ሊዝበን  ከአባታቸው ቪግሎ ድያስ ጉተረስ እና እናታቸው ካንድዳ ደ ኦልቨራ ተወለዱ። አባታቸው እኤአ በ2009 ዓም አርፈዋል።

- ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቃትን ተከትሎ ለተመሰረተው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዘጠነኛው ዋና ፀሐፊ ናቸው።

- እኤአ ከ1995 እስከ 2002 ዓም የፖርቹጋል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል።

- እኤአ ከ1999 እስከ 2005 ዓም የዓለም አቀፍ ሶሻሊስት (socialist international) ፕሬዝዳንት ነበሩ።

- እኤአ ከ2005 እስከ 2015ዓም  የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽነር ሆነው አገልግለዋል።

- ወደ ፖለቲካው ዓለም ከመግባታቸው በፊት ፊዚክስ፣ቴሌኮምኒኬሽን ሲግናል  እና ኤሌክትሪክ ኢንጂነሪንግ ተምረዋል።

- ወደ ፖለቲካው የገቡት የኢትዮጵያ አብዮት ሲፈነዳ በ1966 ዓም (1974 እ ኤአ) የፖርቹጋል ሶሻሊስት ፓርቲ አባል በመሆን ነበር።

- በፕሬዝዳንትነት ሀገር የመራ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ ሲሆን የመጀመርያው ሰው ይሆናሉ።

- የካቶሊክ አማኝ እና ዩንቨርስቲ እያሉ የወጣት ካቶሊካውያን ወጣቶች ማለትም ¨የብርሃን ቡድን¨  ¨Group of Light¨  ንቁ ተሳታፊ ነበሩ።
- አንቶንዮ ለእውነት የቆሙ ተብለው ይነገርላቸው ነበር።የፖርቱጋል የቀድሞ ቅኝ ግዛት የነበረችው ምስራቅ ቲሞር ነፃነቷን ማግኘት እንደሚገባት የተሟገቱ ሰው ነበሩ።ለገዛ ሀገራቸው ፖርቱጋል ሳያደሉ እውነት እንደተናገሩ ይነገርላቸዋል።

- የፖርቹጋል፣ስፓኒሽ፣ፈረንሳይኛ እና እንግሊዝኛ አቀላጥፈው ይናገራሉ።

ምንጭ: - የተባበሩት መንግሥታት ድረ-ገፅ፣
               - ቢቢሲ ዘገባ 

               
ቪድዮ ከተባበሩት መንግስታት ገፅ የተወሰደ






ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Wednesday, December 14, 2016

በጎንደር አቡነ ኤልሳዕ በኮማንድ ፖስቱ ታስረው ተፈቱ:: ሊቀ አዕላፍ ቀለመ ወርቅ አሻግሬ እንደታሰሩ ነው


አቡነ ኤልሳዕ
Ethiopian Orthodox Tewahido Church Bishop (Abune) Elsae was under prison by TPLF command post.

የሰሜ ጎንደር ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የሆኑት ብጹዕ አቡነ ኤልሳዕ በጎንደር ኮማንድ ፖስት ትናንት ታህሳስ 4, 2009 ዓ.ም ከ9፡00 ሰዓት ታስረው የቆዩ ሲሆን ሕዝብ ቁጣውን ሲያሰማ ወዲያውኑ እንደተለቀቁ ሆኖም ግን ከርሳቸው ጋር አብረው ታስረው የነበሩት ሊቀ አዕላፍ ቀለመወርቅ አሻግሬ በኮማንድ ፖስቱ እንደታሰሩ መሆኑን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታወቁ::

አቡነ ኤልሳዕ
===========
የሰሜን ጎንደር ዞን ሀገር ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ ሊቀ አዕላፍ ቀለመ ወርቅ አሻግሬ እንዲሁም ብጹ አቡነ ኤልሳዕን ለ እስር የዳረገው ጉዳይ በጎንደር ሕዝቡ አሁንም በከፍተኛ ቁጣ ላይ በመሆኑና እነዚህ የሃይማኖት አባቶች ከመንግስት የተሰጣቸውን ወጣቱን የማረጋጋትና ከመንግስት ጎን የማሳለፍና የማሳመን ሥራ በተገቢው መንገድ አልሰራችሁም በሚልና የመስቀል በዓል በጎንደር እንዳይከበር አድርጋችኋል በሚል ምክንያት እንደሆነ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል::
አቡነ ኤልሳዕ በኮማንድ ፖስቱ ተይዘው ከታሰሩ በኋላ ሕዝቡ ተከትሎ በመሄድ ቁጣውን በማሰማቱ ወዲያውኑ ሲለቀቁ ለቀ አዕላፍ ቀለመወርቅ አሻግሬ በኮማንድ ፖስቱ ተይዘው እንደታሰሩ ነው:: ሊቀ አዕላፍ ቀለመወርቅ አሻግሬና አቡነ ኤልሳዕ በተጨማሪም በጎንደር ገበሬዎች የህወሓት መንግስት ጋር እየተዋደቀበት ባለበት በዚህ ወቅት ታቦት ይዛችሁ በመውጣት ገበሬውን አሳምኑና ተኩስ እንዲያቆም አድርጉ ተብለው ፈቃደኛ አልሆኑም; ገበሬውንም አላሰመኑም ትግሉን ይደግፋሉ የሚሉ ክሶች እንደቀረቡባቸው የገለጹት ምንጮች በአሁኑ ወቅት ጎንደር በዚህ የተነሳ ውጥረት ውስጥ እንደምትገኝ ገልጸውልናል::

አቡነ ኤልሳዕ ማን ናቸው?
=================
የቀድሞው አባ ኅሩይ ወልደ ሰንበት የአሁኑ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ በ1930 ዓ.ም ተወለዱ ጸዋትዎ ዜማ፣ ቅኔ፣ ትርጓሜ መጻሕፍት፣ ፍትሐ ነገሥት፣ ባሕረ ሐሳብና ሐዲስ ኪዳንን ተምረዋል፡፡ በ1945 ዓ.ም ከብፁዕ አቡነ ሚካኤል ዲቁና በ1964 ዓ.ም ምንኩስናን በደብረ ሊባኖስ ገዳም ተቀብለዋል፡፡ በ1965 ዓ.ም ከብፁዕ አቡነ ሚካኤል ቅስና በ1969 ዓ.ም ከብፁዕ አቡነ ሰላማ ቁምስናን ተቀብለዋል፡፡ በደብረ ጽጌ ገዳም በመዘምርነትና በቅዳሴ አገልግለዋል፡፡ ጥር 13 ቀን 1971 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ እድ የከፋ ሀገረ ስብከት ኤጲስ ቆጶስ ተብለው ተሹመዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው፡፡

ምንጭ = ዘሐበሻ 


ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church is in turmoil in Athens, Greece.

His Holiness Abune Mathias I, Patriarch of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, met with Greece's Ambassador to Ethiopia, Antonios Sg...