ጉዳያችን/ Gudayachn
ታህሳስ 8/ 2009 ዓም ( December 16,2016)
==============================
አንቶንዮ ጉተሬስ (Antonio Guterres) በፈረንጆቹ አቆጣጠር ጥር 1/2017ዓም ሥራ ይጀምራሉ።
የመንግሥታቱ ድርጅት ባለፈው ጥቅምት/ 2009 ዓም ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ አዲስ ዋና ፀሐፊ መርጧል። አዲሱ ዋና ፀሐፊ ፖርቱጋላዊው አንቶንዮ ጉተሬስ በማስፈፀም አቅሙ እየተዳከመ የመጣውን ድርጅት ያነቃቁታል ተብሎ ይታሰባል።የተባበሩት መንግሥታት አዲስ የመዋቅር ለውጥ እንደሚያስፈልገው የምወተውቱ ብዙዎች ናቸው።አሁን ባለው የዓለም ሰላም መታወክ በተለይ በመካከለኛው ምስራቅ የሶርያውን ግጭት ጨምሮ እንደ ሀገር መቆም ያቃታቸው የሊብያ እና የየመን ጉዳይ፣የደቡብ ሱዳን ግጭት እና የሩስያ እና አሜሪካ ውጥረት ሁሉ ድርጅቱን አንቶንዮ ጉተሬስን በስልጣን በሚቆዩባቸው በመጪዎቹ አምስት አመታት ውስጥ ወጥረው የሚይዙ ጉዳዮች ናቸው።ይህ ማለት በእነኝህ አመታት የሚፈጠሩት አዳዲስ ክስተቶች እና ድርጅቱ የገባበት ከፍተኛ የሙስና እና የተዝረከረከ አሰራር ማስተካከልን ጨምሮ ማለት ነው።

አንቶንዮ ጉተርዮስ ማን ናቸው?
- አንቶንዮ ጐርዮስ ሚያዝያ 30፣1949 እኤአ በፖርቹጋሏ ከተማ ሊዝበን ከአባታቸው ቪግሎ ድያስ ጉተረስ እና እናታቸው ካንድዳ ደ ኦልቨራ ተወለዱ። አባታቸው እኤአ በ2009 ዓም አርፈዋል።
- ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቃትን ተከትሎ ለተመሰረተው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዘጠነኛው ዋና ፀሐፊ ናቸው።
- እኤአ ከ1995 እስከ 2002 ዓም የፖርቹጋል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል።
- እኤአ ከ1999 እስከ 2005 ዓም የዓለም አቀፍ ሶሻሊስት (socialist international) ፕሬዝዳንት ነበሩ።
- እኤአ ከ2005 እስከ 2015ዓም የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽነር ሆነው አገልግለዋል።
- ወደ ፖለቲካው ዓለም ከመግባታቸው በፊት ፊዚክስ፣ቴሌኮምኒኬሽን ሲግናል እና ኤሌክትሪክ ኢንጂነሪንግ ተምረዋል።
- ወደ ፖለቲካው የገቡት የኢትዮጵያ አብዮት ሲፈነዳ በ1966 ዓም (1974 እ ኤአ) የፖርቹጋል ሶሻሊስት ፓርቲ አባል በመሆን ነበር።
- በፕሬዝዳንትነት ሀገር የመራ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ ሲሆን የመጀመርያው ሰው ይሆናሉ።
- የካቶሊክ አማኝ እና ዩንቨርስቲ እያሉ የወጣት ካቶሊካውያን ወጣቶች ማለትም ¨የብርሃን ቡድን¨ ¨Group of Light¨ ንቁ ተሳታፊ ነበሩ።
- አንቶንዮ ለእውነት የቆሙ ተብለው ይነገርላቸው ነበር።የፖርቱጋል የቀድሞ ቅኝ ግዛት የነበረችው ምስራቅ ቲሞር ነፃነቷን ማግኘት እንደሚገባት የተሟገቱ ሰው ነበሩ።ለገዛ ሀገራቸው ፖርቱጋል ሳያደሉ እውነት እንደተናገሩ ይነገርላቸዋል።
- የፖርቹጋል፣ስፓኒሽ፣ፈረንሳይኛ እና እንግሊዝኛ አቀላጥፈው ይናገራሉ።
ምንጭ: - የተባበሩት መንግሥታት ድረ-ገፅ፣- ቢቢሲ ዘገባ
ቪድዮ ከተባበሩት መንግስታት ገፅ የተወሰደ
ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com