ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, December 14, 2016

በጎንደር አቡነ ኤልሳዕ በኮማንድ ፖስቱ ታስረው ተፈቱ:: ሊቀ አዕላፍ ቀለመ ወርቅ አሻግሬ እንደታሰሩ ነው


አቡነ ኤልሳዕ
Ethiopian Orthodox Tewahido Church Bishop (Abune) Elsae was under prison by TPLF command post.

የሰሜ ጎንደር ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የሆኑት ብጹዕ አቡነ ኤልሳዕ በጎንደር ኮማንድ ፖስት ትናንት ታህሳስ 4, 2009 ዓ.ም ከ9፡00 ሰዓት ታስረው የቆዩ ሲሆን ሕዝብ ቁጣውን ሲያሰማ ወዲያውኑ እንደተለቀቁ ሆኖም ግን ከርሳቸው ጋር አብረው ታስረው የነበሩት ሊቀ አዕላፍ ቀለመወርቅ አሻግሬ በኮማንድ ፖስቱ እንደታሰሩ መሆኑን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታወቁ::

አቡነ ኤልሳዕ
===========
የሰሜን ጎንደር ዞን ሀገር ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ ሊቀ አዕላፍ ቀለመ ወርቅ አሻግሬ እንዲሁም ብጹ አቡነ ኤልሳዕን ለ እስር የዳረገው ጉዳይ በጎንደር ሕዝቡ አሁንም በከፍተኛ ቁጣ ላይ በመሆኑና እነዚህ የሃይማኖት አባቶች ከመንግስት የተሰጣቸውን ወጣቱን የማረጋጋትና ከመንግስት ጎን የማሳለፍና የማሳመን ሥራ በተገቢው መንገድ አልሰራችሁም በሚልና የመስቀል በዓል በጎንደር እንዳይከበር አድርጋችኋል በሚል ምክንያት እንደሆነ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል::
አቡነ ኤልሳዕ በኮማንድ ፖስቱ ተይዘው ከታሰሩ በኋላ ሕዝቡ ተከትሎ በመሄድ ቁጣውን በማሰማቱ ወዲያውኑ ሲለቀቁ ለቀ አዕላፍ ቀለመወርቅ አሻግሬ በኮማንድ ፖስቱ ተይዘው እንደታሰሩ ነው:: ሊቀ አዕላፍ ቀለመወርቅ አሻግሬና አቡነ ኤልሳዕ በተጨማሪም በጎንደር ገበሬዎች የህወሓት መንግስት ጋር እየተዋደቀበት ባለበት በዚህ ወቅት ታቦት ይዛችሁ በመውጣት ገበሬውን አሳምኑና ተኩስ እንዲያቆም አድርጉ ተብለው ፈቃደኛ አልሆኑም; ገበሬውንም አላሰመኑም ትግሉን ይደግፋሉ የሚሉ ክሶች እንደቀረቡባቸው የገለጹት ምንጮች በአሁኑ ወቅት ጎንደር በዚህ የተነሳ ውጥረት ውስጥ እንደምትገኝ ገልጸውልናል::

አቡነ ኤልሳዕ ማን ናቸው?
=================
የቀድሞው አባ ኅሩይ ወልደ ሰንበት የአሁኑ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ በ1930 ዓ.ም ተወለዱ ጸዋትዎ ዜማ፣ ቅኔ፣ ትርጓሜ መጻሕፍት፣ ፍትሐ ነገሥት፣ ባሕረ ሐሳብና ሐዲስ ኪዳንን ተምረዋል፡፡ በ1945 ዓ.ም ከብፁዕ አቡነ ሚካኤል ዲቁና በ1964 ዓ.ም ምንኩስናን በደብረ ሊባኖስ ገዳም ተቀብለዋል፡፡ በ1965 ዓ.ም ከብፁዕ አቡነ ሚካኤል ቅስና በ1969 ዓ.ም ከብፁዕ አቡነ ሰላማ ቁምስናን ተቀብለዋል፡፡ በደብረ ጽጌ ገዳም በመዘምርነትና በቅዳሴ አገልግለዋል፡፡ ጥር 13 ቀን 1971 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ እድ የከፋ ሀገረ ስብከት ኤጲስ ቆጶስ ተብለው ተሹመዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው፡፡

ምንጭ = ዘሐበሻ 


ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

የመጀመርያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት የነበሩት ክብርት አምባሳደር ሣህለወርቅ ዘውዴን በክብር አለመሸኘት የኢትዮጵያን ክብር ብቻ ሳይሆን ለሴት ልጅ ያለንን የክብር ልኬት የሚያሳይ ነው።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሣህለወቅ ዘውዴ ጉዳዩ የዲሞክራሲ ባሕላችን ያኋልዮሽ ጉዞ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የኢትዮጵያ ታዳጊ ሴትና ወንድ ልጆች የምናስተምራቸው ምንድን ነው? የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሲሰናበቱ እንዴት...