The 1980s Ethiopian famous Athlete Miruts Yifter has died.
ቪድዮ: ምሩፅ ይፍጠር በሞስኮ ኦሎምፒክ 1980 እኤአቆጣጠር 1974 ዓም
ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com
ኃይሌ ገብረ ስላሴ ወደ ሩጫው ዓለም እንዲገባ ምሩፅ ይፍጠር ምክንያት እንደሆነው ደጋግሞ ተናግሯል።ምሩፅ ይፍጠር በሞስኮ ኦሎምፒክ ማሸነፉ የወቅቱ ድል ብቻ ሳይሆን ዛሬ ላሉን አትሌቶች ልባቸው ወደ አትሌቲክስ እንዲሸፍት ያደረገ አኩሪ የኢትዮጵያ አትሌት ነው። ኃይሌ ገብረ ስላሴ ምሩፅ ኦሎምፒክ ያሸነውን በዜና ስሰማ ውስጡ ለአትሌቲክስ ሩጫ መነሳቱን እና እንደ እርሱ በሆንኩ የሚል ምኞት እንዳደረበት በተለያየ ጊዜ በሰጠው ቃለ መጠይቅ ገልጦ ነበር።
ምሩፅ ይፍጠር በተለይ በሞስኮ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ካደረገ በኃላ ስሙ በመላው ኢትዮጵያ እና በዓለም ተናኝቶ ነበር። የሞስኮ ኦሎምፒክ አሸንፎ ሲመጣ ከአየር መንገድ ጀምሮ በግልፅ መኪና ሲገባ በሺህ የሚቆጠር የአዲስ አበባ ነዋሪ በሆታ እና በእልልታ ተቀብሎት ነበር።በወቅቱ ኮለኔል መንግስቱ ቤተ መንግስት ድረስ አስጠርተው ሽልማት አድርገውለታል። ምሩፅ በወቅቱ ከመንግስት ካገኘው ሽልማት ውስጥ የታርጋ ቁጥሯ 00001 የነበረ አዲስ መኪና እና በቦሌ መንገድ ኦሎምፒያ አጠገብ ዘመናዊ የመኖርያ ቪላ ነበሩ።
ምሩፅ በህክምና ሲረዳ ከቆየ በኃላ ማረፉ ተነግሯል። የምሩፅ ይፍጠርን ነፍስ በገነት ያኑርልን።ቪድዮ: ምሩፅ ይፍጠር በሞስኮ ኦሎምፒክ 1980 እኤአቆጣጠር 1974 ዓም
ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com