Wednesday, March 22, 2017

የኦስሎ ዩንቨርሲቲ ምሩቁ የሱማሊያው አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር ማናቸው? ጠ/ሚሩ የካቢኔ አባሎቻቸውን ትናንት አስተዋውቀዋል። Somalian PM announced his cabinet ministers.

የሱማልያው አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚስተር አሊ ካይረ


ጉዳያችን/ Gudayachn 
መጋቢት 13/2009 ዓም (March 22,2017)

የሱማልያው አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚስተር አሊ ካይረ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ከተመረጡ እና በፓርላማ ስልጣናቸው ከፀደቀ ገና ሶስተኛ ሳምንቱን ቢይዝም አዲሱ ካቢናቸውን መስርተዋል።
የመጀመርያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሞቃዲሾ እንደጨረሱ የሚነገርላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር በ1994 ዓም እኤአ በኖርዌይ ዋና ከተማ በሚገኘው የኦስሎ ዩንቨርስቲ ተማሪ የነበሩ እና በሱማሌ ተማሪዎች ህብረት እንቅስቃሴ ጉልህ አስተዋፅኦ እንደ ነበራቸው ለማወቅ ተችሏል። 

በኦስሎ ዩንቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ´ማይነራቸውን´ ሶሾሎጂ የጨረሱ ሲሆን በመቀጠል በኤደንበርግ ቢዝነስ ኮሌጅ( Edinburgh Business School) የማስተርስ ዲግሪ አግኝተዋል። ከምርቃት በኃላ ሚስተር አሊ ካደር ወደ ኦስሎ ተመልሰው በአንደኛ ደረጃ መምህርነት በመቀጠል ደግሞ በኖርወጅያን ስደተኞች ካውንስል (Norwegian Refugee Council) ዋና መስርያ ቤት ውስጥ በአስተባባሪነት ሰርተዋል።በመሃል ለግል ሥራ ካቆሙ በኃላ ተመልሰው ወደ  የኖርወጅያን ስደተኞች ካውንስል መስርያቤት ውስጥ በመግባት ለ9 ዓመታት በማገልገል እስከ ሪጅናል ዳይሬክተርነት ደረጃ  ደርሰው ነበር።በመስርያ ቤቱ ውስጥም በምስራቅ አፍሪካ በተለይ ሰሜናዊ  ኬንያ ውስጥ ሰርተዋል።

በሰሜን ኬንያ በኖርወጅያን የስደተኞች ካውንስል ኃላፊ በነበሩበት ወቅት በነበረው የፀጥታ ችግር የተለያዩ ሃገራት የስራ ባልደረቦቻቸውን በሞት  ያጡ ሲሆን በኃላፊነታቸው ሳብያ የፀጥታ ሁኔታው በሚገባ እንዲጠበቅ አላደረጉም ተብሎ መስርያቤታቸው ሲከሰስ እርሳቸውም በዋናነት  በኖርዌይ ፍርድ ቤት ፊት ቀርበው ነበር።በመቀጠል የሚስተር አሊ ካይረ የስራ መስክ ያመራው  በእንግሊዝ ካምፓኒ ´ሶማ ኦይል´ (Soma Oil) ውስጥ ነበር። ሚስተር አሊ ከእዚህ ወር መጀመርያ ጀምሮ የሱማሌ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዋል።በትናንትናው እለት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲሱን ካቢኔ አስተዋውቀዋል።

በአዲሱ ካቢኔ ውስጥ ስድስት ሴት ሚኒስትሮች ተሹመዋል።ይህ ሁሉ ሆኖ የሱማሌ ሁኔታ ግን ገና መረጋጋት ይጎድለዋል።በትናንትናው እለትም ወደ ቤተ መንግስት የሚያመራ መንገድ ላይ በቆመ አንድ አውቶብስ ላይ የተጠመደ ፈንጅ ፈንድቷል።አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከአሁኑ የሕወሓት አስተዳደር ጋር ያላቸው ግንኙነት የተቀዛቀዘ መሆኑን የሚናገሩ አሉ።ለእዚህም ማስረጃ የሚያደርጉት በሱማሌ የተሾሙ ሹማምንት የመጀመርያ ጉዞ የሚያደርጉት ወደ ኢትዮጵያ ሲሆን ሚስተር አሊ ግን የመጀመርያ ጉዟቸውን ያደረጉት ወደ ሳውዲ አረብያ መሆኑን ነው።


የፕሬዝዳንት አሊ አዲሱ ካቢኔ አባላት ስም ዝርዝር ከእዚህ በታች ይመልከቱ። 


Somalia’s Premier Hassan Ali Khayre on Tuesday announced his cabinet ministers.
Mr. Khayre made the announcement at a press conference in the Somali capital, Mogadishu.

The names of the new ministers are:

  1. Abdi Farah Juha – Interior Minister
  2. Yousuf  Garad Omar – Minister of Foreign Affairs
  3. Mohamed Abukar Islow – Minister of National Security
  4. Jamal Mohamed Hassan – Minister of Planning
  5. Abdirahman Duale Beyle – Minister of Finance
  6. Khadija Mohamed Dirie – Minister of Youth and Sports
  7. Abdirahman Omar Osman – Minister Of Information
  8. Maryan Qasim Ahmed – Minister of Humanitarian Affairs and Disaster Management
  9. Abdirashid Mohamed Abdullahi – Minister of Defence
  10. Abdirahman Dahir Osman – Minister of Education and Higher Education
  11. Abdirahman Hosh Jibril – Minister of Constitutional Affairs
  12. Maryan Aweys Jama – Minister of Ports and Aviation
  13. Abdi Anshur Hassan – Minister of Posts and Technology
  14. Sheikh Nur Mohamed Hassan – Minister of Livestock
  15. Khadro Ahmed Duale – Minister of Trade and Industry
  16. Abbas Sheikh Abdullah Siraaji – Minister of Public Works and Rebuilding
  17. Abdirashid Mohamed Ahmed – Minister of Petroleum and Mineral Resources
  18. Said Hussein Eid – Minister of Agriculture
  19. Fawzia Yusuf Haji Nur – Minister of Health and Social Welfare
  20. Hassan Hussein Haji – Minister of Justice
  21. Saleh Ahmed Jama – Minister of Labour and Employment
  22. Salim Aliyow Ibrow – Minister of Electricity and Water
  23. Iman Abdullahi Ali – Minister of Religious affairs
  24. Deqa Yasin Haji Yousuf – Minister of Women and Human Rights
  25. Abdirahman Abdi Hashi – Minister of Fisheries and Marine Resources 
  26. Mahad Ahmed Guled – Deputy Prime Ministe  

Six of the new ministers are women.

The new cabinet ministers will face a confidence vote in the parliament next days, according to the Somalia’s constitution.



ጉዳያችን GUDAYACHN 

 www.gudayachn.com

Saturday, March 18, 2017

A complicated hero in the war on dictatorship by Samantha Power (video)

Samantha Power is an author and diplomat who served as the United States Ambassador to the United Nations from 2013 to 2017. Power began her career by covering the Yugoslav Wars as a journalist. From 1998 to 2002, she served as the Founding Executive Director of the Carr Center for Human Rights Policy at the Harvard Kennedy School, where she later became the first Anna Lindh Professor of Practice of Global Leadership and Public Policy. She was a senior adviser to Senator Barack Obama until March 2008, when she resigned from his presidential campaign after apologizing for referring to then-Senator Hillary Clinton as "a monster."

Power joined the Obama State Department transition team in late November 2008. She served as Special Assistant to the President and Senior Director for Multilateral Affairs and Human Rights on the National Security Council from January 2009 to February 2013.

Samantha Power studies US foreign policy, especially as it relates to war and human rights. Her books take on the world's worst problems: genocide, civil war and brutal dictatorships. She's the author of a famous memo (in policy circles) suggesting that US foreign policy is utterly broken -- that the United States must return to a human rights-centered foreign policy or risk its prestige and respect in the world community.

Source: TED.com
    
Please note: - This speech was made in 2008 



ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Sunday, March 12, 2017

አሳዛኝ ዜና - በአዲስ አበባ ከልዩ ልዩ ስፍራዎች ቤታቸው በመንግስት የፈረሰባቸው ሰዎች ተጠግተው የሚኖሩበት አካባቢ በደረሰ የቆሻሻ ክምር ናዳ የበርካታ ሰዎች ሕይወት ጠፋ (ፎቶዎች ይዘናል)

Ethiopia - A landslide in the capital, Addis Ababa, kills over 46 people and over 50 are highly injured. Many children's current condition is not yet known. The number of casualties is increasing every time. The report is not yet finalised. 
The place is known by the residence of   people who have been force fully pushed and displaced by the government from different part of Addis Ababa´s residential areas.
በአዲስ አበባ ከልዩ ልዩ ስፍራዎች ቤታቸው በመንግስት የፈረሰባቸው ሰዎች እና ገቢያቸው ዝቅተኛ የሆኑ ነዋሪዎች ተጠግተው የሚኖሩበት አካባቢ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የቆሻሻ አፈር ናዳ ተንዶ ከ40 በላይ በሚጠጉ ቤቶች ላይ በማረፋ ከ46 በላይ ሰዎች ሲሞቱ ከ50 በላይ ሰዎች ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል ገብተዋል፡፡ በርካታ ህፃናትም በአደጋው ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአደጋው ዘገባ ገና እየተጠናከረ ሲሆን የሟቾች እና የተጎዱት ቁጥር እንዳይጨምር ተፈርቷል።ቢቢሲ በአካባቢው ከ150 በላይ ሰዎች በአካባቢው እንደነበሩ እና አያሌ ቤቶች በቶን በሚመዘን የቆሻሻ ክምር መቀበራቸውን ገልጧል። በቅርቡ በአዲስ አበባ ለእረጅም ጊዜ በነዋሪዎች የተያዙ ቦታዎች ላይ የነበሩ ነዋሪዎች እየተፈናቀሉ እንደነበር እና ብዙ ሺዎች ለጎዳና ላይ ሕይወት መዳረጋቸው ይታወሳል።የተቀሩት ደግሞ ዛሬ አደጋ ወደደረሰበት ቦታ ሄደው በቀን በሚያገኙት ገንዘብ እየተከራዩ እና የላስቲክ መጠለያ እየሰሩ መስፈራቸው ይታወቃል።  ለሞቱት ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን።

"የሞቱት ቁጥር ከ200 በላይ ይሆናሉ።እውነቱ እየተነገረ አይደለም" አዋዜ የደረሰው መልዕክት 
የአለምነህ ዋሴን ዘገባ ከእዚህ በታች ያዳምጡ። 



ከእዚህ በታች የምትመለከቱት አደጋው በደረሰበት አካባቢ የተገኙ ፎቶዎች ናቸው።



Above single photo is from BBC (ከእዚህ በላይ ያለው ፎቶ ብቻ ከቢቢሲየተወሰደ)






ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Friday, March 10, 2017

የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ውሳኔ የወጣት ዮርዳኖስን ሕይወት እንዴት እንዳመሳቀለው (እውነተኛ ታሪክ እና ቪድዮ)

እውነተኛ ታሪክ 
ጉዳያችን/ Gudayachn 
www.gudayachn.com 
====================
ዮርዳኖስ ከንግድ ሥራ ኮሌጅ በባንክ እና ፋይናንስ ተመርቃ ሥራ ከያዘች አንድ አመቷ ነው።እንደተመረቀች ሥራ የያዘችው ከኮሌጁ ጎን የሚገኘው ባለ አስራ አንድ ፎቁ የቤቶች እና ቁጠባ ባንክ ነው።ዮርዳኖስ ከስራ በኃላ ቢያንስ በሳምንት ሁለት ቀናት መርካቶ የሚገኘው ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የመዝሙር ጥናት ትሄዳለች።በእየሳምንቱ ቅዳሜ ከሰዓት በኃላ በ8 ሰዓት ላይ በቤተ ክርስቲያኑ የሰንበት ትምሕርት ቤት አዳራሽ የሚዘጋጀው ጉባኤ ከሌሎች የስራ ባልደረቦቿ ጋር መዝሙር ታቀርባለች።ዮርዳኖስ ስለ ብሔር፣ኤርትራ ስለሚባል ሀገር የምታውቀው ነገር የላትም።እቤት አባት እና እናቷ ስለ ፖለቲካ ሲያወሩ ከመስማት በቀር ነገሩ አይገባትም።ለእርሷ ጧት ሥራ መግባት ከስራ በኃላ ከቦርሳዋ ውስጥ የማይለያትን ነጠላዋን ተከናንባ ቤተ ክርስቲያን ተገኝታ ትምህርት መማር ወይንም በመዝሙር ማገልገል ነው።

ዮርዳኖስ በእንዲህ አይነት ሕይወት ላይ እያለች ነው በ1990 ዓም አንድ ምሽት በለሆሳስ ቤተ ክርስቲያን የተማረችውን መዝሙር እየመላለሰች እያዜመች ነበር አዲስ አበባ አሮጌው አይሮፕላን ማረፍያ  አካባቢ ቶታል ሶስት ቁጥር አውቶብስ ማዞርያ የሚገኘው ቤቷ የደረሰችው።የቤቷን የብረት በር ዘበኛው እንዲከፍትላት ደውሉን ለመደወል ስትል በሩ ክፍት መሆኑን ተመለከተች። በልቧ ዘበኛው ሰፈራቸው የሚገኘው ሱቅ ሲሄድ በሩን ገርበብ አድርጎ እንደሚሄድ ስለምታውቅ እንዳይዘጋበት በማሰብ መልሳ ክፍቱን ትታው ወደ ግቢው ዘለቀች።የእናት የአባቷ ግቢ ተተራምሷል። አባቷ ጋቢ እንዳደረጉ በነጠላ ጫማ፣እናቷ እረጅሙን ቢጃማ እንደለበሱ ቆመዋል ስድስት የሚሆኑ ፖሊሶች እና ሶስት ሲቪል የለበሱ ሰዎች ከእናት እና አባቷ ጋር ድምፃቸውን ከፋ አድርገው ይናገራሉ።ሶስቱ ሲቪል ከለበሱት ሰዎች ውስጥ አንዱ " ምንም ልብስ መቀየር ብሎ ነገር የለም።አሁን ሁላችሁም ወደ ቀበሌ! እዝያ ቃላችሁን ሰጥታችሁ ውሳኔው ይነገራል።የመንግሥታችን ትዛዝ ነው " አለ በትግርኛ ቅላፄ በተሞላ አነጋገር።

ዮርዳኖስ ጉዳዩ አልገባትም እናቷ ልጃቸውን ሲያዩ አቅፈዋት ማልቀስ ጀመሩ።ጥቂት ቆይቶ ግቢው በጎረቤት ሰዎች ተሞላ። ጎረቤቱ እየመጣ ዮርዳኖስን፣ወንድሞቿን እና ወላጆቿን እያየ ለቅሶውን አቀለጠው።ዮርዳኖስ የያዘችውን ቦርሳም እንድታስቀምጥ አልተፈቀደላትም በቆመችበት ከወንድሞቿ፣ወላጆቿ ጋር ወደ ቀበሌ ተወሰደች።ጉዳዩ ለካ የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ኤርትራዊ ደም አለባቸው የተባሉ በሙሉ እየተለቀሙ ወደ ኤርትራ እንዲላኩ ስለተወሰነ ጉዳዩ እቤታቸው መምጣቱ ኖሯል።ዮርዳኖስ መጀመርያ ጉዳዩ የመሰላት የሆነ ወንጀል ተፈፅሞ ያንን ለማጣራት የሚደረግ እንደሚሆን አስባ ነበር።ነገሩ ሁሉ ተረጋግቶ ማታ ተመልሳ የምታጠናውን መዝሙር እና ቅዳሜ ስለሚከበረው የመንፈሳዊ ማኅበሯ ጉዳይ እያሰበች ከቤተሰቧ ጋር ፖሊሶቹ መኪና ላይ ወጣች።በልቧ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ነገሩን ሁሉ ለክፉ አታድርጉት ትላለች።ይህ ሁሉ ጉዳይ ለቤተሰቧ ችግር የማያመጣ ከሆነ በመጪው ቅዳሜ ሻማ ይዛ ልትመጣ ለመርካቶ ተክለ ሃይማኖት ተስላለች።ሆኖም ግን ዮርዳኖስ እና ቤተሰቧ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ከቤት እንደ ቀልድ ወደ ቀበሌ እንደወጡ አልተመለሱም።የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ውሳኔ ነው እና በሁለተኛው ቀን ዮርዳኖስ ከ  ወንድሞቿ እና ወላጆቿ ጋር ኤርትራ ወደተባለችው ምድር  ከተባረሩት 70 ሺዎች ውስጥ ተጨምረው ተላኩ። ዮርዳኖስ የሆነው ሁሉ ሕልም እየመሰላት አብራ ተሰደደች።ለምን እና ማን ይህንን ውሳኔ እንደወሰነ አታውቅም።

በወቅቱ ወደ ኤርትራ የተላኩት ተመልሰው ከኤርትራ ወጥተው ወደ ኬንያ፣የመን እና ሱዳን ተሰደዋል።የተሳካላቸው አውሮፓ እና አሜሪካ ገብተዋል።አንዳንዶቹ ዞረው ተመልሰው ኢትዮጵያ የመጡም አሉ። 

ዮርዳኖስ ስነ ልቦናዋም፣የተወለደችውም የምታውቀውም አዲስ አበባን እንጂ ኤርትራ የምትባል ምድር ናፍቃት አያውቅም።የማያውቁት አገር አይናፍቅም እንዲሉ።ሆኖም ግን ሕወሓቶች  እንደ ቀልድ ቢራ ፉት እያሉ የወሰኑት ውሳኔ ከቤቷ በረንዳ ላይ አስይዞ ከልጅነቷ እየመከሩ ያሳደጉ ጎረበቶቿን በእንባ እያራጨ ወደማታውቀው ምድር ገፋት። ይህ እውነተኛ ታሪክ እና እውነተኛ ስም ነው።

ከእዚህ በታች የምታዩት ቪድዮ በወቅቱ በሕወሓት ውሳኔ ከተባረሩት 70ሺዎች ውስጥ ኤርትራ ሲገቡ የነበረውን ሁኔታ ነው።የሚያለቅሱ አሉ፣ስሜታቸውን ማወቅ ያልቻሉ ነበሩ፣ግራ የተጋቡም ብዙዎች ናቸው።አንዳንዶቹ ያልተከፉ በሚመስል ስሜት እጃቸው ያወዛውዛሉ።ምናልባት ለስነ ልቦና እንደሚሆን መገመት ይቻላል እንጂ በእዚህ ወቅት ማንም ከነበረበት ቦታ ሲሄድ የእዛን ያህል ስሜት ሊኖረው አይችልም።ጉዳዩ አሳዛኝ መልኩ ያመዝናል እና።ዮርዳኖስ እና ቤተሰቧ ከእነኝህ ውስጥ ነበሩ ።ተወደድም ተጠላ የዮርዳኖስ ላይ የደረሰውን የዘመናችን የፖለቲካ ምስቅልቅል የሕወሓት የታሪክ ዶሴ ውስጥ ተፅፎ መጪው ትውልድም ሲያነበው ይኖራል።አንብቦ ምን እንደሚል አሁን ለመገመት አይቻልም።




ጉዳያችን GUDAYACHN

www.gudayachn.com

Tuesday, March 7, 2017

አርቲስቶቻችን ትውልድ እያስተማሩ ነው።የአርቲስት ሚካኤል ሚልዮን አርአያነት ያለው ተግባር።

በተለያዩ የፊልም ትወናዎቹ እና ዳይሬክተርነት የታወቀው አርቲስት ሚካኤል ሚልዮን የዘንድሮውን አድዋ በዓል በዓል እንዲሆን ካደረጉት አርቲስቶች ውስጥ ነው።አርቲስቱ በአድዋ በዓል የአባት አርበኞችን የጦር አለባበስ በመልበስ ለተተኪው ትውልድ ታሪኩን በሚገባ እንዲዘክር ከማድረጉም በላይ ከሌሎች የሙያ አጋሮቹ ጋር በመሆን ሕፃናትን ለማስተማር ላከናወነው ተግባር ሊመሰገን ይገባዋል።

ከእዚህ በታች የምታዩት ፎቶ አርቲስት ሚካኤል ሚልዮን በአድዋ በዓል አከባበር ስርዓት ላይ ትዕይንት ሲያሳይ ሲሆን ከስር በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በሰይፉ ሾው ቀርቦ ያደረገውን አጭር ቃለ መጠይቅ ነው።

ፎቶ : - አርቲስት ሚካኤል ሚልዮን በምንሊክ አደባባይ የካቲት 23፣2009 ዓም የአድዋ በዓል ሲከበር ለበዓሉ ታዳሚ ትዕይንት ሲያሳይ 

ቪድዮ :- ሰይፉ ፋንታሁን  በኢቢኤስ ቲቪ ከአርቲስት ሚካኤል ሚልዮን ጋር ያደረገው ቃለ መጠይቅ።






አርቲስት ሚካኤል ሚልዮን በሰይፉ ሾው


ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Saturday, March 4, 2017

በቅርቡ ከተሰደዱት የቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስትያናት አስተዳዳሪ መላከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ወልደ ትንሣኤ አባተ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ


ከኢሳት ቴሌቭዥን የካቲት 23 እና  መጋቢት 2፣ 2017 እኤአ ስርጭቶች  ላይ የተወሰደ 
በቃለ መጠይቁ ላይ ለጥገና ተብሎ የተተከለው ብረት አብያተ ክርስትያናቱ ላይ አደጋ ማንዣበቡ እና ሌሎችም በርካታ ጉዳዮች ተነስተውበታል።
ክፍል አንድ 


ክፍል ሁለት 




ጉዳያችን GUDAYACHN

 www.gudayachn.com

የመስቀል ደመራ በዓል በንግስት ዕሌኒ ሀገር በግሪክ ቅዳሜ መስከረም 16፣2019 ዓም በከፍተኛ ድምቀት ተከብሮ ዋለ።በግሪክ የምትገንኘው የአቴንስ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን ምእመናን ለቅዱስ ሲኖዶስ አቤቱታቸውን ደግመው አቀረቡ።

======== ልዩ ሪፖርታዥ ======== በእዚህ ርዕስ ስር የሚከተሉትን ንዑስ ርዕሶች ያገኛሉ።እነርሱም ፡  የመስቀል ደመራ ለምን ይከበራል? ግማደ መስቀሉ  ወደ  ኢትዮጵያ እንዴት መጣ? የዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል...