Ethiopia - A landslide in the capital, Addis Ababa, kills over 46 people and over 50 are highly injured. Many children's current condition is not yet known. The number of casualties is increasing every time. The report is not yet finalised.
The place is known by the residence of people who have been force fully pushed and displaced by the government from different part of Addis Ababa´s residential areas.

በአዲስ አበባ ከልዩ ልዩ ስፍራዎች ቤታቸው በመንግስት የፈረሰባቸው ሰዎች እና ገቢያቸው ዝቅተኛ የሆኑ ነዋሪዎች ተጠግተው የሚኖሩበት አካባቢ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የቆሻሻ አፈር ናዳ ተንዶ ከ40 በላይ በሚጠጉ ቤቶች ላይ በማረፋ ከ46 በላይ ሰዎች ሲሞቱ ከ50 በላይ ሰዎች ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል ገብተዋል፡፡ በርካታ ህፃናትም በአደጋው ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአደጋው ዘገባ ገና እየተጠናከረ ሲሆን የሟቾች እና የተጎዱት ቁጥር እንዳይጨምር ተፈርቷል።ቢቢሲ በአካባቢው ከ150 በላይ ሰዎች በአካባቢው እንደነበሩ እና አያሌ ቤቶች በቶን በሚመዘን የቆሻሻ ክምር መቀበራቸውን ገልጧል። በቅርቡ በአዲስ አበባ ለእረጅም ጊዜ በነዋሪዎች የተያዙ ቦታዎች ላይ የነበሩ ነዋሪዎች እየተፈናቀሉ እንደነበር እና ብዙ ሺዎች ለጎዳና ላይ ሕይወት መዳረጋቸው ይታወሳል።የተቀሩት ደግሞ ዛሬ አደጋ ወደደረሰበት ቦታ ሄደው በቀን በሚያገኙት ገንዘብ እየተከራዩ እና የላስቲክ መጠለያ እየሰሩ መስፈራቸው ይታወቃል። ለሞቱት ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን።
"የሞቱት ቁጥር ከ200 በላይ ይሆናሉ።እውነቱ እየተነገረ አይደለም" አዋዜ የደረሰው መልዕክት
የአለምነህ ዋሴን ዘገባ ከእዚህ በታች ያዳምጡ።
ከእዚህ በታች የምትመለከቱት አደጋው በደረሰበት አካባቢ የተገኙ ፎቶዎች ናቸው።

Above single photo is from BBC (ከእዚህ በላይ ያለው ፎቶ ብቻ ከቢቢሲየተወሰደ)
ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com