ጉዳያችን/Gudayachn
መጋቢት 14፣2009 ዓም (March 23,2017)
=================
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ስካንዲንቭያን ሀገሮች የሚያደርገውን በረራ የኖርዌይ፣ኦስሎን በመጨመር ከፍ እንዳደረገ በድረ-ገፁ ላይ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።Three new flights to three new destinations (በሶስት ቀናት ውስጥ ሶስት አዳዲስ መዳረሻዎች) በሚል ርዕስ ስር ያወጣውን መግለጫ የዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች እየተቀባበሉት ይገኛሉ።በእዚሁ መግለጫው ላይም መጋቢት 26-28/2017 እኤአ አየር መንገዱ ወደ ኦስሎ፣አንታናናሪቭ እና ቪክቶርያ ፎል በረራ እንደሚጀምር ይገልፃል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአግልግሎት ጥራቱን ጠብቆ ዘመን ተሻጋሪ እንዲሆን የብዙ ኢትዮጵያውያን ምኞት ነው።አየር መንገዱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚታዩበትን አስተዳደራዊ ጣልቃ ገብነቶች እና የሰራተኞቹን ብሶቶች በአግባቡ እንዲያዳምጥ እና ተወዳዳሪነቱን እንዲጨምር አሁንም የብዙ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ያላሰለሰ ምክር እና ምኞት ነው።
ከእዚህ በታች አየር መንገዱ በእዚህ ሳምንት አጋማሽ ላይ ያወጣው መግለጫ ነው።
Three new flights to three new destinations in just three days
March 22, 2017
Africa’s largest airline group, Ethiopian Airlines, is delighted to announce that it has finalized preparations to launch flights to three new destinations – Victoria Falls, Oslo and Antananarivo – within three days, 26-28 March 2017.
....to read more click here
ጉዳያችን GUDAYACHN
www.gudayachn.com