ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Wednesday, March 22, 2017

የኦስሎ ዩንቨርሲቲ ምሩቁ የሱማሊያው አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር ማናቸው? ጠ/ሚሩ የካቢኔ አባሎቻቸውን ትናንት አስተዋውቀዋል። Somalian PM announced his cabinet ministers.

የሱማልያው አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚስተር አሊ ካይረ


ጉዳያችን/ Gudayachn 
መጋቢት 13/2009 ዓም (March 22,2017)

የሱማልያው አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚስተር አሊ ካይረ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ከተመረጡ እና በፓርላማ ስልጣናቸው ከፀደቀ ገና ሶስተኛ ሳምንቱን ቢይዝም አዲሱ ካቢናቸውን መስርተዋል።
የመጀመርያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሞቃዲሾ እንደጨረሱ የሚነገርላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር 1994 ዓም እኤአ በኖርዌይ ዋና ከተማ በሚገኘው የኦስሎ ዩንቨርስቲ ተማሪ የነበሩ እና በሱማሌ ተማሪዎች ህብረት እንቅስቃሴ ጉልህ አስተዋፅኦ እንደ ነበራቸው ለማወቅ ተችሏል። 

በኦስሎ ዩንቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ´ማይነራቸውን´ ሶሾሎጂ የጨረሱ ሲሆን በመቀጠል በኤደንበርግ ቢዝነስ ኮሌጅ( Edinburgh Business School) የማስተርስ ዲግሪ አግኝተዋል። ከምርቃት በኃላ ሚስተር አሊ ካደር ወደ ኦስሎ ተመልሰው በአንደኛ ደረጃ መምህርነት በመቀጠል ደግሞ በኖርወጅያን ስደተኞች ካውንስል (Norwegian Refugee Council) ዋና መስርያ ቤት ውስጥ በአስተባባሪነት ሰርተዋል።በመሃል ለግል ሥራ ካቆሙ በኃላ ተመልሰው ወደ  የኖርወጅያን ስደተኞች ካውንስል መስርያቤት ውስጥ በመግባት ለ9 ዓመታት በማገልገል እስከ ሪጅናል ዳይሬክተርነት ደረጃ  ደርሰው ነበር።በመስርያ ቤቱ ውስጥም በምስራቅ አፍሪካ በተለይ ሰሜናዊ  ኬንያ ውስጥ ሰርተዋል።

በሰሜን ኬንያ በኖርወጅያን የስደተኞች ካውንስል ኃላፊ በነበሩበት ወቅት በነበረው የፀጥታ ችግር የተለያዩ ሃገራት የስራ ባልደረቦቻቸውን በሞት  ያጡ ሲሆን በኃላፊነታቸው ሳብያ የፀጥታ ሁኔታው በሚገባ እንዲጠበቅ አላደረጉም ተብሎ መስርያቤታቸው ሲከሰስ እርሳቸውም በዋናነት  በኖርዌይ ፍርድ ቤት ፊት ቀርበው ነበር።በመቀጠል የሚስተር አሊ ካይረ የስራ መስክ ያመራው  በእንግሊዝ ካምፓኒ ´ሶማ ኦይል´ (Soma Oil) ውስጥ ነበር። ሚስተር አሊ ከእዚህ ወር መጀመርያ ጀምሮ የሱማሌ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዋል።በትናንትናው እለት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲሱን ካቢኔ አስተዋውቀዋል።

በአዲሱ ካቢኔ ውስጥ ስድስት ሴት ሚኒስትሮች ተሹመዋል።ይህ ሁሉ ሆኖ የሱማሌ ሁኔታ ግን ገና መረጋጋት ይጎድለዋል።በትናንትናው እለትም ወደ ቤተ መንግስት የሚያመራ መንገድ ላይ በቆመ አንድ አውቶብስ ላይ የተጠመደ ፈንጅ ፈንድቷል።አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከአሁኑ የሕወሓት አስተዳደር ጋር ያላቸው ግንኙነት የተቀዛቀዘ መሆኑን የሚናገሩ አሉ።ለእዚህም ማስረጃ የሚያደርጉት በሱማሌ የተሾሙ ሹማምንት የመጀመርያ ጉዞ የሚያደርጉት ወደ ኢትዮጵያ ሲሆን ሚስተር አሊ ግን የመጀመርያ ጉዟቸውን ያደረጉት ወደ ሳውዲ አረብያ መሆኑን ነው።


የፕሬዝዳንት አሊ አዲሱ ካቢኔ አባላት ስም ዝርዝር ከእዚህ በታች ይመልከቱ። 


Somalia’s Premier Hassan Ali Khayre on Tuesday announced his cabinet ministers.
Mr. Khayre made the announcement at a press conference in the Somali capital, Mogadishu.

The names of the new ministers are:

  1. Abdi Farah Juha – Interior Minister
  2. Yousuf  Garad Omar – Minister of Foreign Affairs
  3. Mohamed Abukar Islow – Minister of National Security
  4. Jamal Mohamed Hassan – Minister of Planning
  5. Abdirahman Duale Beyle – Minister of Finance
  6. Khadija Mohamed Dirie – Minister of Youth and Sports
  7. Abdirahman Omar Osman – Minister Of Information
  8. Maryan Qasim Ahmed – Minister of Humanitarian Affairs and Disaster Management
  9. Abdirashid Mohamed Abdullahi – Minister of Defence
  10. Abdirahman Dahir Osman – Minister of Education and Higher Education
  11. Abdirahman Hosh Jibril – Minister of Constitutional Affairs
  12. Maryan Aweys Jama – Minister of Ports and Aviation
  13. Abdi Anshur Hassan – Minister of Posts and Technology
  14. Sheikh Nur Mohamed Hassan – Minister of Livestock
  15. Khadro Ahmed Duale – Minister of Trade and Industry
  16. Abbas Sheikh Abdullah Siraaji – Minister of Public Works and Rebuilding
  17. Abdirashid Mohamed Ahmed – Minister of Petroleum and Mineral Resources
  18. Said Hussein Eid – Minister of Agriculture
  19. Fawzia Yusuf Haji Nur – Minister of Health and Social Welfare
  20. Hassan Hussein Haji – Minister of Justice
  21. Saleh Ahmed Jama – Minister of Labour and Employment
  22. Salim Aliyow Ibrow – Minister of Electricity and Water
  23. Iman Abdullahi Ali – Minister of Religious affairs
  24. Deqa Yasin Haji Yousuf – Minister of Women and Human Rights
  25. Abdirahman Abdi Hashi – Minister of Fisheries and Marine Resources 
  26. Mahad Ahmed Guled – Deputy Prime Ministe  

Six of the new ministers are women.

The new cabinet ministers will face a confidence vote in the parliament next days, according to the Somalia’s constitution.



ጉዳያችን GUDAYACHN 

 www.gudayachn.com

በኢትዮጵያ የእገታ ወንጀል ተሳታፊ አራት አካላት ናቸው። ለችግሩ የመፍትሄ አካላት ሁለት ናቸው።ሁለቱ አካላት ምን ይስሩ?

======= ጉዳያችን ======= በኢትዮጵያ ዜጎችን እያገቱ ገንዘብ የሚቀበሉ ወንጀለኞች ከተራ ወንጀለኝነት አልፎ በታጣቂ ቡድኖች የገንዘብ ማግኛነት መዋል ብቻ ሳይሆን ዜጎችን የማሸበርያ ፋሺሽታዊ ተግባር ሆኗል። እገታ የ...