ወደ የሚፈልጉት ቋንቋ ይቀይሩ Translate to different Languages

Tuesday, March 7, 2017

አርቲስቶቻችን ትውልድ እያስተማሩ ነው።የአርቲስት ሚካኤል ሚልዮን አርአያነት ያለው ተግባር።

በተለያዩ የፊልም ትወናዎቹ እና ዳይሬክተርነት የታወቀው አርቲስት ሚካኤል ሚልዮን የዘንድሮውን አድዋ በዓል በዓል እንዲሆን ካደረጉት አርቲስቶች ውስጥ ነው።አርቲስቱ በአድዋ በዓል የአባት አርበኞችን የጦር አለባበስ በመልበስ ለተተኪው ትውልድ ታሪኩን በሚገባ እንዲዘክር ከማድረጉም በላይ ከሌሎች የሙያ አጋሮቹ ጋር በመሆን ሕፃናትን ለማስተማር ላከናወነው ተግባር ሊመሰገን ይገባዋል።

ከእዚህ በታች የምታዩት ፎቶ አርቲስት ሚካኤል ሚልዮን በአድዋ በዓል አከባበር ስርዓት ላይ ትዕይንት ሲያሳይ ሲሆን ከስር በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በሰይፉ ሾው ቀርቦ ያደረገውን አጭር ቃለ መጠይቅ ነው።

ፎቶ : - አርቲስት ሚካኤል ሚልዮን በምንሊክ አደባባይ የካቲት 23፣2009 ዓም የአድዋ በዓል ሲከበር ለበዓሉ ታዳሚ ትዕይንት ሲያሳይ 

ቪድዮ :- ሰይፉ ፋንታሁን  በኢቢኤስ ቲቪ ከአርቲስት ሚካኤል ሚልዮን ጋር ያደረገው ቃለ መጠይቅ።






አርቲስት ሚካኤል ሚልዮን በሰይፉ ሾው


ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

ህወሓት ሰሜን ወሎ ራያን ወርሮ የገጠር ወረዳዎችን እየዘረፈ ነው። ህዝብ ሲዘረፍ እና በአስር ሺዎች ሲፈናቀሉ የመንግስት የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊው አመራሮች ዝምታቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም።

በሰሞኑ የህወሓት ወረራ ቆቦ ተፈናቅለው የገቡ የሰሜን ወሎ ተፈናቃዮች  በከፊል ፎቶ፡ ቢቢሲ ሚያዝያ 20፣2024 እኤአ ''ቅጥ አምባሩ የጠፋው'' የፕሪቶርያው ውል   ''ስኩዌር ዋን&#...