Monday, August 15, 2016

ከሰባቱ የህወሓት መስራቾች አንዱን ጨምሮ 16 የትግራይ ተወላጆች መግለጫ አወጡ።''ህወሓት ስልጣኑን ይልቀቅ የሽግግር መንግስት ይመስረት'' ብለዋል።



TPLF is at the beginning of the end.
Including the founder of TPLF, former first commander of its army and Ethiomedia editor plus other 13 Tigray province born Ethiopian issued statement. The statement demanded an immediate removal of TPLF from power and establishment of transitional Government in Ethiopia. See the Amharic version of the statement here below.

የመጀመርያው ህወሓትን ከመሰረቱት ውስጥ ዶ/ር አረጋዊ በርሄን እና የመጀመርያው የህወሓት ኮማንደር አቶ ተስፋዬ አፅብሃ   ጨምሮ አስራ ስድስት የትግራይ ተወላጆች ህወሓት ስልጣን እንዲለቅ እና የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት በይፋ ጠይቀዋል።ሌሎች የክልሉ ተወላጆችም እንዲቀላቀሏቸው ጠይቀዋል።መግለጫውን ዘሐበሻ በድረ-ገፁ ላይ ያሰፈረውን ከእዚህ በታች ይመልከቱ።


ከትግራይ ተወላጆች የተሰጠ መግለጫ 8 ነሓሴ 2008
በአጠቃላይ ለ25 ዓመታት ሙሉ ህዝባችንን አፍኖ ሲገዛ የቆየና፣ ለ40 ዓመታት ሰላማዊ ዜጎችን እየረሸኑ አገራችንን እየዘረፉ የቆዩ ባለስልጣኖች ያሉበት ህወሓት/አህአዴግ በተለይ በዚህ ዓመት በኦሮሞና በአማራ ህዝባችን ላይ ጦርነት ከፍቷል። የአገዛዙን የግድያ ወንጀሎች እናወግዛለን፤ የህዝቡን ተቃውሞ እንደግፋለን።
ስለዚህ በአገራችን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲገነባ፣ የህዝባችን አንድነት እንዲጠናከርና የአገራችን ሉኣላዊነት እንዲከበር᎓-
1. ህወሓት/ኢህአዴግ ከስልጣን መወገድ አለበት
2. በኢትዮጵያውያን የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ሲቪክ ማህበሮችና ብቃት ባላቸው ግለሰቦች የሽግግር
መንግስት መቋቋም አለበት።
ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን ዓላማዎች ለማሳካት የሚከተለውን ጥሪ እያቀረብን ፣ እኛም ከህዝባችን ጐን ተሰልፈን ለትግሉ መሳካት የአቅማችንን እንደምናበረክት ቃል እንገባለን።
1. ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ተባብሮና ፋታ ሳይሰጥ አፋኙን አገዛዝ እንዲያስወግድ፣
2. በሰላማዊ ህዝብ ውስጥ የእርስ በርስ ደም መፋሰስ እንዳይከሰት ጥንቃቄ እንዲደረግ፣
3. ሰራዊቱና ሌሎች የመንግስት ታጣቂዎች በህዝባቸው ላይ እንዳይተኩሱ፣
4. ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ካለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ትግሉ እንዲጠናከር፣
5. የትግራይ ህዝብ በራሱ ላይ ብዙ ግፍ የሚፈፅመውንና በስሙ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን
የሚጨፈጭፈውን ህወሓት አውግዞ ከኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ጎን እንዲሰለፍ
በተጨማሪ ነፃነት ባላቸው አገሮች ውስጥ እየኖሩ የግፍ ስርዓቱን ዕድሜ ለማራዘም የሚሞክሩት ግለ ሰቦች፣ በተለይም የህወሓት ደጋፊዎች አደብ ካልገዙ የኢትዮጵያ ህዝብ አንደሚፋራዳቸው እንዲያውቁ፣ ማሳሰብ እንፈልጋለን።
የስም ዝርዝር᎓
1. ህይወት ተሰማ
2. ሕሉፍ በርሀ
3. ስልጣን ኣለነ
4. በየነ ገብራይ
5. ተስፋዬ መሓሪ
6. ተስፋይ ኣፅብሃ
7. ታደሰ በርሀ
8. ነጋሲ በየነ
9. ናትናኤል ኣስመላሽ
10. ዶክተር ኣረጋዊ በርሀ
11. ኣብራሃ በላይ
12. ኪዳነማርያም ፀጋይ
13. ካሕሳይ በርሀ
14. ዘልኣለም ንርአ
15. ደስታ ኣየነው
16. ዶክተር ግደይ ኣሰፋ
በዚህ መግለጫ ይዘት ሊስማሙ ከሚችሉ ሰዎች ጋር በሙሉ ስላልተነጋገርን በዚህ የሚስማሙ ስሞቻቸውን ወደሚከተለው ኣድራሻ ከላኩልን መግለጫውን በድጋሚ እናወጣዋለን᎓:
ethiocivic@gmail.com



ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Friday, August 12, 2016

ሰበር ዜና - አርበኞች ግንቦት 7 እና ኦሮሞ ዲሞክራቲክ ግንባር ጥምረት ፈጠሩ። Breaking News Ethiopia - Patriotic Ginbot 7 for Unity and Democracy (PG7) and the Oromo Democratic Front (ODF) formed an alliance.







የአርበኞች ግንቦት 7 እና በአቶ ሌንጮ የሚመራው የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ግንባር ጥምረት መመስረታቸውን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን በሰበር የእንግሊዝኛ ዘገባው ዛሬ ገልጧል።ስምምነቱን በአርበኞች ግንቦት7 በኩል ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ሲፈርሙ በኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር በኩል አቶ ሌንጮ ለታ ፈርመዋል።
እንደ ኢሳት የእንግሊዝኛ  ዘገባ  ጥምረቱ  ሶስት መርሆዎችን ይዟል። ከብዙ በጥቂቱ ከመርሆዎቹ ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል-
1/ ኢትዮጵያ የበርካታ ብሔረሰቦች እና ሃይማኖቶች አገር መሆኗን፣ መንግስት የሁሉንም የማንነት መብት በእኩልነት እና መከባበር ላይ በመመስረት ማንፀባረቅ  እንዳለበት እና ሁለቱ ድርጅቶችእኩልነት እና የህዝብ አንድነት፣ማህበራዊ ፍትህ፣እኩልነት፣ዜግነት፣ኢኮኖሚያዊ ብልፅግና እና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ያረጋገጠ እውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ፈድራሊዝም ግንባታ ላይ ለመስራት፣
2/ ሁሉም አይነት የፖለቲካ ኃይሎች በነፃ የህዝብ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን፣አምባገነናዊ ስርዓት እንዲያከተም ለማድረግ፣ነፃ ምርጫ ለማስፈን እና ዲሞክራሲያዊ የስልጣን ሽግግር እንዲሰፍን ለማድረግ እና 
3/ ነፃነት፣ፍትህ፣እኩልነት እና ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ ለማስፈን።የመቻቻል፣የውይይት እና ልዩነትን ግልፅ እና ክፍት በሆነ ውይይት መፍታት። የሚሉት በሶስቱ የጥምረቱ መርሆዎች ውስጥ የተጠቀሱ ናቸው።ዝርዝር ስምምነቱን ይዘት ለመመልከት ከእዚህ በታች በእንግሊዝኛ የተፃፈውን ዘገባ ይመልከቱ።
ከእዚህ በታች ያለው ፅሁፍ የተወሰደው ከኢሳት የእንግሊዝኛ ድረ-ገፅ ነው።
Patriotic Ginbot 7 for Unity and Democracy (PG7) and the Oromo Democratic Front (ODF) announced that they have formed an alliance. The Memorandum of Understanding was signed by Prof. Berhanu Nega and Leenco Lataa representing their respective organizations.
Following is the full text of the MoU.
Memorandum of Understanding (MoU) Oromo Democratic Front (ODF) and Patriotic Ginbot 7 (PG7)
August 11, 2016
After several candid discussions and careful considerations of the current political, social, economic and humanitarian situations in Ethiopia, and all the damages caused by successive regimes and the TPLF/EPRDF regime in particular on the welfare and national interests of the peoples of Ethiopia and the security and sovereignty of our country, the ODF and PG7 have made important observations and conclusions. The longer the current regime is allowed to stay in power, the harsher will be the pain, suffering and humiliation endured by the peoples of Ethiopia. Therefore, both parties are fully convinced that a transition from the current TPLF regime towards a new and genuinely federal and democratic state is of utmost urgency.
Both organizations take note of the fact that millions of people in Oromia for the last nine months, and now in the Amhara regions, as well as in the south, coming out and protesting in massive show of defiance, just a few months after the regime claimed a 100 percent victory in the sham elections it conducted in May 2015, and the manner of its reaction to the legitimate popular protests, demonstrate beyond doubt that the regime has lost any semblance of legitimacy. We believe that the mass killings, brutality, and inhuman treatment perpetrated by the TPLF regime against the peaceful protesters are enough indications that the Woyyane clique is determined to control all spheres of life in Ethiopia by sheer use of force and cling to power at all costs. The regime’s unwillingness to function in a multi-party political environment, provided for in its own tailor made constitution, and unabated repression and brutal killings in all parts of Ethiopia, harassment and persecution of the legal opposition, civil society and journalists, as well as gross abuse of power, looting of public and state resources demonstrate that the regime has closed all political space and avenues for reform. Therefore, ODF and PG7 firmly believe that the people have no other choice to end this tyranny and humiliation, but to engage in a concerted and coordinated mass democratic movement, popular uprisings, and rebellion to bring an end to repression, economic exploitation, national humiliation, tyranny, and dictatorship.
ODF and PG7 are mindful of the long standing call of the Ethiopian peoples for unity of all opposition political organizations and their strong desire to see that the different political and civic organizations coordinate their efforts and resources to bring an end to the illegitimate and tyrannical regime. Towards this end, the two organizations pledge to work jointly to bring all credible opposition political groups together into a broad democratic coalition.
Therefore, believing that a coalition of the Ethiopian democratic and liberation forces is the only alternative to get rid of the dictatorial regime and to create a truly united and genuinely democratic federation in Ethiopia, where justice, peace, equality, freedom, and economic prosperity prevail, ODF and PG7 have agreed on this day, August 11, 2016, to form an alliance on the basis of the following three cardinal principles. 
  1. Ethiopia being a multinational, multilingual and multi religious country, the state should respect and equitably reflect all its identities. The two organizations shall strive to build a truly democratic federal state, which promotes and guarantees the equality and unity of its peoples on the basis of social justice, equality, citizenship, economic prosperity, and protects and safeguards the sovereignty of the country.
  1. Bring an end to tyranny, dictatorship, and exclusive monopoly of political and economic power in Ethiopia, and lay the foundation for a democratic system where political power at all levels of government is subject to the free will of the people. All member organizations of the alliance and future coalition shall agree that genuinely free and fair elections are the only path to power. The primary objective of the alliance shall be bringing an end to tyranny and paving the way and laying the ground work for a democratic transition of power.
  1. The paramount purpose of the alliance is to achieve the prevalence of freedom, justice, equality and democracy in Ethiopia, and the empowerment of the people. Hence alliance and future coalition members shall not use minor policy differences to hinder these noble goals. Once they are empowered, the people shall be the ones who decide on alternative political, economic and social policies. The alliance and coalition members shall promote a culture of tolerance and dialogue and resolution of differences through frank and open discussions.
Both organizations, ODF and PG7, have agreed to form a joint working group, composed of representatives from each organization, to undertake all duties of coordinating different tasks as assigned by the agreements between the leaderships of the two organizations. 
Justice and Freedom for all!

Signed:

Leenco Lataa, President   , Oromo Democratic Front (ODF)

Birhanu Nega, Chairman, Patriotic Ginbot 7 (PG7)



ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

Wednesday, August 10, 2016

የነፃነት ትግሉ ዓለም አቀፍ ትኩረት ስቧል።ትግሉን እስከ ነፃነት በመግፋት ዕድሉን እንጠቀምበት።



ኢትዮጵያ የሃያ አንደኛ ክፍለ ዘመን አዲስ ትውልዷ በፀረ ወያኔ የትግል መንፈስ በአዲስ መልክ ነፃነት ወይንም ሞት! ብሎ ተነስቷል።የህወሓት ወያኔ ቡድን በጎጥ ተጠራርቶ ኢትዮጵያን ዳግም በባርነት ቀንበር ለመተብተብ በንፁሃን ኢትዮጵያውያን ገላ ላይ አዲስ ሳንጃ ወድሯል።በሺህ የሚቆጠሩትን ደም በከንቱ አፍስሷል።ብዙዎችን አካለ ስንኩላን አድርጎ የቤተሰብ ሸክም ሆነዋል።ሌሎች ሚልዮኖችን ከሀገር አሰድዷል፣በገዛ አገራቸው የበይ ተመልካች ሆነዋል።
በአንፃሩ ግን ህወሓት ለአድር ባይ እና ለመንደሩ ሰዎች ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ሻንጣ ተሸካሚ እስከ ከፍተኛ የንግድ ሥራ ድረስ በአንድ ጎጥ ሰዎች አስይዞ ኢትዮጵያን የቅምጥል ህወሐታውያን እና የበይ ተመልካች ዜጎች በሚል ከፋፍሏታል።

ከወራት በፊት በኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን የተነሳው ሕዝባዊ አመፅ እና ባለፉት ሳምንታት በጎንደር እና ጎጃም የተነሱት ፀረ ወያኔ ንቅናቄዎች የመላው ዓለምን ትኩረት ስቧል።ይህ ለነፃነት ትግሉ ትልቅ አስተዋፅኦ አለው።ላለፉት ሃያ አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ የትኛውም ክፍል የተደረጉ ፀረ ወያኔ እንቅስቃሴዎች ከአለፈው 1997 ዓም ወዲህ የአሁኑን ያህል የዓለምን ትኩረት ስቦ አያውቅም።በኢትዮጵያ የሥርዓት ለውጥ እንደሚመጣ እና ሁኔታዎች እንዳሉ ሊቀጥሉ እንደማይችሉ ዓለም አቀፍ ሚድያዎች ብቻ ሳይሆን ከወያኔ ጋር የጥቅም ሽርክና ያላቸው መንግሥታትም ተረድተውታል። ይህ ማለት ግን የወያኔ ስርዓት አብቅቶለታል ማለት አይደለም።እያንዳንዱ ግለሰብ የእኔ አስተዋፅኦ ምንድነው? ብሎ መጠየቅ እና ለተግባራዊ ሥራ መነሳት አለበት። በምንም አይነት ሁኔታ ግን ወያኔ በመግደል ብዛት እድሜውን ለጥቂት ጊዜ እየተንገታገተ ያቆይ ይሆናል እንጂ በስልጣን እርከን የመቆየቱ ሁኔታ ግን አብቅቶለታል።

ዓለም ስለኢትዮጵያውያን የነፃነት ትግል ምን አሉ?

           ''የኢትዮጵያ መንግስት በመቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን እየገደለ የምዕራቡ ዓለም ለምንድነው እርዳታ የሚሰጠው?'' ዋሽንግተን ፖስት ጁላይ 9/2016 
''Ethiopia’s regime has killed hundreds. Why is the West still giving it aid?'' Washington post July 9,2016.
/////////////////////////////
''ሰኞ እለት ተቃዋሚ መሪዎች እና አምነስቲ ኢንተርናሽናል እንዳሳወቁት በሳምንቱ መጨረሻ በመላ አገሪቱ በተደረገ ተቃውሞ  የኢትዮጵያ የፀጥታ ኃይሎች አያሌ ሰዎችን ገደሉ።በመንግስት በኩል መደነባበሩ እየጨመረ ነው።'' 
''Ethiopian security forces shot dead several dozen people in weekend protests across the country as frustration with the government grows, an opposition leader and Amnesty International said Monday'' New York times, August 9,016.

//////////////////////////////////////////////////////

''ኦባማ ከጎበኙአት አንድ ዓመት የሆናት ኢትዮጵያ በተቃውሞ እየተናጠች ነው'' ዋሽንግተን ፖስት፣ኦገስት 9፣2016
''A year after Obama’s visit, Ethiopia is in turmoil'' Washington Post, Augest 9,2016
///////////////////////////
''የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በኦሮምያ እና አማራ መንግስት ለተጠቀመውን ከመጠን ያለፈ ኃይል በገለልተኛ አካል መመርመር አለበት''  ሮይተርስ ኦገስት 10፣2016 
''U.N. High Commissioner for Human Rights, said that allegations of excessive use of force across the Oromiya and Amhara regions must be investigated''
//////////////////////////////////////////////////

የአውሮፓ ህብረት  ኦገስት 10/2016 ጉዳት ለደረሰባቸው ሁሉ ማዘኑን ገልጦ ባፋጣኝ ሰላም የሚመጣበት መንገድ እንዲፈለግ ይጠይቃል።
//////////////////////////////////////////////////
የአሜሪካ ኢምባሲ ሰኞ ኦገስት 8/2016 ባወጣው መግለጫ በአመፁ ለደረሰው ጉዳት ማዘኑን ገልፆ ጉዳዩ እንዳሳሰበው ይገልጣል። 
/////////////////////////////////////////////////

ከእዚህ በተጨማሪ ቢቢሲ በተደጋጋሚ፣አልጀዝራ፣ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ፣ ሮይተርስ ተቃውሞውን አስመልክቶ ህወሓት ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ እንደገባ ኢትዮጵያም በብዙ ውጥረት ውስጥ እንዳለች ፅፈዋል።
////////////////////////////////////////////////

በሌላ በኩል የእንግሊዝ መንግስት ዶ/ር አርከበ ዕቁባይን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናትን አስጠርቶ እንግሊዝ የኢትዮጵያ ሁኔታ በእዚሁ ከቀጠለ አዲስ አበባ የሚገኝ ኤምባሲዋን እንደምትዘጋ መግለጧን ኢሳት በነሐሴ 3/2008 ዓም  ዜናው ገልጧል። 

ባጠቃላይ ከላይ የተጠቀሱት ለናሙናነት የቀረቡት ዘገባዎች በሙሉ በሶስት ቀናት ውስጥ ብቻ የወጡ ዘገባዎች ናቸው።ይህ የሚያሳየው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዲሞክራሲ፣ፍትህ እና ነፃነት የሚያደርገው ትግል ከፍተኛ ደረጃ መድረሱን ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፍ ሕጋዊ እውቅና እያገኘ መምጣቱን ነው። ይህ ለትግሉ ትልቅ ዕድል ነው። የፖለቲካ ድርጅቶችም ሆኑ በአገር ቤት እና በውጭ የሚኖር እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ትግሉን በሁሉም አቅጣጫ ማስፋፋት እና ወደ ግብ የማድረስ ኃላፊነት አለበት።


ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

ዝም ያለ ከተስማማ እኩል ይቆጠራል።በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚኖረውን የትግራይን ሕዝብ ይመለከታል (የጉዳያችን ማስታወሻ)



ህወሓት ከመነሻው ጀምሮ ግድያ የጀመረው በትግራይ ሕዝብ ላይ ነበር።የትግራይ ሽማግሌዎች ''የፊውዳል እና የነፍጠኛ አምላኪ'' እየተባሉ በህውሃት ግልፅ እና ስውር የግድያ መንገድ ተፈጅተዋል።የህወሓትን እንቅስቃሴ በቀዳሚነት የተቃወመ የትግራይ ሕዝብ ነበር።የአክሱም እና ተንቤን ሕዝብ ህወሓትን ደግፎ ቆሞ አያውቅም ነበር።ህወሓት በማኔፌስቶው ላይ '' የትግራይ ሕዝብ ትግል ፀረ-አማራ፣ ፀረ-እምፔራሊዝም እና ፀረ ንዑስ ከበርቴ'' መሆኑን ከገለፀ በኃላ አላማውም ''የትግራይ ሪፑብሊክ መመስረት ነው'' ይላል። ይህንን አባባል በመጀመርያ ላይ የተቃወሙት እና ለሰማዕትነት የደረሱት የትግራይ ወጣቶች እና አረጋውያን ነበሩ።ይህ ሁኔታ እስከ 1983 ዓም ሲቀጥል የአክሱም እና ተንቤን ሕዝብ በተለይ በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ጉዳይ ህወሓትን በእየቦታው ሲሞግቱ የነበሩ አሁንም የትግራይ አዛውንት ነበሩ።በ1990 ዓም የተቀሰቀሰው የኢትዮ-ኤርትራ ግጭት ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለሰንደቅ አላማው እና ለኢትዮጵያዊነቱ ያሳየው ፅናት (ህወሓት ኢትዮጵያውያንን በአደባባይ ሲዋሹ ቢታዩም) ለትግራይ ሕዝብ ሰንደቅ አላማ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ዳግም ያረጋገጠ ታሪካዊ አጋጣሚ ነው።  

በ1968 የወጣው የህወሓት ማኔፈስቶ -

ኢትዮጵያውያን የህወሓት የጎጥ ፖለቲካ አይን ያወጣ ቢሆንም ሁሉን ችለው ኢትዮጵያዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ብቻ ሲያተኩር ቆይቷል።አቶ መለስ ሕይወት ሲያልፍ የአዲስ አበባ ሕዝብ ትግራይ ተወለዱ ኤርትራ ሳይል ከአየር መንገድ አስከሬን አጅቦ የወጣው ሕዝብ በኢትዮጵያ ላይ የተፈፀመውን ድርጅታዊ ወንጀልን ማንም እረስቶት አይደለም።በመላው ኢትዮጵያ ለቀናት የዘለቀ ሃዘን ሲታወጅ የኢትዮጵያ ሕዝብ በጨዋነት ቀናቱን በዝምታ አሳልፏል።
ይህ ሁሉ የሚያሳየን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሚገባው በላይ ጨዋ ሕዝብ መሆኑን ነው።ህወሓት ከጎንደር እና ዓለም ከተማ የመብራት ትራንስፎርመር በምሽት ሊሰርቅ እጅ ከፍንጅ የያዘው ሕዝብ የዘር አድልዎ እንደተደረገበት እያየ በአርምሞ አሳልፏል።በያዝነው ዓመትም በአርማጮ እና ወልቃይት ሕዝብ ላይ ህወሓት ከአድዋ እና ሽሬ እናቶችን በመኪና አመላልሶ ጠብመንዣ እያስያዘ በአማራው ሕዝብ ላይ ሁለት ጊዜ በሰልፍ ሲዝቱ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በዜና እወጃው ሲያሳይ የትግራይ ሕዝብ ይቃወማል ተብሎ ይጠበቅ ነበር።

ባለፈው ሳምንት መጨረሻም ጎንደር እና ጎጃም ላይ በህወሓት ሰራዊት ግልፅ የሆነ ወረራ ተፈፅሟል።እስከ አሁን ድረስ እንደ ሁማን ራይት ዘገባ ከአንድ መቶ በላይ ሕዝብ ተገድሏል።በሆስፒታል የሚገኙ በከባድ ሁኔታ የቆሰሉ ደግሞ ከ500 በላይ እንደሆኑ እና ከእነኝህ ከቆሰሉት ውስጥ አሁንም የሞቱት አስከሬን እየወጣ መሆኑ ይታወቃል።አሁንም ከትግራይ ሕዝብ በህወሓት ላይ የተሰማ ተቃውሞ የለም።


ይህ ብቻ አይደለም ዛሬ ሮብ ነሐሴ 4/2008 ዓም ከባህር ዳር እና ጎንደር የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከመቀሌ በአንቶኖቭ አይሮፕላን የመጡ የአጋዚ ወታደሮች ወደ ጎንደር እና ባህርዳር ገብተዋል።ይህም ግልፅ የሆነ የጅምላ ፍጅት ህወሓት ልትፈፅም መሆኑን አመላካች ነው።ይህንንም የሚቃወም የትግራይ ሕዝብ ሰልፍ አልታየም።

ስለሆነም የትግራይ ተወላጅ እስካሁን እየሆነ ላለው ሁሉ ግልፅ ተቃውሞ በህወሓት ላይ ሲያሳይ አይታይም።ይልቁንም በማህበራዊ ድረ-ገፆች ላይ  የትግራይ ተወላጅ መሆናቸውን የሚናገሩት ''ትግራይ ኦንላይን'' እና ''አይጋፎረም'' በገፃቸው ላይ የሚፅፉት አማራውን እና ኦሮሞውን የሚያጣጥሉ እና ንቀት የሚያሳዩ ፅሁፎችን ነው።እነኝህ ድረ-ገፆች አላስፈላጊ ፅሁፎችን ሲለጠፉ አሁንም ከትግራይ በኩል ተቃውሞ የሚያሳይ አንድም የጎላ ድምፅ አልተሰማም።

ባጠቃላይ የትግራይ ሕዝብ ህወሓት ለሚሰራው ግፍ እና አገራዊ ወንጀል ሁሉ ዝም ማለት የለበትም።በእራሱ በትግራይ ህወሓትን የሚቃወም ሕዝብ ለማየት የኢትዮጵያ ሕዝብ እየናፈቀ ነው። አሁን ባለንበት ሰዓት የኢትዮጵያ ሰራዊት ውስጥም ግልፅ የሆነ መለያየት እየታየ ነው።ሰራዊቱ ውስጥ የትግርኛ ተናጋሪ እና ሌላ አካባቢ የመጡ በጥይት እርስ በርስ እንደተጋደሉ ተሰምቷል።ሰራዊቱ ከቀናት ምናልባትም ከሰዓታት በኃላ ሰራዊቱ አፈሙዙን በአቶ አባይ ወልዱ ቅልብ ሰራዊት ላይ እንደሚያዞር ምንም  ጥርጥር የለውም።የትግራይ ሕዝብ ግን የወገኖቹ መጨፍጨፍ እንዳልሰማ ዝም ሊል አይገባም። ይህ ሁኔታ ሁላችንም  አላስፈላጊ ወደ ሆነ መሰረታዊ የአስተሳሰብ ለውጥ ውስጥ እንዳያስገባን እና በግለሰቦች የተፈፀመብን የዘር አድልዎ ወደ ከፋ ድምዳሜ እንዳያደርሰን ያሰጋናል። ነገን አርቆ ማሰብ ለእራስ ነው።የትግራይ ሕዝብ ከእዚህ ሁሉ ውጥንቅጥ ውስጥ ሊወጣ የሚችልበት ቀላሉ መንገድ ህወሓትን መቃወም እና ፋሽሽታዊ አስተሳሰብ ከተፀናወታቸው አባይ ወልዱን እና ግብረ አበሮቻቸውን በቁጥጥር ስር በማዋል እና መሰረታዊ አገራዊ ፖለቲካዊ፣ምጣኔ ሃብታዊ ለውጦች ላይ እና እኩል ተጠቃሚነት ላይ ሲስማማ ብቻ ነው።ከእዚህ ውጭ ግን ''ዝም ያለ ከተስማማ እኩል ይቆጠራል'' እንዲሉ በድርጊቱ ከመስማማት እንዳያስቆጥር ከፍተኛ ስጋት አለ።እጅ አጣጥፎ ሁኔታውን እንደ ሲኒማ ከመመልከት ህወሓትን አደብ አስገዝቶ ለዘላለም ከምንኖርበት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር አንድ መሆን ብቸኛው አማራጭ ነው።


ጉዳያችን GUDAYACHN
 www.gudayachn.com 

ወይ ባልዘፈንሽ፤ ከዘፈንሽ ባላሳፈርሽ (የፓትርያርኩ መግለጫ) በዲ/ን ኢንጅነር ዓባይነህ ካሴ


በዲ/ን ኢንጅነር ዓባይነህ ካሴ 
ትናንት ነሐሴ ፫ ቀን ፳፻፰ በፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የተሰጠው መግለጫ ከወቅታዊነቱ ይልቅ ወገንተኛነቱ ያየለበት እንደኾነ በገሃድ ይነበባል፡፡ ብዙ ጊዜ አሳፍረውናል አሁንም ያው መንገድ እንደተስማማቸው ያሳያል፡፡ ከአንድ ፓትርያርክ የሚጠበቀው ሰብእና እንደዚህ ባለ አስጨናቂ ጊዜ ከማንም ያልወገነ ማዕከላዊ ሀሳብ ይዞ ግልግል ውስጥ መግባት ነው፡፡ በዚህ መለኪያ ፓትርያርክ ማትያስ የሰጡት መግለጫ ሲመዘን ብዙ የሚነሳ የሚጣል ጉድ አለበት፡፡ ይህንን መለኪያ መከተል ካልቻሉ (በልባቸው ምን እያሰቡ ዝም ሊሉ እንደሚችሉ ብናወቅም) ዝም እንዳሉ ቢቀሩ ይሻለን ነበር፡፡
በአበው ብኂል ወይ ባልዘፈንሽ፣ ከዘፈንሽ ባላሳፈርሽ ይባላል፡፡ የማይችል ሰው ስለማይችል አርፎ መቀመጥ ይገባዋል፡፡ እችላለሁ ካለ ደግሞ ጉዳዩ በሚጠብቀው ደረጃ በቅቶ መገኘት አለበት፡፡ ከሁለቱም ያጣ ኾኖ እችላለሁም ብሎ ዕድሉንም አግኝቶ ባገኘው ዕድል ሳይጠቀም ከቀረ ሮቤላዊነት ይኾናል፡፡ (መቼም ሮቤል በተባለ ወጣት “ዋናተኛ” ሪዮ ኦሎምፒክስ ላይ የብዙ ጀግኖች አትሌቶቻችንን ወርቃማ ታሪክ የሚፃረር አሳፋሪ እና አዋራጅ ድርጊት መፈጸሙን ከቀደመው አብረቅራቂ የኦሎምፒክ ገድላችን በፍጹም ተቃርኖ ያስመዘገብነውን አሳፋሪ ኩነት የማያውቅ የለምና) ለእኔ ሁለቱም አንድ ናቸው፡፡
ለሁለቱም ታሪክ በር ከፍታ መድረክ አመቻችታ ተቀበለቻቸው፡፡ አንችልም ብለው ከመድረኩ መራቅ ሲገባቸው በማይችሉበት መድረክ እንደሚችሉ ኾነው ብቅ አሉ፡፡ ያ መድረክ እጅግ በጣም ቢያንስ ከተዋናዮቹ የሚጠብቀው ሚኒማ አለ፡፡ ከሚኒማው በጥቂቱ መውረድም ብዙ አያሳማም፡፡ አፈጻጸሙ ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ከኾነ ግን አዋራጅ ይኾናል፡፡ ከጀርባ ያለው ባንዲራ ነውና፡፡ ውድቀቱ በእነርሱ ብቻ አይቆምም ሀገርንም ያሳፍራል፡፡
የፓትርያርኩ መግለጫ ከወገብ በላይ ታቦት ከወገብ በታች ጣዖት የኾነ ግራ የገባው ኾኖ ይነበባል፡፡ ጸልዩ አስተምሩ የሚሉት እንደታቦት የሚታዩ ናቸውና፡፡ መግለጫ ሰጡ ሲባል መደንገጤ አልቀረም ደግሞ ምን ብለው አዲስ የቤት ሥራ ይሰጡን ይኾን በማለት ከልቤ ተጨንቄ ነበር፡፡ የኾነው እና ያስጨነቀኝ ተገጣጠሙ እናም አሳመመኝ፡፡
በተለይ በተራ ቁጥር ሁለት እና ሦስት ላይ የተቀመጡት ሀሳቦች ምን ማለት እንደፈለጉ ያሳብቅባቸዋል፡፡ 
2. በየአካባቢው የሚገኙ አዛውንቶችና ሽማግሌዎች፣ ምሁራንና አባወራዎች እንዲሁም እማወራዎች ልጆቻቸውንና የአካባቢው ወጣቶችን በመምከርና በማስተማር የሰው ሕይወትን ከጥፋት፣ የሀገር ሀብትን ከውድመት እንዲታደጉ ቤተ ክርስቲያናችን ጥሪዋን ታስተላልፋለች፤
በዚህ ሀሳብ ውስጥ ገላጋይነት ፈጽሞ ስፍራውን እንደለቀቀ ይታያል፡፡ የሚመከረው አንዱ ወገን ብቻ እንደኾነ ያሳያል፡፡ በእርሳቸው ሀሳብ ሌላ የሚመከር አካል የለም፡፡ ወጣቱ አጥፊ መኾኑን ጠቅሰው ምክር እንደሚያስፈልገውም ጠቁመዋል፡፡ በእርግጥ ቦታቸው ይህ ነበርን? አይደለም፡፡ በመካከል ኾነው ቢያንስ ቢያንስ አንተም ተው አንተም ተው በማለት ቃለ ተግሣጹን ለሁሉም በማዳረስ እኔ ልሸምግል ማለት በተገባቸው ነበር፡፡ ጨርሶ ወደ አንዱ አዘንብሎ ከቀሩ የተነሡበት ዓላማ ወይ አልተሳካም ወይ ከጅምሩ ዓላማቸው ሌላ ነበር፡፡

3. ሁሉም ወገኖች አለን የሚሉትን ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ለሚመለከተው አካል በማቅረብ፣በውይይትና በምክክር እንዲሁም በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ በመጓዝ ችግሩን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ያደርጉ ዘንድ ቤተ ክርስቲያናችን ታሳስባለች፡፡
በዚህ መግለጫ ውስጥ “ጥያቄ አለን የሚሉት ወገኖች . . . በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ በመጓዝ ችግሩን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ያደርጉ ዘንድ ቤተ ክርስቲያናችን ታሳስባለች” ይላሉ፡፡ “ችግሩን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት” የሚለውን ስንመለከተው የተጀመረ ጥረት መኖሩን ያሳያል፡፡ የተጀመረ ጥረት ለመኖሩ ምን ያኽል እርግጠኛ ሊኾኑ ናቸው? ካለስ የቱ? አልነገሩንም፡፡ መንግሥት ጉዳዩ ከውጭ ኃይሎች ጋር የተዳመረ መኾኑን ገልጦ እየተናገረ ነው፡፡ ከየትኞቹ የውጭ ኃይሎች ጋር በዚህም በመንግሥት በኩል ምን የተጀመረ ነገር አለ? ካለ ተስፋ ሰጪ ነውና ቢጠቁሙ ሠናይ በኾነ፡፡ አለበለዚያ አለ ብሎ መናገሩ ግምት ውስጥ ይጥላል፡፡

ሌላው በዚሁ መግለጫ ውስጥ “በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ” የምትለው አባባል ወጣቱን በሕጋዊ እና ሰላማዊ መንገድ አልሄድህም ተብላ የምትተረጎም ናት፡፡ ወጣቱ በተባለው መንገድ ሄደ ሲባል ሌላውስ አካል? ነው ወይስ በዘወርዋራው መንግሥት ሕጋዊ ሲኾን ወጣቱ ሕገ ወጥ ነው መባሉ ነው? እንደዚህ ከኾነ ደግሞ አንዱን አጽድቆ ሌላውን መኮነን ስለኾነ ከገላጋይነት ይልቅ ወገንተኝነት አለበት፡፡
ራሱ መግለጫው “በሀገር ውስጥ አለመግባባት ሲፈጠር አንዱን ካንዱ ሳትለይና ሌላውን ሳታገል ሁሉንም በእኩልነትና በልጅነት መንፈስ በማየት ስትመክር፣ ስታስተምርና ስታስማማ የነበረች፣ አሁንም ያለች፣ ለወደፊትም የምትኖር የቁርጥ ቀን እናት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡” በማለት የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሚና ደግሞም መለኪያ ሚዛን አስቀምጦ የተነሣ ነው፡፡ ይኸው መሥፈርት ወይም መዳልው ወይም ሚዛን ወይም መለኪያ በሁለቱ ሀሳቦች ውስጥ አለመገኘቱ ግራ ያጋባ፡፡ አንዱን ካንዱ ሳትለይና ሳታገልል ከተባለ እና አሁንም ያንን ታደርጋለች በሚል ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ከሰበከ በኋላ ይህ ሀሳብ ወዴት እንደመነነ ሳይታወቅ አንዱ ወገን ላይ ብቻ ማትኮር ተገቢነት የለውም፡፡ ለዚህም ነው ወይ ባልዘፈንሽ ከዘፈንሽ ባላሳፈርሽ የተባለው፡፡


ምንጭ= ዲ/ን ኢንጅነር ዓባይነህ ካሴ ፌስ ቡክ ገፅ (https://www.facebook.com/abayneh.kassie.5/posts/1003781496407994) 

ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Monday, August 8, 2016

''ሸዋ ባላመጠ ባመቱ ይውጣል'' ጀግናው የመርሐቤቴ፣መንዝ፣ምንጃር፣እና ይፋት ሕዝብ ለነፃነትህ ተነስ!

መርሃቤቴ ዋና ከተማ ዓለም ከተማ 

''ሸዋ ባላመጠ ባመቱ ይውጣል'' የምትል አባባል አለች።የሸዋ ሰው አንድን ነገር ለእረጅም ጊዜ በሚገባ ከመረመረ በኃላ ለተግባር ይነሳል ማለት ነው።ሃያ አምስት ዓመታት ለማላመጥ ከበቂ በላይ ነው። 

ህወሓት የዋልጌ ግለሰቦች ስብስብ ነው።ህወሓት ኢትዮጵያን ለባዕዳን የሸጡ ወንጀለኞች አባላት ያሉበት ነው።ህወሓት ከናዚዎች የተቀዳ የዘር ፖለቲካ ይዞ የሚንቀሳቀስ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ነቀርሳ ነው። በህወሓት ውስጥ የተሰባሰቡ ግለሰቦች እና በጎጥ ገመድ ተተብትበው የሚያሽቃብጡ ሁሉ ቂም አርግዘው ቂም የሚተፉ ያለንበትን ዘመን የማይመጥኑ እጅግ ያረጀ አስተሳሰብ ይዘው የምንገታገቱ የከንቱዎች ስብስብ ነው። ህወሓት ከመነሻው አላማው ኢትዮጵያን መከፋፈል መሆኑን ያልተረዱ በደርግ ላይ ጥላቻ ያደረባቸው የኢትዮጵያን ልጆች ደም እግሩን እያጨቀየ በደማቸው ላይ  በእግሩ ተረማምዶ አራት ኪሎ ቤተ መንግስት የገባ እና በኃላ ሰማዕታቱን የከዳ የከሃዲዎች ጥርቅም ነው። ይህ ቡድን ከስልጣን መውረድ አለበት።በትዕቢት የተወጠሩ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚደነፉ አድር ባዮቻቸውም ካለ ችሎታቸው ከተንጠላጠሉበት በሕዝብ አጥንት የተገነባ ስልጣናቸው በሕዝብ ኃይል መውረድ አለባቸው። 

ጀግናው የኦሮሞ፣የጎንደር፣ጎጃም እና አዲስ አበባ ሕዝብ ባሳለፍነው ሳምንት ወያኔ በቃ! ብሏል።ካለፈ ያልተማረው  ህወሓት ባዶ እጃቸውን በተሰለፉ ኢትዮጵያውያን ላይ ከመትረጌስ እስከ ከባድ መሳርያ ድረስ በመተኮስ ባለፉት ሰባ ሁለት ሰዓታት ብቻ ከስልሳ በላይ ንፁሃንን ገድሏል።ወያኔ እና አድር ባዮቹ ይህ ሁሉ እልቂት በምፈፀምበት ሰዓት የትግራይ ምክትል ፕሬዝዳንት በተገኙበት ዋሽንግተን ላይ  ውስኪ እየተራጩ ሲጨፍሩ ተመልክተናል።ይህ ብቻ አይደለም የኢትዮጵያ ሕዝብ ያነሳውን ወያኔ ስልጣኑን ይልቀቅ የሚለውን ፍፁም ሕጋዊ ጥያቄ እንደ ትልቅ ድፍረት ቆጥረውት በንፁሃን ላይ የሚፈፀመውን ግድያ ፍትሃዊ አስመስለው ሲናገሩ መስማት የነፃነት ትግሉ ማንን ቀድሞ ማስተማር እንዳለበት ሁኔታውን ግልፅ ያደርገዋል።

የሰሜን ሸዋ ሕዝብ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ በወያኔ ያልተፈፀመበት የግፍ አይነት የለም።ከመርሃቤቴ ዋና ከተማ የዓለም ከተማ እስከ ደብረ ብርሃን ከተሞች እና የገጠር መንደሮች ሁሉ ህወሓት የፈፀመው ግፍ  ምን ጊዜም የሚረሳ አይደለም። በሰሜን ሸዋ ካራ ምችግ በ1982 እና 83 ዓም በዓለም ከተማ የ1997 ዓም ምርጫ ተከትሎ በወጣቶች ላይ ግድያ ተፈፅሟል።በተለይ በዓለም ከተማ በጠራራ ፀሐይ በሕወሃቱ ሹም ሕዝብ በአደባባይ እንዲሰበሰብ አድርጎ በአደባባይ በግል ሽጉጡ የተገደሉት የሁለቱ ወጣቶች ደም አሁንም በዓለም ከተማ የፍትህ ያለህ እያለ ነው። የሰሜን ሸዋ ሕዝብ ከአጎራባቹ የኦሮሞ ማኅበረሰብ ጋር በፍቅር ለአመታት ይኖረ ሆኖ ሳለ ወያኔ ለማጣላት ያልሸረበው ተንኮል አልነበረም። ሆኖም ግን ሊሳካለት አልቻለም።አሁን ወቅቱ ያለፈውን እያነሳን የምንቆዝምበት ወቅት አይደለም።ከኢትዮጵያ ሕዝብ  ጋር ወያኔን በቃ! የምንልበት  ወሳኝ ጊዜ ነው። ሃያ አምስት ዓመት ማላመጥ ይበቃል! ''ሸዋ ባላመጠ ባመቱ ይውጣል'' ጀግናው የመርሐቤቴ፣መንዝ፣ምንጃር፣ዋግኅምራ እና ይፋት ለነፃነትህ ተነስ!

''ልቤ ነው ፍትህ የሻተው
ና! ቶሎ ዳኘው ዳኘው።
ስጠው ፍርዱን ስጠው፣
ችሎቱ ያንተው ነው።''


ጉዳያችን GUDAYACHN www.gudayachn.com

Thursday, August 4, 2016

የጎንደር የበሰለ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ እንቅስቃሴ ህወሃትን ''ከካሮት እና ዱላ'' አንዱን እንዲመርጥ አስገድዶታል ። (የጉዳያችን ማስታወሻ)


አንድ ወቅት አንድ የፖለቲካ ተንታኝ (ስማቸው ይቆየን) ህወሃትን በተመለከተ  ለምንድነው ይህንን ያህል ሕዝብ እየገደለ፣እያሰረ እና እያሰደደ ስልጣን ላይ ለመቆየት የቻለው? ሲሉ ከጠየቁ በኃላ መልሱን ሲመልሱ እንዲህ ማለታቸውን አስታውሳለሁ። 
'' ህወሓት የገጠሙት ተቃዋሚዎች በሙሉ የህወሃትን ተንኮል የሚመጥኑ አይደሉም። ፕሮፌሰር አስራትን ተመልከት።ፕሮፌሰሩ እድሜያቸውን ሙሉ በሽተኛ ሲያድኑ የኖሩ ሰው ናቸው።እንዴት ብለው 17 ዓመት ሙሉ ሰው ሲገድል ከነበረ ህወሓትን የሚመጥን የትግል ስልት እንዴት ይቀይሱ? ሌሎች ተቃዋሚዎችን ተመልከቱ።ግማሾቹ ዳኞች፣የሕግ ሰዎች፣የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ናቸው።እነኝህ ሰዎች ደግሞ ሕግ እና ስርዓት ጠብቀው እንጂ እንደ ህወሓት ሕግን አፈር ድሜ እያስጋጡ አይታገሉም።ስለሆነም ህወሓት የሚመጥነው ተቃዋሚ ያስፈልገዋል።'' ነበር ያሉት።

አሁን ላይ ሆነን ስንመለከት፣የምሁሩን ሃሳብ ማቃለል አይቻልም።ህወሓት ከቅንጅት በፊት ስርዓቱን የተቃወሙ የኢትዮጵያ መምህራን ማህበርን፣ ነፃውን ሚድያ፣የ1997 ዓም ምርጫ እንቅስቃሴ እና ከእዚያ በኃላ የታሰሩት የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎች ተቃውሞ ሁሉ ህወሃትን የሚመጥነው ተቃዋሚ አለማግኘቱን አመላካች ድርጊቶች ሆነው አልፈዋል።ድሮስ ሕግን የሚያውቅ በሕግ ትሞግተዋለህ።እንደ ህወሓት ላላ የሰራውን ሕግ በመደፍጠጥ ለሚታወቅ ስርዓት አብዝቶ ስለ ሕግ በማውራት ህወሓት ኢትዮጵያን በጎሳ ፖለቲካው እንዳይረግጣት ለማድረግ አልተቻለም።በአዲስ አበባ በ1997 ዓም ከ200 በላይ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ሲገደሉ፣ጋምቤላ  ላይ ኢትዮጵያውያን መሬታቸውን ሲነጠቁ፣ከ500 በላይ የኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ለምን ተሰለፋችሁ በሚል ብቻ ከገደለ በኃላ ፣በመቶዎች የሚቆጠሩ የሲዳማ ሕዝብ ሲገደል ሁሉ የነፃነት ትግሉ፣የህወሃትን ትዕቢት የተሞላበት ንቀት የሚመጥን ትግል ያለህ እያለ  ነበር።

ካሮት እና ዱላ 

አቶ መለስ ህወሓት አስጨንቆ የሚታገላት እንደሚያስፈልጋት በምፀት መናገራቸው ይታወሳል። የሰላማዊ ትግልን ያናናቁት አቶ መለስ የትጥቅ ትግል የሚፈልግ ካለ ''መንገዱን ጨርቅ ያድርግለት'' የሚል መልክት አስተላልፈው ነበር።መልክቱ ''እኛ በመጣንበት መንገድ ኑ!'' መሆኑ ነው።ከሰሞኑ በጎንደር የተነሳው ተቃውሞ በህወሓት የአገዛዝ ዘመን ፈፅሞ ያልታየ እና በዓይነቱም ልዩ ነው።የወልቃይት ጠገዴ አማራነት የያዘው የአቤቱታ ኮሚቴ ጥያቄውን በአግባቡ እስከ ፈድሬሽን ምክርቤት እና የተለያዩ የመንግስት አካላት በግንባር  ላቀረበው ጥያቄ ከህወሓት የተገኘው ምላሽ በትዕቢት ''ወልቃይት ትግራይ ነው'' የሚል ''ምን ታመጣላችሁ'' ምላሽ ነበር።

የጎንደር ሕዝባዊ እንቅስቃሴ በአይነቱ ልዩ ነው።ልዩ ያደረገው የህዝቡ ሕብረት ብቻ አይደለም።ደረጃውን የጠበቀ የፖለቲካ አቀራረብ የያዘ መሆኑም ብቻ አይደለም።መላው ኢትዮጵያውያንን ቁስል እና ህመም የዳሰሰ ብቻ ስለሆነም ብቻ አይደለም።እንቅስቃሴው አላማውን የሚያሳካው ካሮት እና ዱላ ለህውሃት በማቅረብም ጭምር ነው።ህወሓት በኃይል ለመጠቀም ሲሞክር ይህ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ዱላ ያቀርባል።ህወሓት ሰላማዊ ለመሆን ሲሞክር ደግሞ ካሮት ያቀርባል።በእዚህም መሰረት ህወሓት ሐምሌ 5 ቀን ኮ/ል ደመቀን ለመያዝ ጦር ሲሰብቅ እንቅስቃሴው ጦር ሰብቆ መጣ።በሐምሌ 24/ 2008 ዓም ከግማሽ ሚልዮን ሕዝብ በላይ በተሳተፈበት ሰልፍ ላይ ህወሓት ሰልፉ አለመፈቀዱን በራድዮ ፋና እና ኢቲቪ ሲያስነገር ዋለ።የጎንደሩ እንቅስቃሴ ግን ካሮት እና ዱላ ይዞ ሰልፉን አካሄደ።በካሮት ሰላማዊ መልኩን አቅርቡ።በዱላው ከኃላ የሚጠብቅ ታጣቂ በማሰለፍ ህወሃትን አስገድዶ ሰልፍ ለማድረግ የቻለ እና በአይነቱ ልዩ ነበር።እንቅስቃሴው በእዚህ አላበቃም ከእሁዱ ሰልፍ በኃላ ሐምሌ 26/2016 ዓም እንቅስቃሴው ለህውሃት ግልፅ ደብዳቤ ፅፏል።የጎንደር እንቅስ ቃሴ ካሮት እና ዱላ አቀራረብ ህወሓትን ከማንቀጥቀጥ አልፎ የስልጣን መሰረቱን አናግቶታል።''በአህያ ቆዳ የተሰራ ቤት፣ፍርስርስ ይላል ጅብ የመጣ እለት'' እንዲሉ በጎጥ ላይ የተመሰረተ የህውሃት ፖለቲካ በቻለው መጠን ሕዝብ በሕዝብ ላይ ለማስነሳት ቢሞክርም ባለመቻሉ የሚይዘው የሚጨብጠው ጠፍቶታል።ህወሓት አሁን የሚመጥነው የትግል ምርጫ ቀርቦለታል።ከካሮት እና ዱላ መምረጥ የህወሓት ምርጫ ነው።




ጉዳያችን GUDAYACHN 
 www.gudayachn.com

The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church is in turmoil in Athens, Greece.

His Holiness Abune Mathias I, Patriarch of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, met with Greece's Ambassador to Ethiopia, Antonios Sg...