Saturday, January 1, 2022

ወገን ቴክኖሎጂ ሶሉሽንስ ኃ.የ.ግ.ማ. ከአቢሲኒያ ባንክ ጋር በመተባበር ''ወገን ፈንድ'' የሚባል የኦንላይን የድጋፍ ማሰባሰቢያ መተግበሪያ አስመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።



  • ቴክኖሎጂው ጎፈንድ ሚ የሚተካ አገልግሎት ይሰጣል።በጎ አድራጊ ድርጅቶች በቀላሉ ሊጠቀሙበት ይችላሉ።

ወገን ቴክኖሎጂ ሶሉሽንስ ኃ.የ.ግ.ማ ለኢትዮጵያ የሚጠቅም ቴክኖሎጂ ይዞ መጥቷል።በያዝነው ሳምንት አጋማሽ ላይ በይፋ የተመረቀው ይሄው ቴክኖሎጂ በእንግሊዝ ሃገር ነዋሪ በሆኑ ኢትዮጵያውያን ዶ/ር በላቸው ጨከነ እና አቶ ሚልዮን በተባሉ ኢትዮጵያውያን ትልቅ አስተዋጾ ወደ ተግባር እንደተቀየረ  ለማውቅ ተችሏል።ቴክኖሎጂው ከአቢኒያ ባንክ ጋር በጋራ የሚሰራ ሲሆን በቴክኖሎጂው ይፋዊ መርሃግብር ላይ በእንግሊዝ የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ እና ሌሎች ኢትዮጵያውያን በቨርችዋል በተዘጋጀው ዝግጅት ላይ ተገኝተዋል።

ከእዚህ በታች በአቢሲንያ ባንክ ድረ ገጽ ላይ የወጣ ዘገባ ነው።

===================

ወገን ቴክኖሎጂ ሶሉሽንስ ኃ.የ.ግ.ማ. ከአቢሲኒያ ባንክ ጋር በመተባበር ወገን ፈንድ የሚባል የኦንላይን የድጋፍ ማሰባሰቢያ መተግበሪያ ታህሳስ 21 ቀን 2014 ዓ.ም. አስመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

በተዘጋጀው የቨርቹዋል የምረቃ ስነ ሥርዓት ላይ ጥሪ የተደረገለቻው የክብር እንግዶች፣ የግብረ ሰናይ ተቋማት ተወካዮች እና በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተገኙ ሲሆን፣ ወገን ቴክኖሎጂ የግብረ ሰናይ ድርጅቶች በማንኛውም ማኅበረሰብ ውስጥ ካላቸው ዘርፈ ብዙ አስተዋጽኦ አንጻር በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ደጋፊዎቻቸውን የሚያስተባብሩበት እና ድጋፍ የሚያገኙበት እንዲህ ያለ መተግበሪያ/platform/ መኖሩ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ገልጿል።

አምባሳደር ተፈሪ መለሰ፣ በዩኬ እና አየርላንድ የኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ሥልጣን አምባሳደር፣ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር በሁሉም ዘርፎች ራሳችንን መቻል እንደሚገባን ገልጸው ነዋሪነታቸውን በውጪ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በፋይናንስ፣ በእውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር እና በሌሎችም መስኮች ለሀገራቸው የሚያደርጉትን ድጋፍ አድንቀዋል። በሌሎች የውጪ ሀገር የድጋፍ ማሰባሰቢያ ቴክኖሎጂዎች ላይ ከመመርኮዝ ይልቅ “የራሳችን በሆነው ወገን ፈንድ መጠቀምና ይኼንኑ ቴክኖሎጂ ማበረታታ ለዘላቂ ትልማችን አማራጭ የሌለው ስለሆነ ሁላችንም ይህንን ጅምር በማበረታታት ለጋራ እድገት በጋራ እንድንቆም” ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

ወ/ሮ ፈሰሴ ገ/ሃና፣ የወገን ቴክኖሎጂ ዋና ሥራ አስኪያጅ ባሰሙት ንግግር ደግሞ “ወገን ፈንድ ዋነኛ ትኩረቱ በኢትዮጵያ ከሚንቀሳቀሱ በጎ አድራጎት ድርጅቶች፤ የሃይማኖት ተቋማት እና ማህበራት፣ እንዲሁም የጤና እክል ገጥሟቸው የወገን እርዳታ ከሚፈልጉ ግለሰቦች ጋር፣ የሀገራችን የሕግ ማዕቀፍ ውስጥ በመሆን ሕጋዊ ገቢ የማሰባሰቢያ እንቅስቃሴዎችን፣ በግሉ ዘርፍ በባንኪንግ ቴክኖሎጂ ግንባር ቀደም ከሆነው ከአቢሲኒያ ባንክ ጋር በመሆን መስራት ነው” ብለዋል።

አቶ አባይ ስሜ፣ የአቢሲኒያ ባንክ፣ የኦንላይን ባንኪንግ አገልግሎት ዳይሬክተር በበኩላቸው አቢሲኒያ ባንክ አለም አቀፍ የክፍያ ቴክኖሎጂን በኢትዮጵያ ለመጀመር ቀዳሚው ባንክ መሆኑን በማስታወስ “ልግስናን እንደ አንድ መገለጫው አድርጎ ለሚያይ ማኅበረሰብ ይኅንን መልካም ተግባሩን የሚያዳብርበት የቴክኖሎጂ መላ ማበጀት እጅግ የሚደነቅ ሥራ ነው” በማለት ለወገን ቴክኖሎጂ ምስጋናቸውን ካቀረቡ በኋላ “በጊዜ እና በቦታ ሳይገደብ ሁሉም ዜጋ የአቅሙን አስተዋጽኦ ማድረግ የሚችልበትን መንገድ በማመቻቸቱ ሥራ ላይ አንድ ባለድርሻ አካል ሆነን ከወገን ቴክኖሎጂ ጋር በመሥራታችን እጅግ ኩራት ይሰማናል” ብለዋል።

በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ ከ350 በላይ የሚሆኑ የሀገር በቀል ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ስብስብ የሆነውን “የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጥምረት ለኢትዮጵያ ህዝብ” የተሰኘውን ጥምረት ጨምሮ የተለያዩ ሀገር በቀል ግብረ ሰናይ ድርጅቶች አባላት እና የቦርድ አባላት የተገኙ ሲሆን ለኢትዮጵያም ሆነ ለአህጉራችን አፍሪካ የሚድያ እና የቴክኖሎጂ አቅምን ማሳደግ እንደሚገባ፣ ሀገራችን ካለችበት ሁኔታ አንጻር ወገን ፈንድ ወሳኝ ወቅት ላይ እንደደረሰ እና ሳታዳሉ ሁሉንም የሲቪክ ማኅበራት ለማገልገል በመነሳታችሁ እናመሰግናለን የሚሉ አስተያየቶች ተሰጥተዋል።

የወገን ቴክኖሎጂ ሶሉሽን ዳይሬክተር እና መስራች ዶ/ር በላቸው ጨከነ እንዲሁም ሌላኛው መሥራች እና ዋና ዴቬሎፐር አቶ ሚሊዮን አጀበ ወገን ፈንድ ነባሩን የኢትዮጵያውያን የመረዳዳት ባህል በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንዲታገዝ ለማድረግ የተዘጋጀ መሆኑን፤ ወገን ቴክኖሎጂ የተመሠረተው በውጪው አለም፣ በተለያዩ መስኮች፣ ከአሥር አመት በላይ ልምድ ባካበቱ ባለሙያዎች እንደሆነ፤ እንዲሁም የወገን ቴክኖሎጂ አላማ ወደሃገራችን የሚደረገው የቴክኖሎጂ እና እውቀት ሽግግር ላይ አስተዋጽኦ ማበርከት በወደዱ ፣ የኢትዮጵያ ልጆች በሚያዘጋጇቸው ቴክኖሎጂዎች በመታገዝ ኢትዮጵያውያን ራሳቸውን እንዲችሉ ማስቻል እንደሆነ ገልጸዋል።

ወገንፈንድን www.wegenfund.com ድህረ ገፅ ላይ ማግኘት ይቻላል።







Thursday, December 30, 2021

Breaking News - #NoMore says Hands Off Somalia! What is happening in Somalia now? (Watch the video)

The Horn of Africa Unites Somalis Sheikh Abdi Hersy and Dr. Hashi, Eritrean organizer Dr. Simon Tesfamariam and Ethiopian organizer Nebiyu Asfaw speak with journalist Hermela Aregawi about the latest imperialist attacks on Somalia.

Video Source - Hermela Tv




Wednesday, December 29, 2021

ኢትዮጵያ በዘመናዊ ታሪኳ ታላቅ ተልዕኮ የሚኖረው ሀገራዊ የምምክር ኮሚሽን ተመሰረተ።ስለኮሚሽኑ ምንነት ምን ያህል ያውቃሉ? ጉዳያችን ያገኘችውን መረጃዎች ታካፍላችኋለች።



  • የእዚህ ኮሚሽን መመስረት ኢትዮጵያ የተቋማት ግንባታ ላይ በሚገባ እየሰራች እንደሆነ የሚያበስር ብስራት ነው።
  • ይህንን ኮሚሽን ማጠናከር፣ማክበር አና በአግባቡ መጠቀም ለኢትዮጵያ ታሪካዊ ዕድል ነው።ዜጎች ሁሉ ከፍተኛ ትኩረት እና አክብሮት ሊሰጡት ይገባል።
ETHIOPIAN MP PASS BILL TO SET UP NATIONAL DIALOGUE COMMISSION 
===================================
ጉዳያችን ልዩ ዘገባ /Gudayachn Special Report
===================================
ታኅሳስ 1፣2014 ዓም የሚኒስትሮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ መሠረታዊ በሚባሉ አገራዊ ጉዳዮች በተለያዩ ጎራዎች የተሠለፉ የፖለቲካ ልሂቃንም ሆኑ ምልዓተ ሕዝቡ ተቀራራቢና በአገራዊ አንድነት ገንቢ አቋም እንዲይዙና አካታች አገራዊ ምክክር ተግባራዊ ለማድረግ፣ ይህንኑ ምክክር በገለልተኝነት ለመምራትና ለማስተባበር የሚችል ቅቡልነት ያለው ተቋም ለማቋቋም የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለውሳኔ መርቶት ነበር። 

በእዚህ መሰረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ታኅሳስ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ፣ በረቂቅ አዋጁ ላይ ተወያይቶ ለዝርዝር ዕይታ ለምክር ቤቱ የሕግ፣ ፍትሕና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቶት የነበረ ሲሆን በእዚሁ ውይይት ላይ  የዴሞክራሲ ተቋማት፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤትና የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች፣ የፍትሕ ሚኒስትርና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሥራ ኃላፊዎችና ሌሎችም አካላት ተሳትፈዋል፡፡በውይይቶቹ ውስጥ ከተነሱት እና አጽንኦት እንዲሰጥባቸው ከተወሱት ውስጥ የኮሚሽነሮች አሰያየም፣ አወቃቀርና የኮሚሽኑ አደረጃጀት ላይ ያላቸውን ሥጋትና የገለልተኝነት ሁኔታዎች ጥቂቶቹ ነበሩ።ከእዚህ ሁሉ ውይይት  በኃላ ዛሬ ታኅሳስ 20፣2014 ዓም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በረቂቁ ላይ ተወያይቶ በአብላጫ ድምፅ አፅድቆታል።

ኮሚሽኑ 11 ያለመከሰስ መብት ያላቸው ኮሚሽነሮች ይኖሩታል።በኮሚሽነሮቹ መብዛት ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ሃሳብ ሰጥተዋል። የኮሚሽኑ ዋና ተግባር ልዩነትና አለመግባባት ለማርገብና ለመፍታት ሰፋፊ አገራዊ የሕዝብ ምክክሮችን አካታች በሆነ መንገድ በማካሄድ አገራዊ መግባባት ለማምጣት የሚሠራ ነው። የኮሚሽኑ መቋቋም በኢትዮጵያ ሃገረ መንግስት የሚመሰረተው አንዱ ተቃዋሚ ሲጠፋ ነው የሚለው አስተሳሰብ በእዚህ ኮሚሽን መመስረት ይቀየራል ተብሎ ይታሰባል።ይህ ግን ሽብርተኛን እና ኢትዮጵያን ለመበተን የሚነሳ አካልን አይመለከትም።

በኮሚሽኑ መመስረት ዙርያ ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ‹‹ሰላም፣ ደኅንነት፣ ዲፕሎማሲና ልማት በኢትዮጵያ አሁናዊ ሁኔታ ምን ይደረግ?›› በሚል ርዕስ  ምሁራንን ያካተተ የፓናል ውይይት አድርጎ ነበር።በእዚሁ ውይይት ላይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሰላምና ደኅንነት ጥናት ተቋም መምህርና ‹‹ብሔራዊ ደኅንነት በኢትዮጵያ›› በሚል የጥናት ርዕስ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን እየሠሩ ያሉት አቶ ዮናስ ታሪኩ ‹‹ደኅንነት›› በሚል ርዕስ ጽሑፍ ያቀረቡ ሲሆን፣ በተለይ ካለፉት 50 ዓመታት ወዲህ በአገሪቱ ውስጥ ‹‹የማንን ደኅንነት እናስጠብቅ›› የሚለው ላይ አለመግባባት መኖሩንና በዚህም ምንክያት የአገሪቱ ደኅንነት ፍትጊያ ውስጥ መግባቱን መናገራቸው ተዘግቧል። በእርሳቸው ጥናታዊ ጽሁፍ ላይ እንደተገለጠው የሃገረ መንግስቱ መጠበቅ የቡድን መብት መጠበቅ ለምሳሌ በቋንቋ እና ማንንነት ላይ ያለው ከለላ ትኩረት እንዲሰጠው የሚፈልጉ የመኖራቸውን ያህል በተቃራኒው ሃገረ መንግስቱ መጠበቅ ላይ ኢትዮጵያዊነትን በሚገባ ይዞ መጓዝ እንዳለበት አጥብቀው የሚያሳስቡ እንዳሉ ገልጠዋል። አቶ ዮናስ ማብራርያቸውን በመቀጠል የሁለቱ ቡድኖች ሃሳብ እርስ በርስ የሚጋጩ አስመስሎ በማቅረብ ችግር የመፍጠር ሁኔታ መሆኑን ገልጠው ይህ ግን ወደ ግጭት ሊያመራ እንደማይገባ አብራርተዋል።

ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተቋቋመው የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለእንዲህ ዓይነት የኢትዮጵያ ሁኔታዎች ዓይነተኛ መፍትሄ የሚሰጥ እንደሚሆን ይታመናል።ይህንን ኮሚሽን ማጠናከር፣ማክበር አና በአግባቡ መጠቀም ለኢትዮጵያ ታሪካዊ ዕድል ነው።ኮሚሽኑ ሁለት አና ከእዚያ በላይ የሆኑ የምክክር ሃሳቦችን ሁሉ የሚያስተናግድ ሲሆን የሦስት ዓመታት ዕድሜ ይኖረዋል።ከእዚህ በተጨማሪ በሀገራዊ ደረጃ የማያግባቡ አጀንዳዎችን መርጦ በሰነድነት አዘጋጅቶ ለውይይት የሚያቀርብ አና የሚቋጩትን በመቋጨት ያልተቋጩትን ደግሞ በውይይት እንዲፈቱ የማድረግ ትልቅ ሃገራዊ አደራ ተቀብሏል። ሌላው እና የኮሚሽኑ ትውልድ ተሻጋሪ መሆኑን የሚያሳየው የኮሚሽኑ ተግባር ደግሞ የውይይት ሰነዶቹ ሂደት ጭምር ለቀጣይ ትውልድ መማርያ እንዲሆኑ በሚገባ በሰነድነት ሰንዶ ለብሄራዊ ቤተ መዛግብት የሚያስረክብ ሲሆን፣ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሰነዶቹን በፈለገ ጊዜ ለመመልከት እንዲችል ሁኔታዎች የሚመቻቹ መሆናቸው ነው። 

የእዚህ ኮሚሽን መመስረት ኢትዮጵያ  የተቋማት ግንባታ ላይ እየሰራች እንደሆነ በሚገባ የሚያበስር ብስራት ነው።በመሆኑም ዜጎች ለኮሚሽኑ ከፍተኛ ትኩረት እና ተገቢው አክብሮት ሊሰጡት ይገባል።የኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ አንዱ ችግር ያሉትን የተለያዩ ሃሳቦች በአግባቡ ሰንዶ እና አስተካክሎ መፍትሄ እንዲያገኙ ለውይይት እና ለህዝብ ውሳኔም ሆነ አስፈጻሚ እና ህግ አውጪ አካል አለመቅረባቸው መሆኑን ማስተዋል ይገባል።አንዳንዶቹ ቀላል የልዩነት ሃሳቦች በእየሚድያው ላይ ይንገዋለላሉ እንጂ እንዴት እና መቼ መፍትሄ እንደሚያገኙ ሃላፊነት የሚወስደው ተቋም ማን እንደሆነ ስለማይታወቅ ሁሉንም ጉዳይ መንግስት ይፍታው በሚል መጯጯህ ብቻ ጉዳዮች ሲንገዋለሉ ከርመው ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚፈልጉ የውጭም ሆኑ የውስጥ አካላት ጉዳዮቹን ለሃገር መበጥበጫ ሲጠቀሙበት መመልከት የተለመደ ነው።አሁን የእዚህ ዓይነት ተቋም መኖር ለኢትዮጵያ ትልቅ ተስፋ ብቻ ሳይሆን ለቀጣይ ልማቷም ያለው አስተማማኝ መሰረትነት የሚናቅ አይደለም።ይህንን ስራ ለሚሰሩ ብቻ ሳይሆን ሃሳቡን ላመነጩ የመንግስት አካላት ሁሉ ከፍ ያለ ክብር እና ምስጋና ይገባቸዋል።የኮሚሽኑን ውጤታማነት ደግሞ በበለጠ የምንረዳው እና የምናመሰግነው በቀጣይ በሚሰራቸው ስራዎች ይሆናል።ለስራዎቹ ስኬቶች ግን የእያንዳንዳችን አስተዋጽዖ አስፈላጊ ነው።

===================///==========



Sunday, December 26, 2021

የትግራይ ሕዝብ ከ3 ሺህ ዓመታት በላይ የሚያውቀው እና አብሮት የኖረውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ለ40 ዓመታት በሚያውቀው ህወሓት እንደማይቀየር የሚያስመሰክርበት ጊዜ አሁን ነው።


እውነት የት ነው ያለችው? የውሸት ፕሮፓጋንዳስ የትኛው ነው? ብሎ መመርመር ከሁሉም የትግራይ ተወላጅ የሚፈለግበት ጊዜ ላይ ነን። ይህ ጊዜ የትግራይ ተወላጆች ከመጪው ትውልድ ቀጣይ ሕይወት አንፃርም እውነቱን መርምረው ወሳኝ ወደሆነው ሀገር የማቅናት ሥራ የሚመጡበት ጊዜ አሁን ነው። 

እውነት ኢትዮጵያ ነች።ኢትዮጵያ ማለት ደግሞ ሁላችንም ነን።ኢትዮጵያን የማይል ትግራይን ይጠቅማል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው።ህወሓት የትግራይን ሕዝብ በሦስት መንገዶች በመጠቀም የእርሱ ተገዢ እንዲሆን አድርጎታል።እነኝህ ሦስቱ መንገዶች - ስጋት በመንዛት፣ በማስፈራራት እና በመደለል ናቸው።

ስጋት  -

ሽብርተኛው ህወሓት በትግራይ ማኅበረሰብ መሃል ስጋት እንዲሰፍን አጥብቆ ይሰራል።ይሄውም ሌላው የኢትዮጵያ ክፍል በሙሉ በትግራይ ተወላጅ ላይ እንደተነሳ አድርጎ የውሸት ፕሮፓጋንዳ እስከ ቤተስብ ድረስ ይነዛል።ይህንን የውሸት ዘመቻ በመንዛት ህወሓት ብቻውን እንዳይቆም እና ትግርኛ ተናጋሪ በሙሉ አብሮት እንዲቆም ለማድረግ ይጥራል።ይህንን የስጋት ስሜት በመፍጠር የትግራይ ማኅበረሰብን በማስደንበር ከሕወሓት ስር እንዲወሸቅለት ለማድረግ ይሞክራል።

ማስፈራራት

ህወሓት በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጪ የሚኖረውን የትግራይ ማኅበረሰብ በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ መልክ ሊያስፈራራው ይሞክራል።በቀጥታ አንድ ለአምስት ባደራጀው መዋቅር ውስጥ ያገተው ሕዝብ ከእገታው እንዳይወጣ በቀጥታ በራሱም ሆነ በቤተሰቡ ላይ ጥቃት እንደሚፈፀም ያስተነቅቃቸዋል። በመሆኑም ከህወሓት ውጭ የሆነ ወይንም ሕወሃትን የሚቃወም የትግራይ ተወላጅ ብቅ ሲል ማኅበራዊ የማሸማቀቅ ዘመቻ ከመክፈት ጀምሮ እስከ የግድያ ዛቻ እና ግድያ ሁሉ ይፈፅማል።ለእዚህም ጋዜጠኛ ሄርሜላ እና እናቷ ጥሩ ማሳያ ናቸው።ሄርሜላ እና ወላጅ እናቷ ላይ እየደረሰ ያለው ማስፈራራት ህወሓት በማሸበር  እውነትን የሚያግት ይመስለዋል።በማስፈራራትም ብዙዎች የትግራይ ማኅበረሰብ አባላት እውነቱን ተናግረው ማኅበረሰባቸውን ወደ ትክክለኛ መንገድ ከመምራት ይልቅ ግራ በተጋባ መንገድ መኖር በመምረጥ ለራሳቸው ጭንቀት አትርፈዋል። ከእዚህ ይልቅ የህወሓትን ማስፈራራት ሰብሮ እውነትን መናገር ነው የትግራይ ማኅበረሰብን ከጭንቀት አውጥቶ ትግራይን ከህወሓት የሽብር ቡድን ፈልቅቆ ማውጣት አስፈላጊ መሆኑን ማመን አለባቸው።

መደለል 

ሦስተኛ የሽብርተኛው ህወሓት የትግራይን ሕዝብ ለመሸበብ የሚጠቀምበት መንገድ መደለል ነው።መደለል በሁለት መንገድ ይጠቀምበታል። አንዱ በጥቅም እና የወደፊት ተስፋው ህወሓት ብቻ እንደሆነ እና ዛሬ የትግራይ ህዝብ መኖር የቻለው ህወሃት በመኖሯ ብቻ መሆኑን ለማሳመን ሲሞክር እፍረት አይሰማውም። በጥቅም መደለል በራሱ ብቻውን በጥቅም ላይ ብቻ የተመሰረተ አይደለም ከጥቅም ጋር አብሮ ማስፈራት አብሮ ውስጡ አለ። ድለላ የውሸት ተስፋም በውስጡ አለበት።ህወሃት እድሜውን ለማስረዘም የትግራይን ህዝብ የሚደልልበት ሌላው መንገድ የማያልቅ የውሸት ተስፋ መስጠት አንዱ መንገድ ነው። ሲሸነፍ እያሸነፈ እንደሆነ ህዝቡን ይደልለዋል።የትግራይን ወጣት አስፈጅቶ የህወሃት መሪዎች ልጆች ውጭ ሃገር በምቾት እየተማሩ እና እየኖሩ፣ ለትግራይ ህዝብ የሞቱት ልጆቹን ጉዳይ እንዳይጠይቅ አፍኖ በሌለ ተስፋ ውስጥ ለመክተት እና ለሌላ እልቂት ያዘጋጀዋል። 

አሁን የትግራይ ህዝብ ከሶስት ሺህ ዓመታት በላይ አብሮ ከኖረው የኢትዮጵያ ህዝብ ይልቅ የ40 ዓመታት የጎሳ ድርጅትን መስማቱን ማቆም ያለበት ጊዜ ነው።ሌላው ቀርቶ ባለፉት ሶስት ዓመታት ውስጥ ብቻ የሆነውን እውነት ተመልክቶ የኢትዮጵያን ህዝብ ከህወሃት መምረጥ የሚገባው ወሳኝ ጊዜ አሁን ነው። ባለፉት ሶስት ዓመታት በኢትዮጵያ የተከናወኑት የለውጥ ሂደቶች ከሁሉም በላይ ለትግራይ ህዝብ እጅግ መልካም መንገዶች የነበሩ ነገር ግን ህወሃት በራሱ ያመከናቸው መሆናቸውን በመምልከት የትግራይ ህዝብ ጠላት ህወሃት እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ አለመሆኑን በቀላሉ መረዳት ይቻላል።ለውጡ በራሱ በኢትዮጵያ ህዝብ የተነሳው በመከላከያ ላይ የተፈጸመው ጥቃት ተከትሎ መከላከያ መቀሌ ከመግባቱ በፊት የነበሩት ሁለት ዓመታት በኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ መንግስት በኩል የነበሩት መልካም ሂደቶች ሁሉ ታሪክ ለመቼውም ቢሆን የሚያነሳው ጉዳይ ነው። መከላከያ መቀሌን ለቆ ከወጣ በኋላም የእርዳታ እህል ወደ ትግራይ እንዲገባ ከማድረግ ጀምሮ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተገልጦ እንደነበረው አስፈላጊው የመሰረተ ልማት አገልግሎቶች እና የመብራት፣የስልክ አገልግሎቶች ሊቀጥሉ በነበረበት ሁኔታ እያለ ነው ህወሃት ወደ አማራ እና አፋር ህዝብ ላይ የዘመተው እና ለህሊና የሚከብድ ግፍ በሰላማዊው ህዝብ ላይ የፈጸመው።

የትግራይ ህዝብ ህወሃትን ከትግራይ ምድር በፍጥነት አለማስወጣቱ የሽብር ቡድኑ የትግራይን ህዝብ ከኢትዮጵያ ለመነጠል እና ለባዕዳን ለመሸጥ የመጨረሻ ሂደቱን እንዲሄድ ዕድል የሚሰጠው ነው።በመሆኑም ይህ ጊዜ በትግራይ ውስጥ ለሚኖረውም ሆነ በውጭ የሚኖረው ማኅበረሰብ ካለ ህወሓት መኖር እንደሚቻል፣ከህወሓት ጋር መኖር ሌላ መከራ ይዞ እንደሚመጣ አና ከአሁን በኃላ ያለው የህወሓት አውሬአዊ  አካሄድ ደግሞ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ለመነጠል የሚሄድበት እንደሚሆን መረዳት ይገባል።ሽብርተኛው ህወሓት በአማራ እና በአፋር ላይ የፈፀመው ግድያ፣አስገድዶ መድፈር እና ዘረፋ አንዱ እና ዋና ዓላማው የትግራይ ሕዝብን ከቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ የመለያያ ግንብ ለመፍጠር የተጠቀመበት ሰይጣናዊ መንገድ ነው።

በመሆኑም በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ለ27 ዓመታት የተፈፀመው ግፍ ሳይበቃ ባለፉት አምስት ወራት በአማራ እና አፋር ላይ  የደረሰው ጥፋት የኢትዮጵያ ሕዝብ ከትግራይ በተነሳ ወረራ መሆኑ እና የትግራይ ሕዝብ የሰጠው የተቃውሞ ምላሽ አለመኖሩ እና ህወሓትን አሁንም አቅፎ መቀመጡ ከባድ ቅሬታ ፈጥሯል።ቅሬታው ውሎ አድሮ የትግራይ ሕዝብ ከሦስት ሺህ ዓመት አብሮት የኖረውን የኢትዮጵያን ሕዝብ በ40 ዓመት እና ዘለቄታ በሌለው በኢትዮጵያ ሕዝብ መወገዱ በማይቀረው በህወሓት ሊቀይረው አይገባም።የትግራይ ሕዝብ እና ማኅበረሰብ በህወሓት ላይ አምርሮ መነሳት፣ማስወገድ እና ለተፈፀሙት ግፎች የኢትዮጵያን ሕዝብ የሚያለሳልስ ሃገራዊ የጋራ የይቅርታ እና የፈረሰውን መጠገን፣የተወሰደውን የመመለስ ተግባር ላይ ሕዝቡ በፍጥነት መመለስ አለበት።ይህ ተግባር ደግሞ ከባዶ የሚመጣ ሳይሆን ካለመጠባበቅ እያንዳንዱ የትግራይ ተወላጅ እንደ ግለሰብ እና ማኅበረሰብ በጋር ደግሞ እንደህዝብ ተነስተው ህወሃትን ከትግራይ ምድር ለመንቀል ሲነሱ ብቻ ነው።ይህ የመነሻው ጊዜ ደግሞ አሁን ነው። 

ቪድዮ =የጋዜጠኞቹ አርአያ ተስፋ ማርያም እና አበበች ካህሳይ ቆይታ በምርኮኞች ካምፕ 

ከኢቢሲ የተገኘ  



Thursday, December 23, 2021

የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ሕዝብ ድርጊት በመቀየሙ ወደ መቀሌ ሰራዊቱን ላለመላክ ወስኗል።ውሳኔው መንግስት በተለያየ ጊዜ ወደ ትግራይ እየገባ እርምጃ እንደሚወስድም ገልጧል።የዛሬው የመንግስት ውሳኔ ሲፈተሽ



=============
Gudayachn /ጉዳያችን 
==============

በእዚህ ጽሁፍ ውስጥ የሚከተሉት ርዕሶች ያገኛሉ። 
  • ውሳኔው ሲፈተሽ ምን ይመስላል?
  • መከላከያ መቀሌ አይገባም ማለትስ ምን ማለት ነው?
  • በቀጣይ የመንግስት ሦስት ትኩረቶች  ምን መሆን አለባቸው?

  • ውሳኔው ሲፈተሽ ምን ይመስላል?

በዛሬው የመንግስት መግለጫ ላይ በዘመቻ ኅብረ ብሔራዊነት በተሰኘው ዘመቻ  የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች  የሽብርተኛው ህወሓትን ወረራ በአፋር እና በአማራ ክልል በድል ካጠናቀቁ በኃላ ሰራዊቱ በአፋር እና ምስራቃዊ የአማራ ክልል ይዞታውን አጠናክሮ እንዲጠብቅ መታዘዙን እና ለእዚህም ሦስት ምክንያቶች መኖራቸውን ገልጧል። ምክንያቶቹም - 

1) ከዚህ ቀደም መከለከያ ሰራዊቱ በትግራይ በነበረበት ጊዜ የተፈፀመበትን ክህደት መነሻ በማድረግና ካለፈው መማር ስለሚያስፈልግ፣

2)  የሽብር ቡድኑ የተገደሉበትን ታጣቂዎች ሬሳ የቻለውን ሁሉ ጭኖ በመሸሹና የመንግሥት ኃይል ወደ ትግራይ ሲገባ መንግሥት በትግራይ ጅምላ ጭፍጨፋ ፈፀመ የሚል በአስከሬን የመነገድ እቅድን እንዳሰበ ስለተደረሰበት እና ከእውነት የራቁ ዓለም ዐቀፍ ተቋማት በኢትዮጵያ ላይ የሽብር ቡድኑን ክስ መነሻ በማድረግ የተለያዩ ወሳኔ ለማሳለፍ እንደሚሰሩ ስለታወቀ፡፡

3) መንግሥት የአገሪቱን የግዛት አንድነት የመጠበቅ ሙሉ ኃላፊነቱን ለመወጣት በየትኛውም ጊዜ ወደ ትግራይ ክልል እየገባ እርምጃ መውሰድ እንደሚችል የሚታመን ስለሆነ መሆኑን የዛሬው መግለጫ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ  ዶ/ር ለገሰ ቱሉ በሰጡት መግለጫ የመንግስትን ውሳኔ አሳውቀዋል

ከእዚህ በተጨማሪ በእዚሁ መግለጫ ላይ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ''መንግሥት አሁን ላይ ምንም የማድረግ አቅም የሌለውን ትሕነግ መልሶ እንዳይነሳ ለማድረግ የሚያስችሉ የተጠኑ እርምጃዎችን በየትኛውም ስፍራ እየገባ ይፈፅማል'' ካሉ በኃላ ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት የአሸባሪውን ትሕነግ ቡድንን ጠራርጎ በማስወጣትና እጁን እንዲሰጥ በማድረግ ስኬታማ እንደነበር ተገልጿል፡፡

ሆኖም ግን የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ መንግሥት በኦሮሚያ ክልል በሸባሪው ሸኔ የሚደርሱ ችግሮችን እንዲሁም በምዕራብ አማራ አካባቢዎች የሚወስዳቸው የተጠኑ እርምጃዎች ይቀጥላል፤ ቀጣይ አቅጣጫዎችንም ያሳውቃል ማለታቸውን ዋልታ ዘግቧል።

ውሳኔው ሲፈተሽ ምን ይመስላል?

የዛሬው የመንግስት ውሳኔ በአንዳንድ ማኅበራዊ ሚድያዎች እንደሚባለው መንግስት ፈጽሞ በትግራይ ያለውን ሁነታ በወታደራዊ የተለያዩ የመቆጣጠርያ መንገዶች አልቆጣጠርም አስፈላጊ ሲሆንም ጥቃት አልፈጽምም አላላለም። ከላይ የመግለጫው ዓረፍተ ነገር ላይ እንደተገለጠው ይልቁንም ከመግለጫው አንዱ ምክንያት መንግስት አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሁሉ ኢርምጃ የመውሰድ አቅም ስላለው መሆኑን ይገልጣል። 

የዛሬው የመንግስት ውሳኔ መንግስት ባለበት ሃላፊነት እንደ መንግስት፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ እንደ ህዝብ ለወንድሙ ለትግራይ ህዝብ ያደረገውን እና የሆነውን የትግራይ ህዝብ ከመጤፍ እንዳልቆጠረው እና ይልቁንም ህወሃት ለፈጸመው ክህደት ተብብሮ መገኘቱ እንዳሳዘነው በደንብ ያሳያል። 

መከላከያ መቀሌ አይገባም ማለትስ ምን ማለት ነው?

ይህ ማለት የኢትዮጵያ ህዝብ በ1983 ዓም ህወሃት በትግራይ ስም ተደራጅታ ስትመጣ ትግራይ መጣ ወይንም የእገሌ ዘር ሳይል አዲስ አበባ ድረስ አስገብቶ ነበር የኢትዮጵያ ህዝብ ዘረኛ አይደለም ማለትም ነው።

ይህ ማለት የትግራይ ህዝብ የኢሳያስ ጦር ወጋኝ ሲል የኢትዮጵያ ህዝብ ከዳር እስከ ዳር ተነስቶ ባድሜ ላይ ከቶ እስከ 70 ሺህ ሰው የረገፈውን አጥንት ተረስቶ ሰሜን ዕዝ ሲወጋ፣የትግራይ ህዝብ ዝም ማለቱ አሳዝኖናል ከባለፈው ትምህርት ወስደናል ማለት ነው።

ይህ ማለት ከሰሜን ዕዝ የተወሰነ ሜካናይዝድ ጦር ወደ ሌላ የኢትዮጵያ ክፍል ይንቀሳቀስ ሲባል የትግራይ ህዝብ ነጠላ አንጥፎ ህጻናት አሰልፎ እንዳልለመነ በኋላ ህወሃት በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ሲፈጽም መጨፈሩ አሳዝኖናል ማለት ነው።

ይህ ማለት በትግራይ ከ20 ዓመታት በላይ ኖረው እዝያው ተዋልደው የኖሩ፣የህዝቡን ሰብል ከመሰብሰብ እስከ ቤቶች እና ትምህርት ቤቶች ሲገነቡ የነበሩ የሰሜን ዕዝ አባላት ላይ ጥቃት ሲፈጻም ልጆቻችን ናቸው ብሎ ለማስጣል የሞከረ ከትግራይ አለመኖሩ አሳዝኖናል ማለት ነው።

በኋላም መከላከያ መቀሌን ከህውሃት ነጻ ካወጣ በኋላ በቡድን እየሆነ ሲያጠቃው ብቻ ሳይሆን አንዳንዶች ምግቡ ላይ መርዝ እየጨመሩ፣ዓይኑ ላይ በርበሬ እየረጩ ለህዝብ ነጻነት የቆመን ሰራዊት መግፋት አሳዝኖናል ማለት ነው።

በእዚ ሳምንት በትግራይ ቴሌቭዥን አንዳንድ ሲቪል እናቶች ሳይቀሩ የኢትዮጵያ መከላከያ ወደ መቀሌ ከመጣ ቃል በቃል ሲሉት የተሰማው ''ዓይናቸው ላይ በርበሬ እጨምራለሁ፣ለመውጊያ መርፌ አዘጋጅቻለሁ'' የሚሉ ንግግሮች መሰማታቸው አሁንም የጥሞና ጊዜውን በአግባቡ ያልተጠቀመ መኖሩን በመመልከቴ አሳዝኖኛል ማለት ነው።

አንዳንድ የሽብርተኛው ህወሃት ደጋፊዎች መከላከያ መቀሌ አልገባም ነገር ግን አስፈላጊ ሲሆን እርምጃ እወስዳለሁ ማለቱን እንደ ሃይማኖት የሚያመልኩት ህወሃት የተረፈላቸው እየመሰላቸው ሲደሰቱ ይታያሉ።መከላከያ መቀሌ አይገባም ማለት ምን ዓይነት መከራ እንዳለበት የሚረዱት ከህወሃት ሳይሆን ከትግራይ ህዝብ ችግር አንጻር ነገሩ የሚረዱት ግን አይደሰቱም። መከላከያ መቀሌ አይገባም ማለት  - 

- የመንግስትም ሆነ የግል ድርጅቶች ሥራ አይጀምሩም ማለት ነው።

- ባንኮች ወደ ሥራ አይገቡም፣ከብሄራዊ ባንክ ጋር ያላቸው ግንኙነት አይኖርም ማለት ነው።

- ለትግራይ የሚላክ በጀት የለም ማለት ነው።

- በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ወጣቶች ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ ፈተና አንዳመለጣቸው ሁሉ የስምንተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናም መፈተን አይችሉም ማለት ነው።

- በትግራይ ያሉ ትምህርት ቤቶች፣ሆስፒታሎች እና ሌሎች አካላት ሁሉ ሥራ አይጀምሩም።ሰራተኞችም ደሞዝ አይኖራቸውም ማለት ነው።

- የውጭ ጥቃት በትግራይ ላይ ቢፈፀም ለምሳሌ ከኤርትራ ወይንም ከሱዳን ቢኖር የኢትዮጵያ መከላከያ ህወሓት እያለ ለመከላከል ስለማይችል  በቅድምያ የህወሓት መወገድ ቅድመ ሁኔታ ይሆናል ማለት ነው።

- አሁን በትግራይ ያለውን የአስተዳደር መዋቅር ህወሓት በአግባቡ እየመራው አይደለም።በብዙ ቦታዎች ለምሳሌ የአክሱም ከተማን ጨምሮ ህዝቡ በራሱ አለቆች አየመረጠ ይተዳደራል አንጂ ትግራይ በአሁኑ ጊዜ ታጣቂ ሁሉ የሚዘርፍባት አንደሆነች ትቀጥላለች ማለት ነው። 

ባጭሩ ህወሓት በቀጣይ ከታሊባን የሽብር ቡድን ጋር ሳይቀር ውል አየገባ ትግራይን ለባዕዳን ለመሸጥ ለማደራደር ይሞከራል ማለት ነው።አስገራሚው ጉዳይ ህወሃትን አንደ ሃይማኖት የሚከተሉት የትግራይ ተወላጆች የትግራይን ወጣት በአፋር አና በአማራ ክልል አስፈጅቶ ቀሪውን አራሱ ረሽኖ አሁንም የቀረውን ለማስጨረስ የሚዘጋጀውን ቅምጥል አመራሩ ግን አሁንም የታሸገ ውሃ ሳይቀር አንዳይጎድልባቸው ሆነው የሚኖሩትን አመራሮች ወንጀል አየሸፈነ ለመኖር የሚሞክር መሆኑ ነው።

መንግስት በቅድምያ ሊያከናውናቸው የሚገቡ ሦስቱ ስራዎች 

መንግስት ሀገር የማቆም አና የማፅናት ትልቅ ታሪካዊ ኃላፊነት የተጣለበት ጊዜ ነው።ይህ ኃላፊነት የመንግስት ብቻ አይደለም፣ ግለሰብ አና የሕዝብም ጭምር ኃላፊነት ነው። የህወሓት የሽብር ቡድን በአፋር እና በአማራ በተለይ ወሎ በሰው ልጅ ይፈፀማል የማይባል ግፍ ፈፅሟል።ከ70 ዓመት መነኩሴ መድፈር እስከ የካህን ሚስት መድፈር፣እናቶችን ልጆቻቸው ፊት መድፈር እና ገንዘብ ቀምቶ ከቤት ገብቶ ከበላ ከጠጣ በኃላ ያበላው ያጠጣውን ቤተሰብ ገድሎ የሄደባቸው በርካታ ምስክሮች በመገናኛ ብዙሃን ስንመለከት ነው የሰነበትነው።አሁን በጦርነቱ ሳብያ የተጎዳውን ህዝብም ሆነ ምጣኔ ሃብቱን እንዲያገግም መንግስት ቅድምያ ሊሰጣቸው የሚገባቸው አንገብጋቢ ጉዳዮች አሉ።እነርሱም -

1) በአማራ ክልል በተለይ በዞን እና ወረዳ ደረጃ ሕዝብ ያመነባቸው አና በጦርነቱ ወቅት በነበራቸው ብቃት አመራር እና በችሎታ የሕዝብ ቅቡልነት ያላቸው አመራሮች እንዲመሩ ማድረግ።በአማራ ክልል በታችኛው መዋቅር ላይ ያለው አመራር በጁንታዊ አስተሳሰብ የተበከሉ፣አቅም የሌላቸው እና ሕዝብ በልዩ ልዩ የስነ ምግባር ጉድለት የሚታሙ መኖራቸው ይሰማል።

2) በኦሮምያ ክልል ያለው ሙስና ቅጥ ያጣ መሆኑ ይሰማል።ከፍተኛ የስልጣን ብልግና አና ያለአግባብ መበልጠግ ላይ ብቻ የሚሰሩ አመራሮች ከብልሹ ነጋዴዎች ጋር በመግጠም ከፍተኛ ጥፋት አየፈፀሙ ነው።ይህንን መንግስት በፍጥነት አጣርቶ መፍትሄ አለመስጠቱ አሳሳቢ ነው።

3) ወደ ትግራይ ክልል የሚተላለፍ ሙሉ ደረጃውን የጠበቀ የጤናማ ፕሮፓጋንዳ ራድዮ እና ቲቪ እንዲሁም ከአየር ላይ የሚበተን ወረቀት ጭምር ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ በህወሓት ስር የኖረውን ሕዝብ ላይ ሥራ መስራት ይፈልጋል።አሁን ባለበት ሁኔታ  ብዙሃን በትግርኛ የሚተላለፉ የራድዮም ሆነ የቴሌቭዥን ስርጭቶች ቢኖሩም በባለሙያ እና በቂ በጀት ተመድቦ የሚጠበቅ ውጤት ባስቀመጠ መልኩ መስራት ይፈልጋል።

ለማጠቃለል፣በኢትዮጵያ ምድር በሽብርተኛው ህወሓት አማካይነት ደም ሲፈስ፣ሕዝብ ሲሰደድ ግማሽ ክፍለዘመን አስቆጥሯል።ባለፉት አራት ወራት ብቻ በአማራ እና በአፋር ላይ የደረሰው ግፍ በፈጠረው ቁጣ እና ስሜት ወደ መቀሌ ሕዝቡም ሠራዊቱም ቢተም ምን ሊፈጠር አንደሚችል  መገመት ይቻላል።በመሆኑም መንግስት የረጅም ጊዜ የኢትዮጵያዊነት አሳቤን ግንዛቤ ባስገባ መልኩ ሰራዊቱ በድንበር ላይ ይዞታውን አስጠብቆ ትዕዛዝ እንዲጠብቅ መደረጉ ለአሸናፊ ሰራዊት ከባድ ውሳኔ ቢሆንም ቆይቶ ግን ኢትዮጵያን በመልካም ይከፍላታል። ሆስፒታላቸው የፈረሰባቸው፣ትምህርት ቤታቸው የተዘረፈባቸው እና ከተሞቻቸው አሁንም በሽብርተኛው ህወሓት የፈረሰባቸው የአፋር እና አማራ ክልል ወጣቶች የፈሰሰውን ሲጠርጉ፣የተሰበረባቸውን ለመጠገን ሲሞክሩ መመልከቱ አንጀት ይበላል።ግፍ ተፈፅሞበት በብዙ ልቀት በልጦ ወደ ሥራ የሚሄድ ወጣት ማየት በራሱ ግፍ ያደረገው በምድር ብቻ ሳይሆን ከፈጣሪም የሚታዘዝ ቅጣት እንደሚያገኝ እማኝ ይሆናል። በአማራም ሆነ በአፋር ክልል ህዝቡ ምግብ ለወራሪዎቹ ሲሰጥ አንድም ቦታ መርዝ ጨምሮ ወይንም ሌላ የተንኮል ሥራ ሰርቶ መስጠቱ አልተሰማም።ከሰኔ፣ 2013 ዓም በፊት በትግራይ ሕግ ማስከበር ሥራ ላይ የነበረው የኢትዮጵያ መከላከያ ላይ ግን አንዳንድ የትግራይ ቦታዎች ብቻ ሳይሆን ጥቅምት 24፣2013 ዓም በሰሜን ዕዝ ላይ ከተፈፀመው ጥቃት ውስጥ አንዱ በመኮንኖች ላይ በራሳቸው የትግራይ ባልደረቦች የሚበሉት ምግብ ላይ መርዝ ተጨምሮ እንደነበር የወቅቱ ዘገባ ነበር።የሽብርተኛው ህወሓት እና አምላክዎቹ ያለባቸው የጥላቻ ጥግ እና የተበደለው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሞራል ልዕልና ሲታይ ያለው እርቀት የትየለሌ የሚያሰኝ ነው።ይህ የሃሳብ ልዕልና የጁንታውን ስነልቦና ላይ የበላይነቱን ተቀዳጅቷል።ቀሪው ስልታዊ አፈፃፀም ብቻ ነው።

==========////============



Tuesday, December 21, 2021

የአንድ ሚልዮን ኢትዮጵያውያን ጉዞ ወደ ሀገር ቤት በቡድን እየሆኑ የሚጎበኙት ቦታ ለማመቻቸት ከወዲሁ ከስር የተያያዘውን ፎርም እንዲሞሉ ጥሪ ቀርቧል።



በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ የመጀመርያ የሆነው ኢትዮጵያ ልጆቿን ወደ ሀገር ቤት ኑ! የሚለው ጥሪ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ዓቢይ እና ከቢሯቸው ከተላለፈ ገና አንድ ወር ቢሆነውም እስካሁን በመቶሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር ቤት የገና በዓልን አስታከው ለመግባት ዝግጅት ላይ ናቸው።

በኢትዮጵያም ብሔራዊ ኮሚቴ መመስረቱ እና ከአዲስ አበባ ከተማ ጀምሮ ክልሎች ፈጣን ዝግጅት እያደርጉ ነው። የአሁኑ ጉዞ በተለይ ኢትዮጵያ በሽብርተኛው ህወሓት የደረሰባት የሽብር ጥፋት የፈረሰውን ለመገንባት፣የተሰበረውን ለመጠገን የሚደረግ ጉዞ ነው።በእዚህ መሰረት ወደ ኢትዮጵያ የሚሄዱ በቡድን በቡድን እየሆኑ ከስር የተለጠፈውን ማስፈንጠርያ (ሊንክ) በመጫን ፎርሙን እንዲሞሉ ማሳሰብያ ተሰጥቷል።በእዚህ መሰረት በሚዘጋጁት ጉብኝቶች መሳተፍ የሚችሉ ሲሆን ኢትዮጵያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ላልሰሙት መረጃውን እንዲያደርሱ ይጠየቃሉ።

በቡድን ሆነው የሚሞሉት ፎርም ሊንክ ከስር ተጭነው ከፍተው ከሞሉ በኃላ ''Submit'' የሚለውን ተጭነው ይላኩ።


========////========

Friday, December 17, 2021

የተ.መ.ድ 33ኛው ልዩ ሰብዓዊ መብት ምክርቤት የጠራው የዛሬው ስብሰባ አብቅቷል።ከ19 በላይ የሃገሮች ተወካዮች ያሉት ገዢ ሃሳቦች፣ እና የስብሰባው አጠቃላይ አንደምታ እና መንግስት ማየት ያለበት መንገድ


የተመድ ሰ/መ/ም/ቤት ስብሰባ ጀኔቫ ሲደረግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሕመድ ከቱርክ ፕሬዝዳንት ኤርጋዶን ጋር 
ውይይት ላይ ነበሩ።የቱርክ አፍሪካ ጉባኤ ዛሬ በአንካራ ተከፍቷል።
ፎቶ = ታኅሳስ 8/2014 ዓም (ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ትውተር ተወስዶ ለጉዳያችን እንዲሆን ሆኖ የቀረበ)

==============
ጉዳያችን ልዩ ሪፖርት
==============
በዛሬው ታህሳስ 8/2014 ዓም የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ንግግር ካደረጉት የሃገራት ተወካዮች ንግግር ውስጥ አብዛኞቹ ህገሮች በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና በተመድ የሰብዓዊ መብት ካውንስል በጋራ የተደረገው ምርመራ አወድሰዋል።የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት መከበር እንዳለበት አስምረውበታል።
ከተናገሩት ውስጥ የ19ኙ ሃገሮች ያሉት ዋና ገዢ ሃሳቦች ከስር ቀርበዋል።ስብሰባው የተደረገው በጄኔቭ የተመድ ስብሰባ አዳራሽ ሆኖ ተናጋሪዎች በኮቪድ ወረርሽኝ ሳብያ በቀጥታ የቪድዮ ስርጭት ነበር የቀረቡት።ስብሰባው በሁለት ክፍል ከምሳ በፊት እና በኃላ የነበረው ስብሰባ በተመለከተ የተባለውን ከእዚህ በታች ቀርበዋል።

በክፍል አንድ ስብሰባ 

በጧቱ ስብሰባ ላይ 19 ሀገሮች ተወካዮች ያሉት ዋና ጭብጦች የሚከተሉት ናቸው።

👉 በጄነቭ  የኢትዮጵያ ባለሙሉ አምባሳደር ዘነበ ከበደ ኢትዮጵያ የቀረበው ረቂቅ ፖለቲካዊ መሆኑን እንደምታምን እና ይልቁንም በህወሓት የተፈፀሙት የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ችላ መባላቸው ላይ አስምረው ተናግረዋል።

👉 የእንግሊዙ አምባሳደር ኮሚሽኑ ውሳኔ እንዲያሳልፍ ለየት ባለ ቶን ሁሉ አጅበው ለማቅረብ ሞክረው ትዝብት ላይ ወድቀዋል።


👉 ፈረንሳይ የተጀመረው የኢትዮጵያ እና የተመድ የጋራ ምርመር ይቀጥል ብላለች

👉 ኩባ የካውንስሉ ስብሰባ በአዳጊ ሃገሮች ላይ የተሸረበ ፖለቲካዊ ቃና ያለው ነው።ቅድምያ መስጠት ያለብን ለኢትዮጵያ ብሄራዊ እና አህጉራዊ ጥረቶች ነው ብለዋል።

👉 ፓኪስታን የተመድ ካውንስል በራሱ ያለፈ ታሪኩ የሃያላንን ፖለቲካ ፍላጎት የማስፈጸም ታሪክ አለው ብለውታል።ይህ ስብሰባ ለፓኪስታን ጥያቄ ፈጥሮባታል ብለዋል።

👉 ኤርትራ ይህ ስብሰባ ፍትሃዊ አይደለም፣የኢትዮጵያን ግዛታዊ አንድነት የሚጻረር እና በህወሃት የተሰራውን ወንጀል ለመሸፈን የሞከረ ነው።ወደ ትግራይ ሄደው የቀሩት የእርዳታ መኪናዎችንም አንስተዋል።

👉 ቦሊቭያ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ፖለቲካዊ ሲሆን አይስማማንም ብለዋል።

👉 ፓራጓይ ሁሉም አካላት ለተራቡት ምግብ እንዲደርስ ያድርጉ ብላለች

👉 ናይጄርያ ይህ ስብሰባ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የተጻረረ ነው፣የአፍሪካ ህብረትንም ይሁንታ አላገኘም ብላዋለች ።

👉 ኒውዝላንድ ህወሃት ጦርነቱን ወደ አማራ እና አፋር ማስፋፋቱን ገልጣ ዓለም አቀፍ ምርመራ ኮሚሽኑ ቢያደርግ ብላ ቀላቅላለች

👉 አውስትራልያ የኢትዮጵያ መንግስት ምርመራውን በሚኒስቴር ደረጃ አቋቁሞ ምርመራ ላይ መሆኑን እንደግፋለን ብለዋል።

👉 ስዊድን የጥላቻ ንግግሮች ያሳስቡናል ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግስት በሚንስትር ደረጃ አጣሪ ኮሚቴ ማቋቋሙን አድንቀዋል።

👉 አየርላንድ የአፍሪካ ህብረት ማደራደር እንደሚደግፉ ተናግረዋል።የጥምር ሪፖርቱ በተሰጠው አስተያየት መሰረት ክትትል ይፈልጋል፣መብት የጣሱም ለፍርድ ሊቀርቡ ይገባል ብለዋል።

👉 ኢራን ማናቸውም ጉዳይ የኢትዮጵያን አንድነት በማይነካ መልኩ በአፍሪካ ህብረት በኩል መከናወን ይገባዋል ብለዋል።

👉 ሲሪላንካ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ካለምንም የውጭ ጣልቃ ገብነት ስራውን እንዲሰራ መደረግ አለበት ብለዋል።

👉 አሜሪካ ጉዳዩ ያሳስበናል ብለው ምግብ ወደ ትግራይ አልሄደም፣የትግራይ አማጺዎችም በአማራ እና አፋር ግፍ ፈጽመዋል፣የኤርትራ መንግስትም ጣልቃ ገብነት መቆም አለበት ብለዋል።

👉 ደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ መንግስት የጥምር ምርመራ ውጤት መቀበሉን እናመሰናለን።በእዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋትን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጠዋል።

👉 ሩስያ ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተገዢ ነች። ኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ፖለቲካዊ ተጽኖ ያለበት ማናቸውም ውሳኔ አይሰራም።ኤክስፐርቶችን ከውጭ በመላክ የሚደረግ ስራም ውጤታማ አይሆንም።

👉 ቻይና በኢትዮጵያውያን ችሎታ እና ጥበብ ችግሮችን የመፍታት አቅም ትተማመናለች። የአፍሪካ ህብረት ተሳትፎ ታበረታታለች።

ከእዚህ በተጨማሪ የተለያዩ ዓለም አቀፍ እና አካባቢያዊ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች አጫጭር ዕይታዎቻቸውን አካፍለዋል።

በክፍል ሁለት ስብሰባ 

በክፍል ሁለት ማለትም ከምሳ በኃላ በነበረው ስብሰባ ላይ ድምጽ ከመሰጠቱ በፊት የምክር ቤቱ አባላት እና ኢትዮጵያ ሃሳብ እንድትሰጥ በተጠየቀው መሰረት የሚከተሉት ሀገሮች ይህንን ብለዋል።

👉 የኢትዮጵያ አምባሳደር ዘነበ ከበደ በድጋሚ ተቃውሞ አሰምተዋል።

👉 የኤርትራ አምባሳደር የአፍሪካ ቡድን በሙሉ ውድቅ እንዳደረገው ገልጠዋል።

👉 የሩስያ አምባሳደር ረቂቁን እንደምትቃወም እና የአፍሪካ ችግር በአፍሪካውያን መፈታት አለበት ብላለች።

👉 ቬንዝወላ ይህ ፖለቲካዊ ቃና ያላው ረቂቅ ነው፣ኢትዮጵያ ይህንን እንደማትቀበል ገልጣለች፣ኢትዮጵያ በተመድ እና የኢሰመኮ የተደረገው ምርመራ መቀበሏን ሁሉ ገልጣ ነው ይህንን ረቂቅ እንደገና ኮሚሽኑ ያመጣው ስለሆነም ረቂቁን አንቀበልም ብላለች።

 👉 ቻይና የሰብዓዊ ሁኔታ ፖለቲካዊ ቃና ሲኖረው እንደማፅማማ፣እኛ የኢትዮጵያን ስጋት እንረዳለን ስለሆነም ድምፃችንን በመቃወም ነው የምንሰጠው ብላለች።

👉 ፊሊፒንስ ይህ ረቂቅ ተግባራዊ እንዳይሆን ነው ድምፅ የምንሰጠው ካለች በኃላ የኢትዮጵያ መንግስት በተመድ እና በኢሰመኮ የተደረገውን ምርመራ ተቀብሎ እያለ እና በሚኒስትር ደረጃ የሚያጣራ ኮሚቴ መስርቶ እያለ ሌላ ውሳኔ አያስፈልግም።የሰብዓዊ መብት ጉዳይ የሀገር ሉዓላዊነትን ማክበር አለበት ብላለች።

በመጨረሻም የድምፅ መስጠቱ ስነስርዓት ተካሂዶ እንግሊዝ እና አሜሪካን ጨምሮ 21 ሀገሮች አዎን ሲመርጡ 15 ሀገሮች ቻይና እና ሩስያን ጨምሮ አይሆንም ብለዋል። የቀሩት 11 ሀገሮች ድምፀ ተአቅቦ አድርገዋል።

የስብሰባው አጠቃላይ አንደምታ እና መንግስት ማየት ያለበት መንገድ  

በድምፅ ውጤቱ መሰረት የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት ኤክስፐርቶች በመላክ ላለፈው አንድ ዓመት የነበረውን ሁኔታ አጥንቶ እንዲያቀርብ የሚል ሲሆን ኢትዮጵያ ውሳኔውን የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ የተጠናወተው መሆኑን በመግለጫዋ አስታውቃለች።ሆኖም ግን አሁንም ኢትዮጵያ የህወሓት የሽብር ቡድንን በቶሎ ለሕግ አቅርባ እስከሄደች ድረስ እና ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣውን ልዑክ ማንነት ( ውሳኔውን አልቀበልም ብላ ውድቅ ካላደረገችው) እስከመወሰን እና ቪዛ የምትሰጠው እና የማትሰጠውን እስከመወሰን ድረስ የራሷ ተግባር ነው። ሌላው የአፍሪካ ሀገሮችን አስተባብራ ዲፕሎማሲያዊ ግፊት አስደርጋ መልሳ ኮሚሽኑን በሂደት ስብሰባ አስቀምጣ ውሳኔውን ማስቀየር ትችላለች። 

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና የተመድ ሰብዓዊ መብት ምክር ቤት በጋራ በትግራይ ያደረጉት ምርመራ የኢትዮጵያ መንግስት ሲቀበለው የሽብር ቡድኑ ህወሓት አልተቀበለውም።በመሆኑም አሁንም ምርመራው ይደረግ ቢባልም በህወሓት የተፈፀመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፀሐይ የሞቀው ነው።እዚህ ላይ ማወቅ የሚገባው ግን የምዕራባውያን ፍላጎት ኢትዮጵያ ውስጥ ጉዳይ ገብቶ መፈትፈት እና በትግራይ ሕዝብ እና በተቀረው ሕዝብ መሃል ያለ ልዩነት በምርመራ ሂደት እያሰፉ በመጨረሻ ጉዳዩን ማወሳሰብ ነው።ስለሆነም የኢትዮጵያ መንግስት የዛሬውን ውሳኔ አስመልክቶ የሩቁ ግባቸውን ተመልክቶ ለትውልድ የሚጠቅም ብልህነት ያለው ውሳኔ መወሰን ይገባዋል።

ባጠቃላይ የዛሬው የውሳኔ ሂደት የሚያሳየው የተባበሩት መንግሥታት አባል ሀገሮች መሃል ያለው ልዩነት በግልጥ መስፋቱን እና ድርጅቱ ለውጥ ካላደረገ በቀር ውሳኔዎቹ ሁሉ የውሃ ላይ ኩበት እየሆኑ መሄዳቸው እንደማይቀር ነው።የዛሬው ውሳኔ ከሩስያ እና ቻይና በተጨማሪ ፊሊፒንስ እና ቬንዝዌላ ያሰሙት የምሬት ንግግር ከምዕራቡ ጋር የደረሰው ፍጥጫ የመጨረሻ ጫፍ እንደደረሰ በደንብ የሚያሳይ ነው። በእዚህ ጊዜ ኢትዮጵያ ውሳኔዎችን ባለመቀበል ለፍትህ መቆሟን በማሳየት የጀግና ጀግና ሆና በብዙ ሀገሮች አንጀት አርሳ እንደምትወጣ መመልከት ይቻላል።የመጨረሻው መጨረሻ ግን ኢትዮጵያውያን በሽብር ቡድኑ የተዋለባቸውን ግፍ በትግራይ ሕዝብ ላይ እንዳይፈፀም በጨዋነት በመንቀሳቀስ የሽብር ቡድኑን በፍጥነት መደምሰስ እና የትግራይ ህዝብንም ከመከራው አላቆ የህወሓትን ፕሮፓጋንዳ እና እኛኑ ለማጋጨት ያሰፈሰፉትን ባዕዳን አሳፍረን ችግራችንን ስንፈታ ሁሉም ያፍራል።

በዛሬው የተመድ ሰብዓዊ መብት ምክርቤት ስብሰባ ላይ ድምፅ የሰጡ የ47 ሀገሮች ዝርዝር እና የድምፃቸው ውጤት 



The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church is in turmoil in Athens, Greece.

His Holiness Abune Mathias I, Patriarch of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, met with Greece's Ambassador to Ethiopia, Antonios Sg...